uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ጎበኙ፡፡… See more

photo content
+7

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተለምዶ ኬሻ በጠረባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል:: የእሳት አደጋው ሌሊት የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሃመድ በአካባቢ ያሉ ቤቶች የተገነቡበት ግብአት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ እንዲሁም አካባቢው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱ ተደማምሮ አደጋዉ እንዲሰፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። ኮማንደር አህመድ መሃመድ ጨምረው አደጋውን ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች በፍጥነት ደርሰው ሰፊ ርብርብ ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው አካባቢው መኪና የማያስገባ በመሆኑ እና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች በመኖራቸው ምክንያት የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም ገልጸዋል::

photo content
+4

ባህሎቻችን የወል ትርክት አምባ” በሚል መሪ ቃል በከተማችን ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚከናወነውን 16ኛ የባህል ፌስቲቫል ሳምንት ዛሬ አስጀምረናል። ባህሎቻችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው ለሀገር ግንባታ፣ ለህዝቦች መቀራረብ፣ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ለሰላም እና ለወል ትርክት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። መላው የከተማችን ነዋሪዎች የሚያጋምዱን እና ከሌላው የዓለም ክፍል የሚለዩን ባህሎቻችን ሃብቶቻችን መሆናቸውን በመረዳት፣ የተዘጋጀውን የባህል ፌስቲቫል በጊዮን ሆቴል በመገኘት እንድትጎበኙ ጥሪ አቀርባለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+8

በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኤግዚቢሽን እና የኮንቬንሽን ማዕከል - “አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ን ገንብተን በማጠናቀቃችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። እንኳን ደስ ያለን ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ Jalqabarratti Waaqni nu gargaare haa galatoomu Giddugala Igzibiishinii fi Konveenshinii sadarkaa idil addunyaa eeggatte - "Giddugala Addis Intarnaashinaal Konveenshin" ijaarree xumuruu keenyaan gammachuu guddaatu nutti dhagahama. Baga Gammanne Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተመራ ያለው የፋይዳ ምዝገባ አፈፃፀም ተገምግሞ የተማሪዎች የምዝገባ ማስጀመርያ ይፋ ሆነ የሃገር አቀፉ የፋይዳ ምዝገባ ስርዓት ለሃገር የሚኖረውን አስተዋፅዖ ከግምት በማስገባት የስርዓቱን ተፈፃሚነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስተባበር የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በጋራ እየመሩት ያለ ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎት ጋር በተያያዘም አስገዳጅ አሰራር ተዘርግቷል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ በዛሬው ዕለት እየተደረገ ያለው ምዝገባ ዝርዝር አፈፃፀም ገለፃ ቀርቦ ግምገማ ተደርጓል። ላለፉት ወራት በተፈጠረው የጋራ ንቅናቄ በከተማው ከ2.1 ሚሊዮን በላይ አዲስ ተመዝጋቢ መመዝገብ መቻሉን ከዚህ መካከል 900 ሺህ የሚጠጋው ምዝገባ በቀጥታ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መዋቅር ጽ/ቤቶች የተካሄደ ምዝገባ መሆኑ በሪፖርት ቀርቧል። በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተገኙበት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል። በዛሬው ዕለት በይፋ የተጀመረው የትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ንቅናቄ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የሚመራ ሲሆን ዕድሚያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናት በዘመቻ ምዘገባ እንደሚከናወን ተነግሯል። ለዚህም የትምህርት ማህበረሰቡን እና የተማሪ ወላጆችን ከሚወክሉ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት በዝግጅት ምዕራፍ ተከናውኗል። የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን በከተማው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የቅጥር እና ዝውውር እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ከምዝገባ ስርዓቱ ጋር እንዲቀናጅ በአስገዳጅ ስርዓትነት የተቀመጠ ሲሆን የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታም እንደሆነ ይፋ አድርጓል። የካቲት 21/ 2017 አ.ም ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የስብሰባ፣ የኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ዘርፍን(MICE) ለማጠናከር ለምናደርገው ጥረት አንድ ተጨማሪ አቅም ነው። አለም አቀፍ ደረጃን እንደጠበቀ ተቋምነቱ የንግድ ቱሪዝምን በማሳደግና አለምአቀፍ ኹነቶችን በመሳብ ሀገራችንን የስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ እንድትሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታል። Giddugalli Konveenshinii Idil-addunyaa Addiis tattaaffii damee walgahii, konfaransiifi egzibiishinii cimsuuf taasifnuuf humna dabalataa tokkodha. Dhaabbatichi sadarkaa idil-addunyaasaa akkuma eegetti tuuriizimii daldalaa guddisuufi taateewwan idil-addunyaa hawwachuudhaan biyyi keenya akka bakka hawwata walgahii duree taatu gahee olaanaa qaba. The Addis International Convention Center is the latest addition to of our ongoing efforts to strengthen the Meetings, Incentives, Conferences, and Exhibitions (MICE) sector. As a world-class venue, it plays a crucial role in attracting international events, fostering business tourism, and positioning the country as a premier destination for global gatherings.

አገልጋይ | የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዶ/ር እሸቱ ለማ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ቆይታ …

photo content

መረጃ- የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎትን በተመለከተ የልደት ምዝገባ እድሳት፣ የልደት ምዝገባ ግልባጭ/ምትክ፣ የልደት ምዝገባ እርማት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ያውቃሉ? እንግዲያውስ ከላይ የተጠቀሱንት አገልግሎቶች ለማግኘት ወደ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አጀንሲ ሲመጡ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላትዎን ያረጋግጡ የዕድሳት አገልግሎት ሲሆን የቀድሞውን ሰርተፍኬት ዋናውንና ኮፒውን መያዝዎን፤ የኢምባሲ ማረጋገጫ ሲሆን ከኢንባሲው ስለጉዳዩ የሚገልጽ ደብዳቤ እና የኢምባሲው ተወካይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት እና ቪዛ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ፤ ጥያቄው በውክልና ከሆነ ስለጉዳዩ በግልጽ የሚያሳይ ልዩ (Specific) ህጋዊ የውክልና ማስረጃ የወካይ እና የተወካይ በዘመኑ የታደሰና ሙሉ መረጃ የያዘ መታወቂያ፣ ወይም ፓስፖርት እና ቪዛ የወካይ ኮፒ፣ የተወካይ ዋናውንና ኮፒ፣ ከውጭ ከሆነ የታደሰ ፓስፖርት ወይም ዜግነቱን የሚገልጽ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም የስደተኞች መታወቂያ የተወካይ ዋናውንና ኮፒ የወካይ ኮፒ ለእርማት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ፤ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ የልደት ማስረጃ ጠያቂዎች እናት እና አባት ሁለቱም በአካል ቀርበው ማውጣት ካልቻሉ አባት ለ እናት ወይም እናት ለአባት ውክልና በመስጠት ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ፤ ማስረጃው የሚወጣው በአሳዳሪና በሞግዚት ወይም በተንከባካቢ ከሆነ ስለ ጉዳዩ የሚገልፅ ህጋዊ የፍርድ ውሳኔ ማስረጃ ፤ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የኩነት ምዝገባ ደጋፊ ሰነዶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጋገጥና እና በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተመመዝገብ እና የተመረጋገጥ መሆኑን፤ •የአገልግሎት ክፍያን በሚመለከት ለኢትዮጵያውያን ብር 100/አንድ መቶ/ ብር፣ ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙ Boost this post to get more reach for Addis Ababa City Manager's Office.

photo content
+9

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞቃዲሾ ሲደርሱ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

photo content
+5

"የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል" ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ። በ2ኛው ዙር የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት 7ኛ ኮሪደር ከሳር-ቤት መካኒሳ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የኮሪደር ልማት ስራው የደረሰበትን ደረጃ የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመስክ ጉብኝትና ቅኝት ተካሂዷል። በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ጨምሮ ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል። በመስክ ምልከታው የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኮሪደር ልማት ስራው በሚፈለገው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ኢንጂነር ወንድሙ አክለውም የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነትና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት በቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰው ኮንትራክተሩን፣ ማህበራትንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለያየ መንገድ ማገዝ እንደሚገባ ተናግረዋል። ከሳር ቤት መካኒሳ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት ስራ ላይ የመንገድ ደረጃ ማሻሻልና ምቹ ማድረግ፣ ሰፊ የእግረኛ መንገድ፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የህፃናት መጫዎቻ ስፍራዎችና የታክሲና የአውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች ይገኙበታል። በተጨማሪም የህንፃዎች እድሳት፣ የቆዩ ህንፃዎችን በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ማስገባት፣ የሳይክል መንገድ፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ማሶገጃ መስመር ዝርጋታ፣ የደህንነት ካሜራ መስመር ዝርጋታ፣ የትራፊክ ፍሰት መቆጣጠሪያ እና የስፖርት ሜዳ የልማቱ አካል ናቸው። የካቲት 19/ 2017 አ.ም #laftocommunication

photo content
+2