cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሰነ-ፅሑፍ (መልካም ሐሳብ!)

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
186
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የመፈተኛ ቀን በዚህ ሳምንት ይፋ ይሆናል። በቀኑም መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን። #SHARE ||| #JOIN @FDRE_MOE @FDRE_MOE
Показати все...
የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ገለጸ፡፡ ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ ፈተናው በበይነ መረብ (በኦንላይን) እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ገልጸዋል፡፡ ለፈተናው የሚያስፈልጉ የግብዓትና የስልጠና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። #SHARE ||| #JOIN @FDRE_MOE @FDRE_MOE
Показати все...
እ-ረ-ኞ-ች! በዛች በትንሽዬዋ ከተማ አዎ በዛች ገጠራማ ስፍራ እንደውም... ማን ነበር ስማቸው እንኳን? አምጡልኝማ!... ዘንግቼው ነው እንጂ'ኮ... አረ ምላሴ ለይ ነው ስማቸው... እዉይ እዉይ አስታወስኳቸው... እ-ያ-ያ። አዎ ከነ እያያ ቤት ጀርባ... በነገራችን ለይ አቶ እያያ ማለት ትጉ የስራ ሰው... በእርሻውም ሆነ በእርባታው የተዋጣላቸው... የተከበሩ ላከባቢዉም ነዋሪ የሚተርፉ ሰው ናቸው። እናም ከቤታቸው ሳይሆን ከቤታቸው በስተጀርባ ታላቅ መብረቃዊ ደስታ ወርዷል። እኔም የዚህ ደስታ ተካፋይ መሆንን ሻትኩና ወደነ እያያ ቤት ማዝገም ጀመርኩ። ሁለት ጎልማሳዎች ፎጣ ያገለደሙ ሁለቱም ቆምጥ የታጠቁ ሁለቱም ቁንጣ ያነገቱ አንደኛው ባለ ዋሽንታም ሁለቱም ከቅርብ ርቀት ለይ በመሆን... ከነ እያያ ቤት ጀርብ ስለተከሰተው ነገር ሊያስረዱኝ ጀመር። እንደዚ በማለት... ቅረበን ወዳጄ ምንነግርሕ አለን ጊዜ ስጠንና አንተ ብቻ አድምጠን። ግሩም ነው ድንቅ ነው ዛሬ የሰማነው ባይናችን ያየነው ከ'ያያ ቤት ሗላው ከበስተጀርባው እንዲ ነው የሆነው... አዎን ስማንማ አጃኢብ ነው ጉድ ከሜዳው ነበርን ከብቶችን ስናግድ ላይን ያዝ ሲያደርግ ቀኑ ሲጨላልም እረፍትን ስንሻ እኛም ስንዳከም... ዛሬ ቀኑ ትንሽ አድካሚ ነበር ከተማው ግርግር በዝቶበት ነው የዋለው አዎ ሰሞኑን ምርጫ ያለ ይመስላል ለዛም ነው መሰለኝ ህዝብ ቆጠራው እንዲህ የተጠጧጧፈው። ወይ ደሞ የበጀት ድጎማ ሊደረግ ይሆናል። ከተማዋ ገና እየበለፀገች ያለች ከመሆኗ የተነሳ... ውኋ መበራት የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች ብቻ ብዙ ነገሮች አልተሟሉም። ታዲያ ህዝብ ቆጠራው ወይ ከምርጫ ጋር አሊያም ከበጀት ጋር... ዋሽንቴን ሳጫውት እርሱም ሲያዜምልን ከወደ ሰማያት መላዕክት መጡብን ታላቅ ብርሐን አየን ጭንቅ ጥብብ አለን እጅግ ግራ ገባን አዎን በጣም ፈራን። ማደሪያ የሌለን ነንና እረኞች ተኝተን ማናድር ብለን ስለ በጎች ማረፊያ የለንም ምን እንበላቸው እያል ስንማከር ልናሳውቃቸው... አትፍሩ አደንግጡ ስሙ'ንጂ ምስራች ሴቲትቱ በግርግም ወንድ ልጅ ወልዳለች የተወለደው ልጅ በዚህም በማታ መድሀኒት ነው እርሱ ክርስቶስም ጌታ። የከተማው ተወላጅ በሙሉ ከያለበት ተሰብስቦ እዚ መቷል ሁሉም በትውልድ ቀዬው መቆጠር አለበትና። እናማ ዘመድ ያለው ወደ አዝማድ ገንዘብ ያለውና የቀናው ደሞ ወደ እንግዶች ማረፊያ ይጣደፋል። ግማሹ ወደ ህዝብ ቆጠራ ጣቢያዎች ሌላው ወደ ማረፊያው ከቅርብ ከተሞች የመጡትም ወደ መንደራቸው አንዳንዱ ደሞ አግር ለማፍታታት... መላዕክት በደስታ የዘመሩለትን ልናየው ልንዳሰው በጉዞ ፈጠንን ሕፃኑን በጨርቅ እንደጠቀለሉት ከበረቱ ግርጌ ከጫፍ አስቀመጡት። ለካስ ነገሩ እንዲህ ነው... እንቆጠር ብለው ወደዚች ከተማ የመጡ ባልና ሚስት እድል አልሰመር ብሏቸው ለጎናቸው ማረፊያ ባጡ ጊዜ እያይዬ ቤት ጀርባ ወደነበረው ወደዚህ በረት ይመጣሉ... እንደው ድካማቸውን የሚያስታግሱበት ስፍራን ለማግኘት ከነበራቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ... በዚህ መሐል ነበር ሴቲቱ በምጥ የተጣደፈችው... በለስ ሲቀናት ወንድ ልጅ.... ሳለች አጠገቡ የወለደች እናት አባት ተብዬውም በተሰየመበት ኮከብ የመራቸው ሰባ ሰገኖቹ የሩቅ ሐገር ጠቢብ ለኛ እንግዶቹ ለተወለደው ልጅ ስጦታን ሰውለት ይሔ ሲያስገርመን ወድቀው ሰገዱለት... አለቀ! "9፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። 10፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ 11፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። 12፤ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። 13፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። 14፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ። 15፤ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።" ሉቃ. 2:9-15
Показати все...
እንቅልፍ አልወስድህ ብሎኝ ነበር! እንጃ ብቻ ንጋትን አጥብቄ ሰለሻትኩ መሰለኝ ለሊቱም አልገፋ አለኝ! ሲነጋ ገና የሚሉት የክርስቶስ መወለድን መክንያት በማድረግ የሚከበር ክብረ በዓል ይከበራል። እኔ ግን ከበዓሉ ይልቅ ላያቸው የጓጓሁት ሶስት ትእይንቶችን ነው። 1ኛ በዓሉን አስመልክቶ የተገዙልኝን አዳዲስ ልብሶች ለብሼ አዲሱን ጫማዬን ተጫምቼ ባለ ቀይ ቀለሙን ኮፊያ ራሴ ለይ ደፍቼ... (ይህን ሁሉ ሲነጋ አይደለም የምከውነው እ... እ መኔ ሞኝ ነውና ሁሉንም ነገር ልብስብስ አድርጌ ነበር የተኛሁት ያው አዲስ ጫማም አይደል የተጫመትኩት አልጋ ስለማያቆሽሽ ነዋ...) በቃ ዝንጥ ማለትን ሲሆን.... 2ኛው ደሞ (ዘንድሮ ኑሮ ተወደደ ስትል እማዬን ሰምቻት ነበረ ይህ ማለት ደሞ ያ የለመድነው በግ ቀርቶ በዓሉን በዶሮ ልናሳልፍ ነው! ሲ-ያ-ሳ-ዝ-ን) እናም ዶሮዋ ስትታረድ በፈላ ውኋ ሻወር ስትወስድ ሽሮ እየቀቧት ማሳጅ ሲያደርጓት አንገቷ ለይ እስከርቭ ሸብ ሲደረግ... እናም ብዙ ምራቅ ሚያስውጡ ትእይንቶችን መመልከት! 3ኛው እና ዋነኛው (ወነኛው አልኩ እንዴ 3ተኛው እና የመጨረሻው... አሁን በምን ሒሳብ ነው ዋነኛ ሐሳብ 3ተኛ ለይ የሚመጣው... ባለ 3 ነጥብ መግለጫ ለይ ነው'ኮ ይህ የተለመደው ታዲያስ እኔ ይሔን ከወዴት አመጣው!) ከበዓሉ ጋር በየት በኩል እንደሚገናኙ አላውቅም ነገር ግን ከሕፃን እስከ አዋቂ ሴት ወንድ ሳይል ሰፋ ወዳለ ሜዳ በመጓዝ የሚመለከቱት የገና ጨወታ ነው። ከላይ ቀጥ ብሎ ወደ ስሩ የተጣመመ ዱላ አንግበው ደቦልቦል ያለ ነገር ያሳድዱበታል ፈርጠም ያሉ ወጣቶች እና ጎልማሶች... ይህን ጫወታ ከበዓሉ ጋር ለማያያዝ ይህን መላ መት ፈለሰፍኩ... ያች ድቡልቡል ነገር በኤደን ገነት የነበረችው እፀ-በለስ ስትሆን ሴጣን ስትወክል... ከሴቲቱ የሚወለድ ራስህን ይቀጠቅጣል። (ቆይ ግን ለምንድነው የምቀባጥረው።) ወደ ሐሳቤ ልመለስ... የጨለመ ሁሉ ይነጋልና እኔም ከእንቅልፌ ነቃው ስነቃ ግን ከወደ እግሬ ቀለል አለኝ... በፍጥነት በርድ ልብሱን ገልጬ ስመለከት... ልብ ምቴ... ወይኔ ጉዴ... በዛሬው ቀን... አይሆንም.... ብርክ ያዘኝ... (በጣም ትገርማላቹ ግን እንዴት አልጋ ለይ ሽንቱን... በላቹ ታስባላቹ ነውር አይደል'ንዴ ሆ ጉድ እኮ ነው! እኔ እዚህ ቆሜ በማነበው አነርሱ ቀድመው ይገምታሉ። ህም አ-ጃ-ኢ-ብ... እናማ ማታ ተጫምቼው የነበረው አዲሱ ጫማዬ ከእግሬ ወልቆ (ተሰርቆ ይሁን እንዴ 🤔) ፈጥኜ ካልጋው ልወርድ ስል... ፊት ለፊቴ... ይህማ የማም ስራ መሆን አለበት። ሳሎን ደረስኩ ጌታ ሆይ... ዶሮው ለቁርስ ደርሶ... ወይኔ ጉጉቴ... ሶስተኛው ዋነኛ ሊሆን ነው መሰለኝ... ና ለቁርስ ታደም ቢሉኝም ብሶቴ ይወጣልኝ ዘንድ ወደ ጓሮ አለፍኩ። አንዲት ብጫኪ የወደቀች ወረቀት አገኘሁና... 😭😭የመጨረሻው ፀሎት😢😢 "የዋህ ነበርኩ ሲበዛ ምስኪን ስሔድ ስራመድ እንኳ ቀና የማልል በቃ ሁል ጊዜ ያጎነበስኩ..." "አቤቱ አምላኬ ሆይ 🙏 ጊዜዬ እይኸው እንደምታየው ገና ነው! አንድ ፍሬ ልጅ ምንም የማላውቅ እኮ ነኝ! ☹️ አቤቱ አምላኬ ሆይ 🙏 እባክህን እቺ ፅዋ ትለፈኝ 😳 ምክንያቱም ልቀበላት ዝግጁ አይደለሁምና! ግን... አምላኬ ሆይ 🙏 ፍቃድህ ከሆነ... እባክህን የኔን ፀሎት የኔን ፍቃድ ስማልኝ! 😔 ደሞ ያ... 👉 በ300 ብር የሸጠኝንም ገበሬ... ያው የብር ሱስ 🤑 ተጠናውቶት እንጂ በጣም ይወደኝ 😍 እንደነበረ አብሬው በቆየሁበት ሶስት (3) አመታት ውስጥ አረጋግጫለው! ቂምም አልቋጠርኩበትም! እንደውም ይቅር ብዬዋለው!" ...እያለ ፀሎቱን 🙏 ወደ አምላኩ ማድረሱን ቀጥሏል! ይህ ልጅ የስጋ አባት ባይኖረውም እንደ አባት የሚሆንለት... ደሞ እያበላች እያጠጣች ያሳደገች እናት ነበረችው! በጥንቃቄ በጥበብ እና በሞገስ ስላሳደጉት ሰውነቱ ያማረ የደለደለ ለአይንም ማራኪ ነበር! "አቤቱ አምላኬ ሆይ 🙏 መንፈሴ ተረብሽዋል ከፊት ለፊቴ የተጋረጠብኝ ሞት እጅጉን አስፈርቶኛል! አምላኬ ሆይ 🙏 እንዲያው እቺን የሞት ድግስ በተአምርህ አሳልፈህ ይህን በዓል አስቤው እውል ዝንድ ብትረዳኝ..😔 ከማገኘው ከበቆሎው ከስንዴው ከጥራጥሬው... መስዋቴን አቀርብልሃለው! 🙁" ... ገና ፀሎቱን ሳይጨርሰው አንገቱ... "አምላክ ሆይ 🙏 በቃ አንተም ጨከንክ... 😢 በቃ ከሆነ አይቀር... 😭 ነብሴን እንካ ተቀበለኝ... ነብሴን አ-ደ-ራ...😭 ደሞ... የሚያደርጉትን በርግጥ ያውቁታል... ቢሆንም ግን ምህረትህን አብዛላቸው! 😞 እህ... ህ... ህ... ህ..." ... ብሎ የመጨረሻውን የጣር ድምፅ አሰምቶ 'ዝም' 🤬 አለ! ሁለቱን እግሮቹን በግራ እግር ተረግጦ... ክንፎቹን ደሞ በቀኝ እግር ተረግጦ... አንገቱ በቢላዋ... ከዛም በላዩ ላይ ሳፋ ተደፋበት!... 🐓🐓🐓🐣🐔🐔🐔 እናማ ያንን ምስኪን በዚ መልክ ነበር ወላጆችህ የነጠቁን... ምን ይሔ ብቻ... እንባ በተቀላቀለ ደምፅ ያመለጡኝን ትዕይንቶች ይዘረግፍልኝ ጀመር ያ ጫጩት አውራ ዶሮ እኔም የሚነግረኝን በዛች ብጫቂ ወረቀት እፅፍለት ነበር። ምን ይሔ ብቻ እናታችን የነገውን ትውልድ በብዛት አስቀጥላለው በሚል እሳቤ ብስንት ጣርና ምጥ የወለደቻቸውን የዛሬ ፍሬዎች የነገ አበቦችን... እንባው ንግግሩን ገታው... እንደምንም ራሱን አረጋጋና... ነብስ የማጥፋት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ጄኖሳይድ ጭምር ነው የተደረገብን.... እዚ ጋር ወደራሴ መለስ አልኩና የተለምዶው ታህሳስ 29 በደረሰ ቁጥር ምንድነው ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው የሆነ በዓል? የሆነ ዝግጅት? የሆነ ዝክር? ምብልና መጠጥ? ወይስ የአንድዬ ውልደቱን? አዎ በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ቃልም እግዚአብሔር ነበር!... ፍፁም አምላክነቱ ዘላለም የነበረ ያለና የሚኖር ነው። ታዲያ ውልደቱ የፍፁም ሰውነቱ... አመተ ፍዳ አመተ አለምን ወደ አመተ ምህረት... ለካስ በውልደቱ ብዙ ስጦታ አጊንተናል... አበቃ!
Показати все...
ሲገባኝ.... እኔና ወንድሜ ወንድም ጋሼ ስማኝማ የሆነ ነገር ሁልጊዜ ያሳስበኛል... ገና ከማለቴ አዎ ፊትህ ያስታውቃል... አለኝ። እህ ብዬ በውስጤ ያለውን አካፍለው ጀመር... የሰላምን ዋጋ የምናውቀው ግን ሰላምን ስናጣ ነው አይደል? ሁል ጊዜ የሚገርመኝ ቤ/ክ ስለ ሰላም የመንፀልየው ችግር ሲገጥመን መሆኑ... የችግር ቀን የሰላም እጦት ጊዜ የመከራ ወቅት ፀሎታችን አይጣለው ነው። ፀሎታችን ተሰምቶ መልስ ያገኘን ጊዜ መከራው ሲያልፍ ግን... ሌላ ታሪክ ውስጥ እንገባለን። አሁንስ ምርር ያለኝ ነገር ቢኖር... ምን አለበት ግን ፀሎታችን መልስ ሲያገኝ ማመስገን ብናውቅ የመከራም ጊዜ ሁሌ በፊታችን አለና ከቀኖች አልፈን ዘመኑን ለመዋጀት... ከቀን አጀንዳ ወተን የዘመን አጀንዳ ከራስ ከግል ከሆነ ነገር ተላቀን ስለ ሌሎች ስለ ሐገርና መንግስት... እንደውም አንዱ ቅርብ ምን አለኝ መሰለህ... እኛ ማለት እኮ የማንፀልይለትን መንግስት የመንወቅስ ያልመከርነውን የምንቆጣ... (ኦ ኦ ይህች ነገር ትቅርብኝ መሰለኝ! የወንድሜ መልስ ናት!) ብቻ ምን ልበልህ ስለ ፀሎት ያለን ግንዛቤ... ስለ ምን እንደምንፀልይ እንዴት እንደምንፀልይ... በሚገባ ተረድቼሐለው አለኝ ካደመጠኝ በሗላ። መፃፍ ቅዱሴን ሳጠና ሁለት ክፍሎች ቀልቤን ሳቡት... "ሁል ጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።" ኤፌ. 5:20 "ሳታቋርጡ ጸልዩ በሁሉ አመስግኑ ይህ የእግ/ር ፍቃድ በክርስቶስ እየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" 1ኛ ተሰ. 5:17-18 እነዚህ ሁለት ሐሳቦች አንብቤ ሳበቃ ደሞ... "እንግዲህ እግ/ርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር #ልመናና_ፀሎት_ምልጃም_ምስጋናም ስለ #ሰዎች_ሁሉ ስለ #ነገስታትና ስለ #መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ #ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ #ሊድኑ እውነቱንም ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግር/ር በመድጏኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።" 1ኛ ጢሞ. 2:1-4 በውኑ የኔ ያንተ ፀሎት ይህን ይመስላልን???
Показати все...
"ሳስበው ገረመኝ 😳" እኔና ወንድሜ ከፊቴ የሚነበብ ነገር ቢኖር አንድ ነገር ብቻ ነው እሱም መገረም... ይህን አይቶ ይመስለኛል ወንድም ጋሼ ወደኔ ጠጋ አለና የተገረምክ ትመስላለህ በሰላም... ጥያቄ ይሁን አስተያየት በውል ባለየውም ያስገረመኝን ነገር እንዲህ እያልኩ ነገርኩት "ምን መሰለህ ከሞት በኋላ የሚጠብቀኝን ነገር ሳስብ እኮ ነው... በስመ አብ አስበህዋል ግን በወርቅ የተሰራ መንገድ... በእጅ ያለተነካው ክርስቶስ ሊያዘጋጅልን የሄደው መኖሪያችን... እነ ሙሴ እነ ዳዊት እነ ጳውሎስን ስናገኝ... የመላዕክት ዝማሬ... የሃያ አራቱ ሽማግሌዎች... አረ ስንቱ... ታዲያ ይሄ አያስገርምም...!?" ከማለቴ አዎ አያስገርምም አለኝ ወንድሜ ወንድሜ በጤናው አይደለም መሰለኝ አሁን ይሔ እንዴት አያስገርምም!? ቆይ ከዚህ በላይስ ምን የሚያስገርም ነገር አለ!? እርሱ ግን እንዲህ አለኝ ክርስቶስ በዲያብሎስ ሲፈተን... ለኔ ከሰገድክልኝ ይህን ሁሉ... ሲለው ጊዜ ምን ነበር መልሱ... አየህ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር አንድ ብቻ ነው... ቤተ መፃህፍትን ቤተ መፃፍ ያስባለው ጣራና ግርግዳ አይምሰለህ ወይም በውስጡ ተቀምጠው ሚያነቡ ሰዎች... በውስጡ ያሉት መፃህፍት እንጂ... ከቤቱ ይልቅ ትኩረት ሚሻው መፃፉ ነው። መንግስተ ሰማያትንም.... ያስባለለው... ትኩረት የሚገባውም... ብቻ ክርስቶስ ይኑር እንጂ የትስ ቢሆን... (መዝሙር 139:8) ከሱ ጋር እንሁን እንጂ የትም ቢወስደንስ.... አረ እንደውም ዮሐንስ ምን አለ!? 1ኛ ዮሐ. 3:2 "ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለን እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።" ዘውትር ይህን ቃል አስብ አለኝ ወንድም ገሼ... ከክርስቶስ ዳግም ምፃት በፊት ከልብህ ያወጣኸውን ከፊትህ የደበዘዘውን የመስቀሉን ምስል አጥራ የፍርድ ቀን ዘምሬልህ (ለዛውም ማ-ራ-ና-ታ አሜን ጌታ እየሱስ ሆይ ቶሎ ና። ና ጌታ ጌታ ሆይ ና ጌታ ጌታ ሆይ ጊዜህ አልደረሰም ወይ!?) አገልግዬህ ፌሎ ሁላ እንዳልተካፈልኩ... አይ አኔ አላወኩህም እንዳትባል ሲርበኝ መች አበላኸኝ ሲጠማኝ መች አጠጣኸኝ ስታረዝስ መች አለበስከኝ... እንዳትባል (ክርስትናህ የመድረክ አገልግሎት ሳይሆን አንድ ያለህ ምትክ የሌለው ማንም ተክቶህ ሊኖርልህ የማይችለው ህ-ይ-ወ-ት-ህ ይሁን!) 1ኛ ዮሐ. 3:3 "በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹህ እነደ ሆነ ራሱን ያነጻል።" ሁልጊዜ ናፍቆትህ ረሐብህ መሻትህና ተስፋህ ክርስቶስ ይሁን... ታዲያ ተቀምጦ በመጠበቅ ሳይሆን በቃልና በፀሎት (መቼስ ንስሃ መግባት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ይመስል ዘንድ ከፀሎት ርዕሳችን ውስጥ አውጥተነዋል!) ወደ ክርስቶስ ፍፁም ሙላት በማደግ (በኑሮህ እና በህይወትህ)... እርሱ ንጹህ እነደሆነ ልክ እንደዛ ራስህን እያነፃህ ይሁን። "የሚመጣ በደመና የሚከብር በዚች ምድር የሚነግስ እ-የ-ሱ-ስ"
Показати все...
በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል❗️ ⚡️ዛሬ በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ⚡️የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠውም ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡ ⚡️በዚህም በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡ ⚡️በቴክኒክ ችግር የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስም ርብርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ⚡️በዚህም በቀጣይ አንድ ሰዓት ውስጥ ደረጃ በደረጃ ኃይል የማገናኘት ስራዎች የሚሰሩ መሆኑን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 🦁• @ThinkAbyssinia •🦁
Показати все...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል ! የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዎስ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የህግ ማስከበርና የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል ብለዋል። ተማሪዎች ይህንን ተገንዝበው ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አሳስበዋል። ምንጭ:- ትምህርት ሚኒስቴር @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Показати все...
✍✍✍ጉተማ ቡድሀ✍✍✍✍ በ6ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ቡድሀ እንዲ ይለናል(practical guide to true way of living✍ ✍መጥፎ አጋጣሚ ሁሉ ከምስራቅ ወይም ከምዕራብ ይመጣል ብለ አታስብ!ይልቅስ የመጥፎ ነገር መነሻ ሁሉ አይምሮ ነው!✍✍✍✍ ✍እናም ከምታየው👍 አለም👍 እራስህን ጋርደህ ውስጣዊ አእምሮህን ነፃ ብትለቀው ድርጊት ሁሉ የሞኝ ስራ ይሆናል🙊🙊🙊 ✍✍ከቡድሀ ሀይማኖት ውጪ የጉተማ በድሀን ፍልስፍና ጠቃሚ ያልነውን ሀሳቦች በቅርብ ቀን ይዘን እንቀርባለን!✍✍✍✍✍✍ ✍✍coming soon✍✍✍✍✍ @praisebyart1 @praisebyart1
Показати все...
✍✍✍መንፈሳዊ ቤት✍✍✍ ✍ part one 1 ✍የእግ/ር ቤተመቅደስ ሚባለው እግ/ር የሚገኝበት ስፍራ ማለት ነው። በብሉ ኪዳን ጊዜ የእየሩሳሌም ሰዎች ለእግ/ር ስግደት የሚያቀርቡበት ልዩ ቤት ነው። ያኔ የሚሰራው ቤት ሰዋዊ ቢሆንም የሚፈፀመው ስርአት ሰዋዊ አደለም፣ባህላዊም አለም። ቤተ መቅደሱ ውስጥ የእግ/ር መገኘት ስለሚኖር ቅድስና የተሞላበት ስርአት ብቻ ነበር ሚከናወንበት። ✍✍ቅድስ ቤት✍✍1ዜና22-8 *ያኔ ለእግ/ር ቤት ሲሰራ ሰው ስለፈለገና ስለፈቀደ ሳይሆን እግ/ር ራሱ የተቀደሰና-የተለየ ሕይወት ሲያገኝ ነው። ✍ዳዊት ለእግ/ር ቤት ለመስራት አልተመረጠም። ምክንያቱም የደም ሰው-የጦርነት ሰው ነበር። ስለዚህ ዳዊት ለእግ/ር ቤት ቢሰራ የረከሰ እንጂ ቅድስ ሊሆን አይችልም ቤቱን ሚሰራው ከረከሰ መቅደሱም የረከሰ ነው የእግ/ር መገኝት ወፍ.......... ✍ የዳዊት ልጅ ሰለሞን ግን ዳዊት ያላገኘውን እድል አጊንቶ ነበር። ከዳዊት በተሻለም እግ/ር ሰለሞንን መርጦት ነበር።ለእግ/ር የተገኘ። ✍ቤተ መቅደስ በባህሪው መቀደስ ይፈልጋል-(ማር.11-15)ጌታ ጅራፍ ያነሳበትን ክፍል ማየት ይቻላል። ✍ ✍ካህን...✍✍ ካህን ማለት በሰውና በእግ/ር መካከል ሆኖ ሰውና እግ/ር የሚያገናኝ ነው። (ደላላ በሉት😁) በብሉ ኪዳንም ለክህነት ስራ የተመረጠው የሌዊ ዘር ብቻ ነበር። ከሱ ዘር ውጪ በዛ አካባቢ ሌላ ሰው አደለም መቅደስ ውስጥ በዛ አካባቢ ውርውር ሲል ከታየ ይገደል ነበር🙈🙊🙊🙊 ✍ሌዊ ዘር-ሀጢያት ያስተሰርያል-ከሱ ዘር ውጪ ወፍ ሀጢያት ሊያስተሰርይ ሚችል አልነበረም። የሌዊ ዘር ያው እንደኛው ስጋ ለባሽ ስለሆኑ መቅደስ ውስጥ ረክሰው ከተገኙ እሬሳቸው በገመድ እየተጎተተ ሚወጣበት አጋጣሚ ነበር። 🙊🙊🙊🙊🙊🙊🙊 በሙሴ ስርአት መንፈሳዊ ቤት እና ካህን ይሄን ይመስል ነበር። ሁሉንም ያላሳተፈ እና ሀጢያተኛና ፃድቅ ብሎ አንድን ከአንድ የለያየ ነበር። ክርስቶስ ግን በአዲሱ ኪዳን ቤተ መቅደሱንም-ካህኑንም ለውጦታል ይሔስ የተለወጠው ቤትና ካህን ሁሉንም አሳታፊ ሆኑዋል?? ✍ በአዲስ ኪዳን መንፈሳዊ ቤት በክፍል 2ምናየው ይሆናል:: ** ✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ አዘጋጅ=ዳጊ ማን @praisebyart1 @praisebyart1
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.