cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Useful quotes for u

It is a collections of useful saying, quotes, and status. አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን ምግቧን (ፍሬዋን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል፡፡ (14:24-25)

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
170
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እስልምና ኢቅረዕ በሚል አንቀፅ የሚጀምር እምነት ነው። መጀመርያ መማር ከዚያ ልሎችን ማስተማርን የእምነቱ አስኳል ተጣሪዎች እንጂ ፈራጆች እንዳንሆን ያዙናል።ወደ ኢስላም በመልካም ግሳፄና በጥበብ በመጣራት ሌሎች ወደ ኢስላም እንዲቀርቡ ማድረግ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ሆኖ ሳለ እኛ ግን ሰዎች ላይ በመፍረድ በመስደብና በማሸማቀቅ እያራቅናቸው እንገኛለን ለመሆኑ ግን እኛ ከእነሱ እንደምንሻል በምን ይሆን ያረጋገጥነው! የአላህ ቃልስ "ነፍሶቻችሁን አታጥራሩ ከእናንተ ውስጥ አላህን ፈሪ ማን እንደሆነ እርሱ ብቻ ነው የሚያውቀው" አይደል እንዴ የሚለው!  یَا أَیُّهَا الَّذِینَ آمَنُوا لا یَسْخَرْ قَومٌ مِنْ قَوْمٍ عَسَى أَنْ یَکُونُوا خَیْرًا مِنْهُمْ وَلا نِسَاءٌ مِنْ نِسَاءٍ عَسَى أَنْ یَکُنَّ خَیْرًا مِنْهُنَّ وَلا تَلْمِزُوا أَنْفُسَکُمْ وَلا تَنَابَزُوا بِالألْقَابِ بِئْسَ الاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الإیمَانِ وَمَنْ لَمْ یَتُبْ فَأُولَئِکَ هُمُ الظَّالِمُونَ﴿١١﴾ "49:11 - እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡" ሱረቱል ሁጁራት አንቀፅ 11 ኢስላም እንዲኖረን የሚሸው ስብእና ባማረ ስነምግባር ላይ የተገነባ ነው።እራሳችንን አክብረን ሌሎችን እንድናከብር ያዘናል።የኢስላም አላማዎች "መቃሲደል ሸሪዓ" ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሙስሊሙን ክብር መጠበቅ ነው። የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱም ከእጁም ሰላም የሆኑለት ሰው ነው ብለዋል ። ኢብኑ መስዑድ (ረድየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሌላ ሃዲስ ደግሞ ሙስሊምን መስደብ ወንጀል ነው።መጋደሉ ደግሞ ክህደት ነው ይላሉ መምህራችን አሽረፈል ኸልቅ! ሌሎችን በስነ ምግባራችን ጠርተን ወደ ኢስላም ማምጣት ሲጠበቅብን ያሉትን ስህተቶቻችንን እንዲያርሙ በጥበብ ከመንገር ይልቅ በስድብ እንገፋቸዋለን! ከመነሻው እነርሱ እንዲስተካከሉ ቢሆን ኖሮ ደግመን ደጋግመን ጥሪ ባረግንላቸው እና ባስታወስናቸው ነበር። ግና እኛ ከሌሎች መሻላችንን ማንፀባረቅ ስለሆነ የምንሻው ከማስተማር ይልቅ ስድብና ነቆራን መርጠናል ይህ ሙስሊሞች ላይ ስህተት ስንመለከት ብቻ አይደለም።ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችንም ስለ ኢስላም አንድ ነገር ሲፅፉ አልያም ሲጠይቁ በስነ ስርዓት ከመመለስና ከማስረዳት ይልቅ ስድብን እንመርጣለን። በአንድ ድንበር ውስጥ አብረን የምንኖር የድንበር ወንድሞቻችን ላይ ድንበር በማለፍ እኛንም እስልምናንም እንዲጠሉና እንዲጠራጠሩ በር እንከፍታለን።በእርግጥ ይህ ነገር ከግንዛቤ እጥረት ተነስቶ ሊሆን ይችላል የሚደረገው ግና ፍፁም ስህተት ነው።ሌሎች ወደ ቀናው እንዲመጡ ምክንያት መሆን ባንችል እንኳ ከኢስላም እንዲርቁ ገፍታሪ መሆን የለብንም።ሰዎች ኢስላም ምን ይላል ሚለውን ሳይሆን ቀድመው የሚመለከቱት ሙስሊሞች ምን ይላሉ የሚለውን ነው።ንግግራችንም ሆነ ተግባራችን ኢስላምን የሚወክል በመሆኑ ከኢስላማዊ አስተምሮ የተቀዳ ይሁን አልያም ተናገሩ ብሎ የሚያስ ገድደን የለምና ዝም እንበል "መድሃኒት ስለወሰድነው ሳይሆን ፈውስ የሚሰጠው በአግባቡ ስንጠቀመው ነው" እስልምናም ምሉእነት ነው ብለን ስለፎከርን ሳይሆን ውብ ሆኖ የሚታየው በእኛ ህይወት ውስጥ ስጋና ደም ለብሶ ሲከሰት ብቻ ነው።እየናረ የሚገኘውን የስድብ ፍጆታችንን መቀነስ ካልቻልን ስለ ኢስላም የምንፈጥረው ገፅታ በጥላሸት የተሞላ ነው የሚሆነው! ይህን ፅሁፍ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!! በድምፅ የደረሰኝን መጣጥፍ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘውት በፅሁፍ ገልብጬ አቀርብኩላችሁ። እኔም ሰዎችን የማስተማር ጥበብ የጎደለን ይመስለኛል! በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጊዜ አንድ እእራቢይ(ዘላን ወይም የገጠር ሰው) በሚሰግዱበት መስጂድ ውስጥ ወደ አንድ ጥግ ዞር አለና ሽንቱን መሽናት ጀመረ።ሰሃቦችም በጣም ተቆጥተው እና ገንፍለው አደነባበሩት የአለም እዝነት የሆኑት ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግን ሰሃቦችን አስቆሟቸውና ተውት ይጨርስ አሏቸው። ሸንቶ እንደጨረሰ ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀረብ ብለው የሚሰገድበት ቦታ ውስጥ እንዲህ እንደማይደረግ በጥበብ አስተማሩት ያ አእራቢይም እንዲህ ነበር ያለው! "አላሁመ እርሃም አነ ወሙሃመዳ ወላ ተርሃም መዓና አሃዳ" "አላህ ሆይ ለእኔና ለሙሃመድ እዘንልን ከእኛ ጋር ለአንድም አትዘን" እዩት ያደረገው ዱዓን ምን ያክል በሰሃቦቹ ተከፍቶ እንደነበር ያሳየናል።ማስተማር፣ዳዕዋ ማድረግ እና የመሳሰሉት ኸይር ናቸው የምናስተምርበትን መንገድ አለማወቅ ግን አደጋ ነው! አየህ የሃቢባችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጥበብ ልቡን እንዴት እንደማረከው! በኢስላማዊ ጥበብ ህይወታችንን እናሳምር!! በቪድዮ ለማየት ለምትሹ👇👇 https://www.facebook.com/belachhizboch/videos/1712446248921929/
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 13
ለምን በሙስሊሞች ላይ በረታን❗️ የማስተማር ጥበብን ዘነጋን ከወቅታዊ ሁኔታችን ጋር የተያያዘ❗ የመጀመርያ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሳለው በእንግድነት እየመጣ የሚያስተምረን መምህር ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የማካካሻ ትምህርት እየሰጠን ይገኛል የመግሪብ ሰላት ከመድረሱ በፊት ይጨርሳል ብለን ብንጠብቅም ማስተማሩን ቀጠለ የመግሪብ አዛን ሲያስተጋባም ብርሃን በጨለማ ቦታዋን እየተነጠቀች ነበርና ከዚህ በኋላ ብዙ አይቆይም በሚል እሳቤ የመግሪብ ሰላትን አስፈቅደን ወጥተን ለመስገድ እያመነታን ነው።በመሃል ግን አንዲት ሴት ልጅ እጇን አውጥታ ይቅርታ መምህር የሰላት ሰዐት እያለፍብን ስለሆነ 5 ደቂቃ ፍቀድልን ሰግደን እንመለስ ስትል ጠየቀች መምህሩ ደነገጠ ምላሽ ሳይሰጣት ለጥቂት ሰከንዶች አትኩሮ ተመለከታት።ተማሪውም ተገርሞ አትኩሮ እየተመለከታት ነው። ሙስሊም ነሽ? ሲል ጠየቀ መምህሩ በአግራሞት ይህ ጥያቄ የመምህሩ ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው።ልጅቷ ስሟ የሙስሊም ቢሆንም ገፅታዋ ግን የሙስሊም ሴት አይመስልም።ሂጃብ ለብሳ አታውቅም።ሙስሊምነቷ ያጠራጥር ነበር። ቆንጆ ስለሆነች ነው መሰለኝ መጥፎ አመለካከት ነበር ለሷ ያለን ዝምተኝነቷ እና ከማንም ተማሪ ጋር አለመቀላቀሏን እንደ አስመሳይነት ነበር የምንቆጥረው።አረ እንደውም ምናለ ስሟን በቀየረችው እያልን በተደጋጋሚ በመጥፎ እናነሳት ነበር።ሙስሊም ነሽ ሲል መምህሩ ጥያቄውን ደገመው ሙስሊም ባልሆን ለሰላት አስፈቅድህ ነበር ስትል መለሰችለት። ጥሩ መስገድ ምትፈልጉ ወጥታችሁ መስገድ ትችላላችሁ አለ። በክፍል ውስጥ ካለው።6ወንድ 5ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል 3ወንዶች እና ይህችው ለሰላት ያስፈቀደችው እንስት ብቻ ለመስገድ ወጣን ከመማርያው ህንፃ ጀርባ በሚገኝ ሳር ውስጥ ለመስገድ ገባን።ይህች ልጅም ከቦርሳዋ ውስጥ አባያና ሂጃብ አውጥታ ለበሰች።ትንሽዬ ተጣጣፊ መስገጃዋን አንጥፋ ከእኛ ኋላ ፈንጠር ብላ መስገድ ጀመረች ኢቃም ብለን መስገድ ብንጀምርም ሃሳቤ ግን ልጅቷ ጋር ነው። እንዴት ገፅታዋን ብቻ አይተን እንደዛ በመጥፎ ሳልናት!ለምንስ ቀርበን ልናናግራት አልሞከርንም።ከእኛ ተሽላ የሰላት ሰዓት አሳስቧት ማስፈቀዷ ለምን ግርምት ፈጠረብን እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች በአእምሮዬ እየተመላለሱ ሰላቱን ሰግደን ጨርሰን ወደ ክላስ ተመለስን ክላስ ገብቼ ትምህርቱን ከመከታተል ይልቅ ሃሳቤ ልጅቷ ጋር ነበር ብዙ ሳይቆይ መምህሩ ትምህርቱን ጨርሶ አሰናበተን።ከኋላ ስለነበር የምቀመጠው ልጅቷ ቀድማኝ ስለወጣች እየሮጥኩ ተከተልኩና ስሟን ጠርቼ አስቆምኳት።እህት አለም በአላህ አውፍ በይኝ ስላንቺ በጣም መጥፎ ነገር አውርቻለው።ድንበር አልፌብሻለው አልኳት። መሬት መሬቱን እየተመለከተች በለመጣ ፈገግ አለችና አንተ ብቻ አይደለህም ይህን አይነት አመለካከት ያለህ ሙስሊሙ በሙሉ እንዳንተ ነው።አልያም ከአንተ በከፋ ነው የሚያስበኝ አለች።ጥቂት ዝም ካለች በኋላ ሳግ እየተናነቃት ይገርመሃል አያቶቼ ስለ እስልምናፕምንም አያቁም እኔም የተማርኩት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነው። የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በሙሉ ሙስሊም ያልሆኑ ናቸው በእርግጥ አካባብያችን ሙስሊም ስለሚበዛ ሂጃብ ሲለብሱ እመለከት ስለነበር የሙስሊሞች የማንነት መገለጫ ነው ብዬ ሳስብ መልበስ ጀምሬ ነበር።ቤተሰቦቼ ግን አልፈቀዱም የእራሴ ክላስ ስላለኝ እዛ ገብቼ በመቆላለፍ ሰላቴን እሰግድ ነበር።ወደ ዩንቨርስቲ ስገባ የተወሰነ ነፃነቴን ስለማገኝ በተቻለ መልኩ ስለ እምነቴ ለማወቅ እና ለመተግበር ምኞቱ እና ፍላጎቱ ነበረኝ።ግና ዶርሜ ውስጥ የነበሩት ሙስሊም እህቶቼ ጥሩ አልተቀበሉኝም የጁምዓ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ ሳቀና ሰላቱ ምን ያደርግልሻል።ወይ ጥቅልል ብሎ መግባት ወይ መውጣት ሲሉ ተናገሩኝ የሚያቀርበኝ ጠፋ የሚያስተምረኝ ከጎኔ ሆኖ የሚያበረታታኝ አጣው።በተቃራኒው የሚሰድበኝና የሚተቸኝ ግን በርካታ ነው። ኢስላምን የማያውቅ ቤት ውስጥ እንደማደጌ በአንድ ጀንበር ውስጥ ለውጥ ማምጣት ለኔ ከባድ ነው።ይሁን ቢባል እራሱ ስለ ለውጥ ለኔ ቀርቦ የሚያስረዳኝ የለም በጣም የሚገርመው ሰላታቸውን በትክክል የማይሰግዱ በየፓርቲ ቤቱ በሙዚቃ የሚጨፍሩና በየበግ ተራው ከወንድ ጋር ሲላፉ የሚያመሹ ሁሉ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከእኔ የተሻሉ እንደሆኑ በማሰብ በንቀት አይን ይመለከቱኝ ነበር።ሂጃብ መልበስ በጣም ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ መላበስ ግን ከባድ ነው።ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃባቸውን ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ከቤተሰቤ ስርቅ ሂጃቤን ስለመልበስ ነበር የማስበው ግና...አለችና በረጅሙ ተነፈሰች... እቴዋ ሰልመሽ ያደርሽው ሙእሚኗ የተከበርሽው ሰብአዊ ክብርሽን አጥተሽ ደም እንባ ያንቆረቆሽው ስልጡን ዘመን ላይ ተፈጥረሽ እግር ስር የተረገጥሽው የኑሮሽ አሻራ በዛ ላይፋቅ ወይ ላይነሳ ለፆታሽ መብት ተነፍጎ ለጥቅምሽ ነጋ ደግድጎ ለጎዳሽ ማረግ ፈልጎ ላትሰለጥኚ ተጠልፈሽ በሰለጠነ ተልፈሽ ሃፍረት ማረግሽን ተዘርፈሽ መብትሽ መብትሽ ለቆጨሽ ተገድፈሽ ለምታሰሚው ኡኡታ እርቃን አልሆንም ስሞታ አታድሙኝ ላልሽው አታጥቁኝ በእውቀት አክብሩኝ አትናቁኝ የሃዋ ዘር ነኝ እወቁኝ!!! ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠች ሄደች። ....ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠች ሄደች። ለደቂቃዎች በድንዛዜ ውስጥ ቆሜ ሳስብ ሳስብ እራሴን ነቅንቄ ወደ ዶርሜ መመለስ ጀመርኩ "ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃብ ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ሂጃብን ለመልበስ ከቤተሰቤ መራቅን ነበር የማስበው ሂጃብ መልበስ ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ ግን መላበስ ግን ከባድ ነው።" እነዚህ ቃላቶችን ደጋግሜ እያሰብኩ ዶርም ደረስኩ ጓደኞቼ ምንም አላሉም ምን ሆንክ እያሉ ሲጮሁብኝ ነበር ከአይኖቼ እንባ እየፈሰሱ እንደነበር ያወቅኩት።ዛሬ ይሃንን ትዝታዬን የቀሰቀሰው ክስተት ደግሞ ይህ ነበር።የፌስቡክ ኖትፊኬሽኔን ስመለከት በርካታ የፌስቡክ ጓደኞቼ ኮሜንት የሰጡበትን ፖስት አገኘው ምን ይሆን ብዬ ወደፔጁ ጎራ አልኩ #ሃሊማ #አብዱረህማን የምትባል ዘፋኝ ፔጅ ነው።ኮሜንቶቹን ማንበብ ጀመርኩ ሙስሊሞች የሰጡት ኮሜንት በአጠቃላይ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ለምን አንደኛውን አትከፍሪም?ለምን ስምሽን አትቀይሪም?ወደ እሳት ተጣሪ!የሰይጣን ተላላኪ! መሰል እጅግ ከባባድ ኮሜንቶችና ሌሎች አስቀያሚ ስድቦች ሞልተውታል። አስደነገጠኝ በተለይም ልጅቷ ለአንዳንድ ኮሜንቶች የሰጠችው ምላሽን ሳነብ የበለጠ ደነገጥኩ።አሁን ይቺ ልጅ ብትከፍር ተጠያቂው ማነው⁉️ የሚገርመው ደግሞ በኮሜንት ውስጥ አንድም ሊያስተምራት የሞከረ የለም።አረ እንደውም የአንዳንድ ተሳዳቢዎችን አካውንት ስመለከት የሂጃብ ትርጉም የሌለው ጨርቅ እራሳቸው ላይ ጣል አድርገው በሜክአፕ ሌላ ፊት ደርበው ጭብጨባ ፍለጋ በርካታ ፎቶዎችን ለጥፈዋል። እጅግ በጣም የሚገርመው የበርካታ ዘፋኞችና የዘፈን ፔጆችን ሳይቀር ላይክ አድርገዋል።👇👇👇
Показати все...
እረኛው በጎችን ይዞ ወደ ማደሪያቸው አስገብቶ በሮችን ሁሉ በሚገባ ዘጋው። የተራቡ ቀበሮዎች በጎቹን ሊበሉ ሲመጡ በሮች ሁሉ በሚገባ ተዘግተው አገኙት። በሮችን አልፈው መግባትን ተስፋ የቆረጡት ቀበሮዎችም፤ በጎቹን ከበሮች ቁጥጥር ውጭ ለማድረግ ሴራቸውን ይጠነስሱ ጀመር። በመጨረሻም ቀበሮዎቹ (የበጎች ነፃነት ይከበር) የሚል መፍክር ይዘው የበጎቹን ማደርያ ዙርያ ለመዞር ወሰኑ። በጎችም ለነሱ ነፃነት እንዲከበር ቀበሮዎች ትልቅ አብዮት እንዳቋቋሙ ሲሰሙ ልባቸው ወደ ቀበሮዎቹ ይሸፍት ጀመር። የነፃነት አብዮቱን ለመቀላቀል በርካታ በጎችም የግቢያቸውን አጥር በቀንዶቻቸው ይነቀንቁ ጀመር። ከረጅም ግዜ ረብሻ እና ትርምስ በኋላ በጎቹ ማደሪያቸውን አፍርሰው አብዮቱን ለመቀላቀል ወደ ጫካዎች ፈረጠጡ። ቀበሮዎችም ከበጎቹ ኋላ ይሮጡ ጀመር፤ እረኛውም ከኋላ ኋላ እየሮጠ አንዴ በድምፁ አንዴ በብትሩ ሊመልሳቸው ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም። አብዮታዊ ሩጫው ቀጥሏል፤ በጎች ከፊት ቀበሮዎች ከኋላ....ብዙም ሳይርቁ ቀበሮዎች እና በጎች ያለ እረኛ ያለ ከልካይ ሰፊ በረሃ ላይ ተፋጠጡ። ያች ቀን የነፃነት አብዮትን ፍለጋ ለወጡት በጎች ጨለማ ስትሆንባቸው፤ ሴራን ላሴሩት ቀበሮዎች ግን የደስታ እና የፈንጠዝያ ቀን ነበረች። በማግስቱ እረኛው ተነስቶ ወደ አብዮት የወጡትን በጎች ፍለጋ ወደ በረሃው ሲያቀና፤ የነፃነት መገለጫ የሆኑ ቀበሮዎች ነፃነትን ፍለጋ የወጡትን በጎች ስጋዎቻቸውን በልተው፣ አጥንቶቻቸውን በመሰባበር ሜዳው ላይ በትነዋቸው አገኘው። _____________________________ ድሮ የሰማናት ተረት ናት አይደል!!! ግን በአለማችን የሚገኙ የሴቶች የነፃነት አብዮትን እና ቀበሮዎችን ምን ያህል እንደሚመሳሰሉ አስተውላችሁታል!!!? የሴቶች ነፃነት አብዮት የሙስሊም ቁጥብ፣ ጨዋ እና እንቁ ሴቶችን በቀላሉ ሊያገኝ አይችልም። ምክንያቱም፦ አባቶቻቸው ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል። ምክንያቱም፦ቤታቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘዋል። ምክንያቱም፦ ሂጃብ አድርገዋል። ለዝያም ነው የሰው ቀበሮዎች <የሴቶች ነፃነት> የሚል መፈክር ይዘው ሚስተዋሉት። አላማው ግን <የሴቶች ነፃነት> ሳይሆን <ወደ ሴቶች መድረሻ ነፃነት> ነው። ©Al kewser https://t.me/usefulquotesforyou
Показати все...
Real Heroes
Показати все...
IMG_0145.MP410.00 MB
Real Heroes
Показати все...
IMG_0145.MP410.00 MB
EID MUBARAK
Показати все...
የረመዳን 27ተኛ ለሊት ★★★★★★★★★★★ በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ83 ዓመት ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ ሰሀባዎች ውስጥ፥ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም ለይለተል-ቀድር የረመዳን 27ተኛ ለሊት ላይ ናት ይሉ ነበር! ይህች ለሊትም ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ላይ ናትና እንበራታ!
Показати все...
Oh allah don't make this world our biggest concern! አላህ ሆይ ዱንያን ትልቁ ሃሳባችን አታድርጋት!
Показати все...
🤲 58
Oh allah don't make this world our biggest concern! አላህ ሆይ ዱንያን ትልቁ ሃሳባችን አታድርግብን!
Показати все...
🤲 1
Useful Quotes for You sent you a gifft https://gifft.me/l/#TNDizsQAc1
Показати все...

Funny Quest with Personal Message at End. Send and receive gifts in a surprising way!