1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር የነበራቸውን ቆይታ በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ።
See less
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚፈጠሩ የሰራተኛ የዲሲፕሊን ግድፈቶችን እንደማይታገስ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጽ/ቤት የካቲት 26 ከረፋዱ 10:52 በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ተፈጠሮ የቀረበውን የተገልጋይ ቅሬታ መነሻ በማድረግ ጉዳዩን የተከታተለ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በማሰባሰብ ኤጀንሲው በወቅቱ አቶ ናትናኤል በቀለ በጽ/ቤቱ የፈፀሙት ጥፋት ከባድ ጥፋት በመሆኑ የዲሲፕሊን ክስ ሂደትን ሳይጠብቅ ከስራ በማገድና መጋቢት 4/2017ዓ.ም ጉዳያቸው ለዲሲፕሊን እንዲቀርብ በማድረግ እርምት እንዲወሰድ ተደርጎል::
ይህንኑ ሁኔታ አስመልክቶ ድርጊቱ ከተፈፀመና እርምት ከተወሰደ ከ20 ቀናት በኋላ ዛሬ መጋቢት 16/2017ዓ.ም ኢቲቪ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ማብራርያን አካቶ ለነዋሪው ለማድረስ በዜና እወጃ ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂቸር ወንድሙ ሴታን አቅርቧል።
https://youtu.be/C0lhiEhE3X0?si=-4fPn-IFQ-89hazy
ተቋሙ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሰራተኛ ስነ-ምግባር ላይ የሚቀርቡ ከፍተኛ ቅሬታን ለመፍታት በስልጠና ከማብቃት ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ መሆኑን ገልፆ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጽ/ቤት እንዲሁም በ119ኙም የወረዳ ጽ/ቤቶቻቸው የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዕከል በካሜራ ዕይታ የሚከታተል ሲሆን የአገልግሎት ቅሬታ ሲፈጠርም ተጠያቂ የሚያደርግበት ግልፅ አሰራር በመዘርጋት ሙሉ ለሙሉ ችግሮችን መቅረፍ ባይችልም በአገልግሎቱ ላይ ቀላል የማይባሉ መሻሻሎች ማስመዝገቡን ገልጿል።
ኤጀንሲው ምንም እንኳን የሚድያ ተቋማት የሚሰጡትን ጥቆማ እና ቅሬታዎች በበጎነት ተቀብሎ ለማረም ሁሌም ዝግጁ ቢሆንም ተቋማት መጠናከር የሚችሉት ዜጎች በቅድሚያ ተቋማት የዘረጓቸውን የቅሬታ አፈታት ስርዓት መገልገል ሲችሉ ነው ብሎ ያምናል።
ተቋሙ ኢቲቪ ለሰጠው ሽፋን እና የጥቆማ መንገድ አድናቆቱን እየገለፀ ማንኛውም ቅሬታ ወይም ጥቆማ ሲኖር በ7533 መደወል የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን የከተማችን ተገልጋዮች የአንድ ሰራተኛ የዲሲፕሊን ግድፈት የተቋሙን ሙሉ የአገልግሎት አሰጣጥ የማይገልፅና ህብረተሰቡ ምስጋና የሚቸራቸው ታትረው በቅንነት የሚያገልግሉ በርካታ ሰራተኞችም ያሉ መሆኑን በመረዳት መሰል ክፍተቶችን ለማረም አሁንም ኤጀንሲው አበክሮ የሚሰራ መሆኑን በአክብሮት ይገልፃል።
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጃፓን አለም ዓቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ)ጋር በዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር፣ በአቅም ግንባታ እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ በጋራ የሚሰሩበትን ሁኔታ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በፅ/ቤታቸው የጃፓን አለም ዓቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ የልኡካን ቡድን አባላትን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱ ወቅት የጃፓን አለምዓቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደርን በማዘመን ረገድ የተቋማትን ቅንጅት በማጠናከር፣ የፖሊሲና የህግ ማእቀፎች ትግበራ፣ በአቅም ግንባታና የህዝብ ተሳትፎን በማጠናከር ረገድ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።
መጋቢት 16/ 2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ ተካሄደ
------------------------------
መጋቢት 15 ፣ 2017 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ፤
በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጋራ በመሆን በረቂቅ አዋጁ ላይ የአስረጂ መድረክ አካሂደዋል፡፡
በመድረኩም ላይ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ፈትያ አህመድ የአስረጂ መድረኩን አስፈላጊነት እና ዓላማ በረቂቅ አዋጁ ላይ ጥልቅ ምልከታ በማድረግ ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በማግኘት አስፈላጊ እና ተጨማሪ ግብዓት በመሰብሰብ ረቂቅ አዋጁን ለማጠናከር መሆኑን ገልፀዋል።
የከተማ፣ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው ሀገር ያለችበትን የኢኮኖሚ ግስጋሴ እና የከተሞች መስፋፋት እንዲሁም የማኅበረሰብ ዕድገት ማዕከል ያደረገ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ሆኖ ሲወጣ የከተሞችን ብሎም የሀገርን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ በሚያስችል ዓውድ መቃኘት ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ በረቂቅ አዋጁ ላይ አስፈላጊ ግብዓቶችን በመሰብሰብ ጠንካራ አዋጅ ማዘጋጀት ይቻል ዘንድ የአስረጂ መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
በዚህም መሠረት በረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅነት ያሻቸዋል የተባሉ በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች እና ከባለሙያዎች ተነስተዋል።
በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአካባቢ ሕግና ደረጃ ዴስክ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ታደሰ፤ ነባሩን አዋጅ ቁጥር 513/1999 መቀየር ካስፈለገባቸው ገፊ ምክንያቶች ውስጥ ከከተሞች መስፋፋት ጋር በተያያዘ የሚመነጨው የቆሻሻ ማመንጨት መጠን መጨመርን ተከትሎ ነባሩ አዋጅ ይህን ለማስተካከል ጉድለቶች ስላሉበት መሆኑን ጠቁመዋል።
እንዲሁም ቆሻሻዎች በአንድ ቦታ ሲከማቹ በሚኖረው መታመቅ እና በሚፈጠረው ሙቀትና መርዛማ ጋዝ አማካኝነት ለአየር ንብረት ብክለት አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ አቶ ወንድወሰን ጠቅሰው፣ ቆሻሻውን ከምንጩ ለመቀነስና የአያያዝና የአወጋገድ ስርዓቱን ማሻሻል ማስፈለጉ ሌላኛው ምክንያት መሆኑን አንስተዋል።
በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ኢ/ር) ነባሩ አዋጅ 18 ዓመታት ገዳማ ዕድሜ ያስቆጠር እንደመሆኑ ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ የገጠሩን የሀገሪቱን ክፍል ብዙ ትኩረት ያልሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አረንጓዴ ፣ ፅዱና ውብ ኢትዮጵያን ለትውልድ ከማስተላለፍ አኳያ ተመጣጣኝ የሆነ ሕግ ማስቀመጥ ማስፈለጉንም ዳይሬክተሯ አስረድተዋል።
በመጨረሻም፣ በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦች ረቂቅ አዋጁን የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዙ መሆናቸውን በመጠቆም የተነሡትን ጥያቄዎች ፣ አስተያየቶችና ግብረ-መልሶች በመውሰድ በድጋሚ ረቂቁን እንደሚያስተካክሉ ገልፀዋል
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የጎማ ሪሳይክል ማሽን የሰሩ
ይህ ማሽን ጥቅም ላይ የዋሉ ጎማዎችን በመጠቀም ለህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ለ rubberized አስፓልት እና የእግረኞች መንገድ ታይልስ ለመስራት የሚውል ማቴሪያልን የሚያመርት ነው። ይህንን ማሽን እንዲሰራ መነሻ የሆነውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ”ክህሎት ኢትዮጵያ” ጉብኝት ባደረጉ ጊዜ የሰጡት አቅጣጫ ነው። አስራ አምስት ማሽኖችን በውስጡ የያዘው ፕሮጀክቱ የማሽኑን ዋና ዋና አካላት ለማምረት 2 ወራት ብቻ ፈጅቷል። ማሽኑ 500 ኪሎ ግራም በሰዓት የማምረት አቅም አለው።
This machine repurposes used tires to produce materials for playgrounds, rubberised asphalt, and sidewalk tiles. The idea for its development was inspired by the guidance of Prime Minister Abiy Ahmed during his visit to the “Skill Ethiopia” facility. The project, which includes fifteen machines, took only two months to manufacture the main components. Each machine has a production capacity of 500 kilograms per hour.
#ችግር_ፈቺ_እጆች
ለስራ ፈላጊዎች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች ባለሙያዎቾን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ባለስልጣኑ በካሳንቺስ አካባቢ የተሰራው አዲስ የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት ያደረሰው ድርጅት 510 ሺህ ብር መቅጣቱ ገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ የኮሪደር ልማት አዲስ በተሰራው የመንገድ መሠረተ ልማት ሜልኮን ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ጉዳት ያደረሰው ድርጅቱ 500 ሺህ ብር እና ሁለት ሹፌሮች እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር በድምሩ 510,000 ብር መቅጣቱ ገለፀ።
ድርጅቱ በቸልተኝነት የተሰራው የእግረኞች መንገድ ኮንክሪት ስታምፕ በማውደሙ ለፈጸመው ግዴየለሽነት ተግባር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል፡፡
ባለስልጣኑ ድርጅቱ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ ያወደመውን የእግረኞች መንገድ ከተቀጣበት ሰዓት ጀምሮ በራሱ ወጪ በመገንባት እንዲያስተካክል ውሳኔ የተሰጠው መሆኑንም አሳውቋል።
ህግ በማስከበሩ ሂደት የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ በማድረግ የአፍሪካ ብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ቀንና ሌሊት በሚሰራበት በዚህ ሰዓት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም አሳፊሪ መሆኑ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ በከተማው በልማት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች መሠል ድርጊቶች ከመፈጸም እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ደንብ በሚተላለፉት ላይ ደንብ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እራስን የመቻል እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎች በተተኪ ምርት ለመቀየር የመቻል ሀገራዊ ኅልማችን የሚሳካው ቀጣይነት ባለው ፈጠራ እና ጠንክሮ በመስራት ብቻ ነው። በ'ክህሎት ኢትዮጵያ' ውድድር እማካኝነት ወጣቶች ችሎታቸውን እና ሀሳባቸውን ወደ ትርጉም ያላቸው ተግባራዊ ፈጠራዎች ለውጠው እየተገበሩ በማየቴ ደስተኛ ነኝ።
በፈጠራ ሥራ ላይ የተሰማሩትን በርቱ እያልኩ፣ ሌሎች ወጣቶችም የማህበረሰባችንን አንገብጋቢ ፍላጎቶች እንዲመረምሩ እና ሀገራቸውን ለማገልገል የሚችሉ መፍትሄዎችን እንዲፈጥሩ አበረታታለሁ። በተጨማሪም የንግዱ ማህበረሰብን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እነዚህን እና ሌሎች ወጣት ፈጣሪዎች የማምረት አቅማቸውን ያሳድጉ ዘንድ እንዲደግፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የድጋፍ ስርዓታችንን እናሻሽል!” በሚል መሪ ቃል የዓለም የአእምሮ እድገት ውስንነት (Down syndrome) ቀንን ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር አክብረናል።
ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለሃምሳ ሰው ግን ጌጥ መሆኑን በመገንዘብ፣ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናትን በመደገፍ እና ለማህበረሰባችን በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ሁላችንም የበኩላችንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል።
ዲቦራ ፋውንዴሽን በአእምሮ እድገት ውስንነት የተጠቁ ልጆችን ከተደበቁት አዉጥቶ ፍቅርና እንክብካቤ እንዲያገኙ እንዲሁም የመማር እና የመታከም መብታቸዉ እንዲጠበቅ በማድረጉ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል።
በዚህ ዙሪያ የምትሰሩ አካላትን በሙሉ አቅሞቻችንን ሁሉ አሰባስበን በቅንጅት እንድንሰራ በመጠየቅ፣ የማህበረሰብ ለውጥ ለማምጣት ለምትሰሩት አኩሪ ስራ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በጤና ተቋሞቻችን በአእምሮ እድገት ውስንነት ለተጠቁ ህጻናት ነፃ የህክምና አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑንም እገልጻለሁ። በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ ለተሰማሩ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንደምናደርግ እና ተማሪዎችም በተማሩበት የሙያ ዘርፍ የስራ እድል እንዲያገኙ ሁኔታዎችን የምናመቻች መሆኑን ማሳወቅ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ