cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሙዚቃ እና ሙዚቀኛን ከ ተሙ ጋር🎙🎨

ካሴት ሙዚቃዊ እይታ የማይዳሰስ የለም ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

Більше
Рекламні дописи
269
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
-530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
በዛሬው ፍፃሜ አንዲት ጀግኒት እስት ላመስግን በዛሬው አቀናረብ ደሞ አዲስ የድምፃዊያን ውድድር " ከ አድዋ ባንድ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች" መሀል አንዲት እንስት አለች፡፡ በለያየ ጊዜያት አያታለሁ "ሳክፎኒስት" ሁሌም ደሞ አዲስ ውድድር ሲመጣ እሷን ለመመልከት ነበር የምገኘሁ፡፡ ዛሬ ግን ቦታው ድረስ አየሁ ፡፡ ጀግኒት እንስት ሳክፎኒስት ለ ሌላው ድምቀት እሷ ነበረች፡፡ ባለሽበት ምስጋናዬ ይድረስሽ @biggrs
Показати все...
👍 1
ደሞ አዲስ የባለ - ተስዕጦ የድምፃዊያን ውድድር በደማቅ ሁኔታ የመጀመርያው ምዕራፍ ተጠናቀቀ፡፡ በዋልታ ቲቪ ዘውትር እሁድ ከ ቀኑ 9:00 /ዘጠኝ ሰዓት/ ጀምሮ የሚተላለፈው "ደሞ አዲስ" የባለ ተስዕጦ የድምፃዊያን ውድድር "24'' የባለ ተስዕጦ ድምፃዊያን ይዞ ጀመረው በስተ መጨረሻ ግንቦት 25/ 2016 የመጀመርያ ምዕራፉን ፍፃሜውን አጊንቷል ፡፡ በቦታውም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የድምፃዊያን ቤተሰቦች እንዲሁም የደሞ አዲስ ተወዳዳሪዎች በቦታው በመገኘት እና የቀድሞ ተወዳዳሪ አብርሀም ሸዋንቅጣው ሙዚቃ አቅርቦ  በደሞ አዲስ አማካኝነት ከተወዳጁ ኤልያስ ተባበል እጅ የ አምሳ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሌሎችም ውድድሩን ተከታትለዋል የሚሹትን ሁሉ ደግፈዋል፡፡ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት "የደራሼ ብሔረሰብ'' -ፍና የባለውን ባህላዊ ውብ ዳንስ አቅርበዋል፡፡ተወዳዳሪዎች ለፍፃሜ ያለፉት አብርሀም ኸይሩዮሐንስ ወርቁ እና ማትያስ ደርብ ከ አድዋ ባንድ ጋር የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አቅርበዋልና፡፡ በመድረኩም ወደ ስድስት የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲያቀርቡ የጋሽ ሚኒልክ ወስናቸው ሁለት ሙዚቃዎች፣ የጋሽ ጥላሁንን ገሰሰ ፣ ጌታቸው አስፋው ፣ እሳቱ ተሰማ እና የመሳሰሉት ድምፃዊያንን ቀያይጠው አቅርበውታል፡፡ የዳኞች እና ተወዳዳሪዎች ያሬድ ነጉ ፣ የሺህ ደምመላሽ ፣ ትዕግስት ሀይሉ( እግቱ) በቦታው ተሰይመው አስተያየትም ድጋፍም ሰተዋል፡፡ በመድረኩት የመራው ደግሞ እንግዳሰው ሐብቴ/ ቴዲ/  በዚህ መሰረት "8970" sms በህዝብ ሙሉ ድምፅ አሸናፊ ሲሆኖ ከተዘጋጀው የሁለት ሚልየኑን ብር አንድሚልየኑን ማሸነፍ ሲችል እግቱም በአንፃሩ የአንድ ሚልየን ብር አሸናፊ ሆናዋል ፡፡ "ማትያስ ደርብ" በ2016 ዓመተ ዕህረት የመጀመርያ ምዕራፍ የዋንጫ እና እንዲሁም የምስክር ወረቀት ተቀብሏል፡፡ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌልጅ @biggrs @yenevibe
Показати все...
👍 1
ሰንበት ወግ አመሻሽ "ደሞ አዲስ" የድምፃዊያን ውድድር ድምፃዊት ትዕግስት ሀይሉ እና ተወዳዳሪ ማትያስ ደርብ የሁሉት ሚልየን ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡ በምስል👆 ዝርዝር ጉዳይ👇
Показати все...
👍 1
ዳኞች ለተወዳዳሪዎች የሙዚቃ ምርጫ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መከሩ ፋና ላምሮት የባለ ተስዖጦ የድምፃዊያን ውድድር ሶስተኛ ሳምንት የመጀመርያ ምዕራፍ ተወዳዳሪዎች በአማረ ሁኔታ በተለያየ ክንውኖች ውድድሩ አሳምረው አቅርበዋል ዳኞች ሁሌም በከፍታ ውስጥ ሆነው ዳኝነትን ሰተዋል ኮከብ ባንድ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ከተወዳዳሪዎች ጋር አከናውነዋል፡፡ *ምን አዲስ ነገር ታየ… -የኮከብ ባንድ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾች የልጆች ለውጥ አድርገው ዛሬ ለህዝብ አስተዋውቀዋል አቤል ለዓለም ፡ ድራመራር አቤል ድረስ ፡ ሳክፎኒስት እነዚህ በኮከባ ባንድ ውስጥ አዲስ የመጡ ናቸው ፡፡ - በቦታው የተገኙ ታዳሚዎች ውድድሩን ከመመልከት ባለፈ የራሳቸውን ተህዕጦ እና ለ ፋና ላምሮት ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ገልፃዋል፡፡ አሸናፊ በሪሁን ድምፃዊ ከታዳሚዎች መሀል የጥላሁን ገሰሰ( የድሌ ነሽን ) ሙዚቃ አቀረበ ለተወዳዳሪዎችም ምክርም ለግሷል፡፡ በተጨማሪም ከተዳሚ መሀል ፋና ላምሮት ምንጊዜም የማይጠፋው ተመልካች ዳግማዊ ንጉሴ ስለ ፋና ላምሮት ያለውን የተሰማውን በተጨማሪም ግጥም አቅርቧል፡፡ ከተናገረው መሀል ''ፋና ላምሮት ሳንከፍል የምንማርበት ትምርት ቤት ነው''ሲል ተደምጧል፡፡ -በውድድሩ ከቀረቡት ውስጥ ግጥም ዜማ ቅንብር የሰሩትን እንግለፅ ከ አቀናባሪ ዮሐንስ ተኮላ ፣ ቴዲ ማክ ፣ ኤልያስ መልካ ፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ እና የመሳለሱት ከግጥም ዜማ አንፃር አያ ሙሌ ፣ አበበ መለሰ እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርበዋል፡፡ * ዳኞች ከስልትም ከስሜትም አሳብ ሰተዋል፡፡ የዜማ ሐረጋት/ፍሬዚንግ/ ፣ ትንፋሽ ቁጥጥር እና አጠቃቀም ፣የሙዚቃን  አገላለፅ ፣ የድምፅ ቀለም፣ ቅኝት ፣ ቫይብራቶ/ የድምፅ መንቀጥቀጥ፣ ሪትም፣ የሙዚቃ ምርጫ፣ በራስ ድምፅ ማዜም፣ የሙዚቃው ሐሳብ ፣ መዋሀድ፣ ናዛሊ ቮይስ/ የአፍንጫ ድምፀት/ ፣ ኳንታይዝ፣ ሬንጅ ፣ ቅላፄ፣ የዜማን ማጤን፣ የቃላት መቆራረጥ የመሳሰሉት ተነስተዋል፡፡ * ኮከብ ባንድ (16) ሙዚቃዎች ከ ተወዳዳሪዎች ጋር በመሆን ሙዚቃ አቅርበዋል፡፡ ጋሽ ሙሀሙድ/ዝምታ ነው መልሴ/፣ ሚኒልክ ወስናቸው/ቆንጆ/ ፣ ኩኩ ሰብስቤ እንደ ገና የሰራችሁ/ እንባዬ/ ፣ አበበ ተካ/ወፍዬ/ ፣ ታምራት ሞላ/እንባዬ አልቆም አለ/ ፣ ጥላሁን ገሰሰ/ አምሳሉ/ ፣ ቴዲ ታደሰ/ ሉባንጃዬ/ ፣ ትዕግስት ፋንታሁን/እንደ ተሸፈነ/ ፣ እብስት ጥሩነህ/ በፈጠረህ/ ፣ አሊ ቢራ/ አማሌሌ/ ፣ ተሾመ ምትኩ/ ንገሪኝ/ ፣  ሙሉቀን መለሰ/ ውሀ ወላዋይ/ እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርበዋል፡፡ * ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ይሆን ዘንድ አልስተያየት ሰተዋል፡፡ -ብሩክ አሰፋ :- አንድን ሙዚቃ ስንመርጥ በጥበባዊ መንገድ እንዴት ማቅረብ አለብን ብሎ ማሰብ፡፡ - የሹምነሽ ታዬ:- አንድ ድምፃዊ የሚገመገመው የተለያዩ የሙዚቃ ስራ ሲያቀርብ ነው፡፡ - አማኑኤል ይልማ:- ሙዚቃ ስታቀርቡ አድጎ ከመጣ ችግር የለውም በሁሉም ነገር፡ * ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ እና የተሰባቹንም ከ ነሙሉ ነጥብ እንግለፅ፡፡ -ጴጥሮስ ማስረሻ-59640 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ -ናሆም ነጋሽ-59605 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ -ኤርሚያስ ዳኛው- 58641 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ -ዝንታለም ባዬ- 58247 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ -ዘላለም ፀጋዬ- 58219 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ -ትዕግስት አንተነህ-58199 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡ የእለቱ ተሰናባች የሶስተኛ ሳምንት የመጀመርያው ምድብ ተወዳዳሪ የተለያዩ የሙዚቃ ስራ አቅርቦ ዳኞችን አስገርሟል ከዛም በተጨማሪ ለተለዳዳሪው አሳብ ሰተዋል፡፡ የእለቱ ተሰናባች ጌታነው ስመኝ-57744 አጠቃላይ ነጥብ፡፡ በፋና ላምሮት አብሮነቱን ገልፆ ከ5000 ብር ጋር አሰናብቶታል፡፡ ዘጋሚ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ ፋና ላምሮት መልካም መልካሙን ይግጠመን፡፡
Показати все...
👍 1
የሰንበት ወግ … ፋና ላምሮት ቤት እንዲህ አየን በምስል👆ዝርዝር ጉዳይ👇
Показати все...
''MARDA MUSIC AND SOUND TRAINING CONSULTANCY CENTER"… እጅግ አስደሳች ዜና የፋና ላምሮት ዳኛ የሙዚቃ መምህር ብሩክ አሰፋ በሚያስተምርበት በማርዳ ሪከርድስ(marda music and sound training and consuliancy cinter) '' ነፃ የትምህርት እድል" ከሚሰጣቸው ተማሪዎች መካከል ለኔ እድሉን ሰቶኛል እጅግ ከልብ አድርጌ አመሰግናለሁ መምህሬ፡፡ ሙዚቃ በማወቅ እና በማሰላሰል ውስጥ ሲሻገር ብዙ ልንሰራቸው የሚገባ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ይህ ትምህርት ቤት በኢትዮጲያ ለመጀመርያ ጊዜ ማለት ይቻላል በድምፅ ቁጥጥር(sond system) እያስተማረ ይገኛል፡፡ በዚህ የሙዚቃ ዘርፍ ይንን እድል ስለ ሰጠከኝ ከልብ አመሰግናለሁ እናንተም እዚህ ገብታችሁ የሙዚቃ ክህሎታችሁን ትጨምሩበታላችሁ፡፡❤️
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቤዝ ጊታር ተጫዋች ቶማስ ጎበና አሁን የመጡትን ወጣት ሙዚቀኞችን አድንቋል ! እንዲህ ከ ጋዜጠኞች የተዘነዘረትን ጥያቄ" በአሁኑ ወቅት የሚወጡ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃዎችን ታዳምጣለህ ? " ቶማስ ጎበና እሱም የተሰማውን ሐሳብሰቷል፡፡👇 "አሁን ብዙ ወጣቶችን ነው የምሰማው እውነት ለመናገር። ምክንያቱም ለየት ያለ ነገር ይዘው የመጡትም እነሱ ናቸው። ወግዳዊት ፣ ጀንበሩ ፣ ሮፍናን እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ስራ ነው እየሰሩ ያሉት"። "የማ" የምትባል ከእዮኤል ጋር አሁን የለቀቁት አንድ አልበም አለ። ከተማ ውስጥ የሚገርሙ ሙዚቀኞች ናቸው ያሉት። ስንሻው ሰገሰ በሰሞኑን አዲስ አልበም አውቷል። እነ ሌሉ ፣ እነ ማህሌት ፣ እነ ዮሃና እነዚህ ሁሉ የሚገሩሙ ወጣት ሙዚቀኞች ናቸው"ሲል ሐሳቡን አቀብሏል፡፡ ሙዚቀኛ ቤዝ ጊታር ተጫዋች "ቶማስ ጎበና''::
Показати все...
👍 2
ድምፃዊ፡ ዲበኩሉ ታፈሰ/ዲበ/ ግጥም ፡ ይልማ ገብረ አብ ዜማ፡ ዲበ ቅንብር ፡ ጃኖ ባንድ ርዕስ፡ አይራቅ ዳይሬክተር እን ኤዲተር ፡ አይዳ አሸናፊ አይራቅ የመትመጭበት ቀን የመገናኛው ቀን@biggrs @yenevibe ዳግመኛ ተመልሳችሁ በመድረኩ እና አልበሞችን ብሰማ ደስ ይለናል፡፡
Показати все...
👍 1
የቅዳሜ ምስጋናጃኖ ባንድ በአስር አመት ውስጥ አይተኬ የሙዚቃን ጎዞ የየብቻ አቅም አንድ ላይ ተጣምሮ በርካታ ሙዚቃ መድረክ አስደምማችሁ ጥቂት ደሞ የአልበም እትም አድርሳችሁልናል፡፡ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ከልብ ያመሰግናችኃል፡፡ @biggrs @yenevibe
Показати все...
ትኩስ እና አዳዲስ የመዝናኛ መረጃ እንሆ፡፡ - ከ አዲስ አበባ የቀጠው አቀናባሪ እና የዜማ ግጥም ደራሲ ሮፍናን የሙዚቃ ስልጠና በሐዋሳ ቀጠሮውን ይዟል፡፡ " ROPHNAN'S MASTERCLASS " ሙዚቀኛ ሮፍናን "በሙያዬ የማውቃትን ለማካፈል እንቅፋቶቼን ሌሎች እንዳትመቱ እንድትሻሉም እግዚአብሔር እንደፈቀደላችሁም በሙያችሁም ከእኔ በብዙ ርቀት ተሽላችሁ እንድትሄዱ ሀገርንም በሙያችሁ በልፋታችሁ የተሻለ እንድታገለግሉ እንድታስጠሩም በሚል መነሻ ለ150 ሰዎች በኤሊያና ሆቴል በሚገኘው ሲኒማ ውስጥ ከጥር 27 እስከ 29/ 2016 ዓ.ም መስጠቱ የሚታወቅ ነው።ሙዚቀኛ  ሮፍናን ኑሪ  " ነፀበራቅ "  ፣ " ስድስት " ፣ " ' ዘጠኝ '- ሐራምቤ እና ኖር " የተሰኙ አለበሞችን ከዚህ በፊት ማውጣቱ የሚታወቅ ነው። - የአምባሠሏን ንግስት  ከቅዳሜ ግንቦት 24 /09/2016 ዓ.ም ጀምሮ ገርጂ መብራት ሃይል  ቶቶት  የባህል ምግብ አዳራሽ :: የአንባሰልዋ ንግስት በማሪቱ ለገሰ እና በሌሎች ድንቅ ታዋቂ ድምፃዊያን ልዩ ዜማ እና  በባህላዊ  የሙዚቃ ባንዳችን  ውዝዋዜ  በቦታው ይቀርባሉ ::  ማሪቱ ለገሰ  ወደ አሜሪካ ሳትመለስ  ሳትሄድ የሙዚቃ ስራዎቿን  ያድምጧት በቶቶት በተዘጋጀው ድግስ ያደምጧል፡፡ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ስለ ኮንሰርቱ - ወጣቱ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት ለማቅረብ ቀን መቁረጡ ይታወሳል አሁን ደሞ ቦታን እና አብረውት የሚሰሩት ድምፃዊያንን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ድምፃዊያን ሚካኤል በላይነህ ፣ ሳሙኤል ብርሀኑ (ሳሚ ዳን)፣ ልዑል ሲሳይ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ቦታው  በሚሊኒየም አዳራሽ ይቀርባል፡፡ @biggrs @yenevibe
Показати все...
👍 1