1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪህ ቃል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ አካሂደናል::
ሌተቀን የከተማቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ የጎደሉ በየአካባቢው ያሉ መሰረተ ልማቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመስራት እና በማሰራት በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ ማህበራዊ ጫናዎችን በመቀነስ እና በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በእውቀታቸው ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የከተማችንን ነዋሪዎችን እና የብሎክ አደረጃጀቶችን እስከ አሁን ለሰሩት ስራ እውቅና ሰጥተን የ2017 እቅድ ላይም ተወያይተናል።
ቀና ልብ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የበርካቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለሙ ስራዎችን ለሰራችሁና ላስተባበራችሁ ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም እያመሰገንኩ የከተማችንን ፈጣን ለውጥ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማስቀጠል ከህብረተሰባችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጏል::
በድጋፍ መርሃ ግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እስኪገነባ ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል::
በአካባቢው ያለውን ጥግጊትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ጨምረው ገልጸዋል::
ድጋፉን የተቀበሉት የአካባቢው ነጋዴ ተወካዮች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው ድጋፉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን ተናግረዋል:
የአዲስ አበባ ከተማ የየአፍሪካ ስማርት ከተሞች አዋርድ ተሸላሚ ሆኗ ለች!
ከተማ አስተዳደሩ ሽልማቱን ያገኘነው በከተማችን እየተስራ ባለው የኮሪደር ልማት እና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ለመኖሪያ ምቹ በማድረግ እና ተያይዞም በተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ፤ ቴክኖሎጂ ተኮር የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና አቅርቦት ለነዋሪዎች ያለውን አስተዋፅዖ ጭምር በመለየት የተሰጠ ነው ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባስመዘገባቸው አመርቂ ውጤቶች በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለዉ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተሸላሚ መሆን ችላለች።
የአዲስ አበባ ከተማ ከሌሎች ስማርት የአፍሪካ ከተሞች ጋር ተወዳድራ ሽልማቱን ከሚወስዱ ሶስት ከተሞች መካካል አንዷ መሆን የቻለች ሲሆን ፤ ክብርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባን በመዋክል የተላከው የልኡኳን ቡድን ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ይህ አዋርድ ለአዲስ አበባ ከተማ ሊሰጥ የቻለበት ዋነኛ ምክንያት በኮሪደር ልማት ከተማይቱን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተስማሚ ለማድረግ የተገኘውን አመርቂና ውጤታማ ተግባር መሰረት በማድረግ መሆኑን እና በአርንጓዴ አሻራ የአየር ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለውን ተምሳሌታዊ ተግባር በማስመልከት እንደሆነ ተገልጿል ። በተጨማሪም ሰው ተኮር ስማርት ከተሞች ለትውልድ መገንባት የሚለውን የከተማነት ሀሳብ በከተማይቱ ተግባራዊ በመደረጉ ነው። እንዲሁም ዘመናዊ እና ምቹ ከተማን ለመፍጠር ለአብንትም የእግረኞች መሄጃ እና የሞተር አልባ ተሸከርካሪዎች መንገድ ደረጃውን በጠበቃ ቴክኖሎጂ መገንባታቸውን መሰረት በማድረግ መሆኑን በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስማርት በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎት እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረጉ መሠረተልማት ዝርጋታዎች እንዲሁም ስማርት የነዋሪዎች እና የዜጐች ተኮር ከባቢዎች መገንባታቸው፤ ተያይዘው የተፈጠሩ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፤ እና ብቁ እና አመቺ ልማት ቴክኖሎጂን የተደገፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደታቶች በመተግበራቸው ከተማይቱ ይህንን ሽልማት እንድታገኝ አድርጓታል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሸላሚ መደረጉ ለሀገራችን የገጽታ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል : : በአፍሪካ አህጉር ለሚገኙ መሰል ዋና ከተሞች ተምሳሌት የሚሆን ተብሏል።
ይህ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ በዋናነት በኬንያ መንግስት፣ በናይሮቢ ካውንቲ እና ናይሮቢ በሚገኘው በተመድ የሰዎች ሰፋራ (UN-Habitat) እና ሌሎች አጋር አካላት በትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።
በዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን እየተሳተፉበት የሚገኙ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የአፍሪካ የIT ሚነስትሮች፣ ከንቲባዎች፣ የተለያዩ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ መሆን ችለዋል።
በናይሮቢ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲን በመወከል ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።
የቀጣዩን ጉባኤም አዲስ አበባ የምታስተናግድ መሆኑ ተገልጿል
"የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" አውደ ርዕይ
ባለፉት አምስት ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ ተግባራት የህዝብ ተጠቃሚነትን በተጨባጭ ያረጋገጡ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤ…
See more
በዛሬው እለት ህዳር 12 ቀን 2017 በመዲናችን በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደውን የህዳር ሲፀዳ የፅዳት ንቅናቄ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ይከታተሉ
ራሱን "ፋኖ" ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድንና ሸኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው"፦ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
***
ራሱን "ፋኖ" ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድንና ሸኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። የራሴ የሚሉትንም የጠላቴ የሚሉትንም በአምላክ አምሳያ የተፈጠረውን ክቡር የሰው ልጅን ህይወት አውሬ እንኳን በማይፈጽመው መልኩ በአስከፊ ሁኔታ በሁሉም አማራጮች ይገድላሉ።
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ-ደራ አካባቢ ጽንፈኛው ቡድን የፈፀመው የአረመኔነት ተግባር ይህንኑ የሚያመለክት ነው። ይህ ፈጽሞ ከሰው ልጅ የማይጠበቅ አፀያፊ ድርጊት መወገዝ አለበት።
ዓላማቸው ሁለት ነው። አንዱ ዓላማ በዚህ አሰቃቂ ድርጊት አንዱ ብሔር በሌላኛው ላይ ተነሳስቶ እልቂትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ማድረግ ነው። በዚህም እኩይ ፍላጎታቸውን ማሳከት ነው። ሌላኛው ዓላማቸው በዚህ ኢሞራላዊ ድርጊታቸው በህዝብ ዘንድ ፍርሃት በማንገስ ያሻቸውን ማድረግ ነው።
ሁለቱም ሞታቸውን ያፋጥነዋል እንጂ የሚሳካ አይደለም። ቅዥት እና እኔ ብቻ የሚል ጫፍ የረገጠ ጽንፈኝነት የሚወልደው በመሆኑ እንዲህ አይነት እኩይ ፍላጎት መቼም ቢሆን ተቀባይነት የለውም ብቻ ሳይሆን አይሳካም።
የአንድን ማህበረሰብ ልብ መግዛት የሚቻለው፣ በዚህም የትኛውንም አይነት ፍላጎት ከግብ ማድረስ የሚቻለው ምክንያታዊ በመሆን እና የማህበረሰቡን ህግጋትና ሞራላዊ እሴቶች በመጠበቅ ነው። ለማመን የሚከብደን ኢሞራላዊ ድርጊት በመፈፀም በዓለማችን የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ የቆመለትን ግብ ያሳካ የለም። ለጊዜው አንዳንዶቹ ኢሞራላዊ ድርጊቶች አንድን ውጥን ያሳኩ ይመስሉ ይሆናል። ይህ እንዳልሆነ የፋሽስቶች ታሪክ ምስክር ነው።
በሁለቱም አቅጣጫ ሰሞኑን በሰላሌ ደራ ላይ የተፈፀመው አጅግ ሊወገዝ የሚገባው አይነት ሰውኛ ያልሆኑ ድርጊቶች በመፈጸም አማራና ኦሮሞን ለመጨረስ ያልተሞከረበት ጊዜ የለም። ግን ሁሉም አልተሳኩም ብቻ ሳይሆን በዚህ አይነት ኢሞራላዊ ሁኔታ መቼም ቢሆን አይሳካም። ምክንያቱም የሰው ልጅ በተፈጥሮው ሚዛናዊ፣ ትርፍና ኪሳራን ለይቶ በምክንያታዊነት አቋም የሚወስድና ወደ ድርጊት የሚገባ ነው።
ሸኔ እና ጽንፈኛው ጃውሳ በሚፈጽሙት አሠቃቂ ድርጊቶች ሁለቱን የተወለዱ፣ የተገመዱ፣ ከሌሎች ወንድም እህቶቻቸው ጋር በመሆን በከፈሉት መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ያፀኑትን ህዝቦች በማጋጨት የትኛውንም አይነት እኩይ ፍላጎት ማሳካት አይቻልም።
የጽንፈኞች ፍላጎት ከማፍረስ እና ብጥብጥ ከመፍጠር የተሻገረ አይደለም። ፍላጎታቸው የህዝብ ጥቅም እና መብት ማስከበር ቢሆን ለምን ንጹሃንን ፣ ምስኪን፣ ራሳቸውን መካለከል የማይችሉ ሰዎችን ለምን ይገድላሉ ፣ ያርዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ሴቶች ይደፍራሉ፣ የህዝብና ግለሰቦች ሃብትና ንብረት ያወድማሉ? ዓላማቸው የራሳቸውን እና የሌሎች ሃይሎችን ፍላጎትና ጥቅም ማገልገል ነው።
በእንዲህ አይነት እኩይ ድርጊት የተሰማሩትን አረመኔዎች መላው ህዝብ እና መንግስት በተባበረ ክንድ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅመው ስርዓት እንዲይዙ ያደርጋሉ። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም ይስተካከላል። እየነፈሰ ያለው ሰላምም ይፀናል።
የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ 'የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና' በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ዓውደ ርዕይ ከፍተናል::
ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ ልዕልና በማመን ሀሳብ ይዞ፣ በሀሳብ ልእልና ታግሎ፣ በሀሳብ ልዕልና በህዝብ ተመርጦ ከህዝባችን ጋር ዝቅ ብሎ በመስራት ላይ የሚገኝ የህዝብ ፓርቲ መሆኑን በነዚህ አምስት ዓመታት የተሰሩ ስራዎች የሚመሰክሩና የፓርቲዉን ማንነት እና አላማ በግልፅ የሚያሳዩ ናቸው::
አዲስ አበባን እንደስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከተማችንን ጽዱ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል በማድረግ ቃላችንን በተግባር በመፈጸም እንዲሁም ለሰው ልጆች ቅድሚያ በመስጠት በልማት ስራዎቻችን የነዋሪውን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሰው ተኮር ስራዎችን ሰርተን የበርካቶችን እምባ አብሰናል::
ሆኖም መንገዳችን የሃሳብ ድቀት ባላቸዉ ኋላ ቀሮች ምክንያት ተግዳሮት እና ችግር አልባ አልነበረም። ባጋጠሙን ፈተናዎች ከጐናችን ያጣናቸዉና በመንገድ የቀሩም ነበሩ:: ነገር ግን ፓርቲያችን አሁንም በፅናት እና በድል ወደፊት ቀጥሏል ።
አሁንም ቃላችንን አድሰን፣ ተግዳሮቶችን አስወግደን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን በጀመርነው መንገድ ህዝባችንን ዝቅ ብለን የምናገለግልበት እንዲሁም የኢትዮዸያን ዘላቂ ሰላም እና ብልፅግና በማረጋገጥ በላቅ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና "በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፖርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አስመልክቶ "ህዳር ሲፀዳ "በሚል ማጠቃለያ እና የበጋ ፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በወዳኝነት ፓርክ ተዘጋጀ።
መድረኩን ያዘጋጀት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ በመሆን ነዉ።
የእለቱ የክብር እንግዳ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ አዲስ አበባን እንደ ስሟዉብ አረንጓዴና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ በሁሉም ቦታዎች የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ በመፍጠር ከተማዋን ከቆሻሻ ከማፅዳት በተጨማሪ ግንዛቤ መፈጠሩን ተናግረዉ ይህም ያለብንን ሃላፊነትና የጋራ ባለቤትነትን ያረጋገጥንበት ስኬቱም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ነዉ ብለዋል፡፡
አክለዉም ለከተማች የጋራ የብልፅግና ራዕይ መሳካት ሌት ከቀን ክትትልና ድጋፍ ላደረጉላቸዉ ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋ/ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ላለፉት ሰባት ዓመታት ህዳር ሲታጠን ሳይሆን ህዳር ሲፀዳ ነዉ ብለን በከተማዋ በርካታ ስራዎች መሠራታቸዉን እና ዉጤታማ ለዉጦች በከተማችን መመዝገባቸዉን ገልፀዉ "ፅዳት የአንድ ግለሰብ፤ማህበረሰብ መገለጫ ነዉም ብለዋል፡፡
የፅዳት ስራ ቀድሞ የተጀመረ ቢሆንም በአደረጃጀት፤በግብዓት እና በአሠራር እየተሻሻለ የመጣዉ ከለዉጡ ወዲህ መሆኑን ገልፀዉ በከተማችን የጀመርነዉ የአረንጓዴ ልማት እና የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ለከተማችን ነዋሪዎች፤ለቱሪዝም ምቹና ዉብ በማድረግ ያመጣነዉ ስኬት የጋራ ማሳያዎቻችን ናቸዉ በማለት በመድረኩ ተነሷቷል።
አክለዉም እነዚህ ስኬቶች ብልፅግና ፓርቲ በመሪነት ከከተማዋ ነዋሪዎች ፤መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እና ማህበራት ጋር በቅንጅት በመስራቱ መሆኑን አስታዉሰዉ በፓርቲዉ መሪነት ሰባት ተከታታይ ቀናትን ባደረገዉ የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ በድግግሞሽ 2.4ሚሊዮን ህዝብ በላይ መሳተፉንና 8 ሜትር ኪዩቢክ ደረቅ ቆሻሻ ተሰብስቦ መጓጓዙን ዋ/ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ለማ ገልፀዋል።
በማጠቃለያ ፕሮግራሙ አካባቢን ዉብና ፅዱ ከማድረግ ባሻገር ቆሻሻን ወደ ሀብት ለዉጦ በኢኮኖሚዉ ዘርፍ የገቢ ምንጭ ሊሆን የሚችልባቸውን የቆሻሻ ምርት ዉጤቶችን የሚያሳዩ የመልሶ መጠቀም አዉደ ርዕይ ተዘጋጅቶ የክብር እንግዶችና ተሳታፊዎች የጎበኙበትና ግንዛቤ ያገኙበት እድል መፈጠሩ በዝግጅቱ ተመላክቷል።
በመጨረሻም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና የፅዳት አምባሳደሮች የተዘጋጀላቸዉን የሰርተፊኬትና የዋንጫ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተረክበዋል ።
