cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

መረጃ ማዕድ®️

ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! !

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
459
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
TEDDY AFRO - ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) - [New! Official Single 2022] - With Lyrics

Enjoy! Subscribe! Connect with us for more.

https://www.facebook.com/TeddyAfroMusic/

https://www.instagram.com/teddyafromuzika/

https://store.cdbaby.com/Artist/TeddyAfro1

https://itunes.apple.com/us/artist/teddy-afro/id457707367

https://www.vevo.com/artist/teddy-afro

http://www.dailymotion.com/teddyafro

https://twitter.com/teddyafromusic

www.teddyafromuzika.com © All rights reserved to Teddy Afro

TEDDY AFRO - ናዕት (እያመመው ቁጥር ፪) - [New! Official Single 2022] - With Lyrics
Показати все...
TEDDY_AFRO_ናዕት_እያመመው_ቁጥር_፪_New_Official_Single_2022_Wit_1hMVeENjVew.m4a5.94 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ጤናመረጃ ጥቁር አዝሙድ ለጤናችን የሚሰጠን አስደናቂ ጥቅሞች በጥቁር አዝሙድ ውስጥ ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑ ከ100 በላይ የተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች አሉ። እንደ ካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ብረት፣ ዚንክ፣ ማግኒዥየም፣ ሲኒየም፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ቢ፣ ቫይታሚን ቢ2 ና ሲ የመሳሰሉት ፕሮቲኖች መገኛ ነው። 👉የአለርጂ በሽተኞች አሉታዊ ምልክቶችን ለመቀነስ የሚረዳ እንደ ፀረ-ሂስታሚን በውስጡ ይዟል።መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ለማፅዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። 👉ለስኳር በሽታ የኢንሱሊን መጠንን ለመቆጣጠር፣ ኮሌስትሮልን፣ የሰውነት ዝውውርን ያሻሽላል እንዲሁም ጤናማ የጉበት ሥራን ያበረታታሉ። 👉ደረቅ ሳልን ለማስታገስ ከቡና ጋር ቀላቅሎ መጠጣት ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው፣ የፊት መሸብሸብንና ቴታነስን ለመከላከል ጥቁር አዝሙድን ከሞቀ ውሃ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ይመከራል። 👉እንደ ሣል፣ ትኩሳት፣ አስም፣ የቆዳ ሽፍታ፣ እብጠትና የሆድ ድርቀትን ለማከም አገልግሎት ላይ ይውላል። 👉የፀጉር መሳሳት እና መላጣነትን ይከላከላል፣ የአይን ኢንፌክሽን፣ ህመም እና ደካማ እይታን ለመከላከል ዘይቱ ይጠቅማል። 👉በተበከለ ምግብ አማካኝነት የሚከሰትን ድንገተኛ ትውከትን ለማስቆም ይረዳል፣ የጥርስ ህመምን ለማስታገስ ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከሙቅ ውሃ ጋር ቀላቅሎ በተጎዳው ጥርስ ላይ በማፍሰስ ህመምን ማስታገስ ይቻላል። 👉የደም ግፊትን በጣም ይቀንሳል። ዘይቱ ጸረ-አልባሳት ባህሪዎች የደም ግፊትን እና ሌሎች የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎችን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል። 👉በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ አደገኛ የሆኑ ዕጢዎች መፈጠርን ይከላከላል፣ የወር አበባ ፍሰት እና እንቅስቃሴን ያበረታታል። ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Breaking: የትግራይ ክልል መንግሥት የኤርትራ ሠራዊት ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የሽራሮ ከተማን በከባድ ጦር መሳሪያ ደብድቧል ሲል ዛሬ ማምሻውን በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ከሷል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በሽራሮው የከባድ መሳሪያ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ ባለፉት ሁለት ቀናት የኤርትራ ጦር በሽራሮ በኩል ጥቃት የከፈተው፣ ባለፈው ግንቦት 16 በምዕራብ ትግራይ ዓዲ አውዓላ አካባቢ የከፈተው ጥቃት የትግራይ ኃይሎች በወሰዱት አጸፋ ከሽፎ ጦሩ ክፉኛ በመመታቱ ነው ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና ሦስት የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን ገድለው 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና አራት ወታደሮችን እንደማረኩ ገልጧል። አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም መግለጫው ጨምሮ አውስቷል። የክልሉ መንግሥት በዚሁ መግለጫው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ ለማለት እጅጉን ቢረፍድበትም፣ ፈጽሞ ግን አልመሸበትም በማለት መግለጫውን ቋጭቷል። [ዋዜማ ራዲዮ]
Показати все...
#ሰኔ የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ገልጿል። ምንጭ፦ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ፍርድ ቤት ቀርባለች። ባሳለፍነው ቅዳሜ በፀጥታ ሃይሎች የተያዘችው መዓዛ መሃመድ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው የቀረበችው። ፖሊስ በመዓዛ መሃመድ ላይ " ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት " የሚል ክስ ያቀረበባት ሲሆን በጉዳዩ ላይም መረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የጋዜጠኛዋ ጠበቆች ጋዜጠኛዋ ሰራች የተባለው ወንጀል ተፈፅሞ ቢሆን እንኳን ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ነው ፤ በእስር እንድትቆይ ህጉ አይፈቅድም ሲሉ ተከራክረዋል። አክለውም ጋዜጠኛዋ ከወራት በፊት ታስራ ማስረጃ ሊቀርብባት ባለመቻሉ ነፃ መደረግዋን አስታውሰው አሁንም ሞጋች ጋዜጠኛ መሆኗ እንጂ የሰራችው ወንጀል የለም ይሄንን ፍ/ቤቱ ሊመለከተው ይገባል ሲሉ ሞግተዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ ሰጥቷል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ባንኮች 1.8 ቢሊየን ብር ተመዝበረዋል" ተባለ፡፡ በባንኮች ላይ በሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተነሳ 1.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ ምዝበራ በባለፉት አራት አመታት ማጋጠሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታዉቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓም በሸራተን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት፣ ከደረሰው ምዝበራ ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ ምዝበራው የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነዉ መባሉን ሪፖርተር ጽፏል። በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው * አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣ *ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና * ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው። የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ወተት በሊትር ከ40 ወደ 60 ብር ከፍ ብሏል ከአንድ ወር ወዲህ የወተት ዋጋ በአንድ ሊትር ከ40 ብር ወደ 60 ብር ከፍ ማለቱን አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎችና አከፋፋዮች አረጋግጣለች። አንድ ሊትር ወተት ከወር በፊት ከ30 እስከ 40 ብር ድረስ እየተሸጠ የነበረ ሲሆን፤ ሰሞኑን ግን ወደ 60 ብር ከፍ ማለቱን በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከተለያዩ ቦታዎች በመረከብ አንድ ሊትር ወተት በ30 ብር ለማኅበረሰቡ ያከፋፍሉ እንደነበር የገለጹት ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዓለሙ ተሻገር ሲሆኑ፤ ሰሞኑን ግን በ60 ብር እያከፋፈሉ መሆናቸውን አልደበቁም። ለዋጋ ጭማሬው ዋነኛ ምክንያት የመኖ መወደድ ነው የሚሉት ዓለሙ፤ ይህን ተከትሎም ተኮናታሪዎች ኮንትራት እንዳቆሙ ጠቅሰዋል። ተጠቃሚዎቹ በበኩላቸው ለአዲስ ማለዳ የገለጹት የዋጋ ጭማሬውን ተከትሎ በተለይም ለሕጻናት ሲኮናተሩ የነበሩ እናቶች ከሌላው ኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ መቋቋም ስላልቻሉ ኪራይን ለማቆም መገደዳቸውን ነው።
Показати все...
01:36
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የአቶ #ስንታየሁ ቸኮል መልዕክት ከባሕር ዳሩ እስር ቤት፦ የታፈንነው ከአዲስ አበባ በመጡ የኦሮሞ ፖሊሶች ነው። ለእግዚአብሔር እንኳን አፋቸው ቋንቋን ለመናገር የሚፀየፉ አፋኞች ናቸው። እነዚህ የመንግሥት ኃይሎች በGPS በመጠቀም ያረፍኩበት ክፍል ድረስ መጥተው ነው ያፈኑኝ። አሁን በታገትኩበት የባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያሉ ፖሊሶች ለምን ምክንያት እንደታገትኩ አያውቁም። ከላይ በመጣ ትዕዛዝ "ጠብቁ" ተብለዋል። ምናልባት ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ሌላ ቦታ ሊወስዱኝ ይችላሉ። በዋናነት እዚህ ያመጣኝ የአዲስ አበባው ስውር መንግሥት ነው። ይህንን ሕዝቡ ሊያውቅ ይገባል። በተለይ የአማራ ሕዝብ ይህንን በመገንዘብ በነቂስ ወጥቶ ህልውናውን ማስቀጠል አለበት ምክንያቱም ይህ ሁሉ አፈና የእርሱን ህልውና ያለ ሃይ ባይ ለማጥፋት ነው። ከፈጣሪ ቀጥሎ ሃይላችሁ፤ ትክሻችሁና ጉልበታችሁ መሆኑን አውቃችሁ በነቂስ እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ። ስልኬን ሰብረውታል። ትግሉ ይቀጥላል! ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሕር ዳር 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጌጥዬ ያለው – Getiye Yalew
Показати все...
1.79 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በጁንታው ተላላኪዎች አማካኝነት በጫካ ውስጥ ለህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ3500 ሊትር በላይ ቤንዚን አፋር ሰመራ ሎጊያ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።
Показати все...