cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Orthodox tewahido

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
168
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ጾመ ሰብአ ነነዌ ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም (፳፻፲፫ ዓ.ም) የካቲት ፲፭ ቀን ትጀመራለች፡፡ ‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው /ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡ ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡ እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡ ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡ ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡ ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡ ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ምንጭ፡-ማህበረ ቅዱሳን
Показати все...
✍ ስለ አሥራት ............................................................. በቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ምዕመናን በየንግስ በዓላቱ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች የሚጠየቁትን ገንዘብ ይሰጣሉ። ቤተ ክርስቲያናችንም ከምታገኙት ከአስር አንዱ የእግዚአብሔር ነው ብላ ስለ አሥራት ታስተምራለች። ግን አሥራት በገንዘብ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም አሥራት ማለት እግዚአብሔር ከሚሰጠን ነገር ሁሉ ከአስር አንዱን ለባለቤቱ መስጠት ማለት ነው። የተሰጠን ሁሉ ደግሞ ከእግዚአብሔር ነውና ከእያንዳንዱ ነገር ላይ አሥራት ማውጣት አለብን። ከጊዜያችንስ አሥራት እናወጣለን? በቀን ውስጥ ከተሰጠን 24 ሰዓታት ውስጥ ከአስር አንዱን ስናሰላው 2 ሰዓት ከ 24 ደቂቃ ይሆናል። ይህ ማለት ደግሞ በወር ውስጥ ካሉት 30ቀናት፤ 72ሰዓታት (3ቱ ቀናት) የእግዚአብሔር ናቸው ማለት ነው። በዓመት ውስጥ ከተሰጠን 365 ቀናት ውስጥ ደግሞ 36 ቀናቱ (1ወር ከ6 ቀናት) የእግዚአብሔር ናቸው ማለት ነው። ይህ ሁሉ ስሌት ውስጥ የገባነው ከአስር አንዱን ለማስላት ነው፤ ነገር ግን በየቀኑ የጊዜ አስራታችንን ካወጣን ከወርም፣ ከዓመትም አሥራት አወጣን ማለት ነው። እግዚአብሔር የጊዜ አሥራታችንን ከእኛ ይፈልጋል። እኛ ጊዜያችንን ስለሰጠነው እርሱ ምንም ባይጠቀምም እኛ ግን እንጠቀማለን። አይገርምም ግን? እግዚአብሔር የምንሰጠውን አብዝቶ ሊመልስልን ከእኛ ይጠይቀናል። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር የሆነውን ጊዜ ስለምንነፍገው የእኛ ጊዜያችን ሁሌ የተቃጠለ ይሆናል። ዕድሜያችንን ሳናውቀው ስለሚሄድብን ዕድሜያችንን ለመናገር እንፈራለን። የማናስተውለው ነገር ግን ጊዜያችንን እንድንጠቀም የሚያደርገንም እግዚአብሔር መሆኑን ነው። ብዙ ሰው በማይስማማው ሥራና አኗኗር ውስጥ ጊዜውን ሲያቃጥል አይተናል። ግን ለእርሱ የሚስማማውን ለሚያውቅለት እግዚአብሔር ጊዜውን ስለማይሰጥ ዕድሜው ዝምብሎ ያልፍበታል። ይህችን 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ለእግዚአብሔር በአግባቡ መስጠት ይገባናል። ጠዋት እንደተነሳን ሃያ ደቂቃዋን ውዳሴ ማርያም ብንጸልይባት፣ አንድ ሰዓቷን ቅዱሳት መጻሕፍትን ብናነብባት፣ አንድ ሰዓቷን ቤተ ክርስቲያን ሄደን ኪዳን ብናደርስባት ሞላነው ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ጊዜ መስረቅ ስናቆም የእኛ ጊዜ እንዴት መልካምና የማይባክን እንደሚሆን እስቲ እናስተውል። ከንግግራችንስ አሥራት እናወጣለን? አንደበትን ከነቋንቋው የሰጠ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ከምንናገረው ሁሉ ከአስር አንዱ ስለ እግዚአብሔር መሆን ይኖርበታል። ስንቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስንገናኝ እንነጋገራለን? ብዙዎቻችን ስንገናኝ የምናዘወትረው ፌዝ እና ቀልድ ነው። ከእርሱ ተቃውሞ ባይኖረኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጠው አንደበት ሳይመሰገን መዋል የለበትም። እስቲ አስቡት የእውነት ከአንደበታችን አሥራት ብናወጣ ኑሮ በመናገር(በነቢብ) የምንሰራው ኃጢአት ባልበዛ ነበር። የእግዚአብሔርን ነገር፣ ስለ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና ስለ ቅዱሳን ወዳጆቹ መነጋገር ብንጀምር እንደ ትንፋሽ ወደ ውጭ የምንተነፍሰው ስድብ በጠፋልን ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል የሚናገር አንደበት በንግግሩ ሰውን የማያስቀይምና ሲናገርም የሚሰማ ይሆናል። ከምንሰማውና ከምናየውስ አስራት እናወጣለን? በዚህ ዘመን "ዐይን ቦሙ ወኢይሬእዩ፤ እዝን ቦሙ ወኢይሰምዑ።"/ "ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም።"(መዝ 134:16) ብሎ በቅዱስ ዳዊት ለጣዖት የተነገረው ቃል ለእኛ ቢነገር ይሻለን ነበር። ምክንያቱም ዓይናችንም ጆሮአችንም የሚያየውና የሚሰማው ክፉ ነገር ሆኗልና። ይህ ለምን ሆነ ብንል ዓይናችን ኃጢአትን በመመልከት፣ ጆሮአችንም ከንቱ ነገርን በመስማት ተጠምዶ አሥራቱን ማውጣት ስላቃተው ነው። የዝሙት ፊልሞችን በማየት የሚረክሰው ዓይናችን ቤተ ክርስቲያንን በማየት አሥራት ቢያወጣ የት በደረስን ነበር? "ርዕይክዋ ለቤተ ክርስቲያን፣ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን።" /"ቤተ ክርስቲያንን አየኋት፣ ቤተ ክርስቲያንን ወደድኳት።"ብሎ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ባደረብን ነበር። የሰውን ጉድለት እያፈላለገ ሐሜት ለማዳመጥ የሚተጋው ጆሮአችን በመላዕክት ዜማ የሚቀደሰውን ቅዳሴ ቢሰማ የት በደረስን ነበር? አሁን የምንሰማው ሁሉ ክፉ በሆነበት ዘመን ቸር ወሬ አምላክ ያሰማን ነበር። ሁሉ ከእርሱ፣ ሁሉ ለእርሱ የሆነው አምላክ ከተሰጠን ነገር ሁሉ የእርሱ የሆነውን ለባለቤቱ እንሰጥ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ይርዳን። እመቤታችን ከእቅፍዋ አታስወጣን። የቅዱሳኑ ሁሉ አማላጅነታቸው ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር። አሜን .......//......//.......//.....//.......//........... ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ የካቲት 04/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ 👇👇👇👇👇👇 @ortho1234tewahido
Показати все...
ተወዳጆች ሆይ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጥቶ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነውን? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነውና፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Показати все...
​​#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዘጋዛ ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ አካባቢ የተወለደ ሲሆን የክቡራኑ የመሣፍንት ልጅ ነው:: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ትንሹ ቴዎዶስዮስ ወደ ቤተ መንግስቱ ወሰደው:: በዚያም "አገረ ገዥ ላድርግህ" ብሎ ቢጠይቀው "ትንሽ ቆየኝማ" ብሎት ጠፍቶ በርሃ ገብቶ መነኮሰ:: ቅዱስ ዼጥሮስ በምንኩስና ሲጋደል: ካለበት በርሃ መጥተው በግድ ወስደው: የጋዛ (አሁን የፍልስጤምና እሥራኤል ደንበር) ዻዻስ አደረጉት:: ከደግነቱ የተነሳም በቅዳሴ ጊዜ ሥጋ ወደሙ ሲለወጥ ያየው ነበር:: መላእክትም ያጫውቱት ነበር:: ሕዝቡ ሲያጠፉ በየዋሕነት ዝም ቢላቸውም ቅዱስ መልአክ ገሥጾታል:: የፋርስ ነገሥታት አጽመ ሰማዕታትን ሲያቃጥሉም እርሱ የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን አጽም ይዞ ተሰዷል:: ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል:: #ቅድስት_ቤርሳቤህ ይህቺ እናት አስቀድማ የኦርዮ ሚስት: ቀጥሎ ደግሞ የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት ለመሆን በቅታለች:: ቁጥሯ ከደጋግ እናቶቻችን ሲሆን የድንግል ማርያም ቅድመ አያትም ናት:: አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ ስሟን "ቤትስባ (ቤተ ሳባ)" : ትውልዷንም ከኢትዮዽያ ያደርጉታል:: አምላከ ኤልያስ በምልጃው ለሃገራችንና ለሕዝቧ ርሕራሔውን ይላክልን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ይክፈለን:: #ታሕሳስ_1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤልያስ ርዕሰ ነቢያት 2.ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ 3.ቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) 4.ናቡቴ ኢይዝራኤላዊ 5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት #ወርኀዊ በዓላት 1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር 5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት "+ ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝኩትን: የባሪያየን የሙሴን ሕግ አስቡ:: እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላቹሃለሁ:: መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች: የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል:: +" (ሚል. 4:4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ኃያል ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው:: ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር:: አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር:: እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል:: እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው:: "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት:: ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ:: አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው:: ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ:: ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ:: በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው:: እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ:: በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት:: በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ:: ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት:: እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም:: ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ:: በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው:: "ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው:: ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:- "አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም:: እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም:: አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት:: ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል:: እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል:: <<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>> አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን:: #ኅዳር_25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት 2. ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ) 3. ቅዱስ ሮማኖስ ዝክረ ቅዱሳን
Показати все...
+++ ጤዛ ላሿ ወፍ፤ የእኛ ትውልድ+++ (በከመ ጸሐፈ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ) የእኛ ሊቃውንት በስምንተኛው ሺሕ የሚነሣውን የእኛን ትውልድ ለመግለጽ ምሳሌ አድርገው የሚጠቀሙባት አንዲት ወፍ አለች። ወፏን ዖፍ ሳምኒት ይሏታል። የስምንተኛው ሺሕ ወፍ እንደማለት ነው። የዚያን ትውልድ ትወክላለች ለማለት። ለዚህ ትውልድ ውክልና ያዋሏት በአኗኗሯ ምክንያት ነው። ይህች ወፍ የምትኖረው ባሕር ውስጥ ነው። ውኃ ሲጠማት ግን ለመጠጣት ወደ የብስ ትወጣና ጤዛ ትልሳለች ይላሉ። ስለዚህ ነው የእኛን ትውልድ ዖፍ ሳምኒት የሚሉት። በርግጥም የእኛ ትውልድ በተለይም በአሁኑ ወቅት ያለው እንደዚች ወፍ ባሕር ውስጥ እየኖረ የማይጠጣ ሲጠማም ከባሕር ወጥቶ ጤዛ ፍለጋ የሚንከራተት ትውልድ ሆኗል። የፍቅርና የፍጹም እውነት ባሕር የሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየኖረ በወቅታዊ ችግሩ ጥም ሲነሣበት ካለመጠጣቱም በላይ ጥሙን ለማስታገስ የሚሮጠው በደረቁና ውዕየት በሚሰማቸው የፖለቲከኞች ለማስመሰልና ለተቀባይነት ሲሉ የሚናገሯቸው ንግግሮች ውስጥ ያሉ እነርሱ የሚያረኩ የሚመስሏቸውን ጤዛ ፍለጋ ሲቃትት እንደ ማየት የሚያሳዝን ነገር የለም። ነፍሳትን ነጻ የሚያወጣ፣ የራቁትን የሚያቀርብ፣ የተለያዩትን አንድ የሚያደርግ ፍጹም ሥልጣነ ክህነት የምትሰጥ ባሕር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ ከፖለቲካም የጎሣ ፖለቲካን መሠረት ያደረገ፣ እንኳን በሰማይ በምድርም ከክብሩ ውርደቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚበልጥ ጤዛ የሆነ ሥልጣን ፈልገው ከባሕር ወጥተው የብስ ለየብስ ሲንከራተቱ እንደ ማየት ያለ አሳዛኝ ነገር የለም። እንዲያው ለመጠቆም ያህል ትንሽ ጠቆምኹ እንጂ በዘመናችን ጊዚያዊ የሆነውን የሥልጣን፣ የገንዘብ፣ የዝናና የክብር ጥሙን ለማርካት ሲል ከሚኖርበት ባሕር ወጥቶ ጤዛ ለመላስ ሜዳ ለሜዳ የማይንከራተተው ስንቱ ይሆን? ስንቱንስ መዘርዘር ይቻላል? በተለይ በክህነትና በምንኩስና እየኖረ በዐለማውያንና በደረቁ ፖለቲከኞች መካከል ጤዛ ፍለጋ የማይንከራተት በእውነት ብፁዕ ነው። ይህን የምጽፈው አንባቢዎች ለእነ እገሌ ነው ብለው በስሕተት በምንገምታቸው ሰዎች እንድንሳለቅ አይደለም። እርሱማ ተያይዞ ጉዞ ነው። ይልቁንም ሁላችንም ራሳችንን አይተን እግዚአብሔር እኛንም ሌሎችንም የእውነቱ ባሕር፣ የፍቅሩ ባሕር ፣ የሥርዓቱና የመፍትሔው ሁሉ ባሕር ወደ ሆነችው ወደ ቤተ ክርስቲያናችንና ወደ ሥርዓቷ እንዲመልሰን እርሱን እንጠይቀው ዘንድ ለማሳሰብ ብቻ ነው። ይልቁንም ለመጪው ጾማችን እንደ ቅበላ ግብዣ ወስደነው ራሳችንን ብናዘጋጅበት ምን ያህል አምላካችንን ደስ ባሰኘነው። እንደ ዖፈ ሳምኒት ከባሕር ወጥተን ጤዛ ፍለጋ በየብስ ከመንከራተት እግዚአብሔር ይጠብቀን። መልካም ቀበላ ጾም።
Показати все...
​​ማግባት ስትፈልጉ ይህን አስተውሉ፦ የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ #ጽድቅን #መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ የትዳር ዓላማዎች ኹሉ በዚህ የሚጠቃለሉ ናቸውና፡፡ ስለዚህ አንድ ወጣት፡- ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት የለበትም፤ የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ፥ ላይወልድም ይችላልና፡፡ “በየምግብ ቤቱ መብላት ወጪውን አልቻልኩትም” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ “በገንዘብ እንድንረዳዳ” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ ወጪ መቀነስ መልካም ቢኾንም፥ የትዳር ዋናው ዓላማ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነውና፡፡ እንዲያውም ሊቁ፡- “ክርስቲያን ኾነህ ሳለ ከትዳር አጋርህ ገንዘብ ለማግኘት ብለህ ወደ ትዳር ከምትገባ ምድር ተከፍታ ብትውጥህ ይሻላል” ይላል፡፡ ስለዚህ “ገንዘብን አትሹ፤ የወላጆቹን ባለጸግነት አትመልከቱ፡፡ የትውልድ ቀዬውን ታላቅነትም አትዩ፡፡ እነዚህ ኹሉ ዋና ነገሮች አይደሉምና፡፡ ከትዳር አጋራችሁ ጋር በተድላ በደስታ መኖርን ስትሹ ማየት የሚገባ’ችሁ ንጽሃ ነፍስን፣ ደግነትን፣ ልባምነትንና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ነው፡፡” አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ ነው በሚል ብቻ ማግባት የለበትም፡፡ ይህ በራሱ መልካም ቢኾንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልኾነ አንድ ለአንድ መወሰን ብቻውን የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ አይደለምና፡፡ ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው አንድ ለአንድ የሚወሰኑ አሉና፡፡ ዕድሜዬ እንዳያልፍ ብሎም ኾነ ሰው አግባ ብሎ አስጨንቆት ማግባት የለበትም፡፡ ትዳር ከ “ለምን አታገባም?” ጭቅጭቅ ለማምለጥ የተሰጠ አይደለምና፡፡ “መልኳን ወደድኳት” ብሎ ማግባት አይገባም፡፡ ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለምና፡፡ ይህን አድንቆ ወደ ትዳር ከገባ ያ የማረከው ውበት ከሃያ ወይም ከሠላሳ ቀናት በኋላ አይማርከውምና፤ ይለምደዋልና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ) 🙏🙏@ortho1234tewahido🙏🙏
Показати все...
ሮሜ 8÷34 ብዙዎች የተጣመሩባት ለእምነታቸው መሠረት ያደረጓት እንደ ጥያቄ እንደ መልስም የሚጠቅሷት ብቸኛ ጥቅስ ናት ሮሜ 8÷34 ::  ቃሉ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል:: “የሚማልደው” የሚለውን ቃል ይዘው ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ:: ( ሎቱ ስብሐት) አለማስተዋል ካልሆነ በቀር በዚህ የሚሳሳት ሰው አለ ለማለት አያስደፍርም ምክንያቱም ከላይ ስናነብ የምናገኘው የዚህ ተቃራኒ ነውና::  ከቁጥር 33 ጀምረን እንመልከት “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ... ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” አእምሮ ላለው ይህን መረዳት በጣም ቀላል ነው:: የሚያጸድቅ ክርስቶስ ነው የሚኮንንም ክርስቶስ ነው የሚማልደው ማነው? ማንንስ ይማልዳል? የሚያጸድቅ ማለት አንተ ቅዱስ ነህና መንግሥተ ሰማያት ግባ የሚል እውነተኛና  የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጥ ማለት ነው የሚኮንን ሲል ደግሞ አንተ ኃጥእ ነህና ገሃነመ እሳት ግባ የሚል እውነተኛ ፍርድ የሚፈርድ ማለት ነው::  ቅዱስ ጳውሎስ ፈራጅነቱን ሲያጎላ መጥቶ በእርግጠኝነት “ስለኛ የሚማልደው” ብሎ አይደመድምም:: ነገር ግን እኛ በራሳችን መንገድ መሄድ ስንሻ ያጣመምነው ቃል እንደሆነ ግን እንረዳለን:: ቅዱሳንን የሚንቁ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚጠራጠሩ ሰዎች አምላካቸውን ያከበሩ እየመሰላቸው አማላጅ ነው ይሉታል::  ትክክለኛ ቃሉ “ስለእኛ የሚፈርደው” የሚል ነው:: ከላይም የተጻፈው ይህንኑ ነው የሚገልጸው:: መጽሐፉን በሙሉ መመልከት ትልቅ መልስ ይስገኛል:: ቃሉን በትክክል ለመረዳት ከላይም ከታችም የተጻፈውን ማብራሪያ በሚገባ ማንበብ ያስፈልጋል::  አንድ ጥቅስ ዝም ብሎ ከመካከል መዝዞ አይነበብም ምክንያቱም ቃሉን ለመረዳት አስቸጋሪ በመሆኑ:: ክርስቶስን በተጻፈው መሠረት አማላጅ ነው ብንል እንኳ (ሎቱ ስብሐት) ሌሎች ጥቅሶችንም ማንሣት እንሻለን:: እሽ እኛ በምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ስለ እኛ የሚማልደው” ይላል ስለዚህ “ኢየሱስ አማላጅ ነው” የምትሉ ሰዎች እስኪ በማስተዋል ሁኑና የሚከተሉትን ጥቅሶች፡- v  ሮሜ8÷26  ላይ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” ይላል:: ከዚህ እንደምንረዳው መናፍቃንም ይህንን ጥቅስ ይዘው መንፈስ ቅዱስ ይማልዳል ማለት አለባቸው ማለት ነው:: v  ኤር7÷25  “አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር” ይላል:: እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚለው አብን ነው ከላይ ጀምራችሁ ተመልከቱት:: ስለዚህ በመናፍቃን አስተሳሰብ መሠረት አሁንም አብ ይማልዳል ማለት ነው:: አሁን ከእነዚህ ጥቅሶች በመነሣት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሁሉም ይማልዳሉ ልንል ነው ማለት ነው? ጥሬ ቃል ይዘን የምንሮጥ ከሆነ ከዚህ የዘለለ ድምዳሜ አይኖርም፡፡ ስለዚህ አብም ይማልዳል፤ ወልድም ይማልዳል፤ መንፈስ ቅዱስም ይማልዳል ማለት ነው (ሎቱ ስብሐት)፡፡ በፍጹም እኛ የእነአትናቴዎስና የእነቄርሎስ ልጆች እንዲህ ብለን አናምንም የሉተር ልጆች ግን ያምናሉ::  እኛ አምላካችንን አማላጅ አንለውም:: እኛ የምናመልከው እግዚአብሔር ተማላጅ ነው:: አማላጆቻችንም ቅዱሳን ናቸው:: “ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው::  እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ ክርስቶስ በእኛ እንደሚማለድ ስለክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን” 2ኛቆሮ 5÷18-21 የማስታረቅ አገልግሎት ወይም ምልጃ ለቅዱሳን እንደ ተሰጠ በግልጽ አስቀምጧል:: ቅዱሳን የምልጃ አገልግሎት እንደሚሰጡ በግልጽ እንረዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ሮሜ 9÷5 “ክርስቶስ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው” እንዲሁም ሮሜ 14÷10 ላይ  “ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና” ይላል ፈራጅነቱን ሲገልጥ፡፡ ቅዱሳን በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም የማማለድ ሥራ እንደሚሠሩ ድውይ እንደሚፈውሱ ሙትም እንደሚያነሡ የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡፡  1ኛ17÷22 ላይ “እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ የብላቴናው ነፍስ ወደርሱ ተመለሰች ርሱም ዳነ”  2ኛ ነገ4÷35 ላይ “ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕጻኑ ላይ ተጋደመ ሕጻኑም ዐይኖቹን ከፈተ” 2ኛነገ13÷21 “ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ” ሐዋ3÷7 “…በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው በዚያን ጊዜም ቁርጭምጭሚቱ ጸና” ይላል እናንተ ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ እየጀመራችሁ ሙሉ ታሪኩን ተመልከቱት፡፡  ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የሚል የዘንዶው ደጋፊ ካለ ደግሞ ዮሐ 1÷1 -5 ፣ ሮሜ 9÷5፣1ኛ ዮሐ 5÷20 ያንብብ:: @ortho1234tewahido🙏🙏
Показати все...
H@yohanis Aber: 🌼 ❤ 2013_ዓ.ም አፅዋማት እና በዓላት 🌼 ❤ 1_ የፅጌ ፆም መስከረም 26 ማክሰኞ 2_ የገና ፆም ህዳር 15 3_ በዓለ ገና ታህሳስ 29 ሃሙስ 4_ ጥምቀት ጥር 11ማክሰኞ 5_ ነነዌ ፆም የካቲት 15 ሰኞ 6_ የትንሳኤ ፆም የካቲት 29 ሰኞ 7_ ደብረ_ዘይት መጋቢት 26 እሁድ 8_ ሆሳዕና ሚያዝያ 17 እሁድ 9_ ስቅለት ሚያዚያ 22 አርብ 10_ ትንሳኤ ሚያዝያ 24 እሁድ 11_ ርክበ ካህናት ግንቦት 18 ረቡዕ 12_ እርገት ሰኔ 3 ሐሙስ 13_ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 13 እሁድ 14_ ፆመ ሃዋርያት ሰኔ 13 ሰኞ 15_ ፆመ ድህነት ሰኔ 16 ረቡዕ 16_ ፆመ ፍልሰታ ነሐሴ 1 ቅዳሜ
Показати все...
🕯 💛 🕯 ✞ እንኩዋን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ 💛 [ ጽዮን ማርያም ] "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) በመጨረሻም ኅዳር 21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን :- ፩. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) ፪.በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) ፫.በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: ፬.በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) ፭. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: ፮.በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: ፯.በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: ፰.በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: 🕯 💛 🕯 " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " =>"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: ፩."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) ፪."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) ፫.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: ፬.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡ 🕯 💛 🕯
Показати все...