cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሙሳ እና ሀሩን

ይህን ሙሉውን ፁሁፍ አዘጋጅቶ ላቀረብልን ወንድማችን አላህ ከይር ጀዛውን ይክፈለው! ኢስላማዊ ወርቃማ ንግግሮች

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
190
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) 🍃ክፍል ስልሳ ስድስት🍃 ============== ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) በተውሂድ ላይ ከፍተኛ ተጋድሎን በማድረግ ከህዝባቸው ጋር ለብዙ አመታት ቆዩ በህዝባቸውም ድርቅና ምክናየት በምድረ በዳ በረሃ ላይ አላህ ለ አርባ አመታት ከዛ እንዳይወጡ መዐቀብ ስለጣለባቸው ኑሯቸውን ከዛው አድርገው መግፋት ግድ ሆነባቸው። በዛው በበረሃ ላይ ሳሉ አላህ (ሱብሀነሁ ተዐላ) ሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) የመሞቻው ጊዜ እንደደረሰ ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) አሳወቃቸው። እናም ሐሩንን (ዐለይሂ ሰላም) አላህ ከወሰነው ቦታ እንዲወስዱት አዘዛቸው። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ወንድማቸውን ሐሩንን ይዘው ሄዱ እዛም እንደደረሱ ሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) የሚያምር የወርቅ አልጋ የመሰለን ነገር ተመለከቱ ከዛም ላይ ጋደም አሉ። በዛው ቅፅበት መለከል መውት ሩሃቸውን ወሰደ። ሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) በዚህ ሁኔታ ከ አዱኒያ ወጡ። ሙሳም (ዐለይሂ ሰላም) ወንድማቸውን ቀብረው ወደ ህዝባቸው ተመለሱ። ለህዝባቸውም ሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) እንደሞተ ና ቀብረውት እንደመጡ ነገሯቸው። በዚህን ጊዜ ተንኮል የማያጣቸው በኒ እስራኤላዊያን ሙሳ ወንድሙን ገሎ መጣ እያሉ አዛ ያደርጓቸው ጀመር። በዚህን ጊዜ ሙሳ እኔ አልገደልኩትም ቀኑ ደርሶ ነው አላህ የወሰደው ይሄን ካላመናችሁ አላህ የ ሐሩንን አስክሬን እዚህ እንዲያመጣውና እንድታዩ አደርጋለሁ አላቸው። በዚህ ተስማሙ አላህም የወርቅ አልጋ ከሚመስለው ላይ እንደተኙ ፊት ለፊታቸው አምቶ አሳያቸው። ሙሳንም አመኗቸው። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ህዝባቸው በጣም ብዙን አዛ አድርገዋቸዋል ግን አላህ ደግሞ ከሚባሉት ሁሉ በማስረጃ ያጠራቸዋል ቁርአን እንድህ ይላል እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደእነዚያ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትኹኑ፡፡ ካሉትም ነገር ሁሉ አላህ አጠራው፡፡ አላህም ዘንድ ባለሞገስ ነበር፡፡ (አል አህዛብ 69) ሙሳም (ዐለይሂ ሰላም) በዛው በረሃ ውስጥ እያሉ እድሚያቸው ገፋ 120 እንደደረሰም ይነገራል። ታዳ አንዴ ወደ ቤታቸው ሲገቡ ቤታቸው ውስጥ የማያውቁት እንግዳ ገብቶ አገኙት። እንዴት ከሰው ቤት ሳታስፈቅድ ትገባለህ ብለው በጥፊ መተው አይኑን አጠፉት። ግን አላወቁትም እንጅ አይኑን ያጠፉት ግለሰብ የሞት መላኢካ (መለከል መውት) ነበር። የሞት መላኢካው ወደ አላህ በመሄድ መሞትን ወደማይፈልግ ባሪያህ ነው የላከኝ አይኔን አጠፋኝ አለው። አላህም አይኑን መለሰለትና ድጋሜ ሂደህ መኖር የምትፈልግ ከሆነ የበሬ ቆዳ ላይ የጅ መዳፍህን አስቀምጥ ና የጅህ መዳፍ ያረፈበትን ፀጉር ብዛት ልክ እድሜ ሰጥቸሃለሁ ወደኔም መምጣት ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው አላቸው ሙሳም (ዐለይሂ ሰላም) መለከል መውት መሆኑን ሲያውቁ ጌታየን መገናኘትን መርጫለሁ አሉ። ሩሃቸውንም ወሰደ። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ህዝቦቻቸው በዛ በበረሃ ለ አርባ አመት እንዲቆዩ ባዘዛቸው ቦታ ላይ ሳሉ ሊከፍቱ የነበረችውንም ከተማ በህዝባቸው ጥመት ሳትከፈት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ሲሞቱ ከሰወ ጋር ማንም አልነበረም የትም እንደሞቱ ማንም አያውቅም መላኢካ ነው የቀበራቸው። ነገር ግን የ አላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የት እንደተቀበሩ አላህ አሳውቋቸው ያውቃሉ እናም ሙሳ የተቀበሩበትን እኔ እንጅ ማንም አያውቀውም ሲሉ ተናግረዋል። ህዝባቸው በበረሃው ቦታ ላይ ቅጣታቸው አልቆ አርባ አመቱን ጨርሰው ሲያበቁ አላህ የተቀደሰችዋን ምድር ከፍተው እንዲገቡ ፍቃዱ ሆነ። ሙሳ ኸድርን ለማገኘት ሲሄዱ ተከትሏቸው የሄደው ጓደኛቸው የሙሳን (ዐለይሂ ሰላም) ቦታ በመተካት የዚያ ህዝብ መሪ ሁኖ የተቀደሰችዋን ምድር ከፍተው ገቡ። የሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ህልም በተተኪው ትውልድ እውን ሆነ። ነብዩ ሙሃመድ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሰማይ በወጡ ጊዜ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላምን) ስድስተኛው ሰማይ ላይ አግኝተዋቸው ነበር። አላህ 50 ሶላት ግዴታ አድርጎባቸው ተቀብለው ሲመጡ ሙሳ ምን ተባልክ ሲሏቸው 50ሶላት እንድንሰግድ ታዘዝኩ ተቀበልኩ ሲሏቸው አይ ኡመቶችህ ይህን አይችሉም አስቀንስ በማለት 5 እስከሚሆን በሙሳ እና በ አላህ መካከል ተመላልሰው አስቀንሰዋል። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ባለውለታችን ናቸው። አላህ በጀነት አብሮ ይሰብስበን። ============================== ተ ፈ ፀ መ ______________________________________ የሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ታሪክ እኛ እዚህ ላይ የተቀስነው ከሞላ ጎደል ለማስገንዘብ እንጅ ምንም የቀረ ነገር የለም ማለት አይደለም ሙሉ ታሪኩን ባማረና በተዋበ መልኩ መማር ማወቅ የፈለገ የቁርአንን ትርጉም ከ ኡለሞች ይማር!። ትክክል የተናገርኩት ከ አላህ ነው የተሳሳቱኩት ከኔ እና ከሸይጧን ነው። https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg ==============================
Показати все...
ወርቃማ ንግግሮች

ሃይማኖትህ የልብህ ምግብ ነው!! የምግብህ ዋና ክፍል ደግሞ ተውሂድ ነው!

https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg

ለስተታችን መታሪሚያ ፣ ለነጋችን መቃናት ፣ ለአብሮነታችን ለተቃና መንገድ ፣ በሃሳብ ተደግፈን በሃሳብ ደግፈን ስንተራረም ዘላቂነት ያለው ደስታና ያማረ ጉዞ አብረን እንዘልቃለን። @Golden_SpeechBot

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) ክፍል ስልሳ አራት °•=========•° ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ፍቹን እስከምነግርህ ድረስ ምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ ያሏቸውን በመርሳት ስህተት ፈፀሙ። የ አላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንድህ ብለዋል፦ ይህች (ስህተት) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) በመርሳት የፈፀሟት የመጀመሪያዋ ስህተታቸው ነበረች። ቀጡሉና እንድህ አሉ፦ አንድ ወፍ እየበረረ መቶ መርከቢቱ ላይ አረፈ። ከዛም ማንቁሩን ከበሀሩ ላይ አንድ ጊዜ ነክሮ አወጣ። ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ሙሳን (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ አሏቸው፦ የእኔ እና ያንተ እውቀት ከ አላህ እውቀት አንፃር ሲታይ ይህ ወፍ ከበሀሩ ካጎደለው መጠን በምንም አይለይም። (አል ቡኻሪ አ ተፍሲር 18/ 2_4 /4725) ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ሙሳን (ዐለይሂ ሰላም) የመጀመሪያውን ስህተታቸውን በይቅርታ አለፏቸው ከዛም ከመርከቧ ወርደው ጉዟቸውን ቀጠሉ። በጉዞ ላይ ሳሉ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) አንድን ልጅ አገኙ ከዛም ገደሉት። (ወርደው) ተጓዙም፡፡ ወጣትንም ልጅ ባገኙና በገደለው፤ «ጊዜ ያለ ነፍስ (መግደል) ንጹሕን ነፍስ ገደልክን በእርግጥ መጥፎን ነገር ሥራህ» አለው፡፡(አል ከህፍ 74) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) በሰዋዊ ህጋቸው የገደለ መገደል እንዳለበት እንጅ ንፁህ ሰው ሲገደል አላስቻላቸውም እና እንዴት ንፁህ ሰው ትገድላለህ በእርግጥ መጥፎ ስራን ሰራህ ብለው ኸድርን ወቀሷቸው። ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ግን መጀመሪያ ያሏቸውን ደገሙላቸው «አንተ ከኔ ጋር ትእግሥትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩህምን» አለ፡፡ (አል ከህፍ 75) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ድጋሜ ተሳሳቱ በዚህን ጊዜ ሁለተኛ ከተናገርኩህ ጓደኝነታችን ያበቃል ቻንሴን ጨርሻለሁ አሉት «ከርሷ (ከአሁኒቱ ጊዜ) በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ አትጎዳኘኝ፡፡ ከእኔ የይቅርታን መጨረሻ በእርግጥ ደርሰሃል» አለው፡፡ (አል ከህፍ 76) አሁንም በይቅርታ አልፈዋቸው ጉዟቸውን ቀጠሉ፦ በጉዟቸውም አንድት ከተማ ደረሱ እናም የአካባቢውን ኗሪወች ምግብ ጠየቁ ግን ሊያስተናግዷቸው ፍቃደኛ አልነበሩም ከለከሏቸው። ኼዱም፡፡ ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች በመጡም ጊዜ ነዋሪዎቿን ምግብን ጠየቁ፡፡ ከማስተናገዳቸውም እምቢ አሉ፡፡ (አል ከህፍ 77) በዛው ከተማ ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን ቤት አገኙ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ቀጥ አድርገው አስተካከሉት። በዚህን ጊዜ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የመጨረሻ የሆነውን ስህተታቸውን ደገሙት። የሰራህበትን ገንዘብ ብትቀበል ጥሩ ነበር በማለት ለኸድር መከሯቸው። በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን ግድግዳ አገኙ፡፡ (ኸድር) አቆመውም፡፡ (ሙሳም) «በሻህ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር» አለው፡፡(አል ከህፍ 77) ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ይህ ለኔ እና ላንተ መጨረሻ ነው እስካሁን የሰራኋቸውን አንተም መታገስ ያልቻልክባቸውን ነገሮች ፍች እነግረሀለሁ ከዛም አበቃ አሏቸው። (ኸድር) አለ «ይህ በእኔና በአንተ መካከል መለያያ ነው፡፡ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልክበትን ፍች እነግርሃለሁ፡፡ (አል ከህፍ 78) https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama ይ ቀ ጥ ላ ል .......
Показати все...
ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

💚 ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ አላህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል‥ አላህ ያውቃል #በአላህ_ምርጫዎች_ተማመን  1

https://t.me/Golden_Speech

2

https://t.me/ALJUEDDAAWA

3 http://telegram.me/QURAN_YELB_BREHAN 4

https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) ክፍል ስልሳ ሶስት °•========•° ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ለ ኸድር የሙጡበት ጉዳይ እውቀት ፍለጋ ስለመሆኑ ነግረው ከምታውቀው ቀጥተኛ የሆነን እውቀት አስተምረኝ አሉት። ኸድርም ከእኔ ጋር ትዕግስት አድርገህ መማር አትችልም አላቸው። (ባሪያውም) አለ «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም፡፡ (አል ከህፍ 67) አስከትሎም መታገስ እንደሚከብዳቸው ነገራቸው። «በዕውቀትም በእርሱ ባላዳረስከው ነገር ላይ እንዴት ትታገሳለህ» (አል ከህፍ 68) በነዚህ የመጀመሪያ ቃላት ምልልሳቸው ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) የሙሳን (ዐለይሂ ሰላም) ስነ_ልቦናዊ ሁኔታ መርምረው አበቁ። ሳያውቁት በትንሽ ቃላት ስለራሳቸው ብዙ ነገሯቸው። እዚህ ላይ ከ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የሚጠበቀው በእራሳቸው የእውቀት ካምፕ ሁነው በራሳቸው መንገድ የተነገራቸውን መረዳት እና በትልቅ ትዕግስት መተግበር ብቻ ነበር። ወይም ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ያስተላለፉት መልዕክት እንድምታ ይህን ይመስል ነበር። ፦ አንተ ከእኔ ጋር ተጎዳኝተህ መታገስ ቀላል ጉዳይ አይሆንልህም። እንዲሆንልህም አይጠበቅም። ምክንያቱም የዚህ አይነት እውቀት ማስተናገድ የምትችልበት ባህሪ የለህም። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ አሉ፦ (ሙሳ) «አላህ የሻ እንደ ኾነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡ (አል ከህፍ 69) ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) እኔን ተከትለህ ለመሄድ ከተስማማህ ሚስጥሩን እስከምነግርህ ድረስ ስለምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ በማለት አስጠነቀቋቸው። «ብትከተለኝም ለአንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር አትጠይቀኝ» አለው፡፡ (አል ከህፍ 70) በዚህ መልኩ ተስማምተው የታወቀ ጉዟቸውን ጀመሩ። የዚህን በጥበብና በትምህርት የተሞላ ጉዞ ዝርዝር ቁርአን በ አማረ ሁኔታ ተርኮታል። ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) መረክብ ተሳፍረው ጉዟቸውን በበሀር ላይ ቀጠሉ በመሀል ጉዞ ላይ ሲደርሱ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) መርከቧን ቀደዷት። ይህን የተመለከቱት ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) አላስቻላቸውም እንድህ አሉ፦ ኼዱም፡፡ በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ ቀደዳት፡፡ «ባለ ቤቶቿን ልታሰጥም ቀደድካትን ትልቅ ነገርን በእርግጥ ሠራህ» አለው፡፡ (አል ከህፍ 71) በዚህን ጊዜ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ከኔ ጋር ታግሰህ መማር አትችልም አላልኩህም ነበር በማለት ከዚህ በፊት የተባባሉትን ለ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) አስታወሷቸው። «አንተ ከኔ ጋር ትእግሥትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን» አለ፡፡(አል ከህፍ 72) ሙሳም (ዐለይሂ ሰላም) ለኸድር እንድህ በማለት መለሱ፦ «በረሳሁት ነገር አትያዘኝ፡፡ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ» አለው፡፡ (አል ከህፍ 73) https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama ይ ቀ ጥ ላ ል.......
Показати все...
ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

💚 ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ አላህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል‥ አላህ ያውቃል #በአላህ_ምርጫዎች_ተማመን  1

https://t.me/Golden_Speech

2

https://t.me/ALJUEDDAAWA

3 http://telegram.me/QURAN_YELB_BREHAN 4

https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama

ሙሳ እና ሐሩን ( (ዐለይሂሙ ሰላም) 🌾ክፍል ስልሳ አምስት🌾 ============== ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) ===================== ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ከ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ጋር በነበራቸው ቆይታ ሶስት ነገር ብቻ ተምረው ግን መታገስ ባለመቻለቸው የተሰጣቸውን ቻንስ አለቀ እናም ፍቹን እነግርህና የኔ ና ያንተ ጓደኝነት እዚህ ላይ ያበቃል በማለት ፍቹን ይተርኩለት ገቡ፦ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የመጀመሪያ መታገስ ያልቻሉባት ትምህርት መርከቢቷ ነበረች እናም ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) መርከቢቷን ለምን እንደቀደዷት ምክናየቱን እንድህ ሲሉ አስረዱት ፦ ይች መርከብ የሚስኪኖች ስራ መስሪያ ስትሆን አሁን መርከቦችን ሁሉ የሚወርስ ንጉስ ይመጣል እናም ይችን የቀደድኳት ንጉሱ የተቀደደች ናት እና አልፈልጋትም ብሎ እንዲተውላቸው ብየ ነው አላቸው። «መርከቢቱማ በባሕር ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች፡፡ ከኋላቸውም መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚይዝ ንጉሥ ነበረና፤ (እንዳይቀማቸው) ላነውራት ፈቀድኩ፡፡(አል ከህፍ 79) ወደ ሁለተኛው ትምህርት መጣ እርሱም ወጣቱ ልጅ ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ንግግሩን ቀጠለ፦ ያን ወጣት ልጅ የገደልኩትማ እርሱ አላህን ፈሪ የሆኑ አባት እና እናት አሉት እናም ለወደፊት ይሄ ልጅ አድጎ በትዕቢት ተሞልቶ ወላጆቹን በክህደት እንዳያስገድዳቸው ስለተፈራ ነው አላቸው። «ወጣቱም ልጅማ ወላጆቹ ምእመናን ነበሩ፡፡ (ቢያድግ) ትእቢትንና ክህደትንም የሚያስገድዳቸው መኾኑን ፈራን፡፡ (አል ከህፍ 80) እናም በእርሱ ምትክ አላህ በፀባይም በማዘንም ከእርሱ የበለጠን እንዲሰጣቸው በማሰብ ነው ይሄን ያደረኩት አላቸው። «ጌታቸውም በንጹሕነት ከእርሱ በላጭን በእዝነትም ከእርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን፡፡* (አል ከህፍ 81) በ አላህ ፍቃድ ኸድር (አለይሂ ሰላም) ልጁን ከ አኼራ ቅጣት ታደጉት ምክናየቱም ልጁ ቢያድግ እርሱም ጠሞ ቤተሰቦቹንም ያጠም ነበር ነገር ግን ኸድር ገና በልጅነቱ ገደሉት እርሱም ልጅ ስለሆነ ከ አላህ ቅጣት ይድናል ለ አቅመ አዳም አልደረሰምና። ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ሶስተኛውን ፍቻቸውን ቀጠሉ እርሱም በረሀብ አንጀታቸው ቀጥ አድርገው የሰሩት ግድግዳ እና ክፍያ ያልጠየቁበትን ምክንያት ነው ሚያብራሩት እንድህ ነበር… ግድግዳው በከተማይቱ የነበሩ የሁለት የቲሞች ነው። እናም እዛ ቤት ውስጥ አባታቸው ከመሞቱ በፊት ወርቅ ቀብሮላቸው ነበር። ልጆቹ ሲያድጉ አውጥተው እንዲጠቀሙበት። እናም ግድግዳው ተበላሽቶ ከፈራረሰ ያ ቦታ ምን እንደነበር ይጠፋል ልጆቹም ያን ገንዘብ ሳያገኙ ይቀራሉ። ግድግዳውን የሰሩበትን ደግሞ መቀበል ያልፈለጉት ልጆቹ የቲም ስለነበሩ የየቲም ገንዘብ መብላት ስለማይቻል ነው። «ግድግዳውማ በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር፡፡ በሥሩም ለእነርሱ የኾነ (የተቀበረ) ድልብ ነበረ፡፡ አባታቸውም መልካም ሰው ነበር፡፡ ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ፡፡ በፈቃዴም አልሠራሁትም፡፡ ይህ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍች ነው» (አለው)፡፡ (አል ከህፍ 82) እናም ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ቁርአኑ ላይ እንደተገለፀው ፍቹን ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ከነገሯቸው በኋላ ይህን ተግባር በፍቃዴ አልሰራሁትም ሁሉም የ አላህ ትዛዝ ነበር። በማለት ከራሳቸው ፈልስፈው እንዳልሰሩት ተናገሩ። ነብዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ሰላም) ወንድሜ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ታግሶ በነበር ብዙ ትምህርቶችን እኖስድ ነበር አሉ። እናም ያ የወርቅ ድልብ ልጆቹ አድገው ሲያወጡት እላውላይ ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሀመድ ረሡለሏህ የሚል ፅሁፍ እንደነበረው ብዙ የሀዲስ ዘጋቢወች አስፍረዋል። የኛ ነብይ ሙሀመድ (ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም) በበፊት የነበሩት አማኞች ሁሉ ወደፊት እንደሚላኩ የግድ ያምኑባቸው የነበሩ ታላቅ ነብይ ናቸው። (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ይ ቀ ጥ ላ ል........
Показати все...
ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) 🌾 ክፍል ስልሳ ሁለት •°°°°°°°°°°°°°°°°°• ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) ሙሳ እና ጓድኛቸው ምሳቸውን ለመብላት በተቀመጡበት ሰአት ጓደኛቸው አሳውን መርሳቱን አስታወሰ። አሳው አልፈውት ወደ መጡት በሀር ውስጥ እንደገባ ለሙሳ ነገራቸው። በሰአቱ እንዳይነግራቸው ጉዳዩን ሰይጣን እንዳስረሳው አሳወቃቸው። ሰይጣን ሁሌም የሰወችን ስኬት አይፈልግም እናም ሙሳ ኸድርን አግኝተው እውቀት እንዳይቀስሙ በድካም አሰልችቶ ሳያገኙት እንዲመለሱ ነበር ፍላጎቱ ግን አልተሳካም። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ጓደኛቸው ይሄን እንደነገራቸው የምንፈልገው ይሄን አይደል በቃ አሳው ወደ ገባበት በሀር መመለስ አለብን አሉ። (ሙሳም) ይህ እንፈልገው የነበርነው ነው አለው፡፡ በፈለጎቻቸውም ላይ እየተከተሉ ተመለሱ፡፡ ( አል ከህፍ 63) የመጡበትን የእግራቸውም ኮቴ እየተመለከቱ ወደ በሀሩ ተመለሱ። በሀሮቹ መጋጠሚያም እንደደረሱ ኸድርን አገኙት። ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከእኛም ዘንድ ዕውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያ (ኸድርን) አገኙ፡፡* (አል ከህፍ 64) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ያን ወሕይ የነገራቸውን ሰው አገኙት። ተራ የሆነ ልብስ ለብሶ ከቋጥኝ ጀርባ ላይ ተቀምጧል። ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ… እኔ ሙሳ ነኝ! አሉት። ሙሳ በኒ እስራኤል? ብሎ ጠየቃቸው። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) አዎን! አላህ ያሰወቅህን እንድታስተምረኝ መጣሁ አሉት። ከሰው ሁሉ የላቀ አዋቂ ነው ነው ብሎ አላህ የነገረኝ ሰው አንተ ነህ? በማለት ጥያቄ አስከተሉ። ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ በማለት መለሱላቸው… ሙሳ ሆይ! እኔ ከ አላህ እውቀት ውስጥ አንተ የማታውቀውን ጥቂት ነገር አውቃለሁ። አንተም ከ አላህ ዕውቀት ውስጥ እኔ የማላውቀውን ጥቂት ነገር ታውቃለህ። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ለኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ይህን ዕውቀት ለመገብየት ያላቸውን ጥልቅ ፍላጎት ነገሯቸው። ከእሳቸው ዘንድ እንግዳ እና አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን መማር ፈልገዋል በሌጣ አዕምሮ ለመረዳት የሚከብዱ ዕውነታዎችን ለመቅስም ጓጉተዋል። ቁርአን… ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን» አለው፡፡ (አል ከህፍ 66) ኸድርም (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ አሏቸው፦ (ባሪያውም) አለ «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም፡፡ (አል ከህፍ 67) «በዕውቀትም በእርሱ ባላዳረስከው ነገር ላይ እንዴት ትታገሳለህ»(አል ከህፍ 68) https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg ይ ቀ ጥ ላ ል .......
Показати все...
ወርቃማ ንግግሮች

ሃይማኖትህ የልብህ ምግብ ነው!! የምግብህ ዋና ክፍል ደግሞ ተውሂድ ነው!

https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg

ለስተታችን መታሪሚያ ፣ ለነጋችን መቃናት ፣ ለአብሮነታችን ለተቃና መንገድ ፣ በሃሳብ ተደግፈን በሃሳብ ደግፈን ስንተራረም ዘላቂነት ያለው ደስታና ያማረ ጉዞ አብረን እንዘልቃለን። @Golden_SpeechBot

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም ) 🍂 ክፍል ስልሳ አንድ 🍂 *•°°°°°°°°°°°°°°°°°°•* ኸድር እና ሙሳ (ዐለይሂሙ ሰላም) ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ከጨንቋኙ ፊርአውን ከተገላገሉ በኋላ ህዝባቸውን በሚመስጥና በሚማርክ ዳዕዋ ሰቧቸው በዚህ ንግግራቸው የተማረከው አንዱ ተከታያቸው ጠየቃቸው። አንቱ የ አላህ ነብይ! ምድር ላይ ከእርሰወ የበለጠ ዕውቀት ያለው ሰው አለን? ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ አሉ፦ እኔ መኖሩን አላውቅም! በዚህን ጊዜ አላህ ወህይ አወረደላቸው፦ ከባህሮቹ መገናኛ ላይ ከባሮቼ ውስጥ አንዱን ባሪያዩን ታገኘዋለህ። ከእኔ ዘንድ ልዩ የሆነ ዕውቀት ሰጥቸዋለሁ። ከሕዝቦች የመረጥከውን አንድ ሰው ይዘህ ወደዚህ ባሪያዬ ሂድ! አላቸው። ይህ ሰው ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) ነበሩ። ኸድር (ዐለይሂ ሰላም) አላህ ትልቅ እውቀት የሰጣቸው ሰው ነበሩ ነብይ እንደሆኑም ይነገራል። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ይህን ሰው ለማግኘት ጉዞን አሰቡ አላህ (ሱብሀነሁ ተዐላ) የሞተ አሳን በዘንቢል እንዲይዙ አዘዛቸው። ከባህሮቹ መገናኛ ሲደርሱ ዐሳዋ ወደ ሂወት ተመልሳ ውሃው ውስጥ ከምትጠልቅበት ቦታ ላይ ኸድርን ታገኛቸዋለህ አላቸው። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የእህታቸውን ልጅ ዩሽዕ ኢብኑ ኑንን አስከትለው ወደ ተነገራቸው ቦታ ጉዞ ጀመሩ። ቁርአን ታሪኩን ያወሳዋል… ሙሳም ለወጣቱ «የሁለቱን ባሕሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምኼድ ድረስ (ከመጓዝ) አልወገድም» ያለውን (አስታውስ)፡፡ (አል ከህፍ 60) ይህ የቁርአን አያ ሙሳ ይህን እውቀት አለው የተባለውን ሰው ለማግኘት እንዴት እንደጓጉ ይገልፃል። ምንም እንኳ አላህን ያናገሩ ታላቅ ነብይ ቢሆኑም ለእውቀት የነበራቸው ፍቅር ግን ልዩ ነው። የቱንም ያክል ቢርቅ ኸድርን ለማግኘት ቆርጠው ተነስተዋል። ጉዟቸውን ቀጠሉ በሁለቱ በሀሮች ሲደርሱ አሳውን ረሱት አሳው ሂወት ዘርቶ ከዘንቢሉ ወቶ ወደ በሀሩ ገባ። ሙሳ እና ጓደኛው ባለማየታቸው ዝም ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ። የሁለቱን መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዐሣቸውን ረሱ፡፡ (ዐሣው) መንገዱንም በባህሩ ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ፡፡ (አል ከህፍ 61) አሳውን በመርሳታቸው ጉዞው ረዘመባቸው መንገድ ላይ አረፍ አሉ ርቧቸውም ነበርና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ጓደኛቸውን ጉዞው አድክሞናል እና ምሳ እንብላ አሉት። ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን፡፡ ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና» አለ፡፡ (አል ከህፍ 62) በዚህን ጊዜ ጓደኛቸው ምሳውን ሊያወጣ ሲል አሳው ትዝ አለው ከሁለቱ በሀሮች መጋጠሚያ እንደገባ። «አየህን ወደ ቋጥኝዋ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሣውን ረሳሁ፡፡ ማስታወሱንም ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፡፡ በባሕሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ (መንገድ) አድርጎ ያዘ» አለ፡፡ (አል ከህፍ 63) https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama ይ ቀ ጥ ላ ል .........
Показати все...
ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

💚 ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ አላህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል‥ አላህ ያውቃል #በአላህ_ምርጫዎች_ተማመን  1

https://t.me/Golden_Speech

2

https://t.me/ALJUEDDAAWA

3 http://telegram.me/QURAN_YELB_BREHAN 4

https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) 🍃ክፍል ስልሳ🍃 ========== ቃሩን በኩራቱ ቀጠለ አንዴ ሰወች በተሰበሰቡበት ቦታ አምሮና ተውቦ በጌጣጌጥ አሸብርቆ ወጣ። በዚህን ጊዜ በኢማን ደካማ እና የዚህችን ብልጭልጭ አለም ከጃይ የሆኑ ሰወች ሲመለከቱት ተልባቸው ወደሱ በመሳብ ምን አለ ለእኛም እንደሱ ሀብት በተሰጠን ብለው ተመኙ። በሕዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ኾኖ ወጣ፡፡ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ብጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና» አሉ፡፡(አል ቀሶስ 79) በዚህን ጊዜ አላህን የሚፈሩት ሰወች ወየውላችሁ የ አላህ ምንዳ ከዚህ እናተ ከምትመኙት ነገር በጣም በላጭ ነው። ለገንዘብ እንደዚህ አትሁኑ የ አላህን ምንዳ ማግኘት ከፈለጋችሁ ባላችሁ ሂወት ተብቃቅታችሁ መታገስ አለባችሁ ሲሉ ገሰፃቸው። እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ለአመነ ሰው መልካምንም ለሠራ በላጭ ነው፡፡ ታጋሾችም እንጅ ሌላው አያገኛትም» አሉ፡፡(አል ቀሶስ 80) ቃሩን የትኛውም ግሳፄ ና ተዐምር ከጥመቱ ሊመልሰው አልቻለም። በድርቅናው ቀጠለ ዘካንም ከለከለ በዚህን ጊዜ አላህ መጥፎ አያያዝን ያዘው። መሬቷ ከነ ሀብት ንብረቱ ወደ ውስጧ ዋጠችው ከነ ሂወቱ መሬት ውስጥ ገባ። በእርሱም በቤቱም ምድርን ደረባን፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ጭፍሮች ምንም አልነበሩትም፡፡ ከሚርረዱትም አልነበረም፡፡ (አል ቀሶስ 81) ወደ ዱኒያ በማዘንበሉና ሌሎችን በመመቅኘቱ ቃሩን በቁሙ መሬት በላችው። ቃሩን ሀብቱ ሊጠቅመው አልቻለም የሱ ግብረ አበሮችም ሊረዱት አልቻሉም አገር እያየው ወደ መሬት ወረደ ገንዘቡ ለ ለዘመድ ይቅር እንኳ አልተባለም። ቃሩን እስካሁን ድረስ ከነ ሀብት ንብረቱ በቀን የ አንድ ሰው ቁመት ያክል ወደ ታች ይወርዳል። የውመል ቂያማ ሲደርስ እርሱም መጨረሻውን ያገኛል። ከዛም ወደ ተቀጣጠለችው የጀሀነም እሳት ይገባል። ትናት እንደዛ አጊጦ ሲመለከቱት የሱን ቦታ ሲመኙ የነበሩ ሰወች አይናቸው እያየ ሲሰጥም ተፀፀቱ። እንድህ አሉ… እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ አላህ በእኛ ላይ (በእምነት) ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር፡፡ ወይ ጉድ! ከሓዲዎች አይድኑም» የሚሉ ኾነው አነጉ፡፡(አል ቀሶስ 82) ቃሩን በዚህ ሁኔታ ፍፃሜውን አገኘ ምድር ላይ አለን ብለው ሲንቀባረሩ የነበሩ ሁሉ ፍፃሚያቸው በሚያስጠላ መልኩ ተፈፅሟል አላህ እንድህ ይላል… ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም (አጠፋን)፡፡ ሙሳም በተዓምራቶች በእርግጥ መጣባቸው፡፡ በምድርም ላይ ኮሩ፡፡ አምላጪዎችም አልነበሩም፡፡(አል አንከቡት 39) ሁሉንም በኅጢኣቱ ያዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡(አል አንከቡት 40) https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama ይ ቀ ጥ ላ ል .........
Показати все...
ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

💚 ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ አላህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል‥ አላህ ያውቃል #በአላህ_ምርጫዎች_ተማመን  1

https://t.me/Golden_Speech

2

https://t.me/ALJUEDDAAWA

3 http://telegram.me/QURAN_YELB_BREHAN 4

https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) ♥ክፍል ሀምሳ ዘጠኝ♥ ============== ቃሩን °°°°° ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ፍፁም አይተዋት የማያውቁትን ሴት ነበር በሰወ ላይ እንትቀጥፍ እና እንዲዋረዱ ለማድረግ ቃሩን ያቀደው። የተዘጋጀችውም ሴት ከሕዝቡ መሀል ወታ ቆመች። የታዘዘችውን ቅጥፈት ለመናገር ስትሞክር ግን ምላሷ ተቆለፈ። ቃል ማውጣት ተሳናት። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) በንዴት ጠየቋት፦ አንች ሴት ! ባህርን በለየው ፣ ተውራትን ባወረደው፣ ጌታ በ አላህ ይሁንብሽ፤ በእውነት መልሺልኝ፦ አውቅሻለሁ ወይ ? ካንች ጋር ግንኙነት አለኝ ወይ? በዚህን ጊዜ ሴትዩዋ በፀፀት ተናገረች፦ ሙሳ ሆይ! በጣም ብዙ ገንዘብ በመስጠት ያታለለኝ እና ይህን ቅጥፈት እንድቀጥፍበዎ ያግባባኝ ቃሩን ነው። ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ሱጁድ ወረዱ፦ ይህ ተንኮሉ በዚህ መልክ ተፈታ ገንዘብ የከፈላት ሴት እርሱኑ አጋለጠችው። ቃሩን አላህ ብዙ ሀብቶችን ሰጠው ሀብቱ ቀርቶ የሀብቱ መያዣ የካዝናውን ቁልፍ በጋርዶች ነበር የሚያሲዘው። አላህ በቁርአን እንድህ ሲል ይገልፀዋል፦… ቃሩን ከሙሳ ነገዶች ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ አመጸ፡፡ ከድልቦችም ያንን መከፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችን (ሸክሙ) የሚከብድን ሰጠነው፡፡ ወገኖቹ ለእርሱ አትኩራ፤ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና ባሉት ጊዜ (አስታውስ)፡፡ (አል ቀሶስ 76) አላህ የዚህ ሀብት ባለቤት አደረገው። ታዳ ሙሳ አንድ ቀን ሂደው ዘካ ማውጣት ያለበትን ያክል አስልተው ነገሩት። ቃሩን እንድህ አላቸው፦ አሁን አይኖችህን ከገንዘቤ ላይ ንቀል ። ይህን ገንዘብ ለፍቸ ያመጣሁት ራሴ ነኝ!… «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» (አሉት)፡፡ (አል ቀሶስ 77) በዚህን ጊዜ የኩራተኛ መልስ መለሰ፦ ቁርአን… (ሀብቱን) «የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው አለ፡፡(አል ቀሶስ 78) በዚህን ጊዜ አላህ ከሱ በፊት በሀይልም በሀብትም የት እንድረስ ያሉትን ሰወች ከዛም አላህ እንዳልነበሩ እንዳደረጋቸው እሱንም ከነሱ ማድረግ እንደሚችል አስታወሰ እንደነ ፊርአውን ሀማን ቁርአን… አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኀይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን (ሀብትን) በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መኾኑን አያውቅምን አመጸኞችም ከኀጢኣቶቻቸው (ምሕረት የሚከተለውን ጥያቄ) አይጠየቁም፡፡(አል ቀሶስ 78) https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama ይ ቀ ጥ ላ ል .........
Показати все...
ላኑፈሪቁ ኢላ የዉመል ቂያማ የዳዕዋ ቻናል

💚 ልቦች የሚመኙትን ነገር ይለምናሉ አላህ ደግሞ በሚሻላት እና በሚበልጠው ነገር ይመልስላታል‥ አላህ ያውቃል #በአላህ_ምርጫዎች_ተማመን  1

https://t.me/Golden_Speech

2

https://t.me/ALJUEDDAAWA

3 http://telegram.me/QURAN_YELB_BREHAN 4

https://t.me/lanufiriquelayewmelqiyama

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂም ሰላም) ⚂ክፍል ሀምሳ ሰባት⚂ ============== ቃሩን °°°°° ቃሩን ከሙሳ ነገዶች ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ አመጸ፡፡( አልቀሶስ 76) ቃሩን የ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ያጎታቸው ልጅ ነበር። ተውራት ለሙሳ ከወረደላቸው ጀምሮ ተውራትን አብዝቶ በማንበብ ይታወቅ ነበር። በጣምም ድህነትም የጠናበት በሌሎች እርዳታ ብቻ የሚኖር ሰው ስለነበር ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዱአ አደረጉለት። ወርቅ የማንጠርና የመስራት ጥበብ ተሰጠው። #ቃሩን በ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ከማመኑ በፊት ከፊርአውን ዘንድ የእስራኤላዊያን ተጠሪ ነበር። በእርሱ ስር የሚሰሩትን በጣም ያሰቀይ ነበር። በሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ካመነ በኃላ ዕውቀት፣ ጥበብና ዐቢድነት ተሰጠው። ነገር ግን የተረገመው ሸይጧን በሰው ተመስሎ በመቅረብ ቀስ በቀስ የልብ ጓደኛ አደረገው። የተመቻቸለትን አጋጣሚ ተጠቅሞ እንድህ አለው፦… አንተ ቃሩን! ሁል ጊዜ በሰወች ችሮታ ከምንኖር አንድ ቀን እየሰራን የቀሩትን ስድስት ቀናት ብናመልክ አይሻልም! ቃሩን በቀረበለት ሀሳብ ተደነቀ። ወደ ከተማ አብረው በመሄድ ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ ዋሉ። የቀሩትን ስድስት ቀናት አንድ ቀን ሰርተው ባገኙት ገቢ እየተጠቀሙ አላህን በመገዛት አሳለፉ። ሸይጧን የመጀመሪያ እርምጃውን ካሳካ በኃላ አሁን ደግሞ እንድህ አለው፦… ኦ ቃሩን! የአንድም ሰው እርዳታ ሳያስፈልገን መኖር ቻልን። ይኸውልህ የሳምንቱን ግማሽ ቀናት በርትተን በመስራት ጠቀም ያለ ገንዘብ እናግኝ የቀሩትንም ቀናት እናምልክባቸው፤ በዚህ መልኩ የምናገኛቸውን ትርፍ ገንዘብ በ አላህ መንገድ በማውጣት ለድሆች እናም ለችግረኞች በመስጠት እኛም ለ አላህ ብለን የመስጠትን እድል እናገኛለን። ቃሩን ወዳጁ ባቀረበለት ሀሳብ ካለፈው የበለጠ ተሳበ። በሃሳቡ ተስማማ። ሸይጧን ያሰበው ተሳካ። መስመሩ ውስጥ ገባለት። የስራ ጊዜ እየበዛ ሄደ። ቃሩን ቀስ በቀስ ዱኒያዊ ሂወት ውስጥ ተነከረ። በፍቅሯ ተያዘ። እቅፏ ውስጥ ገባ። በሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዱዐ አማካኝነት አላህ (ሱብሀነሁ ተዐላ) በሰጠው ጥበብ ተጠቅሞ በሃብት ተጥለቀለቀ። ልቡ በዱኒያ ስስት ተሞላች። ቀድሞ የነበሩትን ባህሪያት ሁሉ አጣ። ሃብቱ ሲጨምር ስነምግባሩ ጎደለ። ዱኒያ አካበተ ስነምግባሩ ግን ነጠፈ። ልቡ በዱኒያ ፍቅር የተሞላችው ቃሩን የሙሳን ምክሮች ማጣጣል ጀመረ። ቁርባኖችን የማረድ ሀላፊ የነበሩት የራሱ ወገኖች ናቸው። እና ለሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) በተሰጡ ጊዜ በውስጡ ደብቆ ያስቀመጣቸው አስቀያሚ ባህሪወቹ እንደ ንጋት ጀንበር ብቅ ማለት ጀመሩ። በጣም ተቆጣ። ራሱን መቆጣጠር አቃተው። https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg ይቀጥላል…
Показати все...
ወርቃማ ንግግሮች

ሃይማኖትህ የልብህ ምግብ ነው!! የምግብህ ዋና ክፍል ደግሞ ተውሂድ ነው!

https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg

ለስተታችን መታሪሚያ ፣ ለነጋችን መቃናት ፣ ለአብሮነታችን ለተቃና መንገድ ፣ በሃሳብ ተደግፈን በሃሳብ ደግፈን ስንተራረም ዘላቂነት ያለው ደስታና ያማረ ጉዞ አብረን እንዘልቃለን። @Golden_SpeechBot

ሙሳ እና ሐሩን (ዐለይሂሙ ሰላም) ⚄ክፍል ሀምሳ ስምንት⚄ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ቃሩን የቁርባን ማረድ ሀላፊት ለ ሐሩን በመሰጠቱ እጅግ በመቆጣት ለሙሳ እንድህ አለው ፦ ሙሳ ሆይ! ቁርባን የማረድን ማዕረግ ለወንድምህ ሐሩን ሰጠኸው። እኔ ተውራትን ከማንም በላይ አሳምሬ እንደማነብ እያወክ ተመሳሳይ ቦታ አልሰጠህኝም። ይህን በደል እንዴት መታገስ እችላለሁ? ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) እንድህ በማለት መለሱለት… ለሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) ይህንን ሀላፊነት የሰጠሁት እኔ አይደለሁም አላህ (ሱብሀነሁ ተዐላ) ነው። ቃሩን ይህንን ካላረጋገጥክልኝ በጭራሽ የምትለውን አልቀበልም! አለ። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የእስራኤላዊያንን መሪወች ሰብስበው እንድህ አሉ… ምርኩዞቻችሁን አምጡ! ሁሉንም ከ አንድ ቦታ ላይ አኑሩ። የምርኩዙ ቀለም ወደ አረንጓዴነት የተቀየረችለት ሰው ቁርባን የማረድ ማዕረግ ለመቀበል የተገባ ሰው ነው። አሉት። ምርኩዞቻቸውንም አመጡ ከሚያመልኩበት ቦታ ላይ ተኖሩ። የሃሩን (ዐለይሂ ሰላም) ምርኩዝ ብቻ አረንጓዴ ሆነች። አረንጋዴ ቅጠሎችንም አበቀለች። ይህ መለኮታዊ ተዐምር ሲፈፀም ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ወደ ቃሩን ዞሩና… ቃሩን እኔ ነኝ እንዴ ይሄን ያደረኩት? አሉት። ቃሩን ተደናገጠ። ያየውን እውነት መቀበል ግን አልፈለገም። ነፍስያው ያለችውን ተከትሎ ነጎደ። ይህ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም! አላቸው። በቁጣ እንደነደደም አካባቢውን ለቆ ሄደ። ትዛዞችን ሁሉ መጣስ ጀመረ። አላህ (ሱብሀነሁ ተዐላ) ሰመያዊ ቀበቶ እንዲታጠቁ እስራኤላዊያኖችን አዘዛቸው። ቃሩን ይህንንም ይህ መሪወችን ከባሪያወች ለመለየት የተደረገ ነው። በማለት አሁንም ተቃወመና ሳይታጠቅ ቀረ። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ለ ቃሩን ህመም ሆኑበት። ምቀኝነት የሰራ አካላቱን አቃጠለው። ሁለመናው ተንገበገበ። ሰወችን በግብዣ እያንበሸበሸ ትኩረት ለመሳብ ሞከረ። ይሄ አልበቃው ብሎ የፈጠራ ታሪክ በመፍጠር ሙሳን ማናደድ ፈለገና እስራኤላዊያንን በማሰባሰብ ሙሳን (ዐለይሂ ሰላምም) በማስጠራት እንድህ አላቸው። አሁን አንተ ሙሳ! በነዚህ ጉዳይወች ላይ የ አላህ ትዛዝ ምን እንደሚል እንድትነግረን እንፈልጋለሁ። የሰረቀ ሰው ቅጣቱ ምንድን ነው? ዝሙት የፈፀመ ሰውስ? ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) መለሱለት፦ የሰረቀ ሰው እጁ ይቆረጣል። ዝሙት የሰራም ይወገራል። ቃሩን ጥያቄውን ደገመ… ጥፋተኛው አንተ ብቶንስ? ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) መለሱለት፦ ያው ተመሳሳይ ቅጣት ። ይህን መልስ እንደሰጡ፣ ቃሉ ከህዝቡ መሐል አንዷን ሴት ተጣራ ቀደም ብለው ወራዳ የሆነ ስምምነት አድርገው ነበር ቃሩን እንዲህ አለ። አንች ሴት ነይ ቅረቢና ባንች እና በሙሳ መካከል የተፈፀመውን አስቀያሚና ሞራል የጎደለው ድርጊት ንገሪን አላት። ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) በዚህ ቅጥፈት ተቆጡ። የሚያደርጉት ጠፋቸው። https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg ይ ቀ ጥ ላ ል.......
Показати все...
ወርቃማ ንግግሮች

ሃይማኖትህ የልብህ ምግብ ነው!! የምግብህ ዋና ክፍል ደግሞ ተውሂድ ነው!

https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzTZHgg

ለስተታችን መታሪሚያ ፣ ለነጋችን መቃናት ፣ ለአብሮነታችን ለተቃና መንገድ ፣ በሃሳብ ተደግፈን በሃሳብ ደግፈን ስንተራረም ዘላቂነት ያለው ደስታና ያማረ ጉዞ አብረን እንዘልቃለን። @Golden_SpeechBot