cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ትኩስ መረጃ Tekus Mereja

Breaking News Join Us

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
500
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በሃይማኖት ሽፋን ግጭት በመቀስቀስ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ! ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ከቀብር ስፍራ ጋር በተያያዘ በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰውን ግጭት መነሻ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቋል፡፡ የጋራ ግብረ ኃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ የተለያዩ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ብሔርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ አጀንዳ በማሰራጨት ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ ለአመታት በገነባው ጠንካራ የሆነ የጋራ እሴት ይህ ሙከራ የከሸፈባቸው ኃይሎች፣ቀሪውን የሃይማኖት ካርድ በመምዘዝ በተለያዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ መጠራጠርና ጥላቻ እንዲፈጠር ብሎም ወደ ግጭት እንዲያመራ በተለያዩ መንገዶች ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡፡ በጎንደር የተከሰተው ግጭት በተለያዩ ዕምነቶች መካከል ግጭት በመቀስቀስ ወደ ሃገራዊ ቀውስ እንዲያመራ የሚደረገው ሴራ አካል መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በዚህ ድርጊት በተሳተፉ አካላት ላይ ተገቢ እርምጃ መወሰደ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡ በዚህ መሰረት በጎንደር በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ሁከቱን ለማባባስ የተንቀሳቀሱ 280 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አመልክቷል፡፡ እንደ መግለጫው፤ በጎንደር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎችም በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር የሚጋብዙ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎችም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም የእምነት ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱ ሃገራዊ ቅርጽ እንዲኖረው ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡ የፌደራል የደህንትና የጸጥታ መዋቅር በድርጊቱ በሚሳተፉት ላይ ብቻ ሳይሆን ከኋላ በመሆን በሚዘውሩት ላይ በቂ መረጃና ማስረጃ ያለው በመሆኑ ተከታታይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቀው መግለጫው፤ ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋ በየትኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚቀሰቅሱ፤ በተለይም ደግሞ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ሃሰተኛና የጥላቻ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን የጠቆመው መግለጫው፤ በዚህ ህግወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም በጥብቅ አሳስቧል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለዓመታት የገነቡት በአብሮነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እኩይ ዓላማ ባነገቡ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሃይሎች እኩይ ሴራ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት በሚፈጥሩት የግጭት አጀንዳ አይሸረሸርም ያለው መግለጫው፤ ህብረተሰቡ ለዘመናት ባዳበራቸው መልካም እሴቶች እንደዚህ አይነት የፈተና ወቅቶችን በውይይትና በሰከነ መንፈስ በመፍታት እንደሚያስመሰክር የጋራ ግብረ ኃይሉ እምነት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ዛሬም ኢትዮጵያን ሌላ የግጭት አጀንዳ በመስጠት ለማተራመስ ሙከራ ቢደረግም በደኀንነትና በጸጥታ መዋቅሩ ከፍተኛ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፤ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ችግሩ እንዳይስፋፋ ያደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክቷል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት የሸቀጥ አቅርቦት እና ዋጋ ንርትን የሚያረጋጋ ጊዜያዊ ቦርድ እንዲያቋቁም ጠይቋል። ማኅበሩን ጥያቄውን ያቀረበው፣ በዋጋ ግሽበት መዋቅራዊ ተግዳሮቶች እና የፖሊሲ አማራጮች ላይ ለ6 ወራት ያስጠናውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። ቦርዱ ቢቋቋም፣ የአገራዊ ምርትና የገቢ ንግድ አቅርቦት ሚዛንን ማስጠበቅ፣ የዋጋ ግሽበትን የሚቀንስ ግብ ማስቀመጥ፣ በግሽበቱ የሚጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን መለየት እና በተለያዩ ኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል ቅንጅት ለመፍጠር ይችላል ተብሏል። Via Wazema @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሀይማኖትን ሽፋን አድርገው የሚነሱ ግጭቶች በቂ ትኩረት ይሻሉ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አሰሰበ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ከሰሞኑ ጎንደር ላይ የተፈጠረውን ያወገዘ ሲሆን በዚው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል:: ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል። @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የአማራ ክልል መንግሥት ሽብር በሚፈጠሩ አካላት የማያዳግም እርምጃ እወስዳለው አለ! የአማራ ክልል መንግሥት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።የአማራ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፤ እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ እኩይ አካላትን እንደማይታገሱ ተናግረዋል። ርዕሠ መሥተዳድሩ "ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡ይህ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ያሉት ርዕሠ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም አሳስበዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ! ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ። 1 ሺህ 443ኛውን የኢድ በአልና ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ፤ ያልተረጋገጠ ወሬ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት አሳዛኝ ድርጊት መፈጸሙ የሚወገዝ እና የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል እንደሆነ ገልጸዋል። ለህዝቡ ቅርብ የሆኑና ተሰሚነት ያላቸው አካላት ግጭት አባባሽ መልእክቶችን በማሰራጨት እልቂት እንዲፈጠር እየሠሩ እንደሚገኙ አመልክተው፤ ህዝቡ የተነገረው ሁሉ አምኖ መቀበል ብቻ ሳይሆን መርምሮ ማረጋገጥ እንዳለበት አስረድተዋል። ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ አካላት እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሀላፊነታቸውን መወጣት ላይ ክፍተት እንዳሉባቸው ገልፀው፤ ችግሩ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አፅንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኮሚቴ በማቋቋም እና ቦታው ድረስ በማቅናት ችግሩን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
የወልዲያ ከተማ አስተዳዳር ‹‹ሰርጎ ገቦች››ን ለመለየት የነዋሪዎችን መታወቂያ ሊቀይር ነው! የወልዲያ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ‹‹ሰርጎ ገቦችን›› ለመለየት እንዲቻል፣ የከተማዋ ነዋሪዎችን በሙሉ መታወቂያ ሊቀር እንደሆነ አስታወቀ፡፡በከተማው ውስጥ ካለው ሁኔታ አንፃር እየተለዩ የሚታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ፣ አዲስ መታወቂያ የሚወስዱ ሰዎች ያላቸውን መታወቂያ ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት መረጃ ጋር እንደሚያመሳክር ገልጿል፡፡ ለወራት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ከቆየች በኋላ በታኅሳስ ወር ላይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆነችው ወልዲያ፣ ‹‹ሰርጎ ገቦች›› የቀድሞውን መታወቂያ መያዛቸውን ለሪፖርተር የተናገሩት የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዳዊት መሰለ (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት የከተማው አስተደዳር የከተማዋን ነዋሪዎች መታወቂያ ለመቀየር ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ እንደ ዳዊት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ከዚህ ቀደም መታወቂያ ሲሰጥ የነበረው መረጃዎችን በመዝገብ ላይ በመጻፍ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በቀበሌዎች መካከል የሚጣራበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረጉ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከአንድ በላይ መታወቂያ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ‹‹ሰርጎ ገብ›› የተባሉትን ሰዎች ማንነት አብራርተው ባይገልጹም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ እንዲይዙ የሚያደርጉ የቀበሌ አመራሮች አሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አሁን መታወቂያ የማደስ አገልግሎት እንዲቆም መደረጉን አክለዋል፡፡ Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስድስት ቅርንጫፎች ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ! በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ስድስት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓም በቁጥጥር ስር ውለው መታሰራቸው ታወቀ። ቅርንጫፍ መስሪያቤቶቹ በአዳማ፣ነቀምት፣ ጅማ፣ጊምቢ፣በደሌ፣መቱ ሲሆኑ ሁሉም መታሸጋቸው ታውቋል።የቅርንጫፍ ሠራተኞቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሪፖርተር ያረጋገጠ ቢሆንም የታሰሩትን ሠራተኞች ብዛትና የታሰሩበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥቧል። Via Reporter @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ሚያዚያ 21 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያዋ የሚገኙ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል። በዚህም መሰረት፦ - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሀያ ሁለት ወይም ዘሪሁን ህንፃ አካባቢ ዝግ ይደረጋል፣ - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ኦሎምፒያ፤ - ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ፤ - ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና ከሜኪሲኮ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚጓዙ ሜክሲኮ አደባባይ፤ - ከጌጃ ሰፈርና ከጎማ ቁጠባ በሰንጋ ተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ የቀድሞው ደሳለኝ ሆቴል መስቀለኛ ላይ፤ - ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ለሚጓዙ ጎማ ቁጠባ ላይ እና ከሜክሲኮ ወደ ፖስታ ቤት ለሚሄዱ ሚትሮሎጂ አካባቢ እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር አካባቢ፤ - ከተክለኃይማኖት በጎላ ሚካኤል ለሚመጡ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ እና ከተክለኃይማኖት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ለሚመጡ ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከተክለ ኃይማኖት በሶማሌ ተራ ወደ ባንኮ ዲሮማ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል። - ከቀድሞ አትክልት ተራ አካባቢ በአሮጌው ፖስታ ቤት ወደ ቸርችል ጎዳና የሚወስደው መንገድ አሮጌው ፖስታ ቤት፤ - ከደጎል አደባባይ ወደ እሪ በከንቱ ደጎል አደባባይ ላይ እና ከአራት ኪሎ በፓርላማ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ሸራተን ሆቴል መውረጃ ላይ፤ - ከአራት ኪሎ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ የሚዘጋ ሲሆን ከካዛንቺስ ሼል ወደ ፍል ውሀና ወደ ባምቢስ የሚወስዱት መንገዶች ካዛንስ ሼል ላይ ከቀኑ7፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል። በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ህብረተሰቡ ፕሮግራሙ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል። @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ሊካሄድ ነው! የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሊካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በሰጡት መግለጫ ÷ የአፍሪካ የክትባት ሣምንትን ምክንያት በማድረግ የሚከናወነው የክትባት ዘመቻው በተለይም በጸጥታ ችግር ምክንያት ክትባት ባልተሰጠባቸው ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡ የክትባት ሣምንቱ ማህበረሰቡ በክትባት ጠቀሜታ ላይ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ለማድረግና የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ የክትባት ዘመቻው ዓላማ በወረርሽኝ ደረጃ ሊነሱ ይችላሉ ተብሎ የተሰጉትን ኩፍኝ፣ ፖሊዮ እና ቢጫ ወባን ለመከላከል መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደረጄ፤ ይህም ተፈናቃይ ዜጎች ባሉባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡ ከወረርሽኝ መከላከል ባለፈ ለሕጻናት የአንጀት ተወሃሲያን መከላከያ፣ ቫይታሚን ኤ እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን በመለየት ሕክምና እንደሚሰጥ መናገራቸዉን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል። @YeneTube @FikerAssefa
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.