uk
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
photo content
+3

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት "ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል በዛሬው እለት ባካሄደው የ2017 በጀት አመት የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤ ለተጠሪ ተቋማቱ በበጀት አመቱ ላስመዘገቡት የላቀ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ውጤት የእውቅናና የሽልማት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካሂዷል። ጽ/ቤቱ "ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት ባካሄደው የ2017 በጀት ዓመት የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ የዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በጽ/ቤቱ ለ5 ተጠሪ ተቋማት የላቀ የአፈፃፀም ውጤት እና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው የዋንጫና የሰርቲፊኬት እውቅናና ሽልማት መስጠቱ ተገልጿል። በዚህም መሰረት፦ 1ኛ.የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 2ኛ.የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ 3ኛ. የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሲሆኑ በአዲስ ከተቋቋመ ገና አመት ያልሟለው እስካሁን ባሳየው በጣም ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም 4ኛ)- የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እንዲሁም 5)- የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮ የዋንጫና ሰርቲፊኬት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

photo content
+9

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት "ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል በዛሬው እለት ባካሄደው የ2017 በጀት ዓመት የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ ለክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶች የእውቅናና ሽልማት የመስጠት መርሀ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት <<ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት>> በሚል መሪ ቃል ባየ2017 በጀት ዓመት የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ ዕውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ባካሄደበት ወቅት በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት ጽ/ቤቱ ሊያሳካ ካቀዳቸው ግብ ተኮር ተግባራት ውስጥ በላቀ ስኬት በማጠናቀቅ በከተማ አስተዳደሩ ካሉት ተቋማት ውስጥ የአረንጓዴ ደረጃ ምድብ ውስጥ በመግባት ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉ ተነስቷል። በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በተካሄደው የKPI እና ቁልፍ ተግባራት ምዘና በጽ/ ቤቱ መዋቅር ስር ያሉ የክፍለ ከተሞች ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤቶች የዋንጫ፣ የዕውቅና ሰርተፍኬት እና የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዚህም መሰረት፦ ከክፍለ ከተሞች በላቀ የአፈፃፀም ውጤት ከ1- 3 የወጡት 1ኛ.አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት 2ኛ.ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት 3ኛ.አቃቂ /ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የዋንጫ፣ ሰርቲፊኬትና ላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። 4ኛ)- የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት 5ኛ)- ለሚኩራ ክ/ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት በጣም በከፍተኛ ውጤት ከ4-5 በመውጣት የዋንጫና ሰርቲፊኬት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። ቀሪዎቹ 6 የክፍለ ከተማ ጽ/ ቤቶች ደግሞ በጣም በተቀራረበ ከፍተኛ ውጤት የአረንጓዴ ሰርቲፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+5

በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተጠናቀቀው የበጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት በመዲናችን ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አመኔታን ያተረፉና በተገልጋዩ ዘንድ እርካታን የፈጠሩ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት "ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት!" በሚል መሪ ቃል ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለመምከር ባዘጋጀው የበጀት አመቱ የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት ለከተማችን ነዋሪዎች የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ስሉጥ፣ ግልፅ ፣ ፍተሃዊ፣ ተደራሽ እና የተገልጋዩን እርካታ የጨመሩ እንዲሆኑ ፅ/ቤቱ መላው መዋቅሩን እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዘገባቸውን አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ ከተማዋን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በተሰራው ስራ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም ተግባር 12 ከመቶ መድረሱን ተናግረው የአደጋ ስጋትን ከመከላከል አንፃር 533 የእሳት ተጋላጭ ቦታዎች በመለየት መፍተሄ እንዲያገኙ መደረጉን አስረድተዋል። ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ ተገባራት የ12.7 ቢሊየን ብር ንብረት ከእሳት አደጋ ማዳን መቻሉን አስታውቀው ከመንገድ መብራት ጋር በተያያዘ መዲናችን በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የሚሰራበት ብርሃናማ ከተማ እንድትሆን ያደረገ ጨለማ አካባቢዎችን ወደ ብርሃን በመቀየር እና የማይሰሩ የመንገድ ላይ መብራት እንዲሰሩ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager በቴዎድሮስ ይሳ

photo content
+1

photo content
+4

photo content
+3

ፕሬስ ሪሊዝ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2018 በጀት አመት እቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የተግባቦት በመፍጠር በላቀ ብቃት ተግባራቱን ለመፈፀም የሚያስችል የ2017 የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤ በነገው እለት እንደሚያካሂድ አስታወቀ ፡፡ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት በነገው እለት ማክሰኞ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ በሚካሄደው የጽ/ቤቱ የ2017 የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አጠቃላይ የአመቱ የስራ አፈጻጸም፣ ከተጠሪ ተቋማት፤ከክፍለ ከተማ እና ወረዳ መላው መዋቅር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ውጤቱ የጋራ ይደረጋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በበላይነት የመምራት፣የማስተባበር፣ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ፣ በጥናት ላይ ተመርኩዞ አዳዲስ አሰራሮችን በመቀየስ፣ ስሉጥ፣ ግልጽ እና ፍትሃዊ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መሠጠቱን የማረጋገጥ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት በተለይም በተጠናቀቀው በጀት አመት የተለያዩ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑንም አውስተዋል። አክለውም ይህንኑ በ2018 በጀት አመት በላቀ ብቃት በመፈፀም የመዲናችን ነዋሪዎች በቴክኖሎጅ የዘመነ፣ ቀልጣፋ፣ግልፅና ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ስማርት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ግንባታን በማፋጠን ለመዲናችን የስማርት ሲቲ ግንባታ ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል። በዚሁ የሴክተር ጉባኤ በበጀት አመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የተጠሪ ተቋማት፤የክፍለ ከተሞች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት እውቅና የመስጠት ስነ ስርአት እንደሚካሄድም አያይዘው አመልክተዋል። ነሐሴ 5/ 2017 ዓ.ም ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ቸር ልብ ያላቸው እልፍ ዜጎች አሉን” ከዲያስፓራ እስከ ሀገር ቤት ካላቸው የሚያካፍሉ፣ ከጎዶሎአቸው የሚሰጡ ፣ በመስጠት ውስጥ ያለን በረከት የተረዱ ፣ ለሀገሬ ምን አደረኩላት የሚሉ፣ ቸር፣ ሀብታም ልብ ያላቸዉ እልፍ ወንድም እህቶች አሉን ። ዛሬም በሀገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት የሚገኘው “ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽን” ዋጋቸው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ 133 አይነት የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብአቶችን አበርክቶልናል ። መሳሪያዎቹ ለኩላሊት፣ ለተኝቶ ታካሚዎች፣ ለፅኑ እና መደበኛ ሕሙማን ህክምና ግልጋሎት የሚያግዙ ናቸው። ሄኖክ አርጋው ፋውንዴሽንን በከተማ አስተዳደሩ፣ በተጠቃሚው ማህበረሰብ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እያመሰገንኩ፤ ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም ለአስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስረክበናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከሁሉም በላይ የልባችንን ቀና መሻት ተመልክቶ በነገሮች ሁሉ መሳካትን ለሰጠን ፈጣሪ ምስጋና ይሁን!!… See more

የአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ ፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች!!… See more