cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ewnet Media

Більше
Рекламні дописи
867
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
-1130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በእሳት አደጋ የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል ወደመ‼️ አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 10:10 ሰዓት አቡኒ የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ተነስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፋብሪካዉ በከፊል መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ። የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢፕድ በሰጡት መረጃ እንዳሉት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦታ ከ56 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርቷል። ባለሙያው የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። በአደጋዉ ለመልሶ መጠቀም ግልጋሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ፋብሪካዉ በከፊል ወድሟል። በፋብሪካዉ የአደጋ ደህንነትን መስፈርት ያልጠበቁ ያገለገሉ የፕላስቲክ ዉጤቶች ክምችት እንዲሁም ስፍራዉ የአደጋ መቆጣጠር ተሽርከርካሪውችን የማያስገባ መሆኑ ለአደጋዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ አድርጓል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። (ኢ ፕ ድ)
Показати все...
👍 1
ነገ በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል‼️ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚቋረጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። በዚህም በቦሌ አትላስ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ ፊጋ፣ ላምበረት፣ አንቆርጫ፣ የተባበሩት፣ ፍየል ቤት፣ ገዳመ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጭላሎ፣ ኮካ፣ አዲሱ ገበያ እና አካባቢዎቻቸው የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል ተብሏል። በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ደንበኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
Показати все...
ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።ተጠርጣሪዎቹ ቴዎድሮስ ታከለ እና ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡ ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በሕግ የማስከበር ሥራው የልማት ተግባራት እንዲከናወኑ ተደርጓል‼️ 🗣የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት በዞኑ የተሠሩ የጸጥታና የልማት ሥራዎችን የሚገመግም መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩም የኮማንዶና አየር ወለድ ዋና አዛዥና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብዴታ እና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጄኔራል አበባው ሰይድን ጨምሮ የሠራዊቱ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል። ብርጋዴል ጄኔራል አበባው በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በዞኑ የጸጥታ ኃይሉን እንደገና ማደራጀት በመቻሉ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የተጀመሩ ሥራዎች ውጤት እንዲያመጡ አስችሏል ብለዋል፡፡ ግብርናው በአግባቡ እንዲከናወን፣ ማዳበሪያn ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ እና ከተሞች ሰላም እንዲሆኑ መደረጉንም አብራርተዋል፡፡ ሕዝቡ ለሠራዊቱና ለመንግሥት የጸጥታ ኃይል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በአጭር ጊዜ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показати все...
👍 1
መሃመድ ሞክበር የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ‼️ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ መሃመድ ሞክበርን የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡ መሃመድ ሞክበር በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ምክትል እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዱላሂን በመተካት ደግሞ አሊ ባጌሪ ካኒ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ አሊ ባጌሪ ካኒ ቀደም ሲል የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ተመላክቷል፡፡ በኢራን ከ50 ቀናት በኋላ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድ መገለጹንም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡ በተያያዘ ዜና በሄሊኮፕተር አደጋው ለደረሰው ሀዘን የተለያዩ ሀገራት ለኢራን ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል። በዚህም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼሃባዝ ሻሪፍ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የቬንዝዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማድሮ እና በርካታ የሀገራት መሪዎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#BREAKING የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሆሴን አሚራብዶልሂያንን ጭኖ ሄሊኮፕተሩ በተከሰከሰበት ቦታ "የተረፈ ሰው የለም" ሲል የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል‼️ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ለሰዓታት ያህል ተራራማ ቦታዎችን ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የነፍስ አድን ቡድኖች የተከሰከሰውን ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ ወድሟል ብለዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Private coin 12 days left Start now !! Use this link to get 100k free coins 👇 PRIVATE COIN Mokrut ende notcoin value yenorewal teblo yetebekal try your luck forex lemejer asebachu capital yelelachu yetekmachuhal launch sidereg tru value yenorewal Good luck !!
Показати все...
Repost from N/a
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Private coin 12 days left Start now !! Use this link to get 100k free coins 👇 PRIVATE COIN Mokrut ende notcoin value yenorewal teblo yetebekal try your luck forex lemejer asebachu capital yelelachu yetekmachuhal launch sidereg tru value yenorewal Good luck !!
Показати все...
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለኢትዮጵያ መንግሥት ላይ "ውንጀላ አቅርበዋል"፤ "መንግሥት አገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለበትም ያልተጠየቁትን ምክር ለግሰዋል" በማለት ወቅሷል‼️ የአምባሳደሩ ንግግር "ትርጉም የማይሰጡ" እና "በበቂ ኹኔታ ያልተጤኑ" ሃሳቦችን ያካተተ ነው ያለው ሚንስቴሩ፣ አምባሳደሩ "በምርጫ የተመረጠውን መንግሥት በኃይል ለመጣል የሚሠሩ ቡድኖችንም በስም ጠቅሰዋል" በማለት ተችቷል። ኢምባሲው፣ በአምባሳደሩ መግለጫ ላይ የተንጸባረቁትን "የፍሬ ነገር ስህተቶች" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ ገልጧል። አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት የመን የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ውስጥ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በሲቪሎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳይ በመጥቀስ "አገር ዓቀፍ የተኩስ አቁም" እንዲደረግ ጠይቀው ነበር።
Показати все...