cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኢትዮጵያ የስላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር

ኦሪት ዘጸአት 23 22፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ። @namroud1 @kinfemichael_petros የዮሐንስ ወንጌል 10 30፤ እኔና አብ አንድ ነን። ድንግል አማላጅ ናት ሲባል በተቃውሞ የሚጮህ እሱ ዲያብሎስ ነው።

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
920
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ዛሬ ስለ ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ሰማዕት ዘዕንበለ ደም መታሰብያ የተጻፈ ጽሁፍ ላይ የተመለከትኩትን ጽሁፍ ላጋራችሁ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Показати все...
(የበኲረ አብ መድኃኔ ዓለም ዋሻ ፍጹማን ገዳም ቅዱሳን አባቶች።) ነሐሴ ፳፱ ቀን ፲ ፱፻፺፱ ዓመተ ምሕረት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ። አሜን። ለተወዳጅ ልጆቻቸውና በአለ ቤታቸው ወለተ ሰንበት እንዲኹም የአለቃ አያሌው ተአምሩ ወልደ ጊዮርጊስ ልጆችም ሆነ የልጅ ልጆች። በጣም የአለቃ አያሌው ተአምሩ ከዚህ ዓለም መለየት ማለት ለመላው ኢትዮጵያ ሞት መሆኑ ግልጽ ነው። የሃይማኖት መሪ፤ የማተባችን ተከራካሪ፤ የጾም የጸሎታችን አዘውታሪ፤ የሊቀ ሊቃውንት አስተማሪ፤ የመናፍቃን ተከራካሪ፤ የመጻሕፍት ፈታች የቅኔው ገበሬ፤ የድጓው የመቋሚያው በሬ፤ ወይ አለቃ አያሌው ነሐሴ ፲ ፯ ተቀበረ ዛሬ። የኢትዮጵያ ዐይኗ ወጣ ዛሬ። እዘኑ እንዘን ዋእኔን ምእመናት ምእመናን፤ ጠፍቷል ዐይናችን። እኛ እንደምናውቀው ሁሉ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቈጠረ ጀምረው ሊቁ አለቃ አያሌው ተአምሩ የመጽሐፉ ጌታ አዋጠው ጠቅላላ ለሁሉም ተስማሚ የሆነውን በአስተዳደር ሊቀ ሊቃውንት ተመለሱ ይህ ሕግ የኮተሊክ ሕግ ቢሉ የተነሡ የጥቅም ፈላጊ ምሁር ነኝ የሚሉ የመናፍቅ ተከታይ ወይም ተባባሪ ሕጉን በመጣስ እንቢ ቢሉአቸው ከራሴ ውርድ ነኝ ብለው ደጉ አባታችን አለቃ አያሌው ተአምሩ ወልደ ጊዮርጊስ በመሪነታቸው አውግዘው እንደ አርዮስ ለይተው የፍራት መንፈስ ወይም የአፍቅሮ ንዋይ ሳይከተሉ የሃይማኖት መሪ የሆኑት ለግል አራሳቸውን ሞት ሳይፈሩ ስለ ሃይማኖት ሲዋጉ መቈየታቸው ግልጽ ነው። ለኛ በጹሑፍ ተገልጾልን ስናዝን ቈይተናል። ሞታቸውን በሰማነ ጊዜ ብቻቸውን አይደለም የሞቱ ሀገሪቱ ናት የሞተች። አሁንም ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር ነው። ለወደፊቱ ልጆች ሆይ! እንደሳቸው እንድትሆኑ ነው የምንለው። ኢየኀድግ ወልድ ግብረ አቡሁ። የሆነው ሁኖ ጽፈውልን የነበረው ሦስት ገጽ ለልጆቻቸው ልንል እናንተም እንደሳቸው ያርጋችሁ ከአባታችን ረድኤት በረከት ከመጻፉም ሆነ ከመቋሚያው ወይም ከልብሳቸው በዚህ ገዳም ቋሚ ተጠሪ ነበሩ። ምኞታቸው የነበረው ብዙ ነው። አራቱን ገጽ ምንጣፍ ከአብራኬ ከወጡትም ሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቸ ተቀብዬ እችለውአለሁ ብለው ነበረ። አሁንም እኛ ግን ለዘለዓለም ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለነፍሰ አቡነ ወልደ ጊዮርጊስ ያድኅኖ እመአተ ወልዳ፤ ለወለተ ሰንበት ይዕቀባ እመአተ ወልዳ ሳይባል አይውልም። እኛ ያለንበት ቦታ ሽቅብ ቢአዩት ሰማዩ እሩቅ ነው ቁልቁል ቢአዩት ምድሩ ጥብቅ ነው። ድምፀ አራዊት፥ ግርማ ሌሊት ነው። ክቡር አባታችን ከዋሻው ታቦቱ ሲወጣ ቦታውን ስለሚአቁት በአለፈው ጊዜ ስምንት ሺሕ ብር ሰጥተው መንበር አሠርተው ገብቶአል። አሁንም ምኞታቸው የነበረ ገና ምንጣፍ ሁለተኛ መቋሚያ ጸናጽል ሦስተኛ መጻሕፍት አራተኛ መቀደሻ ልብስ ነበረ። መራኁት ማለት ደወል ነበረ። እራሳቸው ሠርተው አሰማርተው ሃይማኖት መርተው የተራበ አብልተው የተጠማ አጠጥተው ገዳማትን እረድተው ነው የአለፉ። በጣም የማይዘነጋው የአባታችን ለሦስት መቶ ሰባት ዓመት የቆዩት አባት ነሐሴ ፯ ቀን ተገልጸው ወልደ ጊዮርጊስ ብላችሁ ስም ጥሩ ተብሎ ተነግሮናል። ለራሳችሁ እዘኑ እንጂ ለአባታችን አትዘኑ። እናታችንን መጥናችሁ ጠውሩ። ለእኛም በአታችንን እረጅ ስለ አጣነ እዘኑልን እንላለን የበኲረ አብ መድኃኔ ዓለም ዋሻ ፍጹማን ገዳም። ሰላመ እግዚአብሔር ለሁሉም የእግዚአብሔር ጸጋ አይለያችሁ።»
Показати все...
፩. በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሸ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እንቺም በተድላ በደስታዬ ጊዜ ሽልማት ሆንሽኝ፡፡ በኃሤትም ጊዜ ክብ ዘውዴ ሐቲም ቀለበቴ ነሽ፡፡ ፪. በሐሳቤም ሁሉ አንቺን አደንቃለሁ፡፡ እንዲህም እላለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህል ጸጋ ክብር ሰጠ፡፡ ፫. እግዚአብሔር ከሰው ልጅ የማይተባበሩ ሥስት ልደታትን ተወለደ፡፡ እኔም ዐውቄ አደነቅሁ፡፡ ባራተኛው እንጂ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም፡፡ ፬. አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡ እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡ ሔዋንም ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡ ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡ ፭. ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡ ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡ ፮. ክርስቶስ ግን ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡ ፯. ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል፡፡ ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት ኀያልነት፣ አዚዝነት፣ እልልታ፣ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል፡፡ ፰. ይህ ጥበብ ፍልስፍና ዕጹብ ድንቅ ነው፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል ይህም የሥጋዊ ምሥጢር ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡ ይህም ሰው መሆን ሥጋ መልበስ እጅግ ዕፁብ ድንቅ ነው፡፡ ፱. የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡ ፲. የአዳምን መርግመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት እመቤታችን ሆይ የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡ ፲፩. እሳትና ውሀም ባንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ ነው የሚያስራውንም ያንበሳ ደቦል ፀዓዳ በግዕት በክንዷ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ፲፪. ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በበረትም ለድኆች ልጅ የሰማይ ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ፲፫. ዓለምን ሁሉ የመላ አምላክም ከበረት ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎመገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በረት ከጽርሐ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይም ዳርቻ ሰፋ፡፡ ፲፬. ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ፡፡ ይኽውም አደፍ ጉድፍ ሳይኖርበት ንጽሕት የወለደችው ንጹሕ በግ ነው፡፡ በረት ለንጹሑ መሥዋዕት ሽታ መሰብሰቢያ ሆነ፡፡ ፲፭. ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው ወሰነውም፡፡ በረት የተመሰገነ ነው፡፡ የኃያላን ጌታ በውስጡ ተገኝቷልና፡፡
Показати все...
Показати все...
ወደ ደመናው ይግቡ ፣ ራእዩን ይመልከቱ እንደ ሙሴ እና ኤልያስ ፣ ወይም እንደ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ወደ ደመና ለመግባት በድፍረት እና በደስታ እንሩጥ። መለኮታዊውን ራዕይ ለማየት እና በዚያ የከበረ መለወጥ እንድንለወጥ እንደ ጴጥሮስ እንያዝ። ከዓለም ጡረታ እንወጣ ፣ ከምድር ተነስተን ፣ ከሰውነት በላይ ተነስተን ፣ ከፍጡራን ተነጥለን ወደ ፈጣሪ እንመለስ ፣ ጴጥሮስ በደስታ ወደተናገረው - ጌታ ሆይ ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ጴጥሮስ እንደ ተናገርከው እዚህ መሆን መልካም ነው። ከኢየሱስ ጋር መሆን እና እዚህ ለዘላለም መኖር ጥሩ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ከመሆን ፣ እንደ እርሱ ከመመሰልና በብርሃኑ ከመኖር የበለጠ ምን ታላቅ ደስታ ወይም የላቀ ክብር ሊኖረን ይችላል? እኛ እዚህ መሆናችን ጥሩ ነው ስለዚህ እያንዳንዳችን በልቡ እግዚአብሔርን ስላለን ወደ መለኮታዊው አምሳያችን እየተለወጠ ስለሆነ እኛም በደስታ መጮህ አለብን - እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው - እዚህ ሁሉም ነገር በመለኮታዊ አንፀባራቂ ፣ ደስታ ባለበት እና ደስታ እና ደስታ; በልባችን ውስጥ ሰላም ፣ መረጋጋት እና መረጋጋት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለም። እግዚአብሔር በሚታይበት። እዚህ ፣ በልባችን ውስጥ ፣ ክርስቶስ ወደ እርሱ ሲገባ ፣ ዛሬ መዳን ወደዚህ ቤት መጣ እያለ ከአባቱ ጋር መኖሪያውን ይወስዳል። ከክርስቶስ ጋር ፣ ልባችን የዘላለማዊ በረከቱን ሀብት ሁሉ ይቀበላል ፣ እና እዚያ ለእኛ በተከማቹበት ፣ እንደ መጀመሪያዎቹ ፍራፍሬዎች እና መጪው ዓለም ሁሉ በመስታወት ውስጥ ሲንጸባረቅ እናያለን። ከ ቅዱስ አትናቲዎ ስብከት የተወሰደ እንኳን ለ ደብረታቦር በዓል በሠላም አደረሳችሁ•
Показати все...
_______በሉ አባ ይፍቱን_______ _____________________________ ++..**••..++ ይፍቱን አባታችን የዲማው ገበሬ ቅኔው እርሻዎት ነው ድጓው ደሞ በሬ ሞፈርወ አቋቋምነው መዋስት ዝማሬ ብሉይና ሃዲሳት ፀንተው ያጠመዱ በቅዳሴ ዘርተው አረምን ያፀዱ እምነትን ኮትኩተው እውነትን ያጨዱ ታላቅ ልበ ብርሃን ባለ ግርማ ሞገስ የወንጌል አርበኛ ባለ ፍሬአማ ቄስ ይፍቱን አባታችን ባርኩን እንቀደስ ••••• ለሃገሮ ጠበቃ ለ እምነቶ ዘበኛ ለአማኙ መምህር ለተጣላ ዳኛ ትልቅ ዋርካችን ኖት ለደከምነው ለኛ ሊቁ አባታችን ስጓት ይዘከረን እውነት ለጠፋብን ብራኬው ይድረሰን እግዜርን ለተውነው ስሞ ዋስ ይሁነን ••••• እንደ ነብይ ሁነው ትንቢት ተናግረዋል እንደ ሃዋርያትም ወንጌልን ሰብከዋል እንደ ቅዱሳንም ከእውነትጋርቁመዋል እንደ ሰማእትም በሰው ተገፍተዋል እንደ ኤልያስም ብቾትን ቀርተዋል እንደ ሙሴ ሁሉ ህዝብን አፍርተዋል እንደ ቅዱስቄርሎስ ቁመው ተሟግተዋል እንደ ዲዮስቆሮስ በ እምነት ገዝተዋል ••••• የታመኑ ባርያ ያልወጡ ከቃሉ ባለ ብዙ ፀጋው ባለ ብዙ አክሊሉ ታላቁ አባታችን ፍቅርን የታደሉ ልጆችዎ ተነሱ ሁሉም ተማማሉ በአንድነት አበሩ አለቃ አለቃ አሉ ጌታ አልጣሎትም የማይረሳው እሱ ተሰጥቶታል እና ለሙሴ እያሱ ስላሴ የደነቁ በእያሱ ፈንታ ልጆችዎን አስነሱ ••••• እናም አባታችን ቁጭትዎ ታወቀን ትውልዱ ተረዳው ብስጭትዎ ገባን ልክ እንደተነሳን ከሚስጥሩ እንዳወቅን ልክ እንደ እርስዎ ሁሉ እኛም እንዲሁ ተካድን እናም አባታችን ንፁህ ካህን አጣን ሁሉም አመፁብን ከሃዲዎች አሉን በ መመለስ ፋንታ በሴራቸው ወጉን ትዕቢት ተመርኩዘው በዱላቸው መቱን ስለዚህ ባሉበት በተቀመጡበት በሉ አባ ይፍቱን 11/12/2012 በልጅዎ፦ ሃብተ ቂርቆስ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.