uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
የከተማችን አንዱ ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ውብ፣ ደማቅና ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች ተከብሮ ተጠናቅቋል:: የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ ሆኖ እንዲከበር አስተዋፅዖ ያደረጋችሁ የሀይማኖት አባቶች፣ የከተማችን ወጣቶች፣ ስታስተባብሩ የነበራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ያደረጋችሁ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማችን ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content

ለመላው የአዲስ አበባ ከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለደመራ/መስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ። እኛ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ፣ ሃይማኖት እና ባህል ቢኖረንም ከሌላው አለም ለየት የሚያደርገን በፍቅር፣ በአብሮነት፣ በወንድማማችነት፣ በመተሳሰብ እና በመከባበር የምንኖር መሆናችን ነው። በዚህም አንዳችን ለሌላው በመተሳሰብ ሃይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ ትውፊቶቻችን ፣ስነ ስርዓቶችና በዓላት በድምቀትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር መልካም ምኞት ከመግለፅ ባሻገር ለስኬቱ ተግባራዊ ድጋፍ የምናደርግ መሆናችን ነው። እንደሚታወቀው የመስቀል/ደመራ በአል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገበ በአለም አደባባይ ከፍ ብለን የምንታይበት የጋራ ሀብታችን ነው። በአሉ ከመንፈሳዊነቱ ባለፈም ማህበራዊ እሴቱ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙም የላቀ ነው።ስለዚህም በአሉ በሰላም፣ ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት መላው መዋቅሩን አስተባብሮ አስፈላጊው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን ዝግጅቱን ሁሉ ማጠናቀቁን እየገለጽኩ በአሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንልን በድጋሚ እመኛለሁ! መልካም በአል! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

photo content
+7

የመዲናችን ጽዳት በዘላቂነት ለመጠበቅ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ቆሻሻን ሰብስቦ ከማስወገድ ባለፈ መልሶ መጠቀም (Recycle)ላይ በስፋት በመስራት ዘርፉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ሃብት እንዲፈጥር ማድረግ ይገባል - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን የገለጹት በዛሬው እለት በጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ተገኝተው የስራ ጉብኘት በማድረግ ከኤጀንሲው ሠራተኞች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው። አክለውም በጽዳቱ ዘርፍ በከተማችን የመጣ ተጨባጭ ለውጥ ቢኖርም ከእያንዳንዱ ነዋሪ የሚወጣውን ቆሻሻ ከምንጩ በመቀነስ እና በተለይም ለኮምፖስት ምርት እና በመልሶ መጠቀም ማዋል ረገድ እየተሰራ ያለው ስራ ግን አሁን ካለበት በላቀ ሁኔታ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል ሲሉም በአጽንኦት ገልፀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም የኤጀንሲው ባለሙያዎች በተለያዩ ጊዜያት በጃፓን የወሰዱት የአቅም ግንባታ ስልጠና ያገኟቸውን የልምድ ቅመራ ወደ ተግባር በመቀየር አሁን በመዲናችን ከ12 በመቶ ያልበለጠውን የቆሻሻ መልሶ መጠቀም ትግበራ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ሃብትን ከብክነት መታደግ እንደሚገባም አሳስበዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በማጠቃለያቸው በመዲናችን የቆሻሻ መልሶ መጠቀም እና አወጋገድ ስርአትን ዘመናዊ፣ሙያዊ እና ሳይንሳዊ መንገድን የተከተለ እንዲሆን የተጀማመሩ ስራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በይበልጥ እንዲጎለብት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት በልዩ ትኩረት እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+7

አዲስ አበባ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በተግባር የሚተረጎምባት ከተማ ናት - አቶ ሞገስ ባልቻ በዓላት እንኳን አደረሳችሁ ፣ እንኳን አደረሰን በሚል የምንጠያየቅባቸው የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት ናቸው። የአደባባይ በዓላት ከሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸው ባሻገር ወንድማማችነት እና እህትማማችነትንም በእጅጉ ያጠናክራሉ። በዓላትን ከቤተሰብ ፣ ከጎረቤት ፣ እንዲሁም ከአቅመ ደካሞች ጋር ማሳለፍ እና በአብሮነት ማድመቅ የነበረና የሚኖር እሴታችን ነው፡፡ የበዓላት የአብሮነት መገለጫ የሚጀምረው ከበዓላቱም ቀደም ብሎ ነው። በነገው ዕለት ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የፅዳት መርሀ ግብር ተካሂዷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በፅዳት ፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ እንኳን ለደመራው ዋዜማ አደረሰን አደረሳችሁ በማለት ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችንም ከተማችንም ልዩነት በህብር የሚደምቅባቸው መሆናቸውን በመጠቆም የመስከርም ወር በርካታ የአደባባይ በዓላት የሚከበሩበት መሆኑንና የዓለም ቅርስ የሆነው መስቀል ደመራም አንዱ መሆኑን አውስተዋል። አዲስ አበባ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በተግባር የሚተረጎምባት ከተማ መሆኗን ያስገነዘቡት ሀላፊው የመስቀል ደመራን በዓል በድምቀት ለማክበር ህዝባዊ ውይይቶች መከናወናቸውንና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ መደረጉን አስረድተዋል። አዲስ አበባ እየፀዳች እየተዋበች ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሀይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለእሬቻም ቅድመ ዝግጅት በሚሆን መልኩ ለመስቀል ደመራ ማክበሪያ ለፅዳት የመጡትን ሁሉ በማመስገን በሰላም እንዲከበርም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አቶ ሞገስ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ የሁሉም ሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች በፅዳት ፕሮግራሙ የተገኙት መልካም ምኞታቸውን ለመግለፅ እንዲሁም በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ቦታውን አፅድቶና አስውቦ ለመቀበል መሆኑን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መምህር የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ሀገራችን ብዙ ሀይማኖት ፣ ብዙ ቋንቋ ብዙ እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗን አውስተው በመስቀሉ የምናስተላልፈውም የምንሰብከውም ሰላምን በመሆኑ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ቤተክርስቲያኗም መንግስትም ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።:: በፅዳት ፕሮግራሙ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

photo content
+8

ማምሻውን ካዛንቺስ አካባቢ በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የሚነሱ የተወሰኑ ተነሺዎችን ቤት ጎብኝተናል:: ከሚያማምሩ ፎቆች ጀርባ እጅግ በጣም አሳዛኝ እግር መዘርጊያ እንኳን የሌላቸው፣ በቆርቆሮ እና በሸራ የተለበዱ ያረጁ ፣ መፀዳጃና መኖሪያ ቤት የተቀላቀሉ ፣ መፀዳጃ የሌላቸዉ በቆጥ ላይ ሳይቀር የሚኖሩ እንዲሁም ማብሰያ ቦታ ሳይኖር የሚኖሩበት አስቸጋሪ እና ለመኖር ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አይተናል:: እኛ ጎብኝተን ለመውጣት እንኳን አስቸጋሪ መሆኑን አየን እነሱ ግን ለረዥም አመታት እንደኖሩበት ስናስብ በእጅጉ አዝነናል:: ይህንን ሁኔታ ከመቀየር በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ምንም ስራ የለምና እንደተለመደው ሁሉ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ይህንን አካባቢ በመቀየር ለነዋሪዎችና ለኑሮ ምቹ እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+4

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2017 አ.ም የዝግጅት ምእራፍ ስራዎችን ከአጠቃላይ ካውንስል አባላት ጋር በዛሬው እለት በጋራ ገምግሟል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመሩት በዚህ መድረክ ላይ የጽ/ ቤቱ የበጀት አመት ያለፉት 2 ወራት የእቅድ አፈጻጸም በየዳይሬክተሮች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩ ያለፉት ሁለት ወራት የተቋሙ እቅድ ከማእከል እስከ ታችኛው መዋቅር ያለው ተናባቢነት፣ የቅንጅታዊ ስርአት መጠናከር፣ የተቋማት ሪፎርም መጎልበት፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ በትኩረት ለመምራት እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት የተሻሉ መሆናቸውን ተመልክቷል። በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተጠናከረ ቁርጠኝነት እና በተነሳሽነት ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባም አቅጣጫ ተቀምጧል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+8

አስተማማኝ ሰላማችንን አፅንተን ዘላቂ ለማድረግ ከፀጥታ መዋቅሩ ባሻገር ህዝባችን የሰላምና ፀጥታ ባለቤትነቱን ሊያጠናክር ይገባዋል - ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ እና ህብረብሔራዊ አብሮነትን እንዲያጠናክሩም በየአካባቢው የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከሰላም ሰራዊት ተወካዮች ጋር በተደረገው ከተማ አቀፍ መድረክ ላይ እንደተናገሩት የሰላም ሰራዊቱን አቅም በማጎልበት በተቋማዊ አቅም እንዲመራ ባለፈው ዓመት በንድፈ ሀሳብ ፣ በተግባር ስምሪት እንዲሁም ግብአቶችን ለማሟላት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል። ባለፈው ዓመት በከተማችን የተከበሩ የአደባባይ በዓላት በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ የሰላም ሰራዊቱ የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ሊዲያ የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል እና የፍቅርና የአንድነት መገለጫ የሆነው የእሬቻ በዓል ዘንድሮም በተሻለ ድምቀት እንዲከበሩ አይነትና ቅርፃቸውን የሚለዋውጡ የወንጀል ድርጊቶችንና የአፍራሽ ሀይሎችን ሰላምን የማደፍረስ ሙከራ እንደተለመደው ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅተው በማክሸፍ ዘላቂ ሰላምን እንዲያስቀጥሉ አስገንዝበዋል። ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ እሳትና መሰል ድንገተኛ አደጋዎችም እንዳይከሰቱ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ያስረዱት ሀላፊዋ የህዝብ ሀብት የወጣባቸውና የከተማችንን ገፅታ በእጅጉ የቀየሩ መሰረተ ልማቶችንም በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። አስተማማኝ ሰላማችን አፅንተን ዘላቂ ለማድረግ ከፀጥታ መዋቅሩ ባሻገር ህዝባችን የሰላምና ፀጥታ ባለቤትነቱን ሊያጠናክር እንደሚገባ ያስገነዘቡት ሀላፊዋ የሰላም ሰራዊቱ በሶስት ፈረቃ አካባቢውን ተደራጅቶ ለመጠበት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚዴቅሳ ከበደ በበኩላቸው ህዝባችን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅቶ ሰላሙን በማስጠበቁ ከተማችን እንደ ስሟ እያበበች መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል ብለዋል:: የፀጥታ መዋቅሩ ፣ ህዝባችንና ከእሱ የወጣው ለከተማችን ሰላም ዘብ የቆመው የሰላም አንባሳደሩ የሰላም ሰራዊት የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አቶ ሚዴቅሳ አስገንዝበዋል ። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+1

photo content
+9

በመጭው ቀናት የሚከበሩት የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት በወንድማማችነት እና እህትማማችነት መንፈስ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናገሩ:: በአዲስ አበባ ከተማ በመጭው ቀናት የሚከበሩትን የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የሚያስችል ህዝባዊ ውይይት በዛሬው እለት በ11ዱም ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይቱ ላይ የተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወኑ እንዲሁም ህዝባዊ ውይይት መከያሄዱ በአላቱን በሰላም ፣በአንድነት በህብረት ባማረ መልኩ ለማሳለፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በዓላት በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገቡ መሆናቸው ከኃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓት ከማሻገር በተጨማሪ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኝዎ ስለሚታደሙ የሀገር ገፅታ ከፍ ከማድረግ ባሻገር ትልቅ የቱሪዝም ገቢ በማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ ስለሚኖራቸው በአብሮነት ስሜት ሊከበሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት አዲስ አበባ ከተማ እንግዶቿን ተቀብላ ለማስተናገድ የተለያዩ የቅደመ ዝግጅት ስራው ከወዲሁ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et በመጭው ቀናት የሚከበሩት የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት በወንድማማችነት እና እህትማማችነት መንፈስ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናገሩ:: በአዲስ አበባ ከተማ በመጭው ቀናት የሚከበሩትን የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የሚያስችል ህዝባዊ ውይይት በዛሬው እለት በ11ዱም ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይቱ ላይ የተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወኑ እንዲሁም ህዝባዊ ውይይት መከያሄዱ በአላቱን በሰላም ፣በአንድነት በህብረት ባማረ መልኩ ለማሳለፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በዓላት በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገቡ መሆናቸው ከኃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓት ከማሻገር በተጨማሪ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኝዎ ስለሚታደሙ የሀገር ገፅታ ከፍ ከማድረግ ባሻገር ትልቅ የቱሪዝም ገቢ በማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ ስለሚኖራቸው በአብሮነት ስሜት ሊከበሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት አዲስ አበባ ከተማ እንግዶቿን ተቀብላ ለማስተናገድ የተለያዩ የቅደመ ዝግጅት ስራው ከወዲሁ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+3

በሰፊው የታረሰ የስንዴ ማሳችን። የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለን ቁርጠኝነት ውጤት። Oyiruu qamadii keenyaa bal'inaan qotame. Bu'aa kutannoo wabii nyaataa mirkaneessuuf qabnu mul'isa. Our expansive wheat fields. A product of our commitment to ensuring food security

photo content
+4

በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በቀጣይ በመዲናችን ባማረ እና በደማቅ ሁኔታ በሚከበሩት የመስቀል/ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ። የሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ወሰን መግራ በመሩት በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ሁለቱም በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸው እና እሴታቸው ተጠብቆ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በሚከበሩበት ዙሪያ ከሠራተኞች በሚጠበቀው ሚና ላይ ውይይት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት አቶ ወሰን መግራ እንደገለጹት የመስቀል/ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የአደባባይ በዓላት እና በዩኔስኮ የተመዘገቡ ታላላቅ በአላት እንደመሆናቸው ለበአላ አከባበር ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገራት ወደ መዲናችን የሚመጡ እንግዶችን በአግባቡ ማስተናገድ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ በዚህ ረገድ ሠራተኛውም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ስላለበት ይህን የውይይት መድረክ ማካሄድ አስፈልጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርቦ ምላሽ እና ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ተሳታፊዎችም በአላቱ በደመቀና ባማረ ሁኔታ እንዲከበሩና በዚህም የከተማችንን በጎ ገጽታ ማጉላት እንዲቻል የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንወጣለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et