cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።” — 2ኛ ቆሮ 11፥28

Більше
Рекламні дописи
15 407
Підписники
+424 години
+3007 днів
+1 03230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Please forgive me for my belated reply to your letter which is dear to me. I am not feeling well, and the thoughts about death do not leave me alone. I feel that if I live up to see 1963, I will not pass it through. For me personally,death is desirable. I know that there is future life, that there is God’s mercy for us and there is hope for us believing in the Lord Jesus Christ to enter intothe blissful eternity, rather than an everlasting torturous future. Religious perceptions, though different from the spiritual meaning ofthe world, are also as real as the perceptions of the physical world. The earthly life is not for pleasures but for getting knowledge of oneself and of God. During their earthly life people must make a resolute and irrevocable choice– to strive for good or for evil; for God or for devil. Those seeking God and His truth will find God and the rudiments of a new life here, on earth, and in itsfullness – after death. An egoist looking exclusively for earthly pleasures will find the devil and after death, as of one in spirit with the devil will go to the Devil’s kingdom, Hell, to join the community of downright egoists and evil-doers. Our future destiny is in our hands… Forgive me, if I am writing not quite what I should. I am sorry not to have come to see you this summer. I wish to be farther from this life and from the spirit of this world. This spirit has taken possession of the whole mankind. Only from the outside it is possible to see and to feel the loathsome vileness and ugliness of this spirit. There are very few people in the world today, who are capable of escaping the influence of this evil spirit on them. This is horrible! They say, that a frogmeeting with the eyes of a snake cannot cast its glance away, it starts to cry,but is unable to run away and instead is moving closer and closer to the snake until it fnally gets into its mouth. There are words in one of the evening prayers, pleading: “Lord, take me away from the mouth of the abhorrent serpent, desiring to devour me alive and to throw into the hell.” These words come from human experience. Those possessed by this spirit do not understand them and do not believe those who have freed themselves from it. May the Lord bless you and protect you from evil and lead you to eternal blissfulness after death. God willing, we might see each other in the outer world. Choose God; keep away from the devil in spirit and in deed, so that the Lord’s words: “Who is coming to Me I will not cast out” may be also said about you. #Abbot_Nikon_Vorobiev #Spiritual_letters
Показати все...
29👍 14🙏 6🥰 1
“ተጋድሏችን ለእውነት እንጂ ለቃላት አይደለም!” ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሰው ሐሳቡን የሚገልጸው በቃላት አማካኝነት መሆኑ የታወቀ ነው። ሆኖም ሰው የሚረዳውን ሁሉ አከናውኖ ለመግለጽ ግን ቃላት ብቻቸውን ብቁዎች አለመሆናቸው ግልጽ ነው። አዳዲስ ቃላትን በመፍጠርና ዐረፍተ ነገሮችን በመደርደር ለማስረዳት የሚደክመው ከዚህ የተነሣ ነው። ሰው በሰውነቱ የሚያስባቸውን ሐሳቦች ለመግለጽ እንኳ ቀላል ካልሆነ፣ አምላካዊ የሆኑ ነገሮችን ለመግለጽማ የሰው ልጅ ቋንቋና ገለጻ ምን ያህል ደካማ ይሆን? ነገረ ሃይማኖት ከቃላትና አገላለጾች በእጅጉ ያለፈ ነውና። ኦርቶዶክሳዊ የነገረ ሃይማኖት አረዳድ ከቃላዊነትና ሐተታዊነት ይልቅ ወደ ተመስጧዊነትና አንክሮታዊነት የሚያደላውም ለዚህ ነው። ይህም አሉታዊ አረዳድ (Apophatism - አፖፋቲዝም) የሚባለው ነው። አንድ ሰው ነገረ እግዚአብሔርን የሚማረው ለድኅነት የሚጠቅመውን ያህል እንዲያውቅ፣ ብሎም አላዋቂነቱን ለማወቅ እንዲረዳው እንጂ እግዚአብሔርንና አሠራሩን በተመለከተ ሁሉን አውቃለሁ እንዲልና በዚህ ዐለም እንዳሉ የእውቀት ዘርፎች ዓይነት ራሱን እንደ ባለሞያ እንዲቆጥር አይደለም። ቃላትን የምንፈጥራቸው እኛው ሰዎች ነን። አንድን ሐሳብ ለመግለጽ ወይም ለመወከል ስንል ወይ አዳዲስ ቃላትን እንፈጥራለን፣ አለዚያ ደግሞ የነበረን ቃል አዲስ ወይም የዳበረ ሐሳብ እንዲወክል እናደርገዋለን። በነገረ-ሃይማኖትም አምላካዊ ትምህርቶችን ለመግለጽ የተሄደበት መንገድ እንደዚሁ ያለ ነው። ጥልቅ የሆኑ አምላካዊ ጸጋዎችንና እውነቶችን ለመግለጽ ያስችላቸው ዘንድ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ወይ ነባር ቃላትን አዳዲስ ጽንሰ-ሐሳብ እንዲወክሉ ያደርጓቸዋል፣ አለዚያ ደግሞ እነዚያን ሐሳቦች የሚሸከሙ ቃላትን ለመፈለግና ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ታሳቢ ሊደረግ የሚገባው አንዱ መሠረታዊ ጉዳይ፣ ቃላት የሚወክሉት ሐሳብ እንደየ አረዳዱ የተለያየ ሊሆን የሚችል የመሆኑ ነገር ነው። በሆነ ወቅት ላይ ጤናማ ያልሆነ አስተምህሮን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ ቃላት በሌላ ወቅት ደግሞ ጤናማ የሆነ አስተምህሮን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ለዚህ ጉዳይ ሁነኛ ማሳያ የሚሆነው “homoousion - ሆሞዑሲዮን - ዋሕደ-ባሕርይ ምስለ አብ” የሚለው ቃል ነው። Homos - አንድ ዓይነት ፤ ousia - ባሕርይ ማለት ነው። ይህ ቃል በ325 ዓ.ም. በኒቂያ በተካሄደው የመጀመሪያው ዐለም አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ላይ አባቶቻችን የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ጋር በባሕርይ አንድ መሆኑን ለመግለጽ የተጠቀሙበት ቁልፍ ቃል ነው። ሆኖም ከኒቂያ ጉባኤ ግማሽ ምዕት ዓመት ያህል ቀደም ብሎ በተካሄደው በአንጾኪያ ጉባኤ (264-272) ላይ ጳውሎስ ሳምሳጢ የተባለው መ*ና*ፍ*ቅ# የተወገዘው ይኸን ቃል በመጠቀሙ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ጳውሎስ ሳምሳጢ ይህን ቃል (homoousion - ሆሞዑሲዮን) የተጠቀመው የአብን የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን አካላዊ ህላዌ የሚክደውን የሰብአልዮስን ክህደት በሚወክል መልኩ ስለነበረ ነው። ቀደም ሲል ጳውሎስ ሳምሳጢ የተሳሳተ አስተምህሮን ለመግለጽ የተጠቀመበትና በአንጾኪያ ጉባኤ የተ#ወገዘበ*ት ይህ ቃል፣ በ325 ዓ.ም. በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ከአብ ጋር በባሕርይ አንድ መሆንና የባሕርይ አምላክነት በሚገልጽ መንገድ ጥቅም ላይ በመዋሉ የኦርቶዶክሳዊነት መለያ ቁልፍ ቃል ሆነ። ከዚያ ወዲህ “homoousion - ሆሞዑሲዮን” የሚለው ቃል የኦርቶዶክሳዊነት አጥርና ቅጥር ሆነ። ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ደግሞ ሰዎች የሚያምኑት አስተምህሮ አንድ ዓይነት ሆኖ ሳለ አገላለጻቸው የተለያየ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሊኖር የመቻሉ ነገር ነው። ይህ በአንድ በኩል የቋንቋና የቃላት ውስንነት ውጤት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አጽንኦት አሰጣጣቸውና አገላለጻቸው ሊለያይ ስለሚችል ነው። የቋንቋና የቃላት አጠቃቀም፣ አንድ አስተምህሮ (ሃይማኖት) ያላቸውን ወገኖች የተለያየ ነገር የሚያምኑ ሊያስመስል የሚችልበት ሁኔታ አለ። በዐራተኛው መቶ ዓመት ይህ ሁኔታ ተስተውሏል። በግሪኮችና በላቲኖች መካከል ሃይማኖታቸው አንድ ሆኖ ሳለ የግሪክ ነገረ-ሃይማኖታዊ ቃላትን ወደ ላቲን ቋንቋ ሲተረጉሙ ተመጣጣኝ የሆኑ አቻ ቃላትን ካለማግኘታቸው የተነሣ የተጠቀሟቸው የላቲን ቃላት ሃይማኖታቸው ችግር ያለበት መስሎ እንዲታይ ከሚያደርግበት ደረጃ ደርሶ ነበር። ይህን ሁኔታ የፈታው ታላቁ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ነበር። ቅዱስ ጎርርዮስ ነባቤ መለኮት፣ ስለ ቅዱስ አትናቴዎስ በጻፈው የውዳሴ ድርሰቱ ላይ ይህን ጉዳይና ቅዱስ አትናቴዎስ የፈታበትን መንገድ እንዲህ ገልጾታል፡- “. . . እስካሁን በተናገርኩት ላይ ይህን ለእኔ በተለየ ሁኔታ አስደናቂ ሆኖ የሚታየኝን ተግባሩን [የቅዱስ አትናቴዎስን] ሳልጠቅስ ባልፍ፣ በተለይም ሰዎች ለመለያየትና ላለመግባባት ዝግጁዎችና ምቹዎች በሆኑበት በእኛ ዘመን፣ ከቅጣት ነጻ የሚያደርገኝ አይመስለኝም። ይህን እርሱ ያደረገውን ነገር ልብ ብለን ካስተዋልነው፣ ለዚህ ዘመን ሰዎችም ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣልና። . . . መለያየት ያለው በእኛና በስህተት ውስጥ ባሉት ሰዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ አማኞች በሆኑት ዘንድም ነውና፣ ይኸውም ደግሞ የሚያስከትሉት ነገር በጣም ኢምንት በሆኑ ጥቃቅን አስተምህሯዊ ጉዳዮች (in regard to such doctrines as are of small consequence) እንዲሁም ደግሞ አንድ ዓይነት ትርጉም እንዲኖራቸው ታስበው በሚነገሩ አገላለጾች የተነሣም ነው እንጂ። “አንድ ባሕርይ እና ሦስት አካላት (one Essence and three Hypostases) ማለትን ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መንፈስ እንጠቀማለን፣ ባሕርይ (Essence) የሚለውን የባሕርይ አምላክነትን ለማለት፣ አካላት (Hypostases) የሚለውን ደግሞ የሦስቱን ህልውነትና የየራሳቸውን ገንዘብ ለማመልከት እንጠቀማለን። ሆኖም ጣሊያናውያን ይህንኑ ማለታቸው ቢሆንም ቅሉ፣ ከመዝገበ ቃላታቸው ስስነትና ከቃላት ድህነት የተነሣ፣ በኢሰንስ (Essence) እና በሃይፖስታስስ (Hypostases) መካከል ልዩነት ለማድረግ አልቻሉም። ከዚህ የተነሣም፣ ሰዎች በስህተት ሦስት ባሕርያት (Essences) ብለው የሚያምኑ እንዳይመስላቸው ለማድረግ በሚል ’ፐርሰንስ’ (Persons) የሚል ቃልን ተጠቀሙ። የዚህ ውጤት ግን አሳዛኝም አስቂኝም በሆነ ነበር። ይህ ትንሽ የቃላትና የአገላለጽ ልዩነት የሃይማኖት (አስተምህሮ) ልዩነትን እንደሚያመለክት ተደርጎ ከመወሰድ ደረጃ ላይ ደረሰ። “ከዚያም ‘ሦስት ፐርሰንስ’ (Three Persons) በሚለው አስተምህሮ በውስጡ ሰብአ*ልዮሳዊነት እንዳለው አስጠረጠረ፣ ‘ሦስት ሃይፖስታስስ’ (Three Hypostases) በሚለው አስተምህሮ ውስጥ ደግሞ አር#ዮሳዊ*ነት*ነት እንዳለበት ይጠረጠር ጀመር፤ ሁለቱም በተረጋጋ መንፈስ አንዱ ሌላውን ለመረዳት ጥረት ከሚያደርግ መንፈስ ሳይሆን ከተከራካሪነትና ራስን ብቻ እውነተኛና ተቆርቋሪ ከማድረግ መንፈስ የተወለዱ ናቸውና። ከዚያም ቀስ በቀስ የሆነ ግን የማያቋርጥ የመነቃቀፍና የቁጣ መንፈስ በመካከላቸው እያደገ በመሄዱ፣ ከቃላትና አገላለጽ ልዩነቶች በተጀመረ አለመግባባት፣ መላው ዐለም በሃይማኖት ወደ መለያየት ሊያመራ ከሚችልበት አደጋ ላይ ደርሶ ነበር።
Показати все...
👍 32🙏 2🕊 1
“ይህን እያየና እየሰማ፣ እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰውና ታላቅ የነፍሳት እረኛ እንደ መሆኑ፣ በቃላት ስንጠቃና በአገላለጽ ልዩነት የመጣውን ይህን የመሰለውን አስነዋሪ የመለያየት አደጋ ዝም ብሎ መተው ከተግባሩ አንጻር ተገቢ ሆኖ አላገኘውም። ስለዚህም ለዚህ ደዌ ተገቢ የሆነውን መድኃኒት አደረገለት። በምን ሁኔታ? ቅንና ርኅሩኅ በሆነው መንገዱ ከሁለቱም ወገኖች ጋር ጉዳዩን ተወያየ፣ የሁለቱንም ወገኖች የአገላለጾቻቸውን ይዘትና ትርጉም በጥንቃቄ ከመዘነ በኋላ፣ እና የሁለቱም አገላለጾች አንድ ዓይነት ሐሳብ (መንፈስ) ያላቸው መሆናቸውን ተረዳ፣ በአስተምህሮ ረገድ በምንም ሁኔታ የተለያዩ እንዳልሆኑ ተረዳ። ስለሆነም ሁለቱም ወገኖች ሃይማኖታቸው አንድ በመሆኑ የየራሳቸውን ቃላትና አገላለጾች እንዲጠቀሙ በመፍቀድ፣ በቃላትና በአገላለጾች ልዩነት ብቻ ሊለያዩ የነበሩትን ወገኖች አንድ አድርጎ ጠበቃቸው። ይህ ድርጊቱ ከብዙ ትጋቶቹና ተጋድሎዎቹ፣ ይህ ታላቅ የሃይማኖት ጀግናችን ከተቀበላቸው ብዙ ስደቶቹና መከራዎቹ ሁሉ የበለጠ ዋጋ ያለው ነው፤ . . .” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት፣ በእንተ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቁ. 35-36) ቅዱስ አትናቴዎስ ይህን ያደረገው፣ በ362 ዓ.ም. በእስክንድርያ በእርሱ ሰብሳቢነት በተካሄደ ጉባኤ ነበር። እንግዲህ ሰዎች ሃይማኖታቸው አንድ ሆኖ ሳለ፣ ግን ጥልቅ የሆነው ነገረ ሃይማኖታዊ ሐሳብ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲተረጎም በሚፈጠሩ የቃላትና የአገላለጾች አጥጋቢ አለመሆን የተነሣ ሃይማኖታቸው የተለያየ ሊመስላቸው ይችላል ማለት ነው። በዚህ ላይ ደግሞ በፍቅርና በቅንነት አንዱ ሌላውን ለመረዳት ጥረት በማድረግ ፋንታ ሁሉም የራሱን አረዳድና አገላለጽ ብቻ ኦርቶዶክሳዊ የሌላኛውን ግን ኑ*ፋ*ቄ#ያዊ አድርጎ ለመፈረጅ ከቸኮለ፣ ከዚያ በኋላ መደማመጥና መግባባት ይቀርና መወጋገዝ ብሎም መለያየት ይከተላል። ቃላትና አገላለጾች ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ጥራዝ ነጠቅ አካሄድ ቤተ ክርስቲያንን ከባድ ዋጋ ሲያሰከፍላት ኖሯል። ስለሆነም በትክክል የአስተምህሮ ልዩነት (ኑ*ፋ*ቄ#) የሆነውን የቃላትና የአገላለጽ ልዩነት ከሆነው ለይቶ ለመረዳት መረጋጋት፣ ፍቅር፣ ቅንነትና ትሕትና ይፈልጋል። በዚያውም ላይ ደግሞ የምንጠቅሳቸው ምንጮች ከሌላ ቋንቋ የተተረጎሙ ከሆኑ፣ ጸሐፊዎቹ አባቶች በጻፉበት የመጀመሪያው ቋንቋ ያ ሐሳብ በምን ሁኔታ እንደ ተገለጸ ከምንጩ ወደ ማጣራት መሄድም ሌላው አስፈላጊ ነገር ነው። መተርጉማን የሚተረጉሙት በዚያን ዘመን በነበረው የቋንቋ አረዳድ እንዲሁም ሰው እንደ መሆናቸው በመረዳታቸው ልክ ነውና። ከላይ ለማውሳት እንደ ተሞከረው በሆነ ዘመን ያስወገዘ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞ የኦርቶዶክሳዊነት ቁልፍ ቃል ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የሆነን ቃል “አለ/የለም”፣ “ይባላል/አይባልም” ከሚለው ባሻገር፣ ያ ቃል መቼና በማን እንዲሁም ምን ለማለት ጥቅም ላይ እንደ ዋለ መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። “ነገረ አበው” (ፓትሮሎጂ) የሚባለው ትምህርት ጥቅሙ እዚህ ላይ ነው። የአባቶችን ትምህርት በዝርዝር ወደ መማር ከመግባት በፊት የነገረ-አበውን ትምህርት በአግባቡ መማር ቢቻል ብዙ ችግሮችን ለመፍታት ሰፊ ዕድል ሊሰጥ ይችላል። በዚህም ላይ የሚጠቀሱትን ዘሮች ከተለያዩ ቅጂዎች ጋር ማመሳከርም አስፈላጊ ነው። እንደዚሁም እነዚያ አባቶች ብለዋቸዋል እየተባሉ የሚጠቀሱትን ነገሮች ከጥንት ምንጫቸው ማጣራት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። እነ እገሌ ብለዋቸዋል እየተባሉ በታላላቅ አባቶች ስም ለዘመናት ሲጠቀሱና ሲያወዛግቡ የኖሩ ሆኖም ከምንጫቸው ሲፈለጉ ግን ያልተገኙ አገላለጾችና ሐሳቦች አይታጡምና። ስለሆነም የሆኑ ቃላትን ብቻ በመውሰድ “እንደዚህ የሚል ቃል አለ/የለም”፣ “እንደዚህ ይባላል/አይባልም” ከሚል ባለፈ፣ ያን ቃል የሚሉት/የማይሉት ወገኖች ለምን እንደዚያ እንደሚሉ/እንደማይሉ ሐሳባቸውን ለመረዳት የተወሰኑ እርምጃዎችን መሄድ አስፈላጊ ነው። የኦርቶዶክሳዊነት ምሰሶ የነበረው ታላቁ አባት ቅዱስ አትናቴዎስ “ተጋድሏችን ለእውነት እንጂ ለቃላት አይደለም!” ያለው ለዚህ ነው። ከቃላትና ከአገላለጾች ባሻገር የሆኑ፣ ከጥቅሶችና ገጸ-ንባቦች ባሻገር አስተምህሮን ማዕከል ያደረጉ፣ ከጥቃቅኑ ነገር አልፈው ትልቁን ሥዕል የሚመመለከቱ እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ያሉ አባቶችን አይንሣን! እኛንም እንደዚህ ያሉ አባቶችን ለመስማትና ለመታዘዝ ያብቃን! አሜን! በዚህች ደካማ ተምኔታዊ ጽሑፍ ላይ የቃላትና የአገላለጽ ችግር ካለም ይቅርታ በመጠየቅ ነው! Dn Yaregal Abegaz
Показати все...
72👍 23🕊 4🥰 2
Показати все...
ምክረአበው መ/ር ኃይለማርያም ዘውዱመጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ Henok Haile ኦርቶዶክስ Ethiopia Orthodox ስብከት sibket

በኦርቶዶክስ እምነት ላይ ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በሦስት መምህራን የተሰጡ ግሩም ማብራሪያዎች Orthodox Ethiopia ኢትዮጵያ

15👍 13
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል። በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል። ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5 የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል። በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል። በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል። በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል። ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል። አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9 (#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
Показати все...
127👍 31🥰 6🕊 3🙏 1
ቅዱስ ጳውሎስን በትክክል ስለመረዳት *** ሐዋርያው በገላትያ እና ሮሜ መልእክቶቹ ስለ 'ኦሪት ሕግ' የተናገራቸው ጉዳዮች አሉ። አነዚህን ነገሮች በትክክል ለመረዳት ሐዋርያው ከማን ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ጉዳዩ ከአይሁድ ዘመም ክርስቲያኖች ጋር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሕጉ የተሰጠበትን ዓላማ በሚገባ አና በጥልቀት ካልተረዱ ሰዎች ጋር ነው ጉዳዩ። የመጀመሪያው ያልተረዱት ጉዳይ ሕግ እስራኤልን ከሌሎች አሕዛብ ለመለየት የተሰጠው ተግባር ማብቃቱን እና አሕዛብም በአብርሃም በኩል የተገባላቸው ኪዳን መድረሱን ባለመረዳት በክርስቶስ አንድ ሆነው ሲያበቁ ከአይሁድ የመጡት ከአሕዛብ ከመጡት ለመለየት ሕጉን መጠቀም መፈለጋቸው ነው። ያ ተፈጽሞአል። ክርስቶስ እስራኤልን ከአሕዛብ የሚለየው ሕግ ፍጻሜ ነው፤ ለሁሉም መጥቶአልና። ሁለተኛው ደግሞ ሕግ ያለ ክርስቶስ ማዳን እና ጸጋ ብቻውን ሊያድን እንደማይችል በመዘንጋታቸው እና ከክርስቶስ ማዳን ጋር ማፎካከራቸው ነው። ሕግ ኃጢኣትን በመግለጥ እና መርገምን በማምጣት ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። ይህ የሆነው ሕጉ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን የሰው ልጅ የነበረበት የድካም ሁኔታ ያደረገው ነው። በክርስቶስ ማዳን መንፈሳዊ ጸጋ ሲሰጥ ግን ሕጉ የባርነት መሆኑ ቀርቶ 'የሕይወት እና የእምነት ሕግ' ሆነ። በቀድሞ ሁኔታው 'የሞት ሕግ' ያለውን በአዲሱ ሁኔታ 'የክርስቶስ ሕግ' እያለ መጥራት ጀመረ። በመሆኑም ሕጉ በክርስቶስ አዲስ ኃይል እና ተግባር እንዳገኘ ተናገረ። ሕጉ አሁንም እንደሚጠቅም ግን ደጋግሞ ተናግሮአል። "ኃጢኣት በሕግ ይታወቃልና" በማለት ሰዎች ኃጢኣት የሆነውን ለይተን እናውቅ ዘንድ ሕጉ የግድ እንደሚያስፈልገን ተናግሮአል። (ሮሜ. 3፥20) በመሆኑም የቅዱስ ጳውሎስ ችግር 'ቅዱስ፣ ጻድቅ እና በጎ' ብሎ ከጠራ ከሕግ ጋር ሳይሆን ሕጉን በተሳሳተ እና ግልብ በሆነ መንገድ ከተረዱ ሐሰተኛ ወንድሞች ጋር ነበር። (ሮሜ. 7፥12) የሚያሳዘው ግን የ15ኛው መ/ክ/ዘመን የተሐድሶ አራማጆችም በዚሁ መሰናክል መውደቃቸው ነው። ቅዱስ ጳውሎስን ከትክክለኛው መልእክታቱን በጻፈበት ዘመን ከነበረው ነባራዊ ዓውድ አንጻር ሳይሆን በመካከለኛቹ ዘመናት በሮም ቤተ ክርስቲያን የነበረው ቀውስ በፈጠረው ሌላ ዓውድ ለመረዳት የመሞከር ስህተት ፈጽመዋልና። Dn. Bereket Azmeraw
Показати все...
70👍 32🕊 3😢 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
«ወንድምህን አትናቀው» ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል። "እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Показати все...
206👍 39🙏 33👏 10🕊 6
“If your marriage is like this, your perfection will rival the holiest of monks.” ✝️ St John Chrysostom St John’s advice to husbands : + Never speak to your wife in a mundane way but with compliments, with respect and with much love. + Tell her that you love her more than your own life, because this present life is nothing, and that your only hope is that the two of you pass through this life in such a way that in the world to come, you will be united in perfect love. + Say to her, ‘Our time here is brief and fleeting, but if we are pleasing to God, we can exchange this life for the Kingdom to come. Then we will be perfectly one both with Christ and with each other, and our pleasure will know no bounds. I value your love above all things, and nothing would be so bitter or painful to me as our being at odds with each other. Even if I lose everything, any affliction is tolerable if you will be true to me.’ + Show her that you value her company, and prefer being at home to being out at the marketplace + Esteem her in the presence of your friends and children + Praise and show admiration for her good acts; and if she ever does anything foolish, advise her patiently. + Pray together at home and go to Church; when you come back home, let each ask the other the meaning of the readings and the prayers.
Показати все...
120👍 22🙏 1
08:19
Відео недоступнеДивитись в Telegram
"መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ"
Показати все...
298.19 MB
59👍 13🕊 2👏 1
05:22
Відео недоступнеДивитись в Telegram
"ክርስቶስ ብቻ"
Показати все...
188.98 MB
50👍 9
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.