cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Borfonicon

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
206
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

1: "በስማያት የምትኖር አባታችን ሆይ:" -ፀሎት በአንተ ላይ ያለንን የማያቋርጥ ተደጋፊነትና ግንኙነት የምናሳይበት ነው:: አቤቱ ብዙዎቻችንን ወዳንተ ከመቅረብ የሚያግደን ፍርሃት ወይም ያለመብቃት ስሜት ነው:: ፀሎትን እንፈራለን ርቀትም ይሰማናል: ሆኖም በዚህ ፀሎት እንዳስተማርከን የምንቀርበው ወደ አባትነትህ እንደሆነ ማሰብ እጅጉን ያሳርፈናል:: ይህ አባትነትህ በስጦታ የተገኘ በዋጋ የታተመና ዘላለማዊ ነው:: ይህም ተስፋ የማይናወጥ የእምነትና የመረጋጋት መሰረታችን ይሆናል:: ካንተጋር ያለን ግንኙነት የአምላክና የአምላኪ: የፈጣሪና የፍጡር ብቻ ሳይሆን የአባትና የልጅ መሆኑን ስናስብ በማንኛውም ሁኔታ አንተን መቅረብን እንመርጣለን:: በዚህም አባት ለልጁ ከሚያስበውና ከሚሆነው በላይ እንደምትሆንልን እናምናለን:: አቤቱ ልጆችህ ልንሆን ስላቀረብከንም ምስጋናን እንመልሳለን!
Показати все...
1ኛ ዮሐንስ 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማናቸውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ፣ የአብ ፍቅር በእርሱ ዘንድ የለም፤ ¹⁶ ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም። ¹⁷ ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።
Показати все...
Показати все...
Ene Mefelegew - A song by Shalom - New Amharic Gospel Song SandArt 2020

This song is an honest prayer about a real change in life. It is about a person who fought against who he is and then tried to travel into who he really should became. The song ended up hoping God will give his desire.

Показати все...
image_2020-05-24_20-11-26.png7.26 KB
Показати все...
ራስን ፍለጋ (ጥያቄ አስር) ሁል ጊዜ ተቀባይና ወሳጅ ነኝ ወይስ አቅራቢና ሰጪም ጭምር? መስጠት የሌለበት ወሳጅነት፣ ማቀበል የጎደለው ተቀባይነት፣ መጋበዝ የማያውቅ ተጋባዥነት፣ መጥቀም የሌለበት ተጠቃሚነት . . . በዘመናችን የተለመደ ማሕበራዊ ቀውስ! ሰው ሁል ጊዜ ወደ እርሱ የሚያስገባበትን በር ክፍት አድርጎ ከእርሱ የሚያስወጣበትን በር ግን ሁል ጊዜ ዝግ ሲያደርግ ስለማንነቱ ማወቅ እጅግ አይከብድም፡፡ ከሰዎች የመቀበልና በሰዎች የመጠቀም ሂደት ጤናማነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ሳለ፣ ከዚያው ጋር እኛ ደግሞ “ለሰዎች ምን ያህል እየሰጠን ነው? ሰዎችንስ ምን ያህል እየጠቀመን ነው?” የሚለውንም ጥያቄ በመጠየቅ እውነታው ጋር መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ በሕይወትህ የላቀ ማንነት ውስጥ መግባት ከፈለክ ይህንን ጥያቄ በቁም ነገር ጠይቀህ መልስ ማግኘት አለበህ፡፡ \ቤሰተቦችህ፣ ጓደኞችህ (ወዳጆችህ)፣ ሕብረተሰቡ፣ የተማርክበት የትምህርት ተቋም፣ የምትሰራበት መስሪያ ቤት . . . ለአንተ የሰጡህንና እየሰጡህ ያሉትን አስበው፤ አንተስ ምን ያህል መልሰህ እየሰጠህ ነው? በተቀበልክ መጠን መልሰህ የማትሰጥበት መስክ በሙሉ ቀስ በቀስ ለአንተ መስጠቱን እንደሚያቆም አትዘንጋ፡፡ ምሳሌን በራስህው አካል ላሳይህ፡፡ የአካል ክፍሎችህ ካለማቋረጥ ጠዋት ተነስተህ የምትፈልገውን ነገር ለማድረግ የምትችልበትን ነገሮች በሙሉ ይሰጡሃል፡፡ እግሮችሀ መራመድን፣ እጆችህ መስራትን፣ አይኖችህ መመልከትን . . .፡፡ በዚሁ ልክ ግን ሰውነትህ ከአንተ የሚፈልገውን ካልሰጠኸው አንድ ቀን ለአንተ የሚሰጥህን ያንን ሁሉ የለመድከውን ነገር ማቆሙ አይቀርም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሁል ጊዜ አገልግሎትን የሚሰጡንን እንደ መኪናና የመሳሰሉት አይነት ነገሮችን እንደ ምሳሌ መውሰድ ትችላለህ፡፡ አገልግሎቱን ብቻ በመቀበል፣ መልሰህ ለእነሱ መስጠት ወይም ማድረግ የሚገባህን አገልግሎት ካልሰጠሃቸው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አንድ ቀን እነሱም አገልግሎታቸውን ማቆማቸው አይቀርም፡፡ የውጤቱ ተጽእኖ የሚመጣው አንተው ጋር ነው፡፡ እስቲ ሰሞኑን ማድረግ እንደጀመርነው ዛሬም ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ከእነሱ የተቀበልከውን ያህል ምላሽ እንዳልሰጠሃቸው የምታስባቸውን ሰዎች ወይም ተቋሞች አስብና ምን አይነት ለውጥን ማድረግ እንደምትችል በመጻፍ ለመተግበር ሞክር፡፡
Показати все...
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም። ዮሐንስ 14:27 ---------------------------- 4 Killo Fellowship ----------------------------
Показати все...
Amazing new song by singer Yafet Asefa
Показати все...
@YTAudioBot - 04:04, 3.86 MB
Показати все...
HONEST PICTURES - YAFET ASEFA ____ New Ethiopian dtV-e6EuHjM.m4a3.86 MB
Показати все...
YAFET ASEFA ||እወድሃለሁ|| New Ethiopia Protestant Lyrics Video 2020

#Zeftret_production #Yafet #እወድሃለሁ Subscribe to our channel to get Daily videos of worship, Praise videos, Song Covers.

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.