1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
በመዲናችን አዲስ አበባ በክረምቱ የጎርፍን ተጋላጭነት ለመቀነስ ግብረኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት በክረምቱ ጊዜያት አደጋዎች እንዳያጋጥሙ በበጋ ወራት የአደጋ መከላከል ቅድመ ጥናት መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በወንዝ ዳር ፕሮጀክት የለሙትን ሳይጨምር 64 የጎርፍ መከላከያ ግንቦች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች መሠራታቸውን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ ተቋማትና ክፍለከተሞች የተውጣጡ ግብረሐይል አቋቁሞ የአደጋ ስጋት የመቀነስና አደጋ ቢያጋጥም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበትን አደረጃጀት፣ ማሽነሪ እና የሰው ሀይል ዝግጁ የማድረግና የማጠናከር ስራ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ ያሉ የጎርፍ መከላከል እና የፍሳሽ ማስወገጃ መሠረተ ልማቶች ከተማዋ ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ ከመቶ አመታት በላይ የነበረውን የመሠረተ ልማት ቅንጅት ችግር የፈታና ለመጪው ትውልድም የተመጋጋቢ መሠረተ ልማት ዝርጋታን እውን በማድረግ አደጋን በዘላቂነት በመከላከል ረገድ የተጠናከረ እና መሠረት የጣለ ስራ መሠራቱን ጠቅሰዋል ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም በከተማችን አዲስ አበባ የነበሩ በርካታ በደለል የተሞሉ በፍሳሸ ቆሻሻ የተበከሉ ወንዞችን በማልማት ከወንዞቹ 30 ሜትር ባነሰ ቦታ ምንም አይነት ግንባታ እንዳይከናወን ህግ ወጥቶ ከከተማዋ ማሰተር ፕላን ጋር ተቀናጅቶ እንዲተገበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ከዚህ በሁዋላ በወንዝ ዳርቻዎች አካባቢ የሚለሙ መሠረተ ልማቶች የወንዝ ዳርቻ ጥበቃ ህግን አክብረው እንዲሰሩ ይደረጋል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህም ወንዞች በደለል እንዳይሞሉና እና ለአካባቢው የጎርፍ አደጋ ስጋት እንዳይፈጥሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው መሆኑን ጠቁመዋል።
የከተማችን ነዋሪዎች የአደጋ ተጋላጭነትን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቀነስ አስተዳደሩ የሚሰሩ ስራዎችና የወንዝ ዳርቻ ህጎች ጋር ያይዘው የሚወጡ ህጎች እንዲከበሩ በማድረግ ረገድ እንዲተባበርም ጥሪ አቅርበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
አዲስ አበባ ከተማ በብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ የከተሞች ውድድር (Mayor’s Challenge) 2025 ከመጨረሻዎቹ ለቀጣይ የመጨረሻው ውድድር ከተመረጡ 50 ዕጩዎች መካከል አንዷ ሆናለች።
መዲናዋ ይህንን ደረጃ ያገኘችው በአለም አቀፍ ደረጃ በመርሃ ግብሩ ለመወዳደር ካመለከቱ 630 ከተሞች መካከል ተመርጣ ነው።
በብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ አማካኝነት የሚዘጋጀው ይህ ውድድር ከተሞች ለሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች የሚወስዱትን ችግር ፈቺ የመፍትሄ ርምጃ ፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና ሊሰፋ የሚችል መሆኑን መለየት እና መደገፍን ያለመ ነው።
የዘንድሮው ውድድርም የከተሞችን ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በአዲስ የፈጠራ ሃሳብ በመፍታት ሰው ተኮር የሆነ የከተማ ትራንስፎርሜሽንን ማምጣት መቻል ላይ ያተኮረ ነው።
በዚህም አዲስ አበባ ዘመናዊ፣ የተቀናጀ እና በአንድ ማዕከል የተደራጀ የመረጃ ስርዓትን በመጠቀም የነዋሪዎቿን ችግሮች ለመፍታት ባቀረበችው የመወዳደሪያ ዝክረ ሃሳብ ተመርጣለች።
የአዲስ አበባ ከተማ የፈጠራ ልዑክ ቡድንም በቦጎታ ኮሎምቢያ እየተካሄደ ባለው የብሉምበርግ የውድድር ሃሳቦች ካምፕ ተገኝቷል።
በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የብሉምበርግ የከንቲባዎች ውድድር ከሁሉም አህጉራት ካሉ ከተሞች ተሳትፎን የሚስብ ትልቅ ዓለም አቀፍ ውድድር ሲሆን በዚህ ዓመትም ከምርጥ 50 ከተሞች መካከል ቶሮንቶ፣ ሴኡል፣ ኬፕ ታውን፣ ሲያትል፣ ሳን ፍራንሲስኮ፣ ቫንኮቨር፣ ቡዳፔስት፣ ማርሴይ፣ ሪዮ ዴ ጄኔሮ እና ሌሎችም ከተለያዩ አህጉራት እንደሚገኙበት የብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ መረጃ ያመለክታል።
እነዚህ 50ዎቹ የመጨረሻ እጩዎች አለም አቀፍ በሆኑ ባለሙያዎች የቴክኒክ ድገፍ እየተደረገላቸው ቆይተው የመወዳደሪያ ሃሳቦቻቸውን ያዳብራሉ።
በመጨረሻም የሚመረጡት 25 ተወዳዳሪዎች ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳበቻቸውን ለመተግበር የሚያግዝ ለእያንዳንዳቸው የአንድ ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ይሆናል።
አዲስ አበባ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሽልማቶችን ማግኘቷ ይታወቃል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ አንዳንዶች ያልተገባ አስተያየት ሲሰጡ ተሰምቷል፡፡
በትላንትናው ዕለት የተከሰተው ጎርፉ ወቅቱን ጠብቆ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ ላይ በነበረው ጊዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሙላቱ እና የተሰራለትን ጊዜያዊ ግድብ ጥሶ በመውጣቱ ሆኖ ሳለ አንድንድ ግለሰቦች ግን ወቅቱን ያላገናዘበና ከእውነት የራቀ አስተያየት ሲሰጡት ተሰምቷል፡፡
ይሁን እንጂ መላው ህብረተሰባችን እንደሚረዳው አዲስ አበባ የነበራትን አስቸጋሪ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እንደ አዲስ በመገንባት የተሰራውን ስራ አስተማማኝ መፍትሔ እና በቀጣይም ተጠናክሮ በመላው ከተማዋ ዳርቻ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ሥራ እና ሙያዊ መፍትሔ ነው። ያም ሆኖ ይህን መያዊ እና መሠረታዊ ሥራ ወደ ጎን በመተው አንዳንዶች ያልተገባ ስ ያሜ ሰጥተውታል፡፡
መላው ህብረተሰብ እና የከተማችን ነዋሪ ወቅቱን እና እንዲሁም አዲስ አበባ አሁንም በበርካታ ግንባታዎች ላይ መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምንጩ ካልታወቀ የተዛበ መረጃ እራሱን በመጠበቅ ትክክለኛውን እና ሚዛናዊ የሆነውን መረጃ እንዲመረምር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን በማስመልከት የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ እራሱን ከጎርፍ አደጋ እንዲጠብቅ እናሳስባለን ፡፡
በመጨረሻም ማህበረሰባችን እየጣለ ያለውን ዝናብ እና ወቅቱን እንዲሁም በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ግንባታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጎርፍ የመከላከል ስራው አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከተማው በሚያደርገው የመከላከል ሥራ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia
ለረጅም ጊዜ ይነሳ የነበረውን የህብረተሰብ ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ያልተሟላላቸውንና ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብባቸው በነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የመብራት መሰረተ-ልማት የሟሟላት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብባቸው ከነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከቀራንዮ - አንፎ የሚያዘልቀው አንዱ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ ባለስልጣን መ/ቤቱ የመብራት መሰረተ-ልማት ዝርጋታና ተከላ ስራ በማከናወን የመብራት ፖሎቹ ለህብረተሰቡ በምሽት በቂ ብርሀን እንዲሰጡ በማስቻል በአካባቢው ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የተሳለጠ እና በአካባቢ ያለውን የተሽከርካሪና የእግረኛ እንቅስቃሴ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የማድረግ ስራ አከናውኗል፡፡
ቀደም ብሎ መንገዱ ተገንብቶ የመብራት አገልግሎት ሳይሰጥ በመቅረቱ ህብረተሰቡ በተለያየ ጊዜ ያነሳ የነበረውን ቅሬታ ለመፍታት ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው ጥረት አሁን ላይ አብዛኛውን ስራ በማጠናቀቅ በመንገዱ ውስጥ ያሉትን ፖሎች ማብራት የተቻለ ሲሆን ቀሪዎቹን በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመትከል ማንሰራራት" የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት አመራሮች፣ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምስል ሲቃኝ:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
#አረንጓዴዐሻራ
#GreenLegacy
#PMOEthiopia
ለረጅም ጊዜ ይነሳ የነበረውን የህብረተሰብ ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ያልተሟላላቸውንና ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብባቸው በነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የመብራት መሰረተ-ልማት የሟሟላት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብባቸው ከነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከቀራንዮ - አንፎ የሚያዘልቀው አንዱ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ ባለስልጣን መ/ቤቱ የመብራት መሰረተ-ልማት ዝርጋታና ተከላ ስራ በማከናወን የመብራት ፖሎቹ ለህብረተሰቡ በምሽት በቂ ብርሀን እንዲሰጡ በማስቻል በአካባቢው ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የተሳለጠ እና በአካባቢ ያለውን የተሽከርካሪና የእግረኛ እንቅስቃሴ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የማድረግ ስራ አከናውኗል፡፡
ቀደም ብሎ መንገዱ ተገንብቶ የመብራት አገልግሎት ሳይሰጥ በመቅረቱ ህብረተሰቡ በተለያየ ጊዜ ያነሳ የነበረውን ቅሬታ ለመፍታት ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው ጥረት አሁን ላይ አብዛኛውን ስራ በማጠናቀቅ በመንገዱ ውስጥ ያሉትን ፖሎች ማብራት የተቻለ ሲሆን ቀሪዎቹን በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመትከል ማንሰራራት" የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት አመራሮች፣ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምስል ሲቃኝ:-…
See more
በክረምቱ አልፎ አልፎ የሚኖር ከባድ ዝናብ ሊያስከትል ከሚችለው ቅጽበታዊ ጎርፍ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ ።
በመጪዎቹ አስር ቀናት አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ።
የኢንስቲትዩቱ መግለጫ እንዳስታውቀው በመጪዎቹ አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖራቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።
የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ትንበያው ያሳያል።
ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።
በሚኖረው እርጥበት ዘር መዝራት፣ ትርፍ ውሃን ከማሳ በማጠንፈፍ ማስወገድ፣ የአፈር መሸርሸር ስጋትን ለመቀነስ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጠቁሟል።
ረባዳማ በሆኑ ማሳዎች የውሃ ማንጣፈፍ ስራዎች መስራትና የደረሱ የበልግ ሰብሎችን በሚኖሩ ደረቅ ቀናቶች መሰብሰብ እንዲሁም የሚገኘውን እርጥበት በመጠቀም የመኸር ዘር መዝራት እንደሚገባም አብራርቷል።
በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሚኖረው ዝናብ በአብዛኛው ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖርም መግለጫው ያመላክታል።
አልፎ አልፎ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል አስረድቷል።
ስለሆነም በወንዝ ዳርቻ እንዲሁም ረግረጋማ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውና የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አደጋን በመቀነስ መልካም እድሎችን እንዲጠቀሙም አስገንዝቧል።
የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት፣ወራጅ ውሃን በእግርም ሆነ በቀላል ተሽከርካሪ ለማቋረጥ አለመሞከር፣ የጎርፍ የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን ማፅዳት፣ የዝናብ ውሃ ማሰባሰብና ማጠራቀም እንደሚገባ ተመላክቷል ።
#ኢዜአ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዲሱ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ ጀመረ ።
ከሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተደራሽ ለማድረግ አዲሱ የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች እንዲ ሰጥ ተደርጓል ።
በአገልግሎቱም ለእሳትና ለሌሎች ደንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአንቡላንስ የ24 ሰዓት የነጻ አገልግሎት እንደሚ ስጥ የቅርንጫፍ ጽ / ቤቱ ስራ አስኪያጅ ፍየር ቺፍ ሊቆዲሞስ ቡቼ አስታውቀዋል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሲ ኤምሲ ሳሊተምህርት
ከፍ ብሎ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን የአደጋ ጥሪ መቀበያ ስልክ ቁጥሮች የሚከተሉት ናቸው ።
👉0116-68-47-97
👉0116-66-81-73
👉0116-68-02-36
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማጠቃለያ እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ትኩረቶች…
See more
