1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
በ2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ያለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ በተናበበ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ተከትሎ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከAMN ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ ።
ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችና የተግባቦት ስራዎች የፈጠሩትን የአመለካከት ለውጥ እና ያስገኙትን ውጤት ለማወቅ ለሚካሄድ ሳይንሳዊ ጥናት የኦሬንቴሽን መድረክ ተካሄደ።
ሳይንሳዊ የዳሰሳ ጥናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ፣በተጠሪ ተቋማት እና እንዲሁም በክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ባሉ ሙያተኞች የሚካሄድ ሲሆን የጥናቱ ናሙናም የተለያዩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል ።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ በመሩት በዚሁ የኦሬንቴሽን መድረክ ላይ ከማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ጋር የሁለትዮሽ ተግባቦቱን ለማጠናከር በመላው መዋቅር በበጀት አመቱ 10 ወራት የተከናወኑ ስራዎች እና ያመጡት የአመለካከት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊና ሙያዊ በሆነ ጥናት ማስደገፍ ለቀጣይ ስራዎች ወሳኝ እንደሆነ ተመላክቷል።
የኦሬንቴሽን መድረኩ ዋነኛ አላማ የሚሰበሰበዉ መረጃን ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግና በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የህበረተሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለመለካትና በዚህ መነሻነት የቀጣይ ስራዎችን አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነም ተገልጿል።
በዚህ መነሻነት የሚካሄደው የፋይዳ ጥናት በዋናነት የከተማችንን ነዋሪዎች በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ ያላቸውን የግንዛቤ ደረጃ በተጨባጭ እና ትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት እና በመለካት ያሉ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍቶችን በማረም ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉም ተጠቁሟል።
ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ተገለፀ
" ፋይዳ ለኢትዮጵያ " የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ በመጪው እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን በዛሬው ዕለት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል።
በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቅኔ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ " ፋይዳ ለኢትዮጽያ " በሚል መሪ-ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ እሁድ ግንቦት 3/ 2017ዓ.ም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በዛሬው ዕለት በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎች ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። አቶ ዮዳሄ የፋይዳ ምዝገባ እንደ ሃገር ጅማሮው መልካም የሚባል ቢሆንም በስፋት ከመመዝገብ አኳያ አሁንም የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አክለዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ቴክኒካል ገለፃ ያደረጉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ሩጫው ግንቦት 3/2017ዓ.ም መነሻ እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ እንደሆነና በመርሃ-ግብሩ አትሌቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች በስፋት በሩጫው እንደሚሳተፉ ገልፀዋል። ቢሮ ሃላፊው ለሯጮች የሚሰጠው ቲ-ሸርት ነፃ መሆኑን እና ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሜዳልያ ሽልማት እንደሚኖር የገለፁ ሲሆን ለወንዶች ፣ በሴቶች እና በፓራ ለሚወዳደሩ አሸናፊ አትሌቶች በየደረጃው ሽልማት እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል።
በሩጫ መርሃ ግብሩ ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች ፣ ታዋቂ ሰራተኞች፣ አትሌቶች ፣ አመራሮች ፣ የውጭ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች የሚሳተፉ ይሆናል።
የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ኤጀንሲ የፋይዳ ምዝገባ በጋራ ለመምራት መግባብያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በከተማው ባደረጉት ንቅናቄ 2.3 ሚልዮን አዲስ ተመዝጋቢዎችን ላለፉት ወራት መመዝገባቸውን በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን ይህም በከተማው ላለፉት ሁለት ዓመት ከተመዘገበው ቁጥር አንፃር በአጭር ግዜ ከግማሽ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።
ዛሬ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ካሉት የእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ሰአር ጋር በኢትዮ-እሥራኤል ግንኙነት ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል። ሁለቱ ሀገሮቻችን በታሪክ ሥረ መሠረት ላይ የተገነባ ረዥም ዘመን የቆየ ግንኙነታቸውን ዛሬም ቀጥለዋል። ዛሬ ት… See more
ለመዲናችን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን (International Fire Fighters day) አደረሳችሁ!
የዘንድሮው ዓለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን "ህዝባቸውን ከአደጋ ለመታደግ በጀግንነት፣በቆራጥነት እና በመሥዋእትነት ስራቸውን ለሚያከናውኑት የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞቻችን ክብር እንስጣቸው!" በሚል መሪ ቃል በመላዉ ዓለም እየተከበረ ይገኛል።
እለቱ በመላው አለም የሚከበረው የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በስራቸው የሚያጋጥማቸውን አደጋ ተጋፍጠው የሰው ልጅ ህይወትንና ንብረትን ለመታደግ ለሚከፍሉት ዋጋና ለህዝብ ለሚሰጡት ክቡር አገልግሎት እውቅና ለመስጠት በማለም የሚከበር ቀን ነው።
በመሆኑም በመዲናችን አዲስ አበባም እለቱን በተለያዬ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመዲናችን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እንኳን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
" ፋይዳ ለኢትዮጵያ ! " የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ
የፊታችን እሁድ ግንቦት 3/2017ዓ.ም
በነፃ!
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በጋራ
በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች እና የነዋሪዎች ተጠቃሚነት
#etv #EBC #ebcdotstream #addisababa #corridor #development
የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች አጠቃላይ እይታ:-
👉 የ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች በ7/24 መርህና አመራር በመንቀሳቀስ ለህብረተሰቡ ገለልተኛ በሆነ አቋም ሰብአዊ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ናቸው። ይህም ማለት ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት በማንኛውም ጊዜ ቀንም ሆነ ማታ ዝግጁ ናቸው።
💥 የ7/24 የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አስፈላጊነት:-
👉 የ 7/24 መርህ በድንገተኛ አገልግሎቶች ውስጥ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ዕርዳታ ሁል ጊዜ መገኘቱን ያረጋግጣል። ይህ በተለይ በየደቂቃው በሚቆጠርበት ድንገተኛ ሁኔታዎች ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ወቅታዊ ምላሽ ህይወትን እና ንብረትን በማዳን ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።
💥የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አመራር:-
👉 ለድንገተኛ አደጋዎች በብቃት ምላሽ ለመስጠት ሰራተኞች በሚገባ የተቀናጁ፣ የታጠቁና የሰለጠኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በድንገተኛ አገልግሎቶች ውስጥ ውጤታማ አመራር አስፈላጊ ነው። በድንገተኛ አገልግሎት ውስጥ ያሉ መሪዎች ቡድኖቻቸውን ከፍተኛ ጫና በሚፈጥርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለመምራት ጠንካራ የመግባቢያ፣ የውሳኔ አሰጣጥና ችግር ፈቺ ክህሎቶች ሊኖራቸው ይገባል።
💥 የማህበረሰብ አገልግሎት እና ነፃነት:-
👉 የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ለህብረተሰቡ ገለልተኛ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ቁርጠኝነት ህዝብን ጥቅም መማረጋገጥ ያላቸውን የሙያ ስነምግባር ያሳያል። ራሳቸውን ችለው በመስራት በውጫዊ ተጽእኖ ሳይደናቀፉ ለድንገተኛ ጊዜ ፈጣንና ውጤታማ ምላሽ ይሰጣሉ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለአዲስ አበባ ከተማ የልማት ስራዎች እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚዳስስ ወቅታዊ ዝግጅት ዛሬ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በኢቢሲ ዜና ቻናል ይተላለፋል።
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን
እንኳን ለ84ኛው የዐርበኞች (የድል) በዓል አደረሳችሁ።
ቀደምት እናትና አባቶቻችን ነጻነትን በደም አስከብረው ሀገር አውርሰውናል። በዚህም እንኮራለን። እነዚህ ቀደምት ዐርበኞች በከፈሉት ዋጋ ዛሬ ቀና ብለን በነጻነት ዐደባባይ እንድንራመድ አድርገውናል። በድህነታችንና በኋላ ቀርነታችን ምክንያት ግን ነጻነታችን ሙሉ ሊሆን አልቻለም።
ነጻነታችን የተሟላ እንዲሆን ዛሬ ኢትዮጵያ የሁለተኛውን ዘመን ዐርበኞች ትፈልጋለች። የሁለተኛው ዘመን ዐርበኞች ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና በማድረስ ነጻነቷን ሙሉ የሚያደርጉ ናቸው። በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መስኮች በሚኖረው ሰላማዊ ጦርነት፣ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ታግለው የሚያሸንፉ ዐርበኞች ናቸው።
የዚህ ዘመን ዐርበኝነት ትጥቁ ዕውቀት፣ ክህሎት እና ዲሲፕሊን ነው። ወኔው የሀገር ፍቅር፣ ቆራጥነት እና ንጽሕና ነው። ግቡ የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው።
ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ ሁለቱም ዓይነት ዐርበኞች ያስፈልጋሉ። ይህ ዘመን ደግሞ ይበልጥ ሁለተኛውን አርበኝነት ይሻል። ይሄ ቀን የመጀመሪያውን ዐርበኝነት መዘከሪያ፤ ለሁለተኛው ዐርበኝነት ደግሞ መሰረት ማፅኛ እንደሚሆን ተስፋዬ የላቀ ነው።
መልካም በዓል ይሁን!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ ተቋም ግንባታ ውስጥ በሠላምና ደህንነት ተቋማት ላይ የተሠራው የሪፎርም ስራ አመርቂ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ላይ ከተናገሩት:-
"ከእናንተ የምንጠብቀው የኢትዬጵያን ብሄራዊ ጥቅም ሠላምና አንድነት ለማረጋገጥ ከወንድም ጎረቤት ህዝቦች ጋር በትብብር መሥራት ፤ ከዛ ያለፈ ነገር ካለ ግን በኢትዮጵያን አርበኝነት ታሪካችን የኢትዮጵያን ጥቅም ማስጠበቅ የሁልጊዜ ስራችን ሊሆን ይገባል።"
An excerpt from Prime Minister Abiy Ahmed’s remarks during the National Police Day 116th Anniversary parade:-
“What is expected from you is to work in cooperation with our brotherly neighboring peoples to ensure the peace and unity of Ethiopia in line with our national interests. However, if challenges go beyond that, it must always be our duty to protect Ethiopia’s interests and uphold our proud patriotic history.”
የጎርፍ አደጋ ስጋት ቅድመ የመከላከል ስራ አካል የሆነ የፍሳሽ መሰመሮች ፅዳት ተካሄደ።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኘው የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ቀጣዩን የክረምት ወቅት መግባት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ቀድሞ ለመከላከል በ10ሩም ወረዳዎች በርካታ አካላት የተሳተፉበት የተቀናጀ የጽዳት ዘመቻ ማካሄዱን አስታውቋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነት አቶ ወንድማገኝ ታደሰ በመጪው የክረምት ወቅት ሊደርስ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ቀድሞ በመከላከል በሰዎችና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ቀድሞ ለመቀነስ እንዲቻል በክ/ከተማው ስር በሚገኙ 10ሩም ወረዳዎች የጽዳት ዘመቻ መደረጉንና የተደፈኑ የፍሳሽ መስመሮችንም የማጽዳት ስራ መሰራቱንና ዘመቻው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የተከፈተው እና ለ5 ቀናት የሚቆየው የ2017 “ኢትዮጵያ ታምርት” ወይም ‘Made in Ethiopia’ ኤክስፖ፣ ከወትሮው በተለየ አጠቃላይ 288 አቅራቢዎች ምርታቸውን አቅርበዋል፡፡
የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ወይም ‘Made in Ethiopia’ ንቅናቄ ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ተስፋ ሰጭ ውጤቶች አስገኝቷል፡፡ በጥቂቱም፡-
• ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት በ2014 በጀት ዓመት 4.8 በመቶ የነበረው በ2016 በ8.4 በመቶ አድጓል። በያዝነው የበጀት ዓመት( 2017) በ12 በመቶ ያድጋል ተብሎ ተተንብዮአል፡፡
• የማምረት ዐቅም አጠቃቀማችን በ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት ወደ 61.2% አድጓል፤
• ገቢ ምርት በመተካት በ2014 በጀት ዓመት የነበረው 2.1 ቢሊዮን ዶላር በ2017 9 ወራት ወደ 3.1 ቢሊዮን ዶላር አድጓል፡፡
• የማኑፋክቸሪንግ የኃይል ፍጆታ በ2015 ከነበረበት 3.88 ቢሊዮን ኪሎዋት ሰዓት በ2016 ወደ 4.67 ቢሊዮን ከፍ ብሏል
• የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የብሔራዊ አካውንት መረጃ እንደሚያሳየው(National Account) የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዕሴት ጭማሪ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል፤ይሄም የማኑፋክቸሪንግ ዕሴት የተጨመረበት ምርት በ2014 በጀት ዓመት ከነበረበት 5.3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ፤ በ2016 ወደ 9.25 ቢሊዮን ዶላር አድጓል። ይህ ከፍተኛ የሆነ ዕሴት ጭማሪ ከላይ የተጠቀሰውን ትክክለኛ የምርት ዕድገት የሚያንፀባርቅ ነው።
በቀጣይ ዓመታት ለአግሮ ፐሮሰሲንግ መስፋፋት የሚያግዙ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ማሽኖችን ፣ በገጠር የመስኖ እና የቤት ውሰጥ ኃይል አቅርቦት ችግሮችን የሚፈቱ የነጻ ኃይል ማምረቻ ማሽኖችን፣ እንዲሁም ፈጠራን ማበረታትና አዳዲስ ምርቶችን ወደ ገበያ የማቅረብ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡
"የከተማችን ፅዳት በጥቂት ሰዎች የሚሰራ አይደለም።በህዝብ የሚከወን ሥራ ነው። "
ሜጀር ጄኔራል ካሣዬ ጨመዳ… See more
የሰላምና ፀጥታው አስተማማኝ እንዲሆን የምሽት መብራቶች አይተኬ ሚና አላቸው።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ከዚህ በፊት ተሰርተው አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ ከ72_49 ያሉ የምሽት መብራቶች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደረገ። ይህንን አይነት አገልግሎት ማስጀመር ህብረተሰቡ ያለስጋት መግባትና መውጣት እንዲችል ብሎም የአካባቢው ፀጥታ እንዲከበር አይተኬ ሚና እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አስተዳደር ባለስልጣን የመብራት ጥገና አስተባባሪ አቶ ጌቱ ገብሬገልፀዋል ።
25/08/2017 ዓ.ም
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በከተማችን በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶንን እየጎበኙ ነው !
የአዲስ አበባ ፈጣን ዕድገት በህዝባችን ብቻም ሳይሆን ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ፣ አንዳንድ ሀገራትም ተሞክሮውን ለማስፋትም እንደሚፈልጉ እየተናገሩለት የሚገኝ አንፀባራቂ ድል ነው።
የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የተረዳው ህዝባችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እንዲፋጠን ቀን እና ሌት 7/24 እየተጋ ከሚገኘው አመራራችን ጎን ተሰልፎ ርብርቡን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሌሎችም በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች የቅርብ ክትትል የተጠናቀቀው የካዛንችስ ኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ደግሞ በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለምርቃት በቅቷል።
ካዛንችስ አሁን ላይ በአዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። ከጥልቅ ጉስቁልና ተላቅቃ የከተማችን ድምቀት መሆን ችላለች።
በካዛንችስ እና አካባቢው የተገነቡ 40 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የአስፓልት ፣ 81 ነጥብ 9 ኪ /ሜ የእግረኛ ፣ 20 ኪ /ሜ የሳይክል መንገዶች የህዝባችንን እና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን አሳልጠዋል።
ለካዛንችስ የልማት ተነሽዎች በተሻለ የመኖሪያ አካባቢ የተሻለ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ሲሆን ፤ በንግድ ስራ ተሰማርተው ለነበሩት ደግሞ ለካዛንችስ አዲስ ገፅታ የተሻለ የኢኮኖሚ መነቃቃት መፍጠር የሚያስችሉ ሱቆች ተገንብተዋል።
በካዛንችስ እና በአካባቢው የነበሩ የመሰረተ ልማት ችግሮችን የሚያቃልሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች ፣ 15 የህፃናት መጫዎቻ ፣ 40 የመኪና ማቆሚያ ፣ 19 መፀዳጃ ቤቶችም ፣ የስፖርት ፓርክ ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እና ሌሎችም ተገንብተዋል።
የአዲስ አበባ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አመራሮች እና አባላትም የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ የአዲስ አበባን ስምና ግብር እያገናኙ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
