1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
በመዲናዋ የሠራተኞችን ደኅንነት በማያስጠብቁ ገንቢዎች ላይ ምርመራ ሊደረግ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከሀምሌ 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ቦታዎችን የሚመረምር አዲስ ግብረ-ሃይል ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል።
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አበበ እሸቱ እንደገለፁት ይህ አዲስ ግብረ ኃይል በኮንስትራክሽን ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ የሠራተኞችን ደኅንነት የማያስጠብቁ ወይም የደኅንነት ህጎችን የማያሟሉትን እንደሚለዩ ተናግረዋል።
ይህን ግብረ-ኃይል ማሰማራት ያስፈለገው እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምሮ ደኅንነታቸው ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ ሠራተኞችን እስከ ሞት ድረስ የሚያጋልጥ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ እና ይህንም በአስቸኳይ መከላከል አስፈላጊ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ አደጋዎች በማመላከታቸው ነው ተብሏል።
በኮንስትራክሽን የሥራ ዘርፍ ከተሰማሩት ሠራተኞች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት መደበኛ የደኅንነት ሥልጠና እንዳልወሰዱ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፥ "በከተማችን የግንባታ ስራዎች በሚካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የተለያዩ አደጋዎች ይከሰታሉ፣ ስጋቶችም አሉ። ለዚህ መንስኤው ሰራተኞች ስልጠና አለመውሰዳቸው እና ገንቢዎች ለሰራተኞች ደህንነት ብዙም የማይጨነቁና የደህንነት መጠበቂያ ግብአቶችን በበቂ መጠን ባለማቅረባቸው ነው" ሲሉ ነው የገለጹት።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ከተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ሠራተኞችን በመመደብ 2681 ግንባታዎችን መመልከት መቻሉን አንስቷል።
ከእነዚህ ውስጥም 1300 አካባቢ የሚሆኑት ብቻ ለሠራተኞቻቸው ሄልሜንት እና አንፀባራቂ ማሟላት የቻሉት። ይህ ማለት ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጎችን እያከበሩ አይደለም። አብዛኞቹ ሠራተኞች አደጋ ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል ያሉት ም/ ዋ/ ዳይሬክተሩ ፥ የህንፃ ግንባታ ደኅንነት ያልጠበቀ ኮንተራክተር ወይም አልሚ የ50 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣልበት በህግ ደረጃ ተቀምጧል ብለዋል።
ባለስልጣኑ ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 28/2017 ዓ.ም 500 ለሚሆኑ ስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ለሪል ስቴት አልሚዎች እና የምህንድስና የሙያ ማህበራት ባዘጋጀው "የግንባታ ስራ ቦታ ደህንነት (safety)" የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ዘመናዊ የከተማ ግንባታን ለማሳካት በምናከናውናቸው ትላልቅ የህንፃና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎቻችን ጎን ለጎን ቅድሚያ የምንሰጠው የዜጎቻችንን ደህንነት የማስጠበቅ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ በኋላ የከተማችን ነዋሪዎች ደህንነት (Public safety) አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ግብረሐይል ተቋቁሞ በከፍተኛ ትኩረት ስራውን እንደሚያከናውን አስታውቀው ነበር።
ግብረሐይሉ ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተውጣጣ ሆኖ እንደሚቋቋም በተገለፀው መሠረት የተቋቋመ ነው።
ከዚህ በሁዋላም ይህ አዲስ ግብረ ሀይል በሚለያቸው የደህንነት መስፈርት ባላሟሉ የግንባታ ቦታዎች ላይ እና ለአደጋ አጋላጭ በሆነ ሁኔታ ግንባታ በሚያከናውኑ አልሚዎችና ስራ ተቋራጮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ኢንጅነር አበበ እሸቴ ያስታወቁት።
በመዲናችን አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቱ ከመሰረተ ልማት ግንባታና ዝርጋታ አኳያ እየተጠናከረ የመጣው ቅንጅታዊ ስራ ምን ፋይዳ አስገኝቷል ?
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከፋና ኤፍኤም 98.1 በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸውን አንኳር ሃሳቦች ይከታተሉ።👉
ከሁሉ በላይ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !
በዘንድሮው በጀት ዓመቱ 241.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን 233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 % ማሳካት ተችሏል።
ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት 83.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ እድገት ያሳየ ነው። ያልተሰበሰበው 8 ቢሊዮን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ ነበር።
ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል።
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች፤ ውድ ግብር ከፋዮቻችን፤ ውድ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ውድ ባለድርሻ አካላት ለተገኘዉ ስኬት በራሴ እና በከተማው አስተዳደር ስም እዲሁም በከተማችን ነዋሪዎች ስም አመሰግናለሁ።
ነገም አቅማችን እናንተው ናችሁና ፤ ችግሮችን እያረምን በራስ አቅም፣ በትብብር፣ በጠንካራ እምነት እና የስራ ባህል እየመራናት የከተማችን እድገት ይቀጥላል !!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲመሩ የየቆዩት አቶ ዮናስ አለማየሁ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተሹመዋል።
አቶ ዮናስ አለማየሁ የቀድሞ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ተቋም ከነበረበት በርካታ ችግር መሻገር እንዲችል የሪፎርም ፕሮግራምን በመንደፍ፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ ጽ/ቤት ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞችን በማስተባበር እና በርካታ የአሰራር ለውጦችን በማደርግ በተለይም በሌብነት ላይ ግልፅ የሆነ የማይታገስ አቋም በመያዝ ኤጀንሲው አሁን ላለበት መሻሻል ሚናቸውን ተጫውተዋል።
ከዚህም ባሻገር የፋይዳ ምዝገባ ስርዓት በከተማው በተቀናጀ መልኩ መመራት እንዲችል እንዲሁም ተቋሙን የሚረከቡ ተተኪና ብቁ አመራር በማፍራት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አቶ ዮናስ አለማየሁ በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርነት ቆይታቸው በተቋሙ ለተካሄደው የሪፎርም ስኬት ፣የተቋም ግንባታ ስራዎች እና የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊነትንና ግልፅነት የተላበሰ እንዲሆን ለተወጡት ብቃት ያለው የአመራርነት ሚና ያለውን አድናቆት አየገለፀ አዲስ በተመደቡበት የስራ ሃላፊነት ውጤታማ የአመራርነት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ክላስተር የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ ያለፉት 3 ሳምንት የስራ አፈፃፀም የ12 ተቋማት ሃላፊዎች በተሳተፉበት በዙም ገምግመዋል።
በግምገማው በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ የ3 ሳምንት ስራዎች አፈፃፀም በከተማ ፅዳት ውበትና ፣የአረንጓዴ ልማት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ፣ የአደጋ ስጋት መከላከል እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ፣ የፋይዳ ምዝገባ ስራዎች እና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ህገወጥነትን መከላከል ላይ ያተኮረ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የ90 ቀናት የልዩ ንቅናቄ እቅድ የስራ አፈፃፀም በተለዬ የስራ ተነሳሽነት፣ ትጋት እና በጥብቅ ዲስፕሊን እየተመራ መሆኑን በየጊዜው እየገመገምን ያለነው የእቅዲ በውጤታማነት መፈፀም በህብረተሰባችን ህይወትና የአኗኗር ዘይቤ ላይ የሚያመጣውን ከፍተኛ የሆነ እምርታዊ ለውጥ ስለምንገነዘብ ነው ብለዋል።
አክለውም እቅዱን መተግበር ከጀመርን የአንድ ወር ጊዜ ያህል እንደመሆኑ በ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ፣ የከተማ ፅዳት እና ውበት ስራ ፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ስራዎች፣የፋይዳ ምዝገባ እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት ስራዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ አበረታች አፈፃፀሞች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ስራዎች፣ የአደጋ ስጋት እና የጎርፍ መከላከል ስራዎች፣ ከአካባቢ ጥበቃና የወንዞችን ብክለት ሙሉ በሙሉ ከመከላከል ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችም ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በማጠቃለያቸውም በእቅድ አፈፃፀማችን በሪፖርት የሚላኩ ስራዎችን በመስክ ምልከታ እያረጋገጡና አሳታፊነትን እና ግብረ መልስን መሠረት ያደረገ የማስተካከያ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሄድ በትኩረት እንዲሰራበትም አስገንዝበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ የ90 ቀናት የልዩ ንቅናቄ አጀንዳ ስራዎች መሠረት መዲናችንን ከማንኛውም አይነት የአደጋ ስጋት ከመከላከል ጎን ለጎን የተቋም ግንባታን አጠናክሮ የማስቀጠል ተግባር ያለበትን ደረጃ ለማረጋገጥ የሚያስችል የመስክ ምልከታ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተካሄደ።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በአራት ክፍለ ከተሞች ማለትም በጉለሌ ፣በአዲስ ከተማ፣ በልደታና በአቃቂ ክፍለ ከተሞች ተገኝተው በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተለይም የአካባቢ ጽዳት፣ የአደጋ ስጋት መከላከል፣ የጎርፍ መከላከል ስራዎች እና የፋይዳ ምዝገባ አሁናዊ ንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ተገኝተው ከተቋም ግንባታ ጋር በተያያዘ ምቹ የስራ ሁኔታን የመፍጠር፣ በአደጋ መከላከል ስራው የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር እና የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ መከላከልን ጨምሮ የ90 ቀናት እቅድ ስራዎች በተቋማት፣ በአመራሩና በባለሙያው ተገቢው ተግባቦት እና ቅንጅት ተፈጥሮ እየተከናወነ ስለመሆኑም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማም እንዲሁ በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ በጽዳት አስተዳደር እና የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ ቤት የስራ እንቅስቃሴን የጎበኙት ኢንጅነር ወንድሙ በዚህም በ90 ቀናት የተያዙ የንቅናቄ አጀንዳ ከመደበኛው ስራ ጎን ለጎን እየተፈፀመ ስለመሆኑም ከባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ባካሄዱት ውይይት አረጋግጠዋል ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በኩልም በ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ የተያዙ የአካባቢ ፅዳት፣ የአደጋ ስጋት መከላከል ስራዎች፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ስራዎች፣ የፋይዳ ምዝገባ፣ የማዕድ ማጋራት ፣ ቤት እድሳት ፣ደም ልገሳ እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች በሪፖርት ቀርቧል።
ኢንጅነር ወንድሙ በዛሬው እለት ባካሄዱት የመስክ ምልከታ የልደታ እና የአቃቂ የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የስራ ቦታ አመቺነት፣ የአደጋ ስጋት እና የጎርፍ መከላከል እንዲሁም የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ከተመለከቱ በሁዋላ የእሳት አደጋ ቅርንጫፍ ፅ/ ቤቶች ተቋማዊ አቅም በማጠናከር ምቹ፣ ዘመናዊና ብቃት ያለው የአደጋ ስጋት መከላከል ተቋም የመገንባትን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ በርብርብ ማከናወን አንደሚገባ በአፅንኦት ገልፀዋል።
ከ90 ቀናት ስራዎችም ጋር በተያያዘ በሁሉም አካታች መስፈርት ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ የሞዴል ብሎኮችና ወረዳዎችን የመለዬት ስራን እና የፍሳሽ መስመሮች ማፅዳትና እና ወንዞችን ሙሉ በሙሉ ከብክለት መታደግ ፣ የአደጋ ስጋትን አስቀድሞ የመለየትና መከላከል፣ የፋይዳ ምዝገባን የማጠናከር እና የህብረተሰብ ተሳትፎን በሁሉም ስራዎች የማጎልበት ጉዳይ በከፍተኛ መሰጠት እና የስራ ተነሳሽነት በትኩረት እንዲፈፀም አሳስበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
"ከተማችን አዲስ አበባን የህፃናትና ወጣቶች ተስፋ የሚለመልምባት ለማድረግ በትኩረት እየሰራን ነው" በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በልደታ ክ/ከተማ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክቶችና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ምርቃት ተካሄደ
በምርቃት ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ የማህበረሰቡን ህይወት የሚለውጡ ሁሉንም አካታች የልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለው ከነዚህም ውስጥ የወጣቶችንና የታዳጊ ህፃናትን ተስፋ የሚያለመልሙ ፕሮጀክቶችን በልዩ ትኩረት እያከናወነ ነው በማለት ገልፀዋል።
ባለፍት ዓመታት በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እና የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክቶችን አከናውነናል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚህም የወጣቶችንና የህፃናትን ተስፋ ማለምለም ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት እስከ 2030 ዓ.ም ለህፃናትና ወጣቶች ምቹ ከተማ ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ ልማቶች ሁሉ ወጣቶችንና ህፃናትን ተጠቃሚ ያደረጉ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በምንሰራቸው የማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክቶች የህፃናት መቀንጨር ቀንሷል ወጣቶች እና ህፃናት ብሩህ አእምሮና ጠንካራ ሰውነት እንዲኖራቸው ማድረግ ተችሏል ብለው ወጣቶችን አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ እና በአካል እንዲጎለብቱ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን የማከናወን ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ተናግረዋል።
ዛሬ ያስመረቅናቸው ፕሮጀክቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ብለው ማህበረሰቡ ልማቶቹን ተንከባክቦ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ በማስቻል ረገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን በመንግስት እና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የወጣቶችንና ህፃናትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል ብለው ፕሮጀክቶቹም የወጣቶችንና የህፃናትን ተስፋ በማለምለም የብልፅግና ጉዞን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው በማለት ገልፀዋል።
በዛሬው እለት ያስመረቅናቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ ለሀገር ተረካቢ ህፃናትና ወጣቶች የሰጠውን ትኩረት የሚያሳዩ ናቸው ብለው ነዋሪው እነዚህን ሀብቶች ጠብቆ በማቀየት ለመጭው ትውልድ እንዲያስተላልፍም ጥሪ አቅርበዋል።
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ 122 የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና 1 ሺህ 155 የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ወጣቶች እና ህጻናት እንኳን ደስ አላችሁ !
በአዕምሮ እና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በሰጠነው ልዩ ትኩረት ዛሬ በ11 ክ/ከተማ ተመርቀው ለወጣቶች እና ህፃናት ክፍት ተደርጏል::
👉 122 የስፖርት ማዘውተሪያዎዎች
👉1155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላት
👉ባለፋት 2 ዓመታት ደግሞ ለህፃናት መጫወቻ በድምሩ 3,789
👉ባለፉት 3 ዓመታት ደግሞ የስፖርት ማዘውተሪያ 1,530 ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት ተደርጏል።
የዚህ ሥራ ውጤት ሰው ተኮር መሆናችንን ያስመሰከረ እና የገባነውን ምግ በተግባይ ለመፈፀማችን አንድ ማሳያ ነው።
