1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
ኢንዱስትሪን በተመለከተ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ ሲከናወን ቆይቷል። በዚህም የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ችግሮች የተለዩ ሲሆን ችግሮቹን ለመቅረፍም እየተሰራ ነው። ለአብነትም በዘንድሮው ዓመት ብቻ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የቀረበው የኃይል አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ከጥቂት ዓመት በፊት የአቅርቦት ጥያቄ የነበረበት የሲሚንቶ ምርትም አሁን ላይ ለውጭ ገበያ ጭምር ማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው። የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ 55 አዳዲስ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል።
#የጠሚሩምላሾች… See more
ግብርናን በተመለከተ
"በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል። በስንዴ ልማትም በመኸር 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር እንዲሁም በበጋ መስኖ ልማት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን፤ በዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይስበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት እየተመዘገበ ነው። ለአብነትም ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።"
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡት ማብራሪያ
ወንዝ የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከ 5 ሚሊየን ብር በላይ ተቀጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2,100,000 ብር፤በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 910,000 ብር ፤ በኮልፌ ክፍለ ከተማ 690,000 ብር፤በየካ ክ/ከተማ 600,000 ብር ቅጣት ቀጥቷል።
በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር እና በልደታ ክ/ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን የባለስልጣን መስርያ ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 17 ድርጅት እና 8 ግለሰቦች በድምሩ 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ባለስልጣኑ በተሰጠው ግንዛቤ መሠረት ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
AMN
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ነገ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ
-----------------------
ነገ መጋቢት 11 ቀን ፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤቱ በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
በፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ነው የሚሆነው።
መዲናችን አዲስ አበባን ሳይታክቱና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ዘወትር በማፅዳት ከተማችንን ፅዱ ፣ ንፁህና ማራኪ በማድረግ ላይ ያሉ ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ የመንገድ ፅዳት ባለሙያዎች ከተማችን አሏት።
ከእነዚህ የመንገድ ፅዳት ባለሙያዎቻችን ውስጥ ከ75 በመቶው በላይ ሴቶችና እናቶች ሲሆኑ የከተማችንን ፅዳት ቀን ከሌሊት ፣ከእሁድ እስከ እሁድ ያለ መታከት፣ ብርድ ፣ ዝናብ ፣ ጠራራ ፀሃይና ሌሎችም ተግዳሮቶች ሳይበግራቸው ሙያቸውን በታማኝነትና በቅንነት እየተወጡ ያሉ ናቸው። … See more
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጽዳትን ባህል ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ ገምግሟል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጽዳትን ባህል ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ የሁሉም ወረዳ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞች እንዲሁም ማህብራት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
ለመድረኩ መወያያ ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በጽዳት ዙሪያ በርከታ ስራዎች ተስረተዋል አሁንም መሠረት ላይ ይገኛል፤ በተለይ ሣምንታዊ የንቅናቄ የጽዳት ሥራዎቻችን ስኬታማ ውጤት እየተመዘገበበት የሚገኝ መሆኑና ይህንን ጽዳት ባህል በማድረግ ቀጣይነቱን ማረጋገጥ የሚቻለው በእኛ በግንባር ቀደም ባለቤት የሆን ሥራውን በዋናነት የማስተባባርና የመሥራት እንዲሁም ግብዓቶችን የማሟላት ኃላፊነት ያለብን መሆኑና በቅንጅታዊ አስራሮች ከሌሎች ጽ/ቤትና ተቋማት ጋር መሥራት ይገባል ሲሉ ሰነዱን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ጉልማ በበኩላቸው በበጅት ዓመቱ ጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሪፎርም ተደረጎ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው፤በዚህ መካከል በብዙ መልኩ ሥራዎቻች ውጤታማ እንደመሆናቸው መጠን በሪፎርም ምክንያት በቀጣይ የጽዳት ሥራዎች እንዳይቀዛቀዙ ሁሉም ሠራተኛ በእኩል አቅምና ተነሳሽነት አጠናክራችሁ መስራት ይገባችኃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ህብረተሰቡ የፅዳትና የውበት ስራን የእለት ከእለት ተግባሩ እንዲያደርገው እየተሰራ ያለው የግንዛቤ ስራ ተስፋ ሰጭ ውጤት እየታየበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ
***********
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የቅድመ አደጋ፣ የአደጋ ወቅትና ድህረ አደጋ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የፌደራልና የክልል አስተዳደር ተቋማት የውስጥ አቅም ለመገንባት እንዲቻል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል።
ረቂቅ አዋጁ ቅጽበታዊ አደጋ ሲከሰትና ከአቅም በላይ ሲሆንም የአስቸኳይ ጊዜ እወጃ ሥርዓት ለመዘርጋትና ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የዘላቂ ልማት እና የሰላም ግንባታ እቅዶችን ለማስተሳሰር ያስችላል ብለዋል።
የምክር ቤት አባላትም አዋጁ የሚደረጉ ድጋፎችን ለማቀናጀትና ለተጎጂዎች እኩል ተደራሽ ለማድረግ፤ እንዲሁም ከእርዳታ ጠባቂነት በመላቀቅ ራስን ለመቻል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 16/2017 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በሸገር ከተሞች የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ፤ የአዲስ ከተማና የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች በሸገር ከተማ አስተዳደር ስራ ካሉት ከቡራዩ ፤ከገፈርሳጉጄ እና ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተሞች ጋር በአደጋ ቅነሳና በአደጋ ምላሽ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸዉን የስምምነት ሰነድ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በቀለ ደቻሳ እንደተናገሩት በሸገር ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ክፍለ ከተሞች ጋር በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ያሉባቸዉና የኢንደስትሪ ዞኖች የሚገኙባቸዉ በመሆኑ እነዚህ የልማት ስራዎችን ከእሳትና ከሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እንደሚገባ ጠቅሰዉ ለዚህም በኮሚሽኑ ካሉ ሶስት ቅርንጫፍ ጣቢያዎች አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ረገድና አደጋዉ በአጋጠመ ጊዜም ፈጥኖ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ሀላፊ ምክትል ኮምሽነር ደሳለኝ ፉፋ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በሰነዱ ላይ የተካተቱት ተግባራት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችልና አደጋ በደረሰም ጊዜ ተቀናጅቶ በመስራት የደረሰዉን አደጋ በፍጥነት ለመቆጣጠር የሚያግዝ በመሆኑ ለስምምነቱ ተፈጻሚነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩና ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላትና በኮሚሽኑ የአዲስ ከተማ ፣ የጉለሌና የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
