መምህር እረቂቅ ባህል መድህኒት ቅመማ ፬
Відкрити в Telegram
ትክክለኛውን ገፃችንን ይከታተሉ እውነተኛ መረጃ በማየት ያረጋግጡ በመናፍስት ወጠመድ ለወደቁ የሰው ልጅ በሙሉ በጥበብ ማደስ እና የተለያዩ እጽዋቶች መልካም ስራ የምናስተዋውቅበት ቻናል ነው። ሀሳብ አስተያየት ካላቹ በዚህ ይጠይቁን https://t.me/@mergetaf ይደውሉልኝ 0921780146
Показати більше1 563
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
-430 день
Архів дописів
"የሴት ዛር"
የሴት ዛር ማለት ወንዶች ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር የተለያዩ ችግሮች የምታስከትል የክፉ መንፈስ ዓይነት ናት።
የሴት ዛር ምልክቶች፦በወንዶች የሚከሰቱ ምልክቶች...
የድክመተ ወሲብ ምልክቶች..
በህልም ከተለያዩ ሴቶች ጋር ወሲብ ማድረግ
ሴት ልጅ በምያይበት ሰአት መርበትበት መፍራት
ከሴት ጋር ሲገናኝ በቶሎ መጨረስ
በራስ መተማመን ማጣት
እና የመሳሰሉት...ናቸው።
...የነዚህ ሁሉ መፍትሔ ከዚህ በታች ቀርቦላችኃል።
..የወንዴው ዕሬት ሥር
..የምድር እምቧይ ሥር
..የሴት ዕሬት ሥር
..የሴት ቀስት ሥር(ሴቴዋ)
የእነዚህ ሥር በአንድ አድርቆ ደቄሶ...ግማሹ መታ ማታ በጋለ ማረሻ አድርገህ ለ ፯ ቀን መታጠን።
ግማሹ በትንሽዋ አንድ ማንከያ ከእጽዋቱ በንጹህ ጠጅ በመበረዝ ማታ ማታ ለ ሶስት ቀን በብርሌ ሞልቶ መጠጣት።
የታየ መፍትሔ ነው።
ከስርዋ የሴት ዛር መንፈስ ትወገዳለች።
ይህ ዕፅዋት እንሥላል ይባላል።
እንስላል እንደሚታየው ከግንዱ ወፈር ብሎ ቅጠሎቹ ቀጠን ብለው ዘርዘር ያሉ ናቸው።
እንሥላል በገጠርማ አከባቢ ከ ሀበሻ አረቂ በመቀላቀል ለማድመቅያ ይጠቀሙበታል።
ከዛም አልፎ ለተለያዩ የባህል ህክምናዎችም ይውላል። ከነሱም አንዱ ስንጠቅስ
በወሲብ ጊዜ ቶሎ ለሚረኩ ወይንም ለሚጨርሱ ዋነኛ ጊዚያዊ መፍትሔ ነው።
አጠቃቀሙም እንደሚከተለው ነው፦የእንስላል ስር በአውራ ጣት ልክ ማዘጋጀት በውኃ በደምብ አጥቦ ከ ወሲብ አንድ ሰአት በፊት እስክያልቅ ደረስ በደምብ ማላመጥ እና ውኃ ውኃውን መዋጥ ልጣጩ ግን መትፋት ሲሆን ...ሌላ አማራጭ ደግሞ ለ 3 ሰአታት ያክል እንደሞሟጫ እየተጠቀሙ መቆየት ከዛ በኃላ እርካታዎን ያጣጥሙ።
ምንጭ ከዕፀ ደብዳቤ ተሞክሮ ተግባር ላይ የዋለ::
ማስታወሻ...መፍትሔው ጊዜያዊ ቻ ነው።
ዘለቄታዊ መፍትሔ የምትሹ ካላቹ በውስጥ መስመር አናግሩን።
መፍትሔ ሥራይ ጸረ ማናፍስት!
መልካም ጊዜ።
ማይግሬን እና ጨለማ ለምን ተዋደዱ?
🌿ሽነጥ/ሽነት🌿
፫-ማይግሬን (Migraine Headache)
🙏🏾ይህ በሽታ የዓለማችን 12%የሚሆነው ህዝብ ያጠቃል።አብዛኛው የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ሴቶች ሲሆኑ በሽታው (ከቤተሰብም ሊወረስ ይችላል)👈🏿ይህ ማለት ከቤተሰብ በወረደ የዛር መናፍስ ሐረግ ወደ ልጅ ልጅ ይወርዳል ማለት ነው::
🙏🏾የማይግሬን በሽታ መነሻ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ አይታወቅም።(ይህ ማለት የሳይንሱ ዓለም አይታወቅም ካለ የአጋንንት ስራ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ::
👉🏾ለበሽታው ተጋላጭ የሚያደርጉ ነገሮች ይልና:-
#ጭንቀት
#አነቃቂ ነገሮች (caffeine)
#የተወሰኑ የምግብ ዓይነቶች ማለትም እንደ አይብና አልኮል መጠጦች
#የአየር መለወጥ
#ምግብ አለመመገብ
#የእንቅልፍ መዛባት
#በሴቶች በኩል የወር አበባ ኡደትን ተከትለው የሚጨምሩና የሚቀንሱ የሴት ሆርሞኖች በሽታውን ያባብሱታል።
❌ራስ ምታቱ በሚጀምር ሰዓት ህመምተኛ መድሀኒት በመውሰድ ፀጥ እና ጨለም ያለ ቦታ እረፍት ማድረግ፣የሚለውን ሃሳብ አልስማማበትም!❌
🙏ምክንያቱም ጨለማን ሳይሆን ብርሃንን እንቀዳጅ ዘንድ ፍላጎቴ ነውና::
🙏ጨለማ ተፈጥሮአዊ ክዋኔ ቢሆንም ጨለማ ብርሃንን በምንም አይተካም::
❤️የማይግሬን በሽታ ምልክቶች!
#መነጫነጭ
#እረፍት ማጣት
#የድካም ስሜት መኖር
#የትኩረት ማጣት
#የደረት ላይ ህመም
#የራስ ምታት
#የትንፋሽ መቆራረጥ
#ማቅለሽለሽ
#የምግብ አለመፈጨት
#የእንቅልፍ ማጣት
#የአፍ መድረቅ
#የሰውነት ላብ መብዛት....ይቀጥላል
🙏አንድ የተረሳ ነገር አለ!
ዳሩ ግን የዛር መፍናስቶች፤የዓይነ ጥላ መናፍስቶች፤የመተት መናፍስቶች፤የዘመኑ ሰዶማውያን መናፍስቶች የዚህ ችግር ምክንያት መሆናቸውን የተረዳን ስንቶቻችን ናቸው::።
#የነቃ ትውልድ ያለ እንደሆነ ምክሬን ያድምጥ።ፀበል እንጠጣ፤ እንጠመቅ፤እንጸልይ፤ጥበብን እንጠቀም ጨለማ ውስጥ ከመደበቅ እንውጣ፤
🌿የማይግሬን ፈውስ ሰጪ እጽ
#ሽነት/ሽነጥ ይባላል::
🙏🏾ይህ እጽ የግንዱ አልያም የሥሩ ቅርፊት በንፅህና አድርቀው ፈጭተው የማይግሬን በሽታ ሲነሳብዎት በአውራ እና በሌባ ጣትዎ በመቆንጠር በአፍንጫዎት መሳብ ነው::10 ደቂቃ ሳይሞላ ፈውስ ያገኛሉ::
ይህ ድርጊት እስኪድኑ ድረስ ይጠቀሙ::
🌱በበሽታው የተጠቃ ወዳጅ ዘመድ ይድን ዘንድ ቢሹ የአንድ ሰከንድ ስራ የሆነችው ሼር ማድረግዎን አይርሱ!
🔶ስር ነቀል መፍትሔ ነው::
🌿የተቸገረ ሰው ቢኖር በአድራሻየ መሰረት ብቅ ብሎ እፁን በነፃ መውሰድ ይችላል::
⏩ የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽ0921780146
እሬት/ዕሬት
#ዛሬ በሃገራችን ስለ ሚገኙ የእሬት/ዕሬት/ሬት ዓይነት እና ልዩነት በምስል ወደ 20 የሚጠጉ የእሬት ዓይነቶች እናያለን::
🍀በብዛት ለጥቅም እየዋለ ያለው እጽ ቬራ እየተባለ የሚጠራው እሬት ነው::
ቀሪውን በሂደት የምናይ ይሆናል::
🙏🏾እንዲሁም በእናንተ አከባቢ የተለየ ስያሜ ያላቸው እንደሆነ በኮሜንት ስር ለትውልዱ ታሳውቁልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ::🙏🏾
🍀ሃገር በቀል የሆኑ እጽዋቶችን ሼር በማድረግ ለነቃው ትውልድ እናስተላልፍ::
❤️ የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ0921780146
#ሰላም
#ፍቅር
#ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እንዲሁም ለመላው ዓለም ይሁን።
~ETHIOPIA
~ልዑል እግዚአብሔር ከከፋው እና ዓለምን ካስጨነቀ ክፉ ወረርሺኝ ኮሬና ከተባለው በሽታ በፀጋው ይጠብቀን።
#ዝሆኔ ፤ከማን አንሼ
በተለምዶ ዝሆኔ እየተባለ ስለሚጠራው በሽታ መንስኤው እና መፍትሔው እንሆ!
#የዝሆኔ በሽታ የሚከሰትበት እና የሚተላለፍበት መንገዶች
አንዲት አስተላላፊ ትንኝ በሽታ አምጭ ጥገኛ ተህዋስ(ፓራሳይት) ጤነኛ የሆንን ሰው በመንደፍ ስታስተላልፍ የዝሆኔ በሽታ ይከሰታል።
በበርካታ ክስተቶች በሽታው የህመም ምልክት የለውም። በአንዳንዶቹ ግን በእጅ፣ በእግር ወይም በመራቢያ ፍሬ ላይ ተለቅ ያለ እብጠት ያስከትላል።
ቆዳም እየፈወረ መጥቶ ህመም ሊያስከትል ይችላል። በሽታው እንዲህ ዓይነት የሰውነት ለውጥ በሚያሰከትልበት ወቅት የተጠቃውን ሰው ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችም ይዳርጋል።
በኢትዮጵያ በዚህ በሽታ እስከ 1.5 ሚለሊዮን ሰዎች በችግሩ የተጠቁ እንሉለ አንድ አንድ መረጃዎች ያመለክታሉ።
#የዝሆኔ በሽታ ምልክቶች
#ማሳከክ ፤
#የማቃጠል ስሜት፤
#የቆዳ መሻከር እና ጠንካራ መሆን፤
#አውራ እጣት ቀጣይ ካለው እጣት መለየት፤
#ጤፍ የሚመስል ነገር ከእግር ላይ ይከሰታል
#የእግር ማበጥ
#የወንድ ዘር ፍሬ ማበጥ(hydrocele)
#ሌሎች የአካል ክፍሎች ማበጥ
#የዝሆኔ በሽታ መከላከያ መንገዶች
•በመኝታ ወቅት አጎበር መጠቀም።
•በንፅህ ውኃና በሳሙና የበጠውን እግር ይታጠቡ።
•አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ እግራቸውን ከፍ አድርገው ይስቀሉ።
•እግራቸውን ከቆሻሻ እና ከጉዳት ለመከላከል ጫማ ይጫሙ።
ከዚህ ኣልፎ በሽታው ተስፋፍቶ አልድን ያለ እንደሆነ መፍትሔው ከሊቃውንት አባቶች ማህደር የተገኘ መፍትሔ እንሆ!
#የዝሆኔ መፍትሔ
#የአብሽ ፍሬ
#የሮማን የሥሩ ቅርፊት
#የሎል ሥር
#የዕጸ ሣቤቅ ሥር
#የበለስ ቅጠል
እነዚህ እጽዋቶች ከያሉበት በማቅረብ አድርቀው አዘጋጅተው ቀላቅለው!
ለአንድ ቀን 3 የሾርባ ማንኪያ ከተቀላቀለው መድኃኒት በመቀነስ በወንዴው ዕሬት ጄሉ ወይም ፈሳሹ በመለወስ ጧት የታመመው ክፍል በደንብ አድርገው በመቀባት ፀሐይ ለ ሁለት ሰዓት ያክል ማሞቅ።
ማታ ማታ በደንብ አድርገው የዕሬቱ ግንድ ከውኃ ጋር በማፍላት ለብ ባለ ጊዜ መታጠብ ነው።
ይህ ድርጊት እስኪሻልዎት ድረስ በተደጋጋሚ ይጠቀሙት።
ሙሉ መፍትሔ ይሰጥዎታል።
#ሻሎም ነኝ!!!
ለበለጠ መረጃ 0921780146
ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉልን።
#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
#SHARE በማድረግ የተለያዩ መፍትሔዎችን እንዲሁም ጥበብን እናስተዋውቅ።
መልካምነት ለራስ ነው!
አጫጭር መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ።
❤️ሰላም
❤️ፍቅር
❤️ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ!!!
ሰላም ለመላው የዓለም ህዝብ ይሁን::
❌ለስኳር በሽታ የሚከለከሉ አመጋገብ❌
#የህክምና ባለሙያዎችም ቅድመ ስኳርን ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤን እና አመጋገብን ማስተካከል እንደሚገባ ይመክራሉ።
ከዚህ አንጻር አንድ ሰው የቅድመ ስኳር ምልክት በታየበት ጊዜ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ምግቦች ባይመገብ ይመረጣል፤
❌የፍራፍሬ ጭማቂ
#የፍራፍሬ ጭማቂ የበዛ ስኳርና የያዘና በጥሬው ከሚመገቡት ፍራፍሬ በበለጠ ጣፋጭ በመሆኑ በቅድመ ስኳር ምልክት ወቅት መመገቡ ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልን ስሚያሰፋ አይመከርም።
❌አልኮል መጠጥ
የአልኮል መጠጦች በውስጣቸው ያለው የስኳር መጠን ቢለያይም የስኳር በሽታ ታጋላጭነትን ያሰፋሉ።
አልኮል የሚጠጡ ሰዎች አንድም በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል አልያም በተቃራኒው ይወርዳል።
ይህ ደግሞ የቅድመ ስኳር ምልክት ለታየባቸው ሰዎች እጅጉን አደገኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ለዚህም አልኮልን ማስወገድ አልያም የስኳር መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ እንደ ወይን ያሉ የአልኮል መጠጦችን በውሃ በመበረዝ መጠቀም።
❌ቅባት የዛባቸው ምግቦች
ቅባት የበዛባቸው ምግቦች የኢንሱሊንን ስራ በማስተጓጎል የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ ይችላሉ።
❌ጣፋጭ (ስኳር የበዛባቸው) ምግቦች
#ስኳር ለሰውነታችን አስፈላጊ ቢሆንም በብዛት መውሰድ ግን ለስኳር ህመም ተጋላጭ ስለሚያደርገን በቅድመ ስኳር ህመም ወቅት ማስወገድ ይገባናል።
ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ካስፈለገም ከተዘጋጁ በኋላ ሳይሆን በጥሬው (በፍራፍሬ) መልክ ቢመገቡ ከጣፋጭ ምግቦች ማግኘት የሚገባዎትን በቂ የስኳር መጠን ያገኛሉ።
ባለሙያዎቹ ጣፋጭ ምግቦችን አለመመገብ ሳይሆን መመጠኑን ይመክራሉ።
❌ሩዝ፣ ነጭ ዱቄትና ዳቦ
#ሌላው እና በቅድመ የስኳር ወቅት መዘውተር የሌለበት ምግብ ደግሞ ሩዝ እና ከስንዴ የሚዘጋጅ ነጭ ስንዴና ዳቦዎችን ነው።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ነጭ ዱቄት በፋብሪካ በሚመረትበት ወቅት በሚኖረው የማቀነባበር ሂደት ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ያጣል።
በዚህ ሂደት የሚቀረው ነገር የስኳር መጠኑ ብቻ በመሆኑም የቅድመ ስኳር ምልክት በሚታይ ጊዜ መጠቀሙ አደጋ እንዳለው ይገልጻሉ።
የስኳር ብሽታን እንዴት እናስታግስ?
📕የአያቶቻችን እውቀት እንዲህ ይላል::
☘️የሴት ዕሬት ግንድ ጭማቂ
☘️ከአብሽ ጭማቂ ጋር
👇መጠናቸው
#የዕሬቱ ጭማቂ ግማሽ የውኃ ብርጭቆ
#የአብሽ ጭማቂ ግማሽ የውኃ ብርጭቆ
👆አንድ ላይ በማቀላቀል ጧት ጧት በባዶ ሆድ አንድ አንድ ብርጭቆ ለሰባት ቀን ይውሰዱ::
🙏ውጤቱን ከሳምንት በኃላ በማየት ምስክር ይሁኑ::
በአማን ዘተፈትነ!!!
#የሴት ዕሬት ከዕሬቶች ሁሉ የምትለይበት እሾህ የሌላት እና ወደ ቅጠል የሚያደላ ግንድ ያላት ልዩ ዘርፈ ብዙ መፍትሔ ናት::
ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል::
#ሼር በማድረግ ሀገር በቀል የሆኑት የዕጽዋት ጥቅምን ልወዳጆቻችን እናካፍል::
🙏 የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉ ስልኮች በስራ ሰዓት ይደውሉልኝ:
0921780146
✝ሳዶር✝አላዶር✝ዳናት✝አዴራ✝ሮዳስ✝
📖ለጸሎት እንነሳ📖
✔️የዓይነ-ጥላ መናፍስቶችን ድል እንንሳ♥
♣ዓይነ -ጥላ በሳይንሳዊ አባባል የስነልቦና ችግር ይሉታል።
#ዓይነ -ጥላ ከልጅነት ጀምሮ እስከ እውቀት ስነ ልቦናዊ፣ማሕበራዊ፣እንዲሁም አካላዊ ችግሮችን መፍጠር የሚችል በአብዛኛው ሰው የሚገኝ በሽታ ነው።
# ዓይነ-ጥላ የሚባለው ችግር በተለያዩ ሰዎች ቁራኛ ሁነው ለማሰቃየት የተዘጋጁ ፣ህይወትን የሚያጨልሙ፣ በክፉ መናፍስቶች የሚከሰት በሽታ ነው።
#ዓይነ-ጥላ የአጋንንት ሴራ እንዲሁም የክፉ መናፍስት ተንኮል ከሰው ዘንዳ ያላቸው ቅናት እና ተንኮል የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም የምያሸማቁቅበት ክስተት ነው።
#የዓይነ ጥላ ምልክቶች፦ብዙ ጊዜ አጋንንት በቅናት መንፈስ ሰዎችን በመተናኮል በየትኛውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችን የዘወትር ፈተናዎች የሆኑት ጥንተ ጠላቶቻችን ውግያቸው እጅግ በረቀቀ ስልታቸው ከሰዎች ዘንዳ በመላመድ የየእለት ተግባራችንን በመላመድ እንዳናስተውላቸው ወጥመዳቸውን በማጥመድ ለብዙ ፈተናዎች ይዳርጉናል።
♣ከዚህም የተነሳ የዓይነ ጥላ መናፍስቶች የሚፈጥሯቸው ችግሮች ከስር በትንሹ አስቀምጫቸዋለሁ።
#ትዳር መገርገር/ትዳር መበተን
#የበታችነት ስሜት /ጭንቀት
#ተስፋ መቁረጥ/ራስን ማጥፋት
#ብሶተኛ መሆን/መነጫነጭ
#ግለ ወሲብ/ሕልመ ለሊት መከሰት
#ብቸኝነት/ዝሙት/ሴሰኝነት
#እድል መዘጋጋት/ንብረት መውደም
#የወር አበባ ሕመም/ሾተላይ/ጽንስ ማስወረድ
#ሆድ መንፋት/ጋዝ መብዛት
#ከቤተሰብ አለመስማማት
#ማይግሬን/ራስምታት
#ፍርሐት/ድንጋጤ/መርበትበት
#የስራ ስኬት ማጣት/ብር ማባከን
#ቅዠት/ጥርስ ሟፋጨት
ጥያቄ?
በዓይነ ጥላ የተያዘ ሰው በሳሳይኮሎጂስት፣እና በሳይካትሪስት ባለሙያዎች ይድናል ወይስ አይድንም?
♣ምናልባት በዚህ ችግር ተጠቅታችሁ የተለያዩ መፍትሔዎች የሞከራችሁ እስኪ ተሞክሯችሁን በኮሜንት መስጫ ሳጥን አካፍሉን።
📖ለጸሎት እንነሳ📖
♥በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ:ቅዱስ፡ ፩ ፡አምላክ፡ ጸሎት፡ በእንተ፡ ዓይነ- ጥላ ፡ወዓይነ- ወርቅ ፡ሰላም፡ ለዓእይንቲከ፡ ለድንግል፡ በኩራ፡ ሳዳር፡ እለ: ርዕያ፡ በትዕግሥት፡ መሥተራትዓተ፡ ሐራ፡ አላዶር፡ ወሞዓቶሙ፡ ለቤተ፡ አይሁድ፡ ማህበራ፡ ዳናት፡ ወትርዕድ፡ እምግርማከ፡ ሶበ፡ ትኔጽር፡ አዴራ፡ አዕይንቲከ፡ ፍሡሐት፡ ሕማማተ፡ መስቀል፡ ፆራ፡ ሮዳስ፡ ክርስቶስ፡ ጻድቅ፡ ወብርሃን፡ ዘበምራቅከ፡ ከሠትከ፡ አዕይንተ፡ ዕውራን፡ ወበቃልከ፡ ይትፌወሱ፡ ዱያን፡ ዛቲ፡ ነፍስ፡ ሕምምት፡ ወጥውቅት፡ ይእቲ፡ ትርከብ፡ ፈውሰ፡ እምገቦከ ፡በከመ፡ ፈትሐ፡ ኤርምያስ፡ እንተ፡ ኮክኅ፡ ክድንት፡ ይእቲ፡ በደመና፡ሰማይ፡ ከማሃ ፡አሕልፋ፡ ወአሰስላ፡ ለሕማመ፡ ዓይነ፡ ጥላ ፡ወዓይነ ፡ወርቅ፡ ወገርጋሪ ፡ዓይነ፡ ቡዳ፡ ወቁመኛ፡ ወተያዥ፡ ሊተ፡ ለእከሌ፡(የራስ ሙሉ ስም)
እስመ ፡አልቦ፡ ነገር፡ ዘይሰአኖ፡ ለእግዚአብሔር፡ ወአልቦ ፡ዘይሰአነከ፡ ወኩሉ፡ ይትከሃለከ፡ ትሰፍሕ፡ የማነከ፡ወታጸግብ፡ ለኩሉ፡ እምበረከትከ፡ ኦ እግዚእየ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ በዝ፡ ቃለ ፡መለኮትከ፡ ዕቀበኒ ፡ወአድኅነኒ ፡እመከራ ፡ሥጋ፡ ወነፍስ፡ ሊተ፡ ለገብርከ፡ እከሌ፡
(የራስ መጠርያ ሙሉ ስም ይግባ)
✔️ጧት ጧት ሰባት ሰባት ጊዜ በንፁህ ውኃ እየጸለዩ ይጠጡ።
ከቻሉ ማታ ማታም እየጸለዩ ይተኙ መልካም ራእይ ያያሉ።
✔️ትልቅ ጸሎት ነው አበው ይመስክሩ በምትፈልጉት አባት አስመርምሩ ፈውስ ታገኙበታልችሁ ልዩ የፈጣሪ ቅንዋተ መስቀልን እያስተዛዘለ የሚሄድ ጸሎት ነው።
✔️ሼር እናድርግ ሃሳብም እንስጥበት በዚህ ችግር ያልተጎዳ ቤት ከቶም አይኖርምና ለጸሎት እንትጋ በጸሎት የሃገራችን ሰላም እናስጠብቅ::
0921780146
#ሻሎም ነኝ።
✝️ የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
🔺🔻የብር መአድናት እና ጌጣጌጥ መሸጫ🔻🔺
👇👇👇ከተለያዩ የከበሩ መዓድናት እንዲሁም ፍፁም ንፁህ በሆኑ የሃገር ውስጥ እንዲሁም የጣልያን የብር ጌጣጌጥ በማቀናጀት የሚሰሩ ልዩ ልዩ
#ፈርጥ ያላቸው የወንድ ቀለበቶችን🔻🔺
#የተለያዪ መስቀሎች
#የተለያይ ሃብሎች
#የህፃናት ብራስሌቶች
#በብር ላይ የሚፃፉ ማንኛውም ፅሑፎች እንፅጽፋለን::
#ያረጁ ወርቅ እና ብርም እንገዛለን እንሸጣለን::
🙏🏾እንደምርጫዎት ብተለያዩ መጠን እና ከለር ቢሹ ፊሊ የብር እና ጌጣጌጥ መሸጫ ብለው ብቅ ይበሉ::
🔺🔻መምጣት ባይችሉም በነፃ ካሉበት ቦታ ድረስ በታማኝነት እናቀብሎታለን::
☎️አድራሻችን ኮተቤ 02 የረር ህንፃ አጠገብ እንደደረሱ ይደውሉልን::
በዚህ channel ውስጥ የተለያዩ ለአዋቂ ና ለህፃናት የሚሆኑ የብር ጌጣጌጦችን ለእርሶ ምቹ በሆነ መንገድ እናቀርባለን እንሰራለን፡፡
🙏🏾በወርቅ ወይም በብር የሚጻፉ ማንኛውም ጽሑፎች የሰው ስም~ስመ አምላክ~ወዘተ በሚፈልጉት መልኩ መጻፋችን ለየት ያደርገናል::
የቴሌግራም ቻናላችን Join join join በማድረግ ትርፋማ ይሁኑ::
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/+8hzoBGQoSUNkZmM0
https://t.me/+8hzoBGQoSUNkZmM0
https://t.me/+8hzoBGQoSUNkZmM0
እቃ ለማዘዝ በዚህ ያገኙናል ::
0921780146
#ሰላም
#ፍቅር
#ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች ይሁን።
#ETHIOPIA
#ሆዱን ለሚነፋው፣
#ለሚጮህበትም፣
#ለወስፋት
#ለኮሶም
#ጋዝ መብዛት
#ሆድ ውጋት
♦የጦስኝ እና የእንስላል ቅጠል፣
>ከሁለቱም አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በሁለት ብርጭቆ ውኃ በማር ና በጨው አጣፍጠህ በባዶ ሆድ ለ 4 ቀን ጧት ጧት ብትጠጣ ትፈወሳለህ።
እሙን መፍትሔ ነው።
ከጎንዮሽ ጉዳት ውጭ ነው ይጠቀሙበት።
ሻሎም ነኝ።
#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
0921780146
ለበለጠ መረጃ
ቴሌግራም ቻናላችንም ይጎብኙ ስለ ልዩ ልዩ መፍትሔዎችን እንዳስሳለን።
❤️ሰላም
❤️ፍቅር
❤️ጤና ለእምየ ለቅድስቲቱ ሃገር ኢትዮጵያ እንዲሁም ለቅዱሳን ልጆቿ ይሁን።
❗️ስለ ዝምተኛው ገዳይ የጉበት በሽታ❗️ቁ 2
🔴የጉበት በሽታ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ እና መፍትሔ ያልተገኘለት መሆኑ ቢያስጨንቅም ቅሉ በተለያዩ ሃገር በቀል መድኃኒቶች ግን ፈውስ ማግኘት የሚቻልበት አጋጣሚ መኖሩን ደግሞ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ነገር ነው።
🔴5 አይነት የጉበት በሽታ ቫይረስ አይነቶች🔴
✔️ እነዚህም ሄፓታይተስ ኤ፤ቢ፤ሲ፤ዲ እና ኢ ይባላሉ፡፡ከእነዚህ ውስጥ ግን በሽታን በማምጣት የሚታወቁት ቢ እና ሲ የተባሉት ሲሆኑ ሄፓታይተስ ቫይረስ ዲ እና ኢ ደግሞ ብዙም የተለመዱ አይደሉም፡፡
#ያልጠናበት ህመምተኛ የሚያሳያቸውን ምልክቶች#
✔️ ትኩሳት፤
✔️ድካም ድካም የማለት ስሜት ፤
✔️ማቅለሽለሽ፤
✔️የምግብ ፍላጎት ማጣት፤
✔️የሰውነት ሽፍታ እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም ሲሆኑ ትኩሳቱ በጊዜ ሂደት እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን በስተመጨረሻም የታካሚው ሰውነት እና አይኖች ቢጫ መሆን ሊኖር ይችላል፡፡
#የጠናበት የጉበት ህመም በሽታ ያለባቸው#
በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ላይ በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩም! እንደ ድካም እና የመዛል ስሜት ይስተዋልባቸዋል፡፡በሽታው ሳይታከም ከቆየ ወደ Cirrhosis እና የጉበት ካንሰር ሊለወጥ ይችላል፡፡ታማሚው ያለበትን የጉበት ቫይረስ አይነት ለመለየት ቀለል ያለ የደም ምርመራ ማድረግ ይቻላል፡፡የእያንዳንዱን አይነት የጉበት በሽታ በዝርዝር ስናይ!
✔️ሄፓታይተስ ኤ፡-ይህ አይነቱ የጉበት ህመም የሚተላለፈው በቫይረሱ የተበከለ ምግብ እና መጠጥ በመውሰድ ነው፡፡ህጻናት ላይ ምንም አይነት ምልክት የማያሳይ ሲሆን አዋቂዎች ላይ ግን ከላይ የተገለጡትን ምልክቶች እንደ የአይን እና ሰውነት ቢጫ መሆን፤ድካም፤ማቅለሽለሽ የመሳሰሉትን ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡
✔️ሄፓታይተስ ቢ፡-ሄፓታይተስ ቢ እንደ ሲርሆሲስ እና የጠና የጉበት ህመም በማምጣት ይታወቃል፡፡መተላለፊያ መንገዶቹን ስናይ እንደ መርፌ እና ምላጭ የመሳሰሉ የተበከሉ ስለታማ ነገሮች፤ከእናት ወደ ልጅ እና የገብረ ስጋ ግንኙነት ይጠቀሳሉ፡፡ወደ ህክምና አማራጮቹ ስናይ የጠና ህመም የሌለባቸውን ታካሚዎች እንደሚያሳዩት የህመም ምልክቶች ሆስፒታል መተኛትም ቢያስፈልግ አስተኝቶ በማከም ህክምናውን መስጠት ሲቻል የጠና ህመም ያለባቸውን ግን በደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረሱን ቁጥር (viral laod) እንዲሁም የጉበት መቆጣትን የሚቀንሱ በመርፌ እና በሚዋጥ እንክብል መልክ የሚሰጡ ሲሆኑ ይህም የበሽታውን ወደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር መቀየር እድሉን ይቀንሳል፡፡
✔️ሄፓታይተስ ሲ ፡- ልክ እንደ ሄፓታይተስ ቢ ሁሉ ሄፓታይተስ ሲም ለጉበት ካንሰር እና ሲርሆሲስ ለሚባለው የጠና የጉበት ህመም የሚዳርግ ሲሆን መተላለፊያ መንገዶቹም ተመሳሳይነት አላቸው፡፡እስከዛሬ ድረስ ሄፓታይተስ ሲ ን ለመከላከል፤ የሚያገለግል ክትባት ያልተገኘ ሲሆን ሄፓታይተስ ሲ በሽታ ታማሚዎችም የተለየ የሚያሳዩት ምልክት የለም በሽታው መኖሩን ለማወቅም የደም ምርመራ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ወደ ህክምና አማራጮቹ ስንመለከት በሳምንት አንድ ጊዜ የሚሰጥ የመርፌ ህክምና እና ለ24-48 ሳምንታት የሚዋጥ መድኃኒት ይገኙበታል፡፡
🔴የሚከለከሉ ነገሮች🔴
✔️የአልኮል መጠጥን እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም።
✔️ማንኛውንም አይነት መድኃኒት ከመውሰዳችን በፊት ለጉበት ጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን ማረጋገጥ።
✔️ያልተረጋገጡ የባህል መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ።
✔️ በቂ እረፍት ማድረግ።
✔️ ጫና የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ መቆጠብ
✔️ እንደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ። በየጊዜው ክትትል ማድረግ
✔️ ከታማሚው ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ።
✔️የሳይንሱ ዓለም ተመራማሪዎች ያስቀመጡት የጉበት በሽታ ምልክቶች እና ጥንቃቄ ይህንን ሲሆን!
#አበው ሊቃውንትም በተመሳሳይ የጉበት በሽታ (ወፌ)የወፍ በሽታ በማለት የሚጠሩት አደገኛ በሽታ ነው።
🔴የጉበት በሽታ ቀላል እና ውጤታማ መፍትሔ🔴
🌿የመሬንዝ ተቀጽላ በትንሿ ማንኪያ
🌿የጭቁኝ ቅጠል በትንሿ ማንኪያ
👉👆የመሬንዝ ተቀጽላ በወይና ደግ አከባቢ የሚገኝ ሥሩ መርዛማ ዕጽዋት ሲሆን ቅጠሉ ልምላሜ የተላበሱ መካከለኛ ፍሬ አእዋፋት የሚመገቡት ፍሬ ያለው ሲሆን! ተቀጽላው ግን ፍጹም ከጉዳት ውጭ የሆነ ትርፍ ክፍል አልያም በወፍ ዘራሽ ከመሬንዝ ግንድ ተጣብቆ የሚበቅል ዕጽ ነው።
👉ይህ የመሬንዝ ተቀጽላ ቆርጠው አድርቀው ፈጭተው በትንሿ ማንኪያ በመለካት ከተፈጨ ጭቁኝ ቅጠል ጋር በማቀላቀል ጧት በባዶ ሆድ ከአንድ ሲኒ ቡና ጋር ወይንም ከሞሪንጋ ሻይ ጋር ጨምረው መጠጣት።
የጭቁኙ መጠን በትንሿ ማንኪያ አንድ ይሁን።
👉ይህ ድርጊት ከሰባት እስከ አስራ አራት ቀን ይጠቀሙ!
ከ አራት ሰዓት በኃላ ምግብ ይመገቡ።
⁉️ከአልኮል /ከጥሬ ስጋ/ከጥሬ ወተት/ለአንድ ወር ያክል ይቆጠቡ።
✔️ይህ መልእክት በበሽታው የተጠቃ ሰው ጋር ይደርስ ዘንድ ሼር እናድርግ።
❌ማስጠንቀቅያ!❌
ያለ እውቀት በድፍረት ማንኛው ዕጽዋት ለመድኃኒትነት ከመጠቀም በመቆጠብ ሙሉ ጤንነታችንን እንጠብቅ!
ሻሎም ነኝ!!!
ለበለጠ መረጃ ከስር ባለው ስልክ በስራ ሰዓት ይደውሉልን።👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
❇️የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ
0921780146
መልእክት የምቀበልበት
https://t.me/Shalom
https://www.m/etse.debdaba/
ቴሌግራም ቻናሌ
https://t.me/joinchat/TQcAXSzUFJAiH3BQ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
❤️ወደ ውጭ ሀገር ለመሔድ የዓይነ ጥላ መንፈስ ገርግሮታል?❤️
❓ገርጋሪ መንፈስ ምንድን ነው❓
✅የሚገረግር መንፈስ እና የዓይነ ጥላ መንፈስ ነገዳቸው ምድራውያን አጋንንት ሲሆኑ ተግባራቸው የሰው ልጅ ዕድል መስበር እንዲሁም የታሰበ መልካም ስራ ማሰነካከል ነው።
✅የገርጋሪ መንፈስት ማለት፦እጅግ በጣም ብዙ እና አዳጋች እንዲሁም የረቀቀ የሕይወት መሰናክል ይዘው የሰው ልጅ አእምሮን የሚቆጣጠሩ ከዘመናዊ ሕክምና ጋር የተላመዱ የወደቁ መናፍስት ናቸው።
✅የሚገረግሩ መናፍስት፦ ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ድረስ ዕድልን የሚሰልቡ ከራሳችን ባህሪ ጋር በመመሳሰል የራሳቸውን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ተንኮለኞች መናፍስት ናቸው።
✅የሚገረግሩ መናፍስት ስራ፦ ሰዎች በተለያዩ ምክንያት የውጭ ሀገር ዕድል አግኝተው ምክንያቱ ሳይታወቅ ጉዳዩን ማስተጓጎል፣እንቅፋት መፍጠር፣በፈተና ሰዓት ማሸበር፣በበሽታ ማስተጓጎል የመሳሰሉት እንቅፋት እንዲከሰት ዋነኛ ተዋናዮች የገርጋሪ መናፍስት ናቸው።
✅የገርጋሪ መናፍስቶች፦ማንኛውም የታቀደ ስራ፣ ይሁን የሕይወት መሰረትን የሚገረግሩ፣የሚያናጉ፣ ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንዳንጠጋ የሚገረግሩ፣የራስ ማንነታችን እንዳንመስል አስከፊ ባሕሪ የሚያጎናጽፉ፣ሞት የሚደግሱ፣የጥፋት ነገድ ናቸው።
✅የሚገረግሩ መናፍስት፦የማይገረግሩት የሕይወት ዘይቤ የለም:: ትዳር እንዳንይዝ፣ልጅ እንዳንወልድ፣ሃብት እንዳናፈራ፣ቤተሰብ ሰላም እንዳይሆን፣ሀገር ሰላም እንዳይፈጠር፣ግልፍተኝነት ባህሪ እንዲኖረን ያደርጋሉ።
✅የሚገርግሩ መናፍስት የልፋት ስራ
📌የውጭ ፕሮሰስ ማቊረጥ
📌ጽንስ ማቋረጥ
📌ትዳር ማቋረጥ
📌ተስፋ ማጨለም
📌የትምህርት ፈተና ማሰናከል
📌ከሰዎች ጋር አለመስማማት
📌መነጫነጭ
📌ራስ ምታት
📌በሰው እንድንጠላ ማድረግ
📌ሀብት መገርገር
📌ስራ መገርገር
📌ጭንቀት መፍጠር
📌ለአደጋ መዳረግ
📌እቃ እንዲበላሽብን መሆን
📌ከፍቅር ጓደኛ ማጣላት
📌በወር አበባ ከቤተ እምነት መከልከል
📌በህልመ ለሊት ከቤተ እምነት መከልከል
📌ልጅ መከልከል
📌እንቅልፍ መንሳት/እንቅልፍ ማብዛት
📌ፍርሃት.....
✅ከላይ የተዘረዘሩት የሚገረግሩ መናፍስቶች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።
✅እነዚህ ችግሮች በእናንተ ዘንድ ያለ እንደሆነ በውጭም በሃገር ውስጥም ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን መፍትሔ የሚሆን ድንቅ ጸሎት እንሆ ልመግባችሁ።
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ጸሎት በእንተ ዓይነ ጥላ ወዓይነ ወርቅ
ገርጋሪ ወአብራሪ የጋራት ኤሎሄ የጋራት ሃሌ ሉያ የጋራት ዮፍታሔ የጋራት ታኦስ አልፋ ቤጣ የውጣ የጋራት ዎዖ የጋራት ኢየሱስ ክርስቶስ የጋራት አማኑኤል ጸባዖት በኃይለ ዝንቱ አስማተ መለኮት በራስ በገጽ በዓይን ወበሽፋፍት በልሳን ወበአፍ በአንገት ወበደረት በእጅ ወበእግር በባት ወበአቁያጻት በራስ ጠጉር ወበእግር ጽፍር ዘሀሎከ ዓይነት ፃእ ከመወጽአ ዮናስ እምከርሰ አንበሪ ከማሁ ፃእ ዓይነት ወዓይነ ወርቅ ዓይነ ጥላ ገርጋሪ ወአብራሪ እምላዕለ ገብርከ እከሌ(የራስ ስም)
✅አሰራሩ✅
መስመር በሌለው ወረቀት በቀይ ቀለም ወይም እስክርቢቶ ጽፈው ቢችሉ በቆዳ ከትበው ካልሆነ በኪሶት ይያዙ።
እንዲሁም ጧት ወይም ማታ ፫ ጊዜ ይጸልዩ።
ልዩ ውጤት ያገኙበታል።
✝ይህ መልካም እና የገርጋሪ ዓይነ ጥላ መፍትሔ ጸሎት እጅጉን መልካም የፈጣሪ ልዩ ስሞች የያዘ መፍትሔ ነውና! ይህ ኃላቀር አስተሳሰባችን ትተን መርምረን እንጠቀምበት።
❤️መፍትሔነቱ ቅዱሳን አባቶች ይመስክሩ!
✅ይህ መልእክት በጭንቅ ውስጥ ላሉ ወንድም እህቶቻችን እንዲሁም ዘመድ ጓደኞቻችሁ ይደርስ ዘንድ ከወደዳችሁ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!
✝የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
0921780146
መልእክት ለማስቀመጥ
https://t.me/Shalomso
የቻናላችን ሊንክ
https://t.me/joinchat/TQcAXSzUFJAiH3BQ
የፌስ ቡክ ድህረገጻችን ለመጎብኘት
https://www.facebook.com/etse.debdaba/
"ጊዜዋ ካለ ከደጅሽ 'ለምን ታመመ ልጅሽ"
Ashwagandha (ጊዜዋ)
#ለዓይነ ጥላ
#ጭንቀት ለማስወገድ!
#የወንድ ድክመተ ወሲብን ያክማል!
#እንቅልፍ ለሚከለክላቸው ፍቱን ነው።
#ለነርቭ ሕመምተኞች!
#ለፀጉር መቁሰል/ለፎሮፎር/ለፈንገስ
#የጤና ሻይ ለማዘጋጀት
#ጊዜዋ በኢትዮጵያውያን የባህል ሕክምና አዋቂዎች ዘንዳ ለብዙ በሽታ ማከምያ እንደሚውል እርግጥ ነው።
#እንዲሁም ዓለማትም በዘመናዊ መልኩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ሕክምና ሲያዘጋጁበት ይስተዋላል።
በህንድ ÷በቻይና÷ ጀርመን:ፍራንስ ÷አሜሪካ እንዲሁም በተለያዩ ዓለማት ዕፀ-ግእዝ/ጊዜዋ/ግዛዋ/ዋሃሌ/አሽዋጋንዳ ዕፅ ሰውን ከበሽታ ሲፈውሱቡት√
#እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የጊዜዋ ሥር እና ቅጠል ዘሩ እስኪጠፋ ከስሩ በመንቀል ለጭሣ ጭሥ ብቻ መጠቀማችን ሊታሰብበት ይገባል።^
#የጊዜዋ ፍቱን እና ተአማኒ መፍትሔዎች!
#፩'ለዓይነ ጥላ ለዛር መናፍስት¶
የጊዜዌ ሥርና ቅጠል በብዛት አሰባስበው ከከርቤ ዕጣን ጋር በማቀላቀል ማታ ማታ ተሸፋፍነው በትንሽ በትንሹ እየለኩ በከሰል እሳት እየጨመራችሁ መታጠን።
ለ 7ቀናት ያክል ይጠቀሙ።
#፪'ለጭንቀት¶
ትል ያልበላው የጊዜዋ ቅጠል በንጽህና በማዘጋጀት የደረቀውን ጧት እና ማታ አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት ትንሽ ማር ጨምረው እንደሻይ እያፈሉ ለ 5 ቀን በሻይ ብርጭቆ መጠጣት ፍቱን ነው።
#፫'ለድክመተ ወሲብ¶
የጊዜዋ ሥሩን በንጽህና አዘጋጅተው ፈጭተው ማታ ማታ በሾርባ ማንኪያ በመለካት በግማሽ ሊትር ወተት እያፈሉ ቢጠጡ የዘር ፍሬ ያበዛል እንዲሁም ፍትወትን ያስተካክላል።
#፬'ለነርቭ ህመም¶
የጊዜዋ ሥር እና ቅጠል በንጽህና አንድ ኪሎ ያክል አዘጋጅተው ፈጭተው ከግማሽ ኪሎ ጥቁር አዝሙድ ጋር ቀላቅለው በ 5 ሊትር ውኃ በማፍላት 3 ሊትር ገደማ ከቀረ በኃላ አጥለው አቀዝቅዘው በማስቀመጥ ጧት ጧት በባዶ ሆድ አንድ አንድ የሻይ ብርጭቆ መጠጣት ፍቱን ነው።
ለ አንድ ወር ገደማ ይጠቀሙ።
#፭'እንቅልፍ ለሚከለክላቸው¶
የጊዜዋ ፍሬ በብዛት ለቅመው ፈጭተው ማታ ማታ በስሱ በአፍንጫዎ በማሽተት እንቅልፍ ማጣትን ይሰናበቱት።
#፮'ለፀጉር መቁሰል/ለፎሮፎር/ለፈነው።
የጊዜዋ ቅጠል በእርጥቡ ጨቅጭቀው ከንፁህ የፀጉር ቅቤ ጋር በማቀላቀል አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት መላ ራስዎትን በመቀባት ለ 4ሰዓታት ያክል አቆይተው ይታጠቡ።ፍቱን ነው።
፯'የጤና ሻይ ለማዘጋጀት¶
ጊዜዋ በተለያዩ የእጽዋት ተማራማሪዎች በተደረገ ጥናት ከ 12 በላይ በሽታን እንደሚያክም ተረድተዋል።
#በሊቃውንት አባቶቻችን ዘንዳም ከክፉ አጋንንት እስከ ስጋ ደዌ በሽታ ሲያክሙበት ይስተዋላል።
#ከዚህም የተነሳ ማንኛውም የጤና ቀውስ ቢደርስብን የጤና ሻይ አዘጋጅተን ብንጠቀም ድንቅ ፈውስ እናገኝበታለን።
¶አዘገጃጀት፣3 የሾርባ ማንኪያ የጊዜዋ ሥር በ አንድ ሊትር ለ 20 ደቂቃ ያህል በማፍላት ከ 5-7 የሻይ ብርጭቆ ይወጠዋል። ትንሽ ማር ወይም ስኳር ይጨምሩበት።
ማስጠንቀቅያ:-እርጉዝ ሴቶች እንዲጠቀሙበት አይመከርም።
¶ሰፊውን የአበው እውቀት ሼር ቢያደርጉት ጊዜዋ በደጁ እያለ ምስኪኑ ያገሬ ሰው አይሞትም¶
#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
ለበለጠ መረጃ ከስር ባለው ስልክ በስራ ሰዓት ይደውሉል
0921780146
መልእክት የምቀበልበት ስልክ
https://t.me/Shalomso
የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ለመሆን
https://t.me/joinchat/TQcAXSzUFJAiH3BQ
ሰላም ፍቅር ጤና ለዚህ ቤት ቤተሰቦች ለሀገራችን ኢትዮጵያ እየተመኘሁ ዛሬ ለወላጅ እናቶች እና አባቶች የሚመለከት!
የአባቶች የጥበብ እውቀት ከዕጸ ደብዳቤ የተገኘ በተለያዩ ሰዎች ሙሉ ድኅነት ያመጣ መፍትሔ ልጠቁማቹ።
!!!ለሚደነግጡ ህጻናቶች!!!
ይህ ህጻናት የሚያስደነግጥ በሽታ የቅዥት በሽታ ይባላል።
ህጻናት በተለያዩ ቆሻሻ ቦታ ሲጫወቱ እንዲሁም በገጠርም በተለያዩ በቤተሰብ ባዕድ አምልኮ መሀል በሚያድጉበት ጊዜ እና ለቤተሰብ በተሠራ ውለሽ በመሳሰሉት ምክንያት መናፍስት ሲጠጉዋቸው!
ተቀምጠው ሳያስቡት የሚያስደነግጣቸው፤ እና በእንቅልፍ ልባቸው እጅጉን እያባነነ የሚቃዣቸው፤ እና የሚያስጮህ ፤ችግር ሲገጥማቸው፤እንዲሁም እጅግ ፍርሀት ፍርሀት ሲላቸው ቶሎ መፍትሔ ካላበጁለት!
እያደጉ በሚሄዱበት ጊዜ እየተቆራኛቸው ስለሚሄድ በጤና ፤በባህሪ ፤በአጠቃላይ ህይወታቸው ላይ ተጽዕኖ ሳይፈጥር ቢቻል በየእምነት ተቋማችሁ የሚፈታበት መንገድ መሞከር ካልሆነ ደግሞ በምስሉ ያምታይዋቸው እጽዋቶች ሙሉ ለሙሉ ችግሩን የሚቀርፉ የመናፍስት ጠላቶች ናቸው።
እነሱም፦
#የዓጋም ሥር
#የጠለንጅ ሥር
#የጅባራ ሥር
#የቀበርቾ ሥር
#የፍየለ ፈጅ ሥር
እነዚህ እጽዋቶች ሥራቸውን፦ መጠኑ በ ትንሽዋ ጣታችን አጽቅ በመለካት ቆርጠን አምስቱንም እጽዋቶች በማድረቅ በአንድነት ደቁሰን በማላም ነፍተን ሁሉንም እጽዋቶች በአንድ ስኒ ጣዝማ ማር በመለወስ!
# ከ 1ዓመት እስከ 3 ዓመት ላሉ ህጻናቶች ግማሽ የሻይ ማንኪያ እንስጥ።
#ከ 3 ዓመት በላይ ለሆኑ ህጻናቶች አንድ የሻይ ማንኪያ በመጠቀም ጧት ጧት በባዶ ሆድ ለ ፯ ቀን እንስጣቸው።
እጽዋት በእግዚአብሔር ዘንድ የየራሳቸው ጥበባዊ ኃይል እንዳላቸው ጠበብት አባቶቻችን ስያስተምሩን ቆይተዋል።እኛም ከአባቶቻችን በተማርነው መሰረት ይሄው መፍትሔ ይሆናችሁ ዘንድ በእንደዚህ መልኩ አቅርበነዋል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በማንም አይደለም።
ሼር በማድረግ በዚህ ችግር ልጆቻቸው ለሚሰቃዩባቸው እናት አባት እናስተላልፍ።
እጽ የሓዩ!
ሻሎም ነኝ።
ለበለጠ መረጃ 0921780146 ብለው በስራ ሰአት ይደውሉ።
