cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አል ኢህሳን ሚዲያ

አላማዪ በተቻለኝ አቅም እና አላህ በሰጠኝ ስጦታ ኡማውን ማገልገል ነው:: For any coment @Letif1

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
368
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

# አግብታ_የፈታች_አልያም_ባል_የሞተባት_ሴት_ክብር ! ≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅ ☞አላህን እንፍራ! ≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅ ☞አንዲት በሰሓቦች ዘመን የነበረች ሴት ባሏ የሞተ አልያም የፈታት ግዜ ሰሓቦች እሷን ለመንከባከብና ለመደገፍ ክብር በተላበሰ መልኩ ይቻኮሉ ነበር። ☞የሰሓቦችን ታሪክ ብናገላብጥ አንዲት ሰሓቢይ ሴት አራት ሰሓቦችን በተለያየ ግዜ እንዳገባች እንረዳለን። አንዱ ሲሞት ሌላውን እያገባች ተከብራ ኖራለች። እሷን የመሰሉ ሴቶችን በንቀትና በጉድለት በፍፁም አይመለከቷቸውም ነበር። ☞ዐቲካ የምትባልን ሴት ተመልከት! የአቡ በክር ልጅ አገባት በጣም ታፈቅረው ነበር እሱም በቃላት ሊገለፅ በማይችል መልኩ ይወዳታል ከግዜያት ቡኃላ ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም ታላቁ ሰሓቢይ ዑመር አልፋሩቅ አገባትና እሱም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም እሷን ለማግባትና ለማክበር የመልእክተኛው ሓዋሪይ የሚባለው ታላቁ ሰሓባ ዙበይር ኢብኑል ዓዋም ተቻኮለ፤ አገባትም። ከጥቂት ግዜ ቡኃላም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ሰዎች ሲሞቱ "በባሎቿ ላይ ሙሲባ የምታመጣ" አልተባለችም። እንደውም "ሸሂድ መሆን የፈለገ ዐቲካን ያግባ!" ተብሏል። ☞የአስማዕ ቢንት ዑመይስን ታሪክ እናገላብጥ። የመጨረሻ ባሏ ታላቁ ጀግና ፈረሰኛው ሰሓቢይ ዐሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ነበር። ከሌሎች ባሎቿ የወለደቻቸውን ልጆች ያጫውት የሷን ጣፋጭ ንግግርና የልጆቿን ጨዋታ በመስማት በደስታ ፈገግ ይል ነበር። በቀደሙ ባሎቿ በፍፁም ቅናት አይሰማውም። "በቀደሙ ባሎችሽ ላይ ስሞቷ ብታሰሚ እቆጣሻለው! በፍፁም በመጥፎ ስታነሺያቸው እንዳልሰማ እነሱ ወዳጆቼ ናቸው።" ይላት ነበር። (ሁሉንም አላህ ስራቸውን ይውደድ!) ☞የትኛዋም ሰሓቢያ ሌላ ባል ስታገባ የመጀመሪያ ባሏን እያወሳች በክህደት አልተጠረጠረችም። ☞የአላህ መልእክተኛም ከእናታችን ዐይሻ በስተቀር ድንግል ሴት አላገቡም። መጀመሪያ ትዳርን የመሰረቱትም ከሳቸው በፊት ትዳርን ከምታውቀው ከእናታችን ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ጋር ነበር። ☞የተፈታችን አልያም ባል የሞተባትን ሴት ማግባት እንዲሁም ከአንድ በላይ ማግባት ስነ ምግባርን የሚጥስ፣ ክብርን የሚነካና የሚጠየፉት የወረደ ተግባር ቢሆን ቀድሞውንም ኢስላም ይከለክለዋል። ስነ ምግባርን፣ ልቅናንና እውነተኛ ሰብኣዊነትን ያስተማረን ኢስላም ነውና! ☞የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አላህን ከፈራች ከፍቺውም ቡኃላ አላህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር ያበጅላታል። ☞ከመጀመሪያ ባልሽ የተሻለ መልካም የትዳር አጋር አላህ ሊሰጥሽ ይከጀላል። መጪው ቀናት በአላህ ፈቃድ መልካም ብስራትና ተስፋ ይዞ ብቅ ይላል። አንገትሽን አትድፊ! ☞እኛም የደረሰባቸውን ሀዘን ለመጠገን መሯሯጥ ይገባናል። በብዛት የሚያጋጥማቸውን ሞራላዊና ማህበረሰባዊ ተፅእኖ በመልካም ለመግፈፍ መታተር ይጠበቅብናል። ☞በክፉ ከሚመለከቷቸው የሰው አውሬዎች ልንከላከላቸውና በደካማ ጎናቸው ለማጥቃት ካሰፈሰፉ ዋልጌዎች ልንጠብቃቸው የበኩላችንን ጥረት ማረግ አለብን። ☞በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ወቅት አግብታ የፈታችን ሴት ለማግባት የሚያስብ የሷን መብት ልክ እንደ አሮጌና ያገለገለ መኪና አስመስሎ ፕሮፖዛል የሚያቀርብ አለ። ☞ይህ በሴቶች መብት ላይ ግፍና በደል ነው። አሏህን ልንፈራ ይገባል! ☞ባል የሞተባት አልያም የፈታች እህትና ልጅ ቢኖረህ ለሷ የምትመኘውን ለሎችም እህቶችን መመኘት አለብህ። ስሜት ካወረው ፅልመት ተላቀህ ሰብኣዊነት የተሞላ ኢስላሚዊ መንፈስ ይኑርህ። ☞ቁምነገሩ ያንተ ወንዳ ወንድነትና ስብእና እንጂ የሷ የቀደመ ትዳር ተፅእኖ አይደለም። ☞በብልሀትና በስነምግባር የተሞላህ መሆንህ በአላህ ፈቃድና ችሮታ ያለፈ ህይወቷን አስረስቶ ስኬታማ ትዳርን በሀሴት ይለግሳታል። ☞ኋላ ቀር የሆኑ አባባሎች ጠፍረው አይከርችሙህ። መመሪያህ ኢስላም ብቻ ይሁን። በሙስሊም እህቶቻችን ላይ አላህን እንፍራ! ከተወሰነ ማብራሪያ ጋር የተተረጎመ! @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
"ስለ ዙል ሒጃ አስር ቀናቶች ጥቆማ‼️" ________________ ✍️በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዛሬ ዕለተ ሐሙስ ነሀሴ 3, 2010 ዓ.ል ነው። በሒጅሪያህ አቆጣጠር ደግሞ ዙል ቂዕዳ 27, 1439 ነው። የዙል ሒጃ ወር ሊገባ ሁለት ወይም ሶስት ቀናቶች ብቻ ይቀራሉ። ስለዚህ ስለነዚህ ቀናቶች አንዳንድ ጥቆማዎችን እንቃኝ። 👉1✔️የዙል ሒጃ የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ታላቅነት✔️ _____________________________ እነዚህ አስርት ቀናቶች አላህ በቁርኣን ላይ የማለባቸው ቀናቶች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፦ "{وَالْفَجْرِ. وَلَيَالٍ عَشْرٍ} [الفجر:1-2]" "በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም።" [አል፡ፈጅር: 1-2] | ታላቁ የቁርኣን ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሢር <<በዐሥር ሌሊቶችም>> በሚለው የተፈለገው የዙል ሒጃን የመጀመሪያ አስርት ቀናቶች ነው በማለት ኢብኑ ዓባስ፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ሙጃሂድና ሌሎችም መናገራቸውን ጠቅሰዋል። {{(ተፍሲር ኢብኑ ከሢር ፥ 4/539-540).}} ከነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከተዘገቡ የሐዲሥ መዛግብቶች ውስጥም የሚከተሉት ይገኙበታል። ( ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر . قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله ، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء ) [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (ቡኻሪ: 2/457) | በተመሳሳይ ገለፃም ከኢብኑ ዓባስ በተወራ ሐዲሥ ስለ ቀናቶቹ ትሩፋትና ታላቅነት ኢማሙ ዳሪሚይ 1/357 በኢስናዳቸው ዘግበዋል። ለተጨማሪ ማብራሪያም ተፍሲር ኢብኑ ከሢር 5/412 ላይ ይመልከቱ። 2✔️"በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሚወደዱ ተግባራቶች" _________________________ ✔️ሐጅና ዑምራ ✔️ፆም ✔️ ተክቢር፣ ተህሊልና ሌሎች ዚክሮችም ጭምር ✔️ተውበት፣ ከወንጀል መራቅ ✔️መልካም ስራንና ዒባዳን ማብዛት፡ ሶላት ሶደቃ፣ ጅሃድ ✔️የማረጃው ቀንም ኡዱሕያን መተግበርና ሌሎችም 👉كان النبي صلى الله عليه وسلم يصوم تسع #ذي_الحجة ويوم عاشوراء وثلاثة أيام من كل شهر . أول اثنين من الشهر وخميسين " "ነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም #የዙል_ሒጃን ዘጠነኛው ቀን፣ የዓሹራን ቀን፣ ከየወሩ ሶስት ቀናት፣ እንዲሁም በወሩ ውስጥ ሰኞንና ሐሙስን ይፆሙ ነበር።" {{ "ነሳኢይ: 4/205" "ኢማም አልባኒም በሶሒሕ አቡ ዳውድ 2/462 ላይ ዘግበውታል። | 👉( ليشهدوا منافع لهم ويذكروا اسم الله في #أيام_معلومات على ما رزقهم من بهيمة الأنعام ) الحج/28 "ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ #በታወቁ_ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ። " [አል-ሐጅ: 22:28] "أيام_معلومات" <<በታወቁ_ቀኖች>> የሚለውን አገላለፅ ከኢብኑ ዓባስና ኢብኑ ከሢር በተገኘ ዘገባ የዙል ሒጃን አስርት ቀናቶች ለመጠቆም መሆኑ ተዘግቧል። [( الأيام المعلومات : أيام العشر ) ] 👉( ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد ) " ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ ታላቅና አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም። በነርሱም ውስጥ ተክቢር (አላሁ አክበር ማለት)፣ ተህሊልና (ላ ኢላሀ ኢለሏህ ማለት) ተሕሚድን (አልሐምዱ ሊላህ ማለትን) አብዙ።]" [አሕመድ: 7/224] ኢማሙ ጦበራኒይም አል ሙዕጀሙል ከቢር ላይ ዘግበውታል። አላህ ከመልካም ሰሪዎች ያድርገን። ወንድማችሁ፦ "Muraad Ibnu Taadde" _ ነሀሴ 3, 2010 ዓ.ል _________ @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
👉👉ክፍል አንድ👈👈 ፃምን በተመስከተ ሴቶችን የሚመለቱ ሕጎች ↪የረመዷንን ወር መፆም በወንድም ሆነ በሴት ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፤ ፆም አንዱ የእስልምና ማዕዘን ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡ ↴ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) እንደተጻፈ፤ በናንተም ላይ ተጻፈ፤» አል-በቀራህ፡ 183 ⇨አንዲት ወጣት ለአቅመ ሔዋን የመድረስ ምልክቶች ከታዩባት ለምሳሌ: የወር አበባ ማየት ከጀመረች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፆም ግዴታ ይሆንባታል፡፡ እደሜዋ ገና ዘጠኝ ዓመት እያለ የወር አበባ ሊመጣባት ይችላል አንዳንድ ልጆች ሁኔታውን ባለማወቅ ራሷን ህጻን አድርጋ በመቁጠር ላትፆም ትችላለች። ቤተሰቦቿም ላያዟት ይቻላሉ ይህ ከእስልምና ማዕዘናት አንዱን መተው ስለሆነ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ያጋጠማት ረጅም ጊዜ ቢያልፍም እንኳ የወር አበባ ካየች ጊዜ ጀምሮ ያለውን ፆም ቀዷ ማውጣት ትገደዳለች፤ ምክንያቱም ፆሙ በርሷ ላይ እዳ ሆኖ ይቆያልና ነው፡፡ ↪ ረመዷንን ወፃም ግዴታ የሚሆንበት ማን ነው❓ የረመዷን ወር ከገባ በማንኛውም ለአቅመ አዳም/ሔዋን የደረሰኛች ፤ ጤነኛ የሆነ/ች እና ሀገራቸው ውስጥ ነዋሪ የሆነ/ች ወንድና ሴት ሙስሊሞች ሁሉ ወሩን የመፆም ግዴታ አለባቸው፡፡ በወሩ ውስጥ ታማሚ ወይም መንገደኛ የሆነ/ች አፍጥረው በሌላ ጊዜ ያፈጠሩትን ቀን ያህል ቀዷ ያወጣሉ (ይከፍላሉ፡፡) በእድሜ መግፋት ምክንያት ወይም የመዳን ተስፋ በሌለው በሽታ በመጠቃታቸው መፆም የማይችሉ ወንዶች ወይም ሴቶች ካሉ በረመዷን ወር እያፈጠሩ በየ ቀኑ በሀገሩ ላይ ከተለመደው የምግብ አይነት አንድ ቁና ያህል ለሚስኪን ይሰጣሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡ አል-በቀራ 185 فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ .... ..ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፤ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ስው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፣ » ዐብድላህ ቢን ዐባስ (ረድየላሁዐንሁ) አንቀጹን ሲያብራሩ፡ «ይህ ሕግ መፆም ለማይችል አዛውንት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ይድናል ተብሎ ተስፋ የማይደረግ በሽተኛም ብይኑ ከደካማ ሽማግሌ/አሮጊት ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ሁለቱም መፆም የማይችሉ ስለሆኑ ቀዷ ማውጣት የለባቸውም፡፡ ይልቁንም ለያንዳንዱ ቀን ግማሽ ቁና ያህል አንድ ድሃ ይመግባሉ፡፡ ይህን በተመለከተ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡ وَعَلَى ٱلَّذِينَ يُطِيقُونَهُۥ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ «በአነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው፣..., አል በቀራህ፡ 184 ሴት በረመዷን ወር አፍጥራ ሌላ ጊዜ ቀዷ እንድታወጣ የሚያደርጓት ከወንድ የተለዩ ምክንያቶች አሏት፡፡ እነዚህም ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ↪ የወር አበባና የውልደት ደም፡- በወር አበባና በውልደት ደም ጊዜ መፆም ክልክል ነው ፤ በዚህ ጊዜ ያፈጠረችውን በሌላ ጊዜ ትፆመዋለች፤ በቡኻሪና ሙስሊም የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ የሚከተለው ከናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁዐንሀ) ተዘግቧል፡ ‹‹ፆምን ቀዷ አንድናወጣ አንታዘዝ ነበር፤ ሶላትን ግን ቀዷ አንድናወጣ አንታዘዝም ነበር፡፡›› እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁዐንሀ) ይህን የተናገሩት አንዲት ሴት ስለሁኔታው በጠየቀቻቸው ጊዜ ነበር ይህ ጉዳይ ማለትም ፆምን ቀዷ ማውጣትና ሶላትን ቀዷ አለማውጣት ምክንያቱን ከማፈላለግ ባሻገር ሸሪዓው የደነገገውና መመሪያውን ተከትለን መሄድ ብቻ የሚኖርብን ጉዳይ መሆኑን አብራሩላት፡፡ ፃምን ቀዷ ማውጣትና ሶላትን ቀዷ አለማውጣት ያለው ሒክማ (ጥበብ) ምንድን ነው❓ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (አላህ ይዘንላቸው) በ (መጅሙዐል ፈታዋ 25/ 251) ላይ እንዲህ ብለዋል፡- “ሴት የወር አበባ በምታይ ጊዜ የአካላችን መቆሚያ መሠረት የሆነው ደም ስለሚፈስ ኃይሏ ይቀንሳል፤ ትዳከማለች፤ ፆሟም የተስተካከለ አይሆንም፤ ስለሆነም በዚህ ጊዜ በልታ ደም በማይፈሳትና ሰውነቷ የተስተካከለ በሚሆን ጊዜ እንድትፆም ታዛለች፡፡›› ይቀጥላል...... ↘️ አርግዝና እና ማጥባትን በተመስከተ በሴት ወይም በልጇ አልያም በሁለቱም ላይ ጉዳት የሚያስከትሉት በእርግዝናዋና ማጥባትን በተመለከተ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
"ሌባው" የመስጅድ ኢማም ================= ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኝ መስጂድ ኢማም የሆኑትን ሸይኽ ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች። «ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት። ያም ቢሆን ባለቤቷ ኢማሙን ተከትሎ ሶላት ላለመስገድ ወሰነ። ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። ስለዚህ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን ሹክ አላት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው ገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። እርሱም ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ። የመስጅዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ « ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ አለመቅራታችሁ ገርሞኝ ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት። እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን ቃል ከፍተን ያነበብነው? 😢 ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው❗ ወገኖቼ የአላህ ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል። #ውዶቼ ካነበብኩት ላካፍላቹ ብዬ ነው! እንደምትማሩበት ተስፋ አረጋለው! @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
«ጾም» ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ==================== ክፍል አንድ [1]፡ «ቋንቋዊና ሸሪዓዊ» ትርጉም‼️ ================== በ"Murad Tadesse" ******* ✍️ 1) ቋንቋዊ ፍች (ትርጉም)፦ ~~~~~~~ በቋንቋ ደረጃ ጾም (الصَّوْمُ ) ማለት መቆጠብ (الإمساك ) እንደ ማለት ነው። [ምንጭ፥ "ቃሙስ" ሙዕጀሙል መዓኒ] * ይህ መቆጠብ ወይም መከልከል ከመራመድ ወይም ከመንቀሳቀስ ወይም ከመናገር ወይም ከመብላት ወይም ከመጠጣት ወይም ከሌሎችም ነገሮች ሊሆን ይችላል። * አቡ ዑበይዳህ እንዲህ ይላሉ፥ "كل ممسك عن طعام أو كلام أو سير فهو صائم" «ማንኛውም ከምግብ ወይም ከንግግር ወይም ከእንቅስቃሴ ተቆጣቢ (ተሰታሪ)፤ እርሱ ጿሚ ነው።» [ምንጭ፥ "ሙኽታሩ ስ-ሲሓሕ ሊራዚ"፡ ቅጽ 1፣ ገጽ 180 እና 181] * በቃሙስ ላይም፦ "صام صوما وصياما واصطام: أمسك عن الطعام والشراب والكلام والنكاح والسير" «"ሷመ": የሚለው ቃል ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከንግግር፣ ከኒካሕና ከእንቅስቃሴ ተቆጠበ ማለት ነው።» [ምንጭ፥ "አል-ቃሙስ አል-ሙሒጥ" ባቡል ሚም፥ ፈስሉ ስ-ሷድ፡ ቅጽ 1፣ ገጽ 1042]] * ተመሳሳይ ይዘት ያለው ገለጻም በ["ሙዕጀሙል መቃይሲ ል-ሉጛህ"፣ 'ኪታቡ ስ-ሷድ፥ ባቡ ስ-ሷድ ወል-ዋው ወማየተለቲህማ'፡ ቅጽ 3፣ ገጽ 324] ላይ አለ። * ልቅና የተገባውና ኃያሉ አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በቁርኣን ላይ እንዲህ ይላል፥ ﴿فَكُلِي وَٱشۡرَبِي وَقَرِّي عَيۡنٗاۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ ٱلۡبَشَرِ أَحَدٗا فَقُولِيٓ إِنِّي نَذَرۡتُ لِلرَّحۡمَٰنِ صَوۡمٗا فَلَنۡ أُكَلِّمَ ٱلۡيَوۡمَ إِنسِيّٗا.) «ብይም፣ ጠጭም፤ ተደሰችም፤ ከሰዎችም አንድን ብታይ ፦ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰዉን በፍጹም አላነጋግርም በይ።» [ምንጭ፥ "ሱረቱል መሪያም"፡ አንቀጽ ቁጥር 26] በዚህ አንቀጽ ላይ "ሶውም" (صَوۡمٗا ) የሚለው ቃል ከንግግር መቆጠብን (ዝምታን) ለመግለጽ መጥቷል። * ታላቁ የቁርኣን መፈሲር ዓብዱልሏህ ኢብኑ ዓባስ (صَوۡمٗا ) የሚለውን ቃል "صمتا" ዝምታ: أي: إمساكا عن الكلام [ማለትም፥ "ከመናገር መቆጠብ!"] ብለው ተርጉመውታል። [ምንጭ፥ "ተፍሲሩ ጥ-ጦበሪይ"፥ ሱረቱል መሪየም፣ አንቀጽ ቁጥር 26 ፣ ቅጽ 18፣ ገጽ 182 እና 183] * ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና እንዲህ ይላሉ፦ «الصوم هو الصبر، يصبر الإنسان على الطعام والشراب والنكاح، ثم قرأ: ﴿إنما يوفى الصابرون أجرهم بغير حساب﴾» « ጾም ማለት ትዕግስት ማለት ነው። 'ሰው በምግብ፣ በመጠጥና በኒካሕ ላይ ይታገሳል!' አሉና እንዲህ የሚለውን የአላህ ቃል አነበቡ፥ "ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሠጡት ያለ ግምት ነው!" (ሱረቱ ዝ-ዙመር፥ አንቀጽ ቁጥር 10)» [ምንጭ፥ "ሊሳኑል ዓረብ"፡ ገጽ 309] * ✍️ 2) ሸሪዓዊ ፍች (ትርጉም)፦ ~~~~~~ በሸሪዓዊና በቴክኒካዊ ፍች ደረጃ ጾም ማለት፥ "التعبّد لله تعالى، بالإمساك عن الطعام والشراب وجميع المفطرات، من طلوع الفجر إلى غروب الشمس" «ከንጋት መውጣት ጀምሮ እስከ ጸሃይ መጥለቅ ድረስ፤ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከማንኛውም ጾምን አፍራሽ ነገር በመከልከል፣ ከፍና ላቅ ያለውን አላህን ማምለክ ማለት ነው።» * ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ይላሉ፦ «والصوم والصيام في اللغة: الإمساك، وفي الشرع: إمساك مخصوص في زمن مخصوص عن شيء مخصوص بشرائط مخصوصة» «"ሶውምና ሲያም" በቋንቋ ደረጃ መቆጠብ ማለት ነው። በሸሪዓ ደረጃ ደግሞ "ልዩ የሆነ መቆጠብ፣ ልዩ በሆነ ጊዜ፣ ልዩ ከሆነ ነገር፣ ልዩ በሆኑ መስፈርቶች" ማለት ነው።» [ምንጭ፥ "ፈትሑል ባሪ"፡ ሸርሑ ሶሒሑል ቡኻሪ፣ ኪታቡ ሶውም፣ ገጽ 123 - 124] * ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፦ «وفي الشريعة: عبارة عن إمساك مخصوص، وهو الكف عن قضاء الشهوتين شهوة البطن وشهوة الفرج، من شخص مخصوص، وهو أن يكون مسلما طاهرا من الحيض والنفاس وفي وقت مخصوص، وهو ما بعد طلوع الفجر إلى وقت غروب الشمس بصفة مخصوصة، وهو أن يكون على قصد التقرب، فالاسم شرعي فيه معنى اللغة» «በሸሪዓ ደረጃ ጾም ማለት፦ ልዩ ከሆነ ነገር መቆጠብ፥ እርሱም ከሁለት ስሜቶች <ከሆድ ስሜትና ከብልት ስሜት> ጉዳይን ከመፈጸም መብቃቃት ማለት ነው። ልዩ ከሆነ ሰው፥ እርሱም ሙስሊም መሆን፣ ከወር አበባና ከወሊድ ጊዜ ደም የጠራች የሆነች መሆን። ልዩ በሆነ ጊዜ፥ እርሱም ፈጅር ከወጣ በኋላ ጸሃይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ መሆን። ልዩ በሆነ መገለጫ፥ እርሱም ወደ አላህ መቃረብን ታስቦበት መሆን። በሸሪዓዊ ስያሜው ውስጥ ቋንቋዊ ትርጉሙም አለ።» [ምንጭ፥ "አል-መብሱጥ"፡ ቅጽ 3፣ ገጽ 55] * ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላሉ፦ «والصوم في الشرع: عبارة عن الإمساك عن أشياء مخصوصة، في وقت مخصوص» «ጾም በቋንቋ ደረጃ፦ ልዩ በሆነ ጊዜ ውስጥ ልዩ ከሆኑ ነገራቶች መቆጠብ ማለት ነው።» [ምንጭ፥ "አል-ሙጝኒ"፡ ገጽ 3 እና 4] * በአጠቃላይ ጾም ማለት ከመብላትና ከመጠጣት ብቻ መቆጠብ ማለት አይደለም። ሸሪዓዊና ቋንቋዊ ፍቹ ከምግብና ከመጠጥ ያለፈ ትርጉም እንዳለው ያመላክታል። @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
ስለ ቻይና ሙስሊሞች 10 ነገሮች 🔷 ኢስልምናን ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና የደረሰው በዑመር (ረዐ) ኸሊፋነት ዘመን በታላቁ ሰሃባ ‹‹ሰዓድ ኢብን አቢ-ወቃስ›› (ረዐ) እንደሆነ ይነገራል። 🔷 በቻይና የመጀመሪያውን መስጂድ ያሰራውም ሰዓድ ሲሆን ‹‹ሑዓሼንግ›› የሚባልና አሁንም በይዞታ የሚገኝ የ1300 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ መስጂድ ነው። 🔷 በአገሪቱ 80 ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ከህዝቡን 2% ገደማ ይሸፍናሉ። 🔷 ሙስሊሞቹ በብዛት የሚኖሩበት ቦታ ‹‹ዢንጂያንግ›› ሲባል ከአፍጋስታን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ጋር የሚዋሰን ሰፊ ግዛት ነው። 🔷 ‹‹ዢንጂያንግ›› ቀድሞ የዑስማያ ኸሊፌት የተርኪስታን ግዛት የነበረ ሲሆን ኸሊፋው ከወደቀ በኋላ በ1949 ቻይና በሐይል ልትወስደው ችላለች። ግዛቱም ከቻይና ሰፊው ሲሆን በማዕድን የበለፀገ ነው። 🔷 ቻይና ውስጥ ሁለት አይነት ነገድ ያላቸው ሙስሊሞች ያሉ ሲሆን ‹‹ሐም›› እና ‹‹ኡግሁር›› ይባላሉ። ሐሞች ቻይናዊ ሲሆኑ ኡግሁር ደግሞ በመልካቸውም የተለዩ የመካከለኛው ኤዥያ ዝርያዎች እንደሆኑ ይታመናል። 🔷 በቻይና ሁሉም ሙስሊሞች መድሎ ቢደርስባቸው ከፍተኛ በደል የሚፈፀምባቸው ግን የኡግሁር ሙስሊሞች ናቸው። 🔷 የኡግሁር ሙስሊሞች ከሌላው በተለየ በደል የሚደርስባቸው አንደኛው በዘራቸው ቻይናዊ ስላልሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አካባቢው በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ መንግስቱ ህዝቡን የማጥፋት ዕቅድ እንዳለው ይነገራል። 🔷 ቻይና በኡግሁር ሙስሊሞች ላይ ከምትፈፅመው ግፍ መካከል ወላጅና ልጅን መነጣጠል፣ በማጎሪያ ካምፖች ማሰር፣ አካላቸውን መበለት፣ ሰላት፣ ፆምና ቁርኣን መከልከል፣ አልኮል ማስጠጣት፣ የአሳማና ውሻ ስጋ ማስበላት፣ መግደል እና ሌሎችንም ይፈፅማሉ። 🔷 የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ አሰቃቂ ግፍ እየፈፀመ ድርጊቱ ‹‹ሽብርተኝነት›› አልተባለም። 👉 በዑመር (ረዐ) ዘመን የቻይና መንግስት ለፋርስ ንጉስ መጠጊያ እንኳን ለመስጠት ኸሊፋውን በመፍራት እንቢ ማለቱ ይነገራል። ዛሬ የሙስሊም አገራት የኡግሁር ሙስሊሞች አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው እያዩ ከቻይና ጋር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንኳን ማቆም አልቻሉም። ‹‹አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ።›› (ማዒዳህ 82) @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
«ሰላት ላይ ከረሳን» በሰላት ውስጥ ብዙ አይነት መርሳት የሚከሰት ሲሆን ከእነሱ መካከል 5ቱን ለመጥቀስ ያህል፦ ረከዓ ካሳነስን ወይም ከተጠራጠርን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፦ «አንድ ሰው ምን ያህል ረከዓ እንደሰገደ ካላወቀ ወይም ከተጠራጠረ ዝቅተኛውን ቁጥር ይያዝና ቀሪውን አሟልቶ ይስገድ። ከዚያም ሁለቷን የመርሳት ሱጁድ ይጨምር።» (ሙስሊም፥ 571) ብዙዎች የሰገዱትን ረከዓ ቁጥሩ ሲጠራጠሩ ሁለቷን ሱጁድ ብቻ ሰግደው ይተውታል። ይሄ ትክክል አይደለም። ቁጥሩ ካጠራጠረን ዝቅተኛውን ይዘን ቀሪውን ጨምረን መስገድ አለብን። ከዚያም ሁለቷን ሱጁድ እንጨምራለን። ሁለቷ ሱጁድ (ሱጁድ አስሰህው) ለስህተቱ ማካካሻ እንጅ ለረከዓው መሙያ አይደለችም። ምሳሌ ዙሁር የሰገድነው 3 ወይም 4 መሆኑን ከተጠራጠርን ዝቅተኛውን 3 እንይዝና 1 ረከዓ ጨምረን እንሰግዳለን። ከዚያም ለተሳሳትንበት ሁለቷን ሱጁድ እንጨምራለን። ረከዓ ካበዛን የሰገድነው ረከዓ ከታዘዝነው ካለፈ ሁለቷን ሱጁድ እንጨምራለን። ምሳሌ ዙሁር ተሳስተን 5 ረከዓ ብንሰግድ ሁለቷን ሱጁድ ጨምረን እናካክሳለን። (ቡኻሪ፥ 404) ተሽሁድ ከረሳን ሁለት ተሽሁድ ባለባቸው ሰላቶች አንዱን ከረሳን በመጨረሻው ተሽሁድ በኋላ ሁለቷን ሱጁድ እንጨምራለን። ምሳሌ ዙሁር የመጀመሪያውን ተሽሁድ ሳንቀመጥ ረስተነው ብንነሳ ሶስተኛውና አራተኛውን ረከዓ በዚያው አንሰግድና ሁለቷን የማካካሻ ሱጁድ እንጨምራለን። (ቡኻሪ፥ 1230) ካሰላመትን በኋላ የረሳነው ትዝ ካለን አንድ ሰው ሰላት ሰግዶ ካሰላመተ በኋላ የረሳው ረከዓ እንዳለ ትዝ ካለው ምን ያድርግ ለሚለው የተለያየ አስተያየት አለ። እዚያው በሰገደበት ቦታ ተቀምጦ ከሆነ ይነሳና የቀረውን ረከዓ ሰግዶ ከዚያም ሁለቷን ሱጁድ ጨምሮ ይሙላ የሚለው የሁሉም ስምምነት ነው። ከሰገደበት ቦታ ተነስቶ ከሄደ ደግሞ ከመስጂድ ከወጣ ከፊሎቹ ማካካሻ አያስፈልገውም ይላሉ። እነ ኢብኑ ተይሚያህ ደግሞ ትዝ ባለው ቦታ ሁለቷን ማካካሻ መስገድ አለበት ይላሉ። የመጀመሪያዋን ተክቢራ ከረሳን የመጀመሪያዋን ተክብራ ያላለ ከሰላቱ ቀድሞም ስላልገባ በሶላት ውስጥ ትዝ ካለው አቋርጦ እንደገና ይሀርማል። ሰግዶ ከጨረሰ በኋላ ትዝ ካለው ደግሞ እንደገና ይሰግዳል። ሱጁድ አስሰህው የሚሰገደው መቼ ነው? ሁለት አይነት ሀሳብ ያለ ሲሆን በጥቅሉ ነቢዩ (ዐሰወ) ከማሰላመታቸው በፊትም ካሰላመቱ በኋላም ሁለቷን ሱጁድ ስለሰገዱ እነሱ እንደሰገዱበት ሁኔታ መስገድ አለብን የሚል ነው። (እርምትና የሚጨመር ካለ አክሉበት) @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
ንቁ ልቦች **** ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ኢብን ሲይረይን በአንድ ወቅት ዕዳ ውስጥ ገቡ፡፡ በነፍሳቸው ላይ የምርጥ ሰዎች ምርመራ አደረጉ፤ ያ ምርመራ ከነጋዴዎች የገንዘብ ሂሳብ የረቀቀ ነበር፡፡ ይህ ዕዳ በሕይወታቸው ለምን እንደደረሰ ራሳቸውን መርምረው የደረሱበት ውጤት የሚከተለው ነበር፡- “በአላህ እምላለሁ! ይህ ዕዳ በእኔ ህይወት ሊከሰት የቻለው ከአርባ ዓመታት በፊት በፈጸምኩት ወንጀል ሳቢያ ነው፡፡ አንድን ሰው፡- 'አንተ ድሃ!' ስል ተናግሬዋለሁ።" ከዛም ሙሐመድ ኢብኑ ሲይሪይን ስለራሳቸው ያሉትን የሰማ ሰው ለአባ ሱለይማን አድ-ዳራኒ ነገራቸው፡፡ እርሳቸውም፡- “የእነርሱ ወንጀል በጣም ትንሽ በመሆኑ በየትኛው ወንጀላቸው ምክኒያት እንደሚቅቀጡ አወቁ፤ የእኔና የአንተ ወንጀል ደግሞ በጣም ከመብዛቱ የተነሳ በየትኛው ወንጀላችን ምክንያት እየተቀጣን እንደሆነ ማዎቅ ተሳነን፡፡” ሲሉ የሙሐመድ ኢብን ሲሪንን ታላቅነት መሰከሩ፡፡ ኢብኑ ሲይሪን የንቁ ልብ ባለቤት ነበሩ። ታላላቅ ሰዎች በሕይወታቸው ሙሉ የፈፀሙዋቸው ወንጀሎች በጣት የሚቆጠሩ ይሆኑና አይረሷቸውም፡፡ ሰርክ ያስታውሷቸዋል፤ ለነፍሳቸው መገሠጫነት በመጠቀም የከፍታ ማማን መዝለቂያ አድርገው ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በአንፃሩ ወንጀላችን በእጅጉ በመብዛቱ ምክንያት የትኛው ወንጀል የትኛውን መመሰቃቀል እንዳስከሰተ መለየት ተስኖናል፡፡ ታላላቆቹ በሕይዋታቸው አንዳንዴ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎቻቸውን ዘወትር ሲያስታውሱና ሁሌም የሚሰሯቸውን መልካም ስራዎችን ከምንም ሳይቆጥሩ ይስተዋላሉ በአንፃሩ እኔና አንተ ደግሞ በሕይወታችን አንዳንዴ የምንፈፅማቸውን መልካም ስራዎች ዘወትር በማስታወስና ሁሌም የምንሠራቸውን ወንጀሎች ከምንም ባለመቁጠር አደጋ ውስጥ ነን፡፡ መንቃት ይጠበቅብናል፡፡ ------------------------------ ----------------------- አሁን ላለንበት ምስቅልቅል የሁላችንም የግልና የጋራ ወንጀል አስተዋፅኦ አድርጔል። ሁላችንም ተጠያቂዎች ስንሆን መፍትሄውም እኛው ውስጥ ነው ያለው። ቆም ብሎ ማሰብና ወደ ልቦና መመለስ። @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
ከታሪክ አምባ —————— ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:— "በሐጅ ወቅት መካ ውስጥ ነበርኩ። አንድ ከኹራሳን የሆነ ሰው ‘እናንተ ሑጃጆች ሆይ! እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ! ነዋሪዎች! መጤዎች! አንድ ሺህ ዲናር የያዘ ከረጢት ጠፍቶብኛል። የመለሰልኝ ሰው አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ከእሳትም ነፃ ያድርገው። በምርመራው ቀንም ምንዳና ሽልማት ይኖረዋል’ ሲል ሰማሁት። በዚህን ጊዜ ከመካ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ትልቅ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳናዊ ሆይ! ሃገራችን ሁኔታዋ የከፋ ነው። የሐጅ ቀናት ጥቂት ናቸው። ክብረ በአላቱም ውስን ናቸው። የስራ በሮች ተዘግተዋል። ምናልባትም ይሄ ገንዘብ ከድሃ አማኝ፣ ከትልቅ አዛውንት እጅ ወድቆ ወሮታውን እንድትሰጠው ቃል እንድትገባለት ሊከጅል ይችላልና ገንዘቡን ቢመልስ ትንሽ ሐላል ገንዘብ ትቸረዋለህ ወይ?’ አለ። ኹራሳኒው:— ስንት ነው ወሮታው? ስንት ይፈልጋል? አዛውንቱ:— አንድ አስረኛ ይፈልጋል። መቶ ዲናር። የአንድ ሺው 10%። ኹራሳኒው:— አልተስማማም። ‘አላደርገውም። ይልቅ የዚህን ሰውዬ ጉዳይ ወደ አላህ አስጠጋለሁ። በምናገኘውም (የቂያማ) ቀን ወደሱው እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን፣ ያማረ የሆነ መመኪያ’ አለ።" ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ድሃ ሰው የተባለው ይሄ ሽማግሌ መሰለኝ። ምናልባትም የዲናሮቹን ከረጢት አግኝቶት ከሱ ትንሽ ፈልጎ ነው። ተከተልኩት። ወደቤቱ ተመለሰ። እንደጠረጠርኩት ነበር። ‘ሉባባ ሆይ!’ ብሎ ሚስቱን ሲጣራ ሰማሁት። ‘አቤት የጊያሥ አባት!’ አለች። ‘የገንዘቡን ባለቤት እያፈላለገ ሲጣራ አገኘሁትኮ። ላገኘለት ሰው ምንም ሊሰጥ አይፈልግም። ከሱ ላይ መቶ ዲናር ስጠን ብየው ነበር። እምቢ ብሎ ጉዳዩን ወደ አላህ አስጠጋ። ምን ባደርግ ይሻላል ሉባባ? የግድ መመለስ አለብኝ። እኔ ጌታዬን እፈራለሁ። ወንጀሌ እንዳይደራረብ እሰጋለሁ’ አለ። በዚህን ጊዜ ሚስቱ እንዲህ አለች:— ‘ሰውየ! እኛኮ ካንተ ጋር ከአምሳ አመት ጀምሮ በድህነት እየማቀቅን ነው። አራት ሴት ልጆች፣ ሁለት እህቶች፣ እኔ፣ እናቴ አለን። አንተ ዘጠነኛችን ነህ። ፍየል የለን፣ የግጦሽ ቦታ የለን። ገንዘቡን ሁሉንም ውሰድ። ተርበናል አጥግበን። ያለንበትን ታውቃለህ አልብሰን። ምናልባትም አላህ — ዐዘ ወጀለ— ከዚያ በኋላ ያብቃቃህ ይሆናል። ያኔ ቤተሰብህን ካበላህ በኋላ ገንዘቡን ትሰጠዋለህ። ወይ ደግሞ በትንሳኤ ቀን እዳህን አላህ ይከፍልልሃል’ አለች። ሰውየው:— ሉባባ ሆይ! እድሜዬ 86 አመት ከደረሰ በኋላ ሐራም ልበላ ነው? ድህነቴን ይህን ያክል ከታገስኩ በኋላ አካሌን በእሳት ላቃጥል? ለቀብሬ ከቀረብኩ በኋላ የኃያሉን ቁጣ በራሴ ላይ ላስወስን? በፍፁም አላደርገውም ወላ፞ህ!’ አለ።" ኢብኑ ጀሪር እዚህ ላይ እንዲህ ይላሉ:— "የዚህ ሰውዬና የሚስቱ ነገር እያስደነቀኝ ተመለስኩኝ። በነጋታው ያ የዲናሮቹ ባለቤት ልክ እንደ ትላንቱ ሲጣራ ሰማሁት። ያ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳናዊ! ትላንት ያልኩትን ብዬህ መክሬህ ነበር። ሃገራችን ወላ፞ሂ አዝመራውና እላቢው የቀለለ ነው። ገንዘቡን ያገኘው ሰው ሸሪዐን እንዳይፃረር ትንሽ ገንዘብ ብትሰጠው፤ ላገኘው ሰው መቶ ዲናሮችን ስጠው ብልህ እምቢ ብለሃል። ገንዘብህ አላህን — ዐዘ ወጀለ— ከሚፈራ ሰው እጅ ላይ ቢወድቅ በመቶው ፋንታ አስር ዲናሮችን ብቻ ብትሰጠው ምናለበት? እነሱንም ይሰትራቸዋል፣ ይሸፍናቸዋል፣ ቀለብም ይሆናቸዋል’ አለ። ኹራሳናዊው:— ‘አላደርገውም። ገንዘቤን ከጌታዬ ዘንድ እተሳሰበዋለሁ። በትንሳኤ ቀንም ወደሱ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው’ አለ።" "በቀጣዩም ቀን የዲናሮቹ ባለቤት እንደቀደሙት ቀናት ጥሪውን አስተጋባ። አሁንም ያ ሽማግሌ ተነሳና እንዲህ አለ:— ‘አንተ ኹራሳናዊ! የመጀመሪያ ቀን ላይ ገንዘቡን ላገኘው ሰው መቶ ዲናር ስጠው ብዬህ እምቢ ብለሃል። ከዚያ አስር አልኩህ እምቢ አልክ። እሺ አንድ ዲናር ብትሰጠውና በግማሿ የሚፈልጋትን ነገር ቢሸምት፣ በግማሿ ደግሞ የሚያልባት ፍየል ቢገዛና ሰዎችን እያጠጣ ገቢ ቢያገኝ፣ ልጆቹን እያጠጣም ምንዳውን ቢያስብ ምናለበት?’ ኹራሳናዊው:— ‘አላደርገውም። ለአላህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በቂያማ ቀንም ከጌታዬ ዘንድ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው።’ ሽማግሌው:— ሰውየውን ልብሱን ጎተተውና ‘ና ተከተለኝ። ዲናሮችህን ውሰድና ሌሊቱን እንድተኛ ተወኝ። ይህንን ገንዘብ ካገኘሁበት እለት ጀምሮ ሰላም አላገኘሁም’ አለ። ኢብኑ ጀሪር ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ባለ ዲናሩ ሰውየ ከሽማግሌው ጋር ሄደ። ተከተልኳቸው። ሽማግሌው ከቤቱ ገባ። መሬት ቆፍሮ ዲናሮቹን አወጣና ‘ገንዘብህን ውሰድ። አላህን ይቅር እንዲለኝና ከትሩፋቱ እንዲለግሰኝ እለምነዋለሁ’ አለ።” ኹራሳናዊው:— ተቀበለና መውጣት አሰበ። በሩ ጋር ሲደርስ እንዲህ አለ:— ‘አንተ አዛውንት ሆይ! እኔ አባቴ ሶስት ሺህ ዲናር ትቶ ሞቷል፣ አላህ ይዘንለትና። እና ‘ሲሶውን አንተ ይበልጥ ይገባዋል ለምትለው ስጥ’ ብሎኝ ነበር። በዚህ ከረጢት ውስጥ ያስቀመጥኩት ለሚገባው ለመስጠት ነው። በአላህ ይሁንብኝ! ከኹራሳን ከወጣሁ ጀምሮ እዚህ እስከምደርስ ድረስ ካንተ የበለጠ የሚገባው ሰው አላየሁም። ስለዚህ ውሰደው አላህ ይባርክልህና። አማናህን ስለተወጣህ፣ በድህነትህ ላይ ስለታገስክ አላህ በመልካም ይመንዳህ’ አለና ገንዘቡን ትቶ ሄደ። ሽማግሌው ተነስቶ አላህን እየተማፀነ ማልቀስ ያዘ። እንዲህም አለ:— ‘የዚህን ገንዘብ ባለቤት (ሟቹን) በቀብሩ ውስጥ አላህ ይዘንለት። በልጁም ይባርክለት።’ ምንጭ:— ጀምሀረቱል አጅዛኢል ሐዲሢያ፞ህ: 251] ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:— {ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا (٢) وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا} [الطلاق: ٢، ٣]. "ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰፅበታል። አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።" [አጦ፞ላቅ: 2–3] @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
➪የቁጣ መድሐኒት 𒊹︎︎︎በመሰረቱ ቁጣ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪይ ሲሆን ሲበዛና ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚፈጠር ከሆነ ግን እጅጉኑ ይወገዛል ☞︎︎︎በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ደግሞ ይመሰገናል አርአያችንና ውዱ ነቢያችንም (صلى الله عليه وسلم) 𒊹︎︎︎ይቆጡ እንደ ነበረ ታሪካቸው ላይ ተዘግቧል።ነገር ግን ቁጣቸው #የአላህ ድንበር ሲጣስና ዲኑ ሲነካ ብቻ ነበር ለስብእናቸው ለነፍሳቸው ብለው አንድም ቀን ተቆጥተው አያውቁም 𒊹︎︎︎በሁሉም ነገር ☞እርሳቸውን የተከተለ ምንኛ የታደለ ሰው ነው?! ➪"የቁጠኝነትን ባህሪይ ለመከላከልና በሆነ ባልሆነው #የመቆጣትን ችግር ለመቅረፍ የሚከተሉትን ምክሮች ይተግብሩ፦ 1❀ቁጣቸውን ዋጥ ለሚያደርጉና ይቅር ለሚሉ ሰዎች አላህ #አኼራ ላይ ያዘጋጀውን ከፍተኛ ምንዳና ደረጃ ማስታወስ 2 ❁ አዑዙ ቢላህ ሚነሽሸይጧኒር`ረጂም ማለትና #ዚክር ማለት 3𑁍 ከንግግርና መልስ #ከመስጠት መታቀብ (ዝም ማለት) 4✰ ቁጣው የተፈጠረው #ቆመው ከሆነ መቀመጥ፣ ቁጭ ብለው ከሆነም #ጋደም ማለትና ሁኔታን መቀየር፣ 5✫ ውዱእ ማድረግና ከተቻለም ሁለት ረካኣ ሰላት መስገድ ሙሉ ውዱእ ማድረግ እንኳ ባይቻል የተወሰነ #ሰውነት ላይ ውኃ በማፍሰስ ሰውነትን ማቀዝቀዝ፣ 6✩ቁጣና ንዴት የሚያስከትለውን የጤና ችግር እንዲሁም በቁጣ ጊዜ እራሳችን ላይ የሚታየውን #መጥፎና አሳፋሪ የፊት ገፅታ እና የማይገቡ እንቅስቃሴዎችን ልብ ማለትና ይህን ከሰዎች እንደምንጠላው ሁሉ ለራሳችንም መጥላት፣ 7𖣔 ቁጣን መተው ነቢዩን (صلى الله عليه وسلم) መታዘዝ እንደሆነ ማወቅ፥ ምክንያቱም #ነቢዩ ("አትቆጣ!") ብለዋልና ይህም ሊሳካ የሚችለው ለቁጣ የሚዳርጉ ነገሮችን በመራቅና የተቆጡም እንደሆነ ራስን #በመቆጣጠር ብቻ ነው ✪በሆነ ባልሆነው የሚቆጣ ሰው ቤተ-ሰቦቹንና በተለያዩ ምክንያቶች የሚገናኙትን ሰዎች አዛ ስለሚያደርጋቸው እንደሚጠሉት ማወቅና #ከቁጣ በሽታ እንዲገላግለን አላህን ዘወትር መለመን አበቃ! 𒊹︎︎︎አላህ መልካም ባህሪያትን በሙሉ ያግራልን!እርሱ ከሚጠላቸው ባህሪያትና ድርጊቶችም ይጠብቀን @al_ihsan_dawa_channel
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.