cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Більше
Рекламні дописи
123 743
Підписники
+4124 години
+3547 днів
+1 43230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት አምራችና ተወዳዳሪ ማድረግ ያስቻለ መሆኑን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ ************** የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት አምራችና ተወዳዳሪ ማድረግ ያስቻለ መሆኑን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፤ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ግን ኢንቨስትመንት፣ የኢንዱስትሪና ከተማ ልማትን ጨምሮ በሌሎችም ሴክተሮች የሚታይ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ የኢንዱስትሪ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ያሳደገ ውጤታማ ስለመሆኑ አብራርተዋል። በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ ማነቆዎችን በቅንጅት በመፍታት ምርታማ ያደረገና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችንም እውን ያደረገ የተሳካ ንቅናቄ መሆኑን ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተዘግተው የቆዩ 10 ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ በርካቶች እንዲሰማሩ አስችሏል ብለዋል። በቀጣይም ከውጭ የሚገቡ ተኪ ምርቶችን ማምረት ላይ የሚሰማሩ አልሚዎችን ተሳትፎ የማሳደግ ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/847490660738448
Показати все...
👍 3👏 1
• "ሙስናን ለመከላከል እና ለመቀነስ በሚደረጉ ሂደቶች ውስጥ በድርጊቱ የተዘፈቁ አካላትን አካታች ማድረግ መፍትሄው እንዳይገኝ እያደረገ ነው" - ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ • "በ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በሙስና ሊመዘበር የነበረ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ሐብት ማዳን ተችሏል"- የፌደራል የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ***************** ዜጎች በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በሚገለገሉበት ወቅት ለሚገጥሟቸው ብልሹ አሰራሮች መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ በተለያዩ ጊዜያት ተገልጋዮች ሲያነሱ ይስተዋላል፡፡ "አገልግሎት ለማግኘት ወደ አንድ ተቋም ስሄድ 'እጅ መንሻ' እንደምጠየቅ እርግጠኛ ሆኜ ነው የምንቀሳቀሰው" የሚሉት አቶ በቀለ አንዳርጌ (ለዚህ ዘገባ ስማቸው የተቀየረ) የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ በቅርቡ ወደ አንድ ተቋም አገልግሎት ለማግኘት በሄዱበት ወቅት የገጠማቸውን እንዲህ ያነሳሉ፡፡ አገልግሎት ለማግኘት በርካታ ሰዎች ጠዋት ጀምሮ በተቋሙ በመገኘት በወረፋ እየጠበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ከኋላ ለመጡ እና በወረፋው ውስጥ ያልነበሩ ግለሰቦች በትውውቅ እንዲሁም ጥቅማ ጥቅም በማቀበል ሲስተናገዱ ማስተዋላቸውን ይናገራሉ፡፡ አክለውም፤አሁን ላይ አግባብ ያልሆነ ጥቅማ ጥቅም እጠየቃለሁ? ወይስ አልጠየቅም የሚለው ሳይሆን የሚያሳስበው፤ ምን ያህል እጠየቅ ይሆን? የሚለው እንደሆነ ያነሳሉ፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0vsk8k4tJ97ap29yysp3MAD6rqn8KWnP25NxXcVjqRXJFvhep1mjSuf5tHjpb4AT1l
Показати все...
👍 17 3
1 ሺህ 181 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ *************** 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሦስት ዙር በረራ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት 1 ሺህ 181 ዜጎች ውስጥ 1 ሺህ 139 ወንዶች፣ 25 ሴቶች እና 17 ጨቅላ ህፃናት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ከተመላሾች መካከል 6 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ17 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል።
Показати все...
👍 26 26👏 9
ሃማስ በግብፅ አና ኳታር የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ እንደሚቀበል አስታወቀ ************ ሃማስ በግብፅ እና ኳታር የቀረበውን የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ እንደሚቀል በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የሃማስ ቡድኑ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬ የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳቡን መቀበላቸውን ለኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና ለግብፅ የደህንነት ኃላፊ ማሳወቃቸው ተገልጿል። በሃማስ ተቀባይነት ያገኘው የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ ምን አይነት ዝርዝር ጉዳዮች እንዳሉት ለጊዜው አለመገለፁን ሮይተርስ ዘግቧል። በግብጽ የሚገኙ አሸማጋዮች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ እና በሐማስ የተያዙ ታጋቾችን ለማስፈታት ያለመ የሁለት ቀናት ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ውይይቱ እሑድ መጠናቀቁን ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው ሐማስ የልዑካን ቡድኑ ከካይሮ ወደ ኳታር በማቅናት ከአመራሮቹ ጋር እንደሚመክር አስታውቆ እንደነበር ተጠቁሟል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ታጋቾች እንዲፈቱ፤ ለ40 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በእስራኤል እስር ቤቶች የሚገኙ በርካታ የፍልስጤም እስረኞችን መፍታትን ያካተተ ሊሆን እንደሚችል ሲዘገብ ነበር።
Показати все...
👍 18 7👏 6
ታግታ የተወሰደችው የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን በተደረገ የተቀናጀ ክትትል በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ************* ታግታ የተወሰደችው የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ጠንካራ ክትትል በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለችው ህፃን የታገተችው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሳርቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ እንደሆነ ተጠቅሷል። ቸርነት ጥላሁን የተባለው ተጠርጣሪ ከቤተሰቡ ጋር በነበረው ቅርበት ሕፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረና ከአምስት ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለትም ነው ፖሊስ የገለፀው። ግለሰቡ ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ስዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች" ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በኋላ ሕፃኗን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር መቆየቱን ፖሊስ ገልጿል። https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0GstEJzhDoY2rNjxSTwEdoEY7L3iAvPFdLseBRZBNXvN3hHnrBBGh9eZxLSYgaLm2l
Показати все...
👍 38 6👏 2
ቅዱስ ጊዮርጊስ አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ከዋናው ቡድን አሠልጣኝነት አገደ *************** የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ የነበረውን ዘሪሁን ሸንገታን እና የበረኞች አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን ከማሰልጠን ተግባራቸው ማገዱን አስታውቋል። የክለቡ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የዋናውን ቡድን እንቅስቃሴ ከገመገመ በኋላ ተለዋጭ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ይህን ውሳኔ ማሳለፉን ገልጿል፡፡ በምትኩም የዋናው ቡድን ምክትል አሠልጣኝ የነበረው ደረጀ ተስፋዬ ዋና አሠልጣኝ ሆኖ ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥን መወሰኑን ከክለቡ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ እንዲሁም የክለቡ የወጣት ቡድን ዋና አሠልጣኝ የነበረው አሠልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ የዋናው ቡድን ምክትል አሠልጣኝ ሆኖ በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥን መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡
Показати все...
👍 22👏 4 3👎 1
ቭላድሚር ፑቲን የታክቲካል (ስልታዊ) ኒውክሊየር የጦር መሣሪያ ልምምድ እንዲጀመር ትዕዛዝ ሰጡ *********************** ሩስያ ታክቲካል (ስልታዊ) የኒውክሊየር የጦር መሣሪያዎችን የምትፈትሽበት ልምምድ "በቅርቡ" እንዲከናወን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሀሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በልምምዱ የደቡብ ወታደራዊ እዝ በሚሳኤል የሚሳተፍ ሲሆን፤ የአየር እና የባሕር ኃይሎችም የልምምዱ አካል እንደሚሆኑ ተገልጿል። የልምምዱ ዓላማ፥ ስትራቴጂክ ያልሆኑ የኒውክሊየር የጦር መሣሪያዎች ዝግጅት እና የጦርነት ተሳትፎ አቅምን ለመገምገም እንደሆነ ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው። የልምምዱ ምክንያት ደግሞ፥ "አንዳንድ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት በሩስያ ላይ የሰነዘሯቸው ተንኳሽ መግለጫዎች እና ዛቻዎች" መሆናቸውን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፤ ልምምዱ ሠራዊቱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሩስያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደሚችል ለማሳየት ያለመ ነው ብሏል። ሞስኮ ከአህጉር አቋራጭ እስከ አጭር ርቀት የኒውክሊየር መሣሪያዎችን መታጠቋን የጠቀሰው የአርቲ ዘገባ፤ በዩክሬን ግጭት ሰበብ እየተፈጠረባት ባለው ጫና ምክንያት ሩስያ ኒውክሊየር የመጠቀም መብት እንዳላት በፕሬዚዳንት ፑቲን ጭምር ሲገለጽ መቆየቱንም አስታውሷል።
Показати все...
👍 61👏 6👎 1
በመዲናዋ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳይከሰት ተከብሯል ************ በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ሕብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በዋዜማው በተከሰተ የእሳት አደጋ ሕይወቱ ካለፈ አንድ ግለሰብ ውጪ ሌላ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አለመድረሱን ገልጸዋል። ቅዳሜ ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጄነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሰራተኛ በጄነሬተሩ ላይ በተነሳ እሳት ወዲያው ሕይወቱ ማለፉን አመልክተዋል። በበዓል ወቅት ሊኖር ከሚችለው የአደጋ ተጋላጭነትና ስፋት አኳያ አደጋዎች አለመከሰታቸውን ጠቅሰዋል። ኮሚሽኑ ከበዓሉ አስቀድሞ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት ማከናወኑን አስታውሰዋል። ማህበረሰቡ የቅድመ አደጋ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ መተግበሩ በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰው ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Показати все...
👍 52👏 12 9👎 1
የእስራኤል ካቢኔ በአገሪቱ የሚገኘውን የአልጀዚራ ቢሮ ለመዝጋት ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገለጸ *********** የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታኒያሁ ዛሬ በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ባጋሩት መረጃ፥ ካቢኔያቸው በእስራኤል የሚገኘውን የአልጀዚራ ቢሮ ለመዝጋት ከውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፥ ውሳኔው በአልጀዚራ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ እና መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ግን የተባለ ነገር የለም፤ ውሳኔው ዘላቂ ይሁን ጊዜያዊም የታወቀ ነገር የለም። ውሳኔው በእስራኤል እና በአልጀዚራ መካከል የቆየውን ቁርሾ እንደሚያባብሰው ይጠበቃል። የአልጀዚራ ቻናል ባለቤት የሆነችው ኳታር የጋዛን ጦርነት ለማስቆም እየተደረገ ባለው ጥረት ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በዚህ ሰዓት የተላለፈው የእስራኤል ካቢኔ ውሳኔ በሁለቱ አገረት መካከል ውጥረት እንዳያነግስ ተሰግቷል። እስራኤል እርሷን በተመለከተ የተዛቡ ዘገባዎችን ያሰራጫል የምትለውን አልጀዚራን ከሀማስ ጋር በማበር ጭምር ትከሰዋለች። አልጀዚራ በጦርነቱ ወቅት ጋዛን ለቀው ካልወጡ ጥቂት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አንዱ ነው። ቻናሉ አሰቃቂ የአየር ጥቃት እና የሆስፒታል ትዕይንቶችን ከጋዛ በቀጥታ ሲዘግብ እና እስራኤልን በጅምላ ጭፍጨፋ ሲከስ ቆይቷል።
Показати все...
54👍 48👎 13👏 6
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ ************ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የጤና ሚኒስቴር የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በሰንሻይን ፊላንትሮፒ ፋውንዴሽን አረጋውያን መጦሪያ ማዕከል ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ በማዕከሉ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማዕድ ያጋሩት ከሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር ነው። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፥ የትንሳኤን በዓል ስናከብር አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመደገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበትም ገልፀዋል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፥ በዓሉን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና አብሮ በማሳለፍ ሁላችንም የድርሻችንን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን ብለዋል። የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ሳሙኤል ታፈሰ፥ ማዕከሉ በበዓላት ወቅት ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ተግባር ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ላደረጉት አስተዋጽኦም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ማዕከሉ አሁን ላይ ለ700 አረጋውያን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎችም ተመሳሳይ እገዛና ድጋፍ እንዲያደረጉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሰንሻይን ፊላንትሮፒ ፋውንዴሽን ትብብር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነባው የአረጋውያን መጠለያና መጦሪያ ማዕከል በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢዜአ ዘገባ አስታውሷል።
Показати все...
👍 39👏 5 3