uk
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Відкрити в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 19 946 підписників, посідаючи 1 156 місце в категорії Медицина та 1 680 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 19 946 підписників.

За останніми даними від 28 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -539, а за останні 24 години на -5, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.64%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 7.06% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 5 115 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 408 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 9.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 29 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Медицина.

19 946
Підписники
-524 години
-1197 днів
-53930 день
Архів дописів
በአሁኑ ቅፅበት ላይ መኖርን ተለማመድ ============================ የውስጣችንን ሰላም ከሚወስኑ ነገሮች ዋነኛው ”በአሁን ቅፅበት ላይ ምን ያህል እየኖርን ነው?” የሚለው ነው። ትናንት ምንም ይከሰት ምን፤ አምና ምንም ይፈጠር ምን፤ ነገሮች ቢሆኑም ባይሆኑም ያለኸው የአሁኑ ቅፅበት ላይ ነው። ያለ ክርክር ብዙዎቻችን አብዛኛው ጊዜአችንን ስለብዙ ነገር በመጨነቅ ማሣለፍን ተክነንበታል። ያለፋ ችግሮችና ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች አሁናችንን እንዲሸፍኑ እንፈቅድላቸዋለን። በጣም ስለምንፈቅድላቸው መጨረሻ ላይ ተጨንቀን፣አዝነን፣ ተስፋ ቆርጠን ራሳችንን እናገኘዋለን። በግልባጩ ደግሞ ደስታችንንና ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች ለሌላ ቀን እናስተላልፋቸዋለን። “የሆነ ቀን” ከዛሬ የተሻለ ይሆናል ብለን ራሣችንን እንደልላለን። ያ “የሆነ ቀን” ሲመጣ ግን አሁንም ወደፊት ”ሌላ ቀን” እንድጠብቅ ያደርገናል። ስለዚህ “የሆነ ቀን” የተባለው ቀን መቼም አይመጣም። ጆን ሌነን እንዳለው “ሕይወት ማለት ሌሎች እቅዶችን በማውጣት ተወጥረህ እያለ የሚከሰተው ነገር ነው።” እቅዶችን በማውጣት ላይ ተወጥረን እያለን ልጆቻችን እያደጉ ነው። የምንወዳቸው ሰዎች ወይ ሀገር ቀይረዋል ወይ ሞተዋል፤ የሰውነታችን ቅርፅ እየተለወጠ ነው፤ ህልማችን ተንሸራቶ እየወደቀ ነው . . . በአጭሩ ሕይወት እያመለጠችን ነው። ብዙ ሰዎች ሕይወትን የሚኖሩት ልክ ለዝግጅት እንደሚደረግ ልምምድ ነው። ህይወት ልምምድ ሳትሆን የዋንጫ ጨዋታ ናት፡፡ ማንም ሰው ነገ በሕይወት ለመኖሩ ማረጋገጫ የለውም። ያለን ጊዜ አሁን ብቻ ነው። ልንቆጣጠረው የምንችለውም አሁናችንን ብቻ ነው። የአሁኑ ቅፅበት ላይ ትኩረት ስናደርግ ፍርሀትን ከአዕምሯችን እናስወጣዋለን። ፍርሀት ማለት ምናልባት ወደፊት ሊፈጠር ስለሚችል ነገር መስጋት ነው። በቂ ገንዘብ ላይኖረን ይችላል፤ ልጆቻችን የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ እያረጀን ነው፤ ልንሞት እንችላለን . . . የመሳሰሉት። ፍርሀትን ለመፋለም ምርጡ መንገድ ትኩረታችንን አሁን ላይ ማድረግ ነው። ማርክ ትዌይን “በሕይወቴ ስለ ብዙ ነገሮች ተጨንቄ አውቃለው። ግን የተወሰኑት ብቻ ናቸው የእውነት የተከሰቱት።” ብሏል። በተሻለ መንገድ ልገልፀው የምችል አይመስለኝም። ትኩረትህን እዚህና አሁን ላይ አድርግ። እንደዚህ ማድረግህ ብዙ ወለድ ይከፍልሀል። ከ"ቀላሉን ነገር አታካብድ" መፅሀፍ የተወሰደ

#የደም_ግፊት_መድሃኒት_ጀምሮ_ማቋረጥ አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት ታማሚዎች መድሃኒት ከጤና ባለሙያ ከታዘዘላቸው በኋላ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ መድሃኒት ያቋርጣሉ :: ይህ ደሞ ለከፋ የጤና እክል ሲጋለጡ እንመለከታለን:: 🔹የደም ግፊት መድሃኒት ጀምሮ ማቋረጥ እንዴት ይከሰታል? ▪️ከግንዛቤ እጥረት፦ለበሽታው በቂ የሆነ ግንዛቤ ካለመኖር የተነሳ መድሃኒትን ይቋረጣል፣ ▪️በመድሃኒቱ የጎንዮሽ ችግር ፣ ▪️ወደ ተለያዩ የእምነት ተቋማት መሄድ፣ ▪️አሁን ተሽሎኛል ብሎ ማሰብ፣ ▪️ተገቢውን የህክምና ክትትል ባለማድረግ፣ ▪️በተለያዩ ምክንያቶች የመድሃኒት አቅርቦት አለማግኘት፣ 🔹መድሃኒት ከተጀመረ በኋላ ማቋረጥ ይቻላል? አንድ ጊዜ መድሃኒት ሃኪም ካዘዘ በኋላ ሃኪሙ እራሱ ይቁም ካላለ በስጠቀር ማቋረጥ ፈፅሞ የተከለከለ ነው 🔸መድሃኒት በድንገት ባቋርጥ ምን ችግር ይመጣል? ያለሃኪም ትዕዛዝ መዳኒት የሚያቋርጡ ታካሚዎች እስከ ሞት የሚዳርግ ችግር ውስጥ ይገባሉ፤ ከነዚህም መካከል ▪️ደም በጭንቅላት ውስጥ የመፍሰስ አደጋ ▪️የልብ ድካም ▪️የኩላሊት ደም ቧንቧ መጥበብ ▪️የአይን ላይ ደም ስሮች መወፈር እና ለ ድንገተኛ ዓይነስውርነት መጋለጥ ▶️ድንገተኛ ሞት 🔹የደም ግፊትን በሽታን ያለ መድሃኒት መቆጣጠር ይቻላል? የደም ግፊት በሽታ ከምንቆጣጠርበት ዘዴዎች ውስጥ አንዱ መድሃኒትን ሳይጠቀሙ በህይወት ስልት(life style)ወይም የአኗኗር ዘይቤያችንን በመቀየር ነው:: 🔹የደም ግፊትን ያለመድሃኒት መቆጣጠር ያለበት ማነው? በሃኪም ትዕዛዝ መሰረት ግፊቱ የመዳኒት መውሰድ ደረጃ ላይ ያልደረሰ ሰው ብቻ 🔹ምን አይነት የአኗኗር ዘይቤ ልከተል? ▪️ውፍረት መቀነስ ▪️የአመጋገብ ስርዓትን መቀየር (አትክልት እና ፍራፍሬዎችን መመገብ ቅባት የበዛበት ምግብ ማስወገድ) ▪️ጨው ያልበዛበት ምግብ መመገብ ▪️አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ▪️አልኮልን አዘውትሮ አለመጠቀም እና ለቀን ከተፈቀደው መጠን አለማለፍ ▪️ሲጋራ አለማጨስ:- ይህ ግፊትን ባይቀንስም ነገር ግን ከበሽታው ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የልብ ህመም ይቀንሳል። 🔥ስለዚህ የደም ግፊትን መድሃኒት ማቋረጥ ለተለያዩ የጤና እክሎች ስለሚዳርግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ከደም ግፊት በሽታ ጋር ተያያዥ ጥያቄ ካላችሁ ፃፉልን!! የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

ዶክተር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ ነኝ ቪማክስ የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ብዙዎቻቹ በ inbox የምትጠይቁኝ ነገር ነው vimax ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መዳኒት ትንሽ ነገር ልበል እንደምታውቁት በማህበራዊ ሚድያ ብስፋት የሚያስተዋዉቁት ነገር ነው። ከማህበራዊ ሚድያ ደሞ እውነተኛ ነገር ማግኘት አዳጋች ነገር ነው እናም ዝም ብላቹ ከፊስቡክ ወይም ከቴሌግራም የሚለቀቁትን ማስታወቅያዎች አምናቹ ምንም አይነት መዳኒት ባትገዙ ጥሩ ነው በጣም አደገኛ ሊሆንባቹ ይችላል በተለይ የዉስጥ ደዌ ችግሮች ያሉባቹ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል የህክምና ባለሞያዎን ማመከር አለባቹ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች የብልት አልቆም ማለት የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የቁመት ማጠር እና/ የመቀጠን ችግር ቶሎ የመጨረስ ችግር በአጠቃላይ ከለይ የጠቀስኳቸው የስንፍፈተ ወሲብ ችግሮች እንዳለባቹ ካረጋገጣቹ ችግሩን በህክምና ሞክራቹ ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች አሉ ግን ኬት ማግኘት እንዳለባቹና የትኞቹ ናቸው ትክክለኛና ፈዋሽ የሆኑትን ማወቅ ይኖርባቹኃል ቢያንስ ቢያንስ ስለ መዳኒቶቹ Google ላይ ማጣራት እና Original ምን አይነት እንደሆነ መለየት ትችላላቹ የጎንዮሽ ጉዳቱቹ ምንምን እንደሆኑ Google ይነግራቹኃል በህክምና ሞክራቹ ወይም ሀኪም ማማከር ፈርታቹ መዳኒት ለመጠቀም የምትፈልጉ በጥያቅያቹ መሰረት ስለ Vimax የተወሰነ ነገር ልበላቹ እና ኬት እንደምታገኙ አድራሻ ለምትጠይቁኝ ሰጣቹኃለው Vimax Originally የካናዳ ምርት ሲሆን ጥቅሞቹ 1 የብልት አልቆም ማለት ቆሞ ያለመቆየት ቶሎ መልፈስፈስ ችር ላለበት 2 የቁመት እና የዉፍርት ችግር 3 ቶሎ የመጨርስ ችገር/የዘር ፈሳሽ የማምለጥ vimax አወሳሰድ/አጠቃቀም እንዷ ብልቃጥ 60capsule/60እንክብል ነው ምቲዘው ባለ 30capsule የምቲዝም አለች ግን እኔ የማወራው ስለ original ነው አወሳሰዱ በቀን አንድ አንድ ቢሆን ይመከራል በቀን ሁለት ሁለትም መውስድ ይቻላል። Side Effect/የጎንዮሽ ጉዳት እነሱ እንደሚሉት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ይበሉ እንጅ እኔ ከማቃቸው ተጠቃሚዎች እንደተረዳሁት የጨጓራ በሽታ ያለባቸው ላይ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ነግር ግን ጎን ለጎን የጨጓራ መዳኒት እየወሰዱ የሚጨርሱም አሉ ከዚ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት ጎዳት የለዉም አንድ አንዶች ላይ አላርጂክ ከሞሆን በስተቀር። የሚከለክላቸው ነገሮች መዳኒቱን መጠቀም ከጀመራቹ መዉሰድ/መጠቀም የሌለባቹህ ነገሮች .አልኮል/አረቄ ነገሮች ናቸው። መዳኒቶቹን መግዛት የምትፈልጉ እኔ ትክክለኛው Original Vimax አስመጪዎችን ስልካቸውን ልሰጣቹህ እችላለው መዳኒቱ ሀገር ዉስጥ እንዲሸጥ ገና ፍቃድ ስላላገኘ በዚም ምክንያት ዋጋው በጣም የተጋነነ ነው በዛ ላይ አስመጪዎቹ እየሸጡ ከተያዙ ወይም እጃቸው ላይ ከተገኘ የሚቀጡ ነው የሚሆኑት እናም ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚሸጡት ነገር ግን እኔ በትክክል ስለማዉቃቸው ችግር አይኖርም መዳኒቱም ፍቃድ ሊያገኝ በሂደት ላይም ስለሆን ብዙም አያሳስብም። በተጨማሪም የኔ ምክር ነው ጫት እየቃማቹ መዳኒቱን ባትወስዱ/ባትጠቀሙ ጥሩ ነው ቢያንስ መዳኒቱን እስክጨርሱ ጫቱን ብተዉት እላለው ስለ ጫት የጎንዮሽ ጉዳቶች በቅርቡ ፅፍላቹኃለው። አመሰግናለው የነሱን አድራሻ ለምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ inbox @Dr_Sofonias

የደም ማነስ 8 ምልክቶች የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው፣ የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር(ክንታሮት፣ ቁስለት፣ የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር
የደም ማነስ 8 ምልክቶች የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው፣ የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር(ክንታሮት፣ ቁስለት፣ የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር የመሳሰሉት) አስተዋጽዎ ያደርጋሉ። ያለብዎት የደም ማነስ ቀለል ያለ ከሆነ ወይም ከብዙ ጊዜ በፊት ከተከሰተ ምንም አይነት ምልክት ላናይ እንችላለን። ለማንኛውም አይነት የደም ማነስ የጋራ የሆኑ ምልክቶች እነሆ፦ 1. የትኩረት ማጣት 2. የቆዳ መገርጣት 3. የእንቅልፍ ማጣት 4. የማዞር ስሜት 5. የድካም ስሜት እና ጉልበት ማጣት 6. ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት በተለይ እንቅስቃሴ ስናደርግ 7. የትንፋሽ ማጠር እና ራስ ምታት 8. የእግር ጡንቻ መሸማቀቅ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

ስለ ዛር እና ቆሌ የተደረገ ጥናት ==================== "በኢትዮጲያውን አይሁዳውያን ከአእምሮ ህመም ጋር ተያይዘው ደጋግመው ከሚጠቀሱ መንፈሶች ውስጥ ዛር እና ቆሌ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ የጥናቱ ተሳታፊዎች ዛርና ቆሌ ያውና አንድ አይነት እንደሆኑ ሲገልጹ ሌሎች ግን እንደሚለያዩ በሚከተለው መልኩ ገልፀዋል፦ ቆሌ ሁሉም ሰው ላይ የሚገኝ ሲሆን እንደውም ቆሌ የሌለው(?የራቀው) ሰው ቁም ነገር አይኖረውም።"... the person who has no Kole has no substance." ቆሌ የራሱ ባህርያት ያሉት ሲሆን መፍትሄዎች ይሰጠናል። ዛር በድንገት ሳይጠበቅ የሚመጣ ሲሆን ግለሰቡን ያዞረዋል፤ ያስጓራዋል። አንዳንድ ተሳታፊዎች ቆሌ ድባቴ(Depression)፤ ዛር ደግሞ ሽቅለት (Mania) እንደሚያመጡ ገልጸዋል። አጥኚዎቹም ዛር (?ቀልቡ) ፈረንጅ እንደማይወድ ግምት ወስደዋል። "...one aspect of the Zar as a presenting problem is the message that a 'Ferengi' (Non-Ethiopian) is not welcome." የተሰወሰኑ ሰዎች ደግሞ ቆሌና ዛር የአእምሮ ህመም እንደሆኑ እንደሚያስቡ ተናግረዋል። በዚህ ጥናት ደረጃ ስለ ዛርና ቆሌ የተለያየ አተያይ ለምን እንደተፈጠረ ለመረዳት የሚያስችል በቂ እውቀት የለንም። ምናልባት ባህሉን በትክክል አልተረጎምነው ይሆናል። ወይም በማህበረሰቡ ውስጥም ስለ ዛርና ቆሌ ያለው አተያይ የተለያየ ይሆናል። ጥናቱ እንደሚያሳየው ኢትዮጲያውያን የስሜት መረበሽ አጋጥሟቸው ሲመጡ ባህላቸውና ስለ አእምሮ ህመምና ስለ ስሜት መረበሽ ያላቸውን አመለካከት ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።" ሀሳቦቹ ሙሉ በሙሉ የተወሰዱት ከ Transcultural psychiatry March 1999 Manifestations of Emotional Distress Among Ethiopian Immigrants in Israel, R. Youngman et al ነው። ምስጋና፦በየእለቱ ከተለመዱ የሀገራችን ቋንቋዎች(አንዳንዴም ካልተለመዱ አካባቢያዊ ዘዬዎች) ወደ እንግሊዘኛ 'ህክምናኛ' እየተረጎሙ ለሚሰሩ የአእምሮ ህክምና እና የስነ ልቦና ባለሞያዎች መልካም ጊዜ

ቡና መጠጣት ባህላችን ነው፡፡ ከዚህም አንፃር ስለ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞቹ እናወራለን፡፡ በምድራችን ላይ ከሚሸጡ የትኛውም አይነት መጠጦች ሁሉ በጣም ታዋቂ እና ተወዳጅ ነው ቡና! በአመት በአለም ላይ ከ400 ቢሊየን ስኒ በላይ ይጠጣል፡፡ ግን ቡና ለጤና ይጠቅማል? 1.ቡና ለጉበታችን - በኢጣልያውያን ተመራማሪዎች የተሰራ ጥናት እንዳረጋገጠው ከሆነ ቡና መጠጣት በጉበት ካንሰር ከመያዝ ይከላከልልናል፡፡ ጉበታችን በሂፐታይተስ ወይም በቅባት መብዛት እና በመሳሰሉት በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል፡፡ እነዚህም በሽታዎች በጉበታችን ላይ ጠባሳ እየፈጠሩ በመሄድ የጉበት ካንሰርን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ቡና መጠጣት ግን በጉበታችን ላይ ጠባሳ የመፈጥር እድልን ይቀንሳል፡፡ 2.ቡና እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች - ቡና በውስጡ ለጤናችን የሚጠቅሙን ብዙ ነገሮችን ይዟል፡፡ ለምሳሌ ቫይታሚን ቢ2 (ሪቦፍላቪን) ፣ ቫይታሚን ቢ5፣ ማግኒዚይም እና ፖታሲየም የመሳሰሉትን ለጤና የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮች በአንድ ስኒ ትኩስ ቡና ውስጥ እናገኛለን፡፡ እንዲሁም ቡና አንታይኦክሲዳንት በውስጡ ስለያዘ ጤናችን ለመጠበቅ ይረዳናል፡፡ 3.ቡና ያነቃቃል - ቡና በውስጡ ካፊን የተባለው ንጥረ ነገር ስላለው ከድካም ያነቃቃል እንዲሁም ሀይል ይሰጠናል፡፡ በዚህ ጊዜም አእምሯችን ስለሚነቃቃ የማስታወስ ችሎታችን ይጨምራል፤ የደስታ ስሜት ይሰማናል፡፡ በተጨማሪም ቡና የድብርት ስሜትን ያጠፋል፡፡ 4.ቡና እና አልዛይመር - አልዛይመር በአብዛኛው ከ65 አመት በላይ የሆናቸውን ሰዎች የሚያጠቃ የመርሳት በሽታ ነው፡፡ እድሚያችን እየገፋ በሚሄድበት ጊዜ አልዛይመር እንዳይዘን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ጤናማ አመጋገብን መከተል አለብን፡፡ በተጨማሪም ግን ቡና መጠጣት በአልዛይመር በሽታ የመያዝ እድልን በ65% ዝቅ ያደርገዋል፡፡ 5.የስኳር በሽታን በ50 % ይቀንሳል - ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዘወትር ቡና መጠጣት በስኳር የመያዝ እድልን እጅግ ይቀንሰዋል፡፡ ነገር ግን የተረጋገጠ የስኳር በሽታ ላለባችው የስኳር መጠንን መቀነሱ በተለያ ነገሮች ሊለያይ ይችላል፡፡ 6.በቆዳ እና ጡት ካንሰር የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል - የጡት ካንሰር እና ቡና መጠጣት በቀጥታ ባይገናኝም፤ ቡና መጠጣት በተለይ ላረጠች ሴት በጡት ካንሰር የመየያዝ እድልን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 7.የሰው ልጅ ፀጉር እድገትን ይጨምራል - ቡና መጠጣት የፀጉር ስሮችን በማነቃቃት ለፀጉር እድገት ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የጸጉር መበጣጠስን ይቀንሳል፡፡ 8.የፋይበር አወሳሰዳችንን ይጨምራል - ቡና ከሌሎች መጠጦች የተሸለ የፋይበር መጠኑ ከፍ ያለ ነው፡፡ ፋይበር ደግሞ ለአንጀት ጤንነት፣ ለድርቀት እንዲሁም ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ 9.ድብርትን/ የሚደብት ስሜትን/ ይቀንሳል - ቡና ውስጥ ያለው ካፊን የተባለው ንጥረ ነገር ድብርትን ይቀንሳል፤ በተጨማሪም በድብርት የመያዝ እድልን ይቀንሳል ብለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 10. ኢንፍላሜሽንን ይቀንሳል - ቡና የሰውነት ብግነትን ለመቀነስ የሚረዳ ንጥረ-ነግር በውስጡ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ 11.በፓርኪንሰንስ በሽታ የመያዝ ዕድላችንን ይቀንሳል - አንድ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በቀን ከ2-4 ሲኒ ቡና መጠጣት የፓርኪንሰን በሽታ ምልክቶችን ችጅጉን ቀንሶ ተገኝቷል፡፡ 12.ቡና እድሜን ይጨምራል - በእንግሊዝ አገር የሚገኝ አንድ የጥናት አሳታሚ ተቋም አዲስ የወጣ ጥናት መሰረት አድርጎ እንደጠቆመው በቀን ውስጥ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት የጠጪውን እድሜ ላይ ለውጥ ያመጣል ይላል 13.አዘውትሮ ቡና መጠጣት ከልብ ህመም ይታደጋል ተባለ - በኮሪያ የተደረገ ጥናት እንደሚሳየው በየዕለቱ የተወሰነ ስኒ ቡና አዘውትሮ መጠጣት ከደም ስር መዘጋት ችግር እንደሚታደግና በሰውነት ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በአግባቡ እንዲከናወን በማድረግ ለልብ ህመም ከመጋለጥ እንደሚታደግ አሳይቷል፡፡

👉ወሲብ ለጤና የሚሰጣቸው 11 ጥቅሞች!!! ========================== 👉Dr. Sofonias እባላለው ማንኛውም ጤና ነክ ጥያቄዎችን በቴሌግራም ማቅረብ ትችላላቹ ሊንኩን መጨረሻ ላይ አስቀምጫለው ወሲብ ከስሜት አልፎ ለጤንነም ጠቀሜታ አለው። የጭንቀት መጠንን ከመቀነስ ጨምሮ የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል። ግንኙነት ከፍቅር ጓደኛችን ጋር ያለንን ቅርርብ ይጨምራል። የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን በማጠናከርም ሆነ የተሻለ እንቅልፍ ለመተኛት ይረዳል። ወሲብ ለጤና የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል፦ … 👉1) የብርድ ተጋላጭነትን ይቀንሳል። የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል!!! ወሲብ ማዘውተር የምንታመምበትን ግዜ ይቀንሳል። ግንኙነት የሚያዘወትሩ ሰዎችን ግንኙነት ከማያደርጉ ሰዎች ጋር ያነጻጸረ ጥናት ይህንኑ ይናገራል። ግንኙነት ሰውነትን ባክቴሪያ፣ ቫይረሶች እና ሌሎች ጀርሞችን የሚከላከልበትን አቅም እንዲያዳብር ያስችለዋል። በግንኙነት ብቻ እራሳችንን ከበሽታ መጠበቅ ባንችልም ጤነኛ የሆነ የወሲብ ህይወት አለን ማለት የተሻለ የበሽታ መከላከል አቅም አለን ማለት ነው። ከጤነኛ ግንኙነትም በተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት እንዲሁም ተገቢውን ክትባቶች መውሰድ ጤንነታችን በዘላቂ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መንገዶች ናቸው። … 👉2) የግንኙነት ፍላጎት መዳከምን ለማስተካከል!!! የግንኙነት ፍላጎት መዳከምን ለመቅረፍ ግንኙነት ማድረግ ይመከራል። ግንኙነት ማድረግ ስሜት እንዲጨምር ያደርጋል። በሴቶች ላይ በግንኙነት ግዜ የሚፈጠር የህመም ስሜት እና የብልት መድረቅን ለመቀነስ ግንኙነት ማዘውተር ይመከራል። ግንኙነት የሴት ብልት እንዳይደርቅ ያደርቃል። ወደ ብልት አካሎች ደም ዝውውር እንዲፈጠር በማድረግ ተለጣጭነትን ይጨምራል። እነዚህ ነገሮች ለግንኙነት ስሜት መዳከም መፍትሄ ይሆናሉ። … 👉3) የሴቶችን ሽንት መቆጣጠር ችሎታ ይጨምራል!!! 30 ፐርሰንት የሚሆኑ ሴቶች በህወት ዘመናቸው የሽንት መቆጣጠር ችግር ያጋጥማቸዋል። በግንኙነት ግዜ የስሜት ጣሪያ መድረስ የሴትን የዳሌ ጡንቻዎች ያጠነክራል። የነዚህ ጡንቻዎች መጠንከር የሽንት መቆጣጠር ብቃትን ይጨምራል። … 👉4) የደም ግፊት ለመቀነስ!!! የደም ግፊት ህመም ካለባቸው በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች አንዱ ነዎት? ግንኙነት የደም ግፊት መጠንዎን ለመቀነስ ይረዳል። ብዙ ጥናቶች በወሲብ እና በወረደ ሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መሃከል ግንኙነት እንዳለ ይናገራሉ። ሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ማለት በደም ግፊት ንባብ ላይ የመጀመሪያው ቁጥር ነው። ግንኙነት ከአመጋገብ ለውጥ፣ አካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ጭንቀት መቀነሻ መንገዶች በተጨማሪ ለደግ ግፊት የሚረዳ መፍትሄ ነው። ነገር ግን ግንኙነት የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች ተተኪ ሊሆን አይችልም። … 👉5) እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ይቆጠራል!!! እንደ የተኛውም አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሲብ ካሎሪ ያቃጥላል። ተቀምጦ ቲቪ ማየት በደቂቃ 1 ካሎሪ ብቻ እንዲቃጠል ያደርጋል። ወሲብ የልብ ትርታን በመጨመር እንዲሁም የተለያዩ ጡንቻዎችን በማሰራት በደቂቃ 5 ደቂቃ እንዲቃጠል ያደርጋል። ግንኙነትን ማዘውተር ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተተኪ አይሆንም። ነገር ግን እንደ ጭማሪ እንቅስቃሴ ጥሩ ነው። … 👉6) የልብ ድካም ተጋላጭነትን ይቀንሳል!!! ጤነኛ ልብ ከፈለጉ ግንኙነትን ማዘውተር ጥሩ ነው። ወሲብ እንደ ኤስትሮጅን እና ቴስቶስተሮን ያሉ ሆርሞኖች መጠናቸው እንዲስተካከል ይረዳል። የነዚህ ሆርሞኖች በሰውነት ውስጥ መዛባት ለልብ ህመም እንዲሁም ለአጥንት በሽታ ተጋላጭ ያደርጋል። የልብ ጤናን ለመጠበቅ ግንኙነት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አንድ ጥናት እንደሚናገረው በሳምንት ሁለት ግዜ ግንኙነት የሚያደርጉ ወንዶች በልብ ህመም የመሞት እድላቸው በግማሽ የቀነሰ ነው። … 👉7) ህመም ለመቀነስ!!! ግንኙነት የህመም ስሜትን ለመቀነስ ይረዳል። ከጓደኛ የሚደረግ ግንኙነትም ሆነ ግላዊ ወሲብ የህመም ማስተናገድ ችሎታችንን ይጨምራል። የስሜት ጣሪያ መድረስ የህመም ስሜት የሚያዳፍኑ ሆርሞኖች እንዲለቀቁ ያደርጋል። አንዳንድ ሴቶች ግላዊ ወሲብ የወር አበባ ህመም እና ራስምታት ለመቀነስ እንደሚረዳ ይናገራሉ። … 👉8) የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል!!! አንድ ጥናት እንደሚናገረው ዘወትር የዘር ፈሳሽ የሚፈሳቸው ወንዶች የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነታቸው ዝቅ ያለ ነው። የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሌሎች መንስኤዎች ቢኖሩም ይህ መንስኤ ተጋላጭነትን የሚቀንሱበት አንዱ ቀላል መንገድ ነው። … 👉9) እንቅልፍ ለማሻሻል!!! ግንኙነት የተሻለ እንቅልፍ እንዲተኙ ያግዛል። ስሜት ጣሪያ መድረስ ፕሮላክቲን የተባለ እንቅልፍ የሚያግዝ ሆርሞን እንዲለቀቅ ያደርጋል። ፕሮላክቲን የመረጋጋት እና የእንቅልፍ ስሜትን ይጨምራል። ከግንኙነት በኋላ ለእንቅልፍ ቅርብ የምንሆንበት ምክንያት ይህ ነው። … 👉10) ጭንቀትን ለመቀነስ!!! ግንኙነት የጭንቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል። ንክኪ፣ መተቃቀፍ፣ መቀራረብ እንዲሁም ግንኙነት የደስታ ሆርሞኖች በሰውነታችን እንዲለቀቁ ያደርጋሉ። የቅርርብ ስሜት የጭንቀት ስሜትን የሚቀንስ ለጤና ተስማሚ የሆነ ድርጊት ነው። … 👉11) ካሎሪ ለማቃጠል!!! ግንኙነትን ካሎሪ ከሚቀንሱባቸው መንገዶች አንዱ ያድርጉ። አንድ ጥናት እንደሚናገረው ግንኙነት በወጣቶች ላይ በግማሽ ሰአት ውስጥ 108 ካሎሪ እንዲያቃጥሉ ይረዳል። … ከጓደኛዎ ጋር ሞክረው ለውጡን ይመልከቱ!! ማንኛውም ጤና ነክ ጥያቄዎችን በቴሌግራም ማቅረብ ትችላላቹ ሊንኩን በመንካት ያገኙኛል 👉 @DrSofonias መረጃውንም ያጋሩ!!! 👉Share

ግለ ወሲ (ሴጋ)ጉዳቱ እና መፍትሄው ====================== 👉 ክፍል አንድ(1) 👉Dr. Sofonias እባላለው ከናንተው በቀረበልኝ ጥያቄ መሠረት ለዛሬ ይሄንን ይዤላቹህ መጥቻለው በጥሞና አንብቡት እና ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉት። 👉ግለወሲብ ምንድነው? ግለወሲብ ጤናማ ካልሆኑ የወሲብ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚመደብና እራስን በራስ የማርካት እንቅስቃሴ ነው ። ግለወሲብ በኔ እምነት በጊዜአዊነት ስሜትን ከማርካት ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም ። ቢኖርውም ከጉዳቱ አይበልጥም።ለዚህም ነው ለወጣቱ ማህበረሰብ ጉዳቱን የበለጠ ለማስገንዘብ የፈለኩት ። አንድ ነገር ለማየት ይሞከራል ፤ ይደገማል ፤ይደጋገማል የተደጋገመ ነገር ደግሞ ልምድ ይሆናል ፤ ልምድ ደግሞ ወደ ሱስ ያመራል እናም ከዛ ሱስ ውስጥ ለመውጣት እጅግ በጣም ከባድ ነው ። ከወሲብ ጋር የተያያዙ የተለያዪ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 95% የሚሆነው የአለም ወጣት በግለወሲብ ሱስ የተያዘ ነው ። ያ ማለት አንድ አምራች ዜጋ የምትፈልግ ሀገር ምን ያህል በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ በግለወሲብ ምክኒያት እንደምትጎዳ ለመረዳት አዳጋች አይሆነም። 👉የሚከተሉት የግለወሲብ ጉዳቶች ናቸው :- 1.የጸጉር መሳሳት 2.እውነተኛ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ችግር 3.ቶሎ መሰልቸት, የሰውነት መዛል 4.አይነ ስውርነት 5.ጭንቀት 6.የወሲብ አካላት ለወሲብ መነሳሳት አለመቻል 7.ያለምንም እርካታ ቶሎ መጨረስ 8.ራስ ምታት 9.የእርካታ ማጣት 10.ወደ ተቃራኒ ፆታ የሚወስደው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፍላጎት ማጣት 11.ለግብረ-ሰዶማዊነት ፍላጎት መጨመር 12.የማስታወስወስ ብቃት ማነስ 13.የታችኛው የጀርባ ህመም 14.ድካም 15.ጭንቀት 16.የስሜት መለዋወጥ 17.የእንቅልፍ ማጣት 18.ትኩረትን መሰብሰብ አለመቻል 19.የብቸኝነትና, እራስን የማግለል ስሜት 20.ግለ ወሲብ ከተደረገ በኋላ የበደለኛነት ስሜት መሠማት ለምን አደረኩት የሚል ቁጭት 21.የወሲብ መነሳሳት ስሜት ማነስ 22.የራስን ሕይወት የማጥፋት ሐሳብ እና ዝንባሌ እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩት የግለወሲብ ጉዳቶች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ቶሎ ሲታዩ በሌሎች ላይ ላይ ደግሞ ዘግይተው ሊታዩ ይችላሉ ። 👉በክፍል ሁለት ደግሞ ግለወሲብን እንዴት ማቆም እንችላለን የሚለውን እናያለን ። ይህ መረጃ እህት ወንድሞቻቸሁ ጋር እንዲደርስ ሼር አድርጉ ። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

ግለ ወሲ (ሴጋ)ጉዳቱ እና መፍትሄው ====================== 👉 ክፍል አንድ(1) 👉Dr. Sofonias እባላለው ከናንተው በቀረበልኝ ጥያቄ መሠረት ለዛሬ ይሄንን ይዤላቹህ መጥቻለው በጥሞና አንብቡት እና ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉት። 👉ግለወሲብ ምንድነው? ግለወሲብ ጤናማ ካልሆኑ የወሲብ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚመደብና እራስን በራስ የማርካት እንቅስቃሴ ነው ። ግለወሲብ በኔ እምነት በጊዜአዊነት ስሜትን ከማርካት ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም ። ቢኖርውም ከጉዳቱ አይበልጥም።ለዚህም ነው ለወጣቱ ማህበረሰብ ጉዳቱን የበለጠ ለማስገንዘብ የፈለኩት ። አንድ ነገር ለማየት ይሞከራል ፤ ይደገማል ፤ይደጋገማል የተደጋገመ ነገር ደግሞ ልምድ ይሆናል ፤ ልምድ ደግሞ ወደ ሱስ ያመራል እናም ከዛ ሱስ ውስጥ ለመውጣት እጅግ በጣም ከባድ ነው ። ከወሲብ ጋር የተያያዙ የተለያዪ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 95% የሚሆነው የአለም ወጣት በግለወሲብ ሱስ የተያዘ ነው ። ያ ማለት አንድ አምራች ዜጋ የምትፈልግ ሀገር ምን ያህል በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ በግለወሲብ ምክኒያት እንደምትጎዳ ለመረዳት አዳጋች አይሆነም። 👉የሚከተሉት የግለወሲብ ጉዳቶች ናቸው :- 1.የጸጉር መሳሳት 2.እውነተኛ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ችግር 3.ቶሎ መሰልቸት, የሰውነት መዛል 4.አይነ ስውርነት 5.ጭንቀት 6.የወሲብ አካላት ለወሲብ መነሳሳት አለመቻል 7.ያለምንም እርካታ ቶሎ መጨረስ 8.ራስ ምታት 9.የእርካታ ማጣት 10.ወደ ተቃራኒ ፆታ የሚወስደው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፍላጎት ማጣት 11.ለግብረ-ሰዶማዊነት ፍላጎት መጨመር 12.የማስታወስወስ ብቃት ማነስ 13.የታችኛው የጀርባ ህመም 14.ድካም 15.ጭንቀት 16.የስሜት መለዋወጥ 17.የእንቅልፍ ማጣት 18.ትኩረትን መሰብሰብ አለመቻል 19.የብቸኝነትና, እራስን የማግለል ስሜት 20.ግለ ወሲብ ከተደረገ በኋላ የበደለኛነት ስሜት መሠማት ለምን አደረኩት የሚል ቁጭት 21.የወሲብ መነሳሳት ስሜት ማነስ 22.የራስን ሕይወት የማጥፋት ሐሳብ እና ዝንባሌ እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩት የግለወሲብ ጉዳቶች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ቶሎ ሲታዩ በሌሎች ላይ ላይ ደግሞ ዘግይተው ሊታዩ ይችላሉ ። 👉በክፍል ሁለት ደግሞ ግለወሲብን እንዴት ማቆም እንችላለን የሚለውን እናያለን ። ይህ መረጃ እህት ወንድሞቻቸሁ ጋር እንዲደርስ ሼር አድርጉ ። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ @DrSofonias

ስንፈተ ወሲብ ወጣት ወንዶች ላይ ===================== የብልት አለመቆም ከ10 እስከ 20 ከመቶ ወንዶች ላይ የሚያጋጥም ክስተት ነው። ድንገት ሲከሰት ድንጋጤና ሀፍረት ይፈጥራል። በቀጣይ
ስንፈተ ወሲብ ወጣት ወንዶች ላይ ===================== የብልት አለመቆም ከ10 እስከ 20 ከመቶ ወንዶች ላይ የሚያጋጥም ክስተት ነው። ድንገት ሲከሰት ድንጋጤና ሀፍረት ይፈጥራል። በቀጣይ ፆታዊ ግንኙነት ላይም "ዛሬም አልቆም ቢለኝስ?" የሚል ፍርሀት ይኖራል። የብልት አለመቆም መንስኤዎች አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ሊሆኑ ይችላሉ። መቆም ማለት ብልት በደም ሲሞላ የሚከሰት ስለሆነ የደምስር ላይ ተፅእኖ የሚያደርጉ ህመሞች አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል። በተጨማሪም ፕሮስቴት እጢ፣ የነርቭ ህመሞች....ወዘተ ስንፈተ ወሲብ ሊያመጡ ይችላሉ። ከ40 አመት በታች የሆነ ሰው ላይ ሲከሰት ግን አብዛኛው መንስኤው ስነልቦናዊ ነው። በእግሊዘኛ ባለሁለት ስንኝ ግጥም አለች። If your mind is ifffy You can't get a stiffy ውርስ ትርጉም "ጭንቅላትህ የሆነ ነገር ከተጠራጠረ፣ ታች ያለው ነገር ደም ሞልቶ አይወጠረ። 3 ስነ ልቦናዊ የስንፈተ ወሲብ ምክኒያቶች አሉ። ጭንቀት(ፍርሀት)፣ ንዴት እና ፀፀት ናቸው። እነዚህ ስሜቶች አንዳንድ ጊዜ ግልፅ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ግን ከአስተዳደግ ጀምሮ የመጡ ተፅእኖዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም የስነ ልቦና ህክምና በማድረግ ይስተካከላሉ። በማህበራዊ ሚዲያ "ለስንፈተ ወሲብ የሚጠቅሙ ምርቶች" በብዛት ይተዋወቃሉ። ነገር ግን ሙሉለሙሉ ስነልቦናዊ ለሆነ ችግር መድሀኒት መውሰድ አየር ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው። ብዙ ሰዎች ብዙ ብር አውጥተው የሚጠብቁትን ውጤት አላገኙም። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም። ዶክተር ሶፎኒ

ስንፈተ ወሲብ ወጣት ወንዶች ላይ ===================== የብልት አለመቆም ከ10 እስከ 20 ከመቶ ወንዶች ላይ የሚያጋጥም ክስተት ነው። ድንገት ሲከሰት ድንጋጤና ሀፍረት ይፈጥራል። በቀጣይ ፆታዊ ግንኙነት ላይም "ዛሬም አልቆም ቢለኝስ?" የሚል ፍርሀት ይኖራል። የብልት አለመቆም መንስኤዎች አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ሊሆኑ ይችላሉ። መቆም ማለት ብልት በደም ሲሞላ የሚከሰት ስለሆነ የደምስር ላይ ተፅእኖ የሚያደርጉ ህመሞች አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል። በተጨማሪም ፕሮስቴት እጢ፣ የነርቭ ህመሞች....ወዘተ ስንፈተ ወሲብ ሊያመጡ ይችላሉ። ከ40 አመት በታች የሆነ ሰው ላይ ሲከሰት ግን አብዛኛው መንስኤው ስነልቦናዊ ነው። በእግሊዘኛ ባለሁለት ስንኝ ግጥም አለች። If your mind is ifffy You can't get a stiffy ውርስ ትርጉም "ጭንቅላትህ የሆነ ነገር ከተጠራጠረ፣ ታች ያለው ነገር ደም ሞልቶ አይወጠረ። 3 ስነ ልቦናዊ የስንፈተ ወሲብ ምክኒያቶች አሉ። ጭንቀት(ፍርሀት)፣ ንዴት እና ፀፀት ናቸው። እነዚህ ስሜቶች አንዳንድ ጊዜ ግልፅ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ግን ከአስተዳደግ ጀምሮ የመጡ ተፅእኖዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም የስነ ልቦና ህክምና በማድረግ ይስተካከላሉ። በማህበራዊ ሚዲያ "ለስንፈተ ወሲብ የሚጠቅሙ ምርቶች" በብዛት ይተዋወቃሉ። ነገር ግን ሙሉለሙሉ ስነልቦናዊ ለሆነ ችግር መድሀኒት መውሰድ አየር ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው። ብዙ ሰዎች ብዙ ብር አውጥተው የሚጠብቁትን ውጤት አላገኙም። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም። ዶክተር ሶፎኒ

የኩላሊት ጠጠር የመከላከያ መንገዶች የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች በታማሚው ውስጥ በሚገኘው የኩላሊት ጠጠር አይነት (የማዕድን ይዘት) ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። የአመጋገብ ሥልት
የኩላሊት ጠጠር የመከላከያ መንገዶች የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች በታማሚው ውስጥ በሚገኘው የኩላሊት ጠጠር አይነት (የማዕድን ይዘት) ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። የአመጋገብ ሥልት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር (መከማቸት) ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል። የኩላሊት ጠጠርን መፈጠርን መከላከል (መቀነስ) የሚቻለው የአመጋገብ ሥልትን በማስተካከልና በሽንት ውስጥ የሚገኙ ለኩላሊት ጠጠር መከማቸት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የማእድናትን መጠን ለመቀነስ የሚረዱ መድሃኒቶችን በመጠቀም ነው። የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን የአመጋገብ ሥልቶችን መከተል የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ እንደሚረዳ ያመለክታሉ፤ • ሲትሬት (በሎሚና በብርቱካን ውስጥ የሚገኝ አሲድ ነው) ያላቸውን ፈሳሾች በብዛት መጠጣት፣ የፈሳሽ አወሣሠዱም በብዛትና በቀን እስከ ሁለት ሊትር የሽንት መጠን እሰኪደርስ ቢሆን ይመከራል። በዚህ መንገድ የሽንትን ፒኤች 6.5 አካባቢ በማድረግ በተለይ በሽንት አሲድ (ዩሪክ አሲድ) ምክንያት የሚመጡ ጠጠሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል። • የካልሺየም አወሳሰድ መጠንን ከ 1000-1200 ሚግ መጠን በቀን ውስጥ ከፍ ማድረግ • የሶዲየም አወሳሰድ መጠንን ከ 2300 ሚግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ • የቪታሚን ሲ የቀን ፍጆታን ከ 1000 ሚግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ • የእንሥሣት ፕሮቲን (ስጋና ሥብን) ከሁለት ጊዜ በታች ማድረግና መጠኑንም ከ 170-230 ግራም እንዳያልፍ መቆጣጠር እና • ኦክሳሌት የያዙ ምግቦችን (ከላይ ተጠቅሰዋል) መቀነስ ናቸው።

#የስንፈተ_ወሲብ_ህክምና (sexual dysfunction) ► ስንፈተ ወሲብ ማለት በየትኛውም የወሲብ ደረጃ(መሻት፣ ፍላጎት፣ እርካታና ጡዘት) ላይ የሚፈጠር ያልተለመደ ስንፈት/ድክመት ማለት ነው። ►
#የስንፈተ_ወሲብ_ህክምና (sexual dysfunction) ► ስንፈተ ወሲብ ማለት በየትኛውም የወሲብ ደረጃ(መሻት፣ ፍላጎት፣ እርካታና ጡዘት) ላይ የሚፈጠር ያልተለመደ ስንፈት/ድክመት ማለት ነው። ► ስንፈተ ወሲብ የተለያየ መንስኤ ያለው ሲሆን በሴቶችንም በወንዶችንም ሊከሰት ይችላል ► ስንፈተ ወሲብ የስነ አዕምሮ በሽታዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ነው(DSM-5) #የስንፈተ_ወሲብዓ_ይነት 1. የፍላጎት አለመኖር ችግር 2. የስሜት አለመቀስቀስ ችግር ብልት አለመቆም 3. በስሜት ያለመርካት ችግር ቶሎ መርጨት 4. ህመም የመፍራት ችግር በግንኙነት ጊዜ ህመም መኖር፣ ከጡዘት በኋላ ህመም መኖር #የስንፈተ_ወሲብ_መንስኤዎች ንስኤዎች 1.የተለያዩ በሽታዎች ➽ የስኳር በሽታ ➽ ከፍተኛ የደም ግፊት ➽ የልብ በሽታ ➽ የተለያዩ የማህጸንና ተያያዥ በሽታዎች ➽ በሴት ሰውነት ውስጥ የኢስትሮጅን ቅመም መቀነስ ➽ የጭንቅላት ጉዳት ➽ የአፈጣጠር ችግር 2. የስነልቦና ችግሮች ✔️ የጥፋተኝነት ስሜት መሰማት/ፍርሃት ✔️ ጭንቀት ✔️ ንዴት/ብስጭት ✔️ የአካለ ጉዳት መኖር ✔️ በፊት አስገድዶ መደፈር አጋጥሞ ከነበረ 3. የተለያዩ መድኃኒቶች 🖊 ለድባቴ የሚሰጡ መድኃኒቶች 🖊 አልኮል አብዝቶ መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ 4. የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት መሻከር 5. ማረጥ/ እርጅና #ለስንፈተ_የሚደረጉ_ወሲብ_ምርመራዎች ▬ አካላዊ ምርመራ ▬ የደምና የሽንት ምርመራ ▬ የስኳር መጠን ምርመራ ▬ የተለያዩ መሳሪያዎች ምርመራ #ስለ_ስንፈተ_ወሲብ_ምን_እናድርግ? ➽ የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል( የተለያዩ ዕፆችን ከመጠቀም መቆጠብ) ➽ ጭንቀት፣ ብስጭትና ንዴትን ማስወገድ ➽ ያለምንም ፍርሃት ከፍቅር ጓደኛ ጋር በግልፅ መነጋገር ➽የስነ ልቦና ሐኪምን ማማከር ➽የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘውትሮ ማድረግ @DrSofonias