cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Aduliz Chronicle

Aduliz Chronicle, a digital magazine based in Addis Ababa develops and presents inspiring business-related and other stories from across Ethiopia and all around the world in English, Amharic, Afaan Oromo, Tigrinya, and other local languages.

Більше
Ефіопія10 831Амхарська8 924Категорія не вказана
Рекламні дописи
193
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ዜና እረፍት🕯 ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ! እዉቁ እና ተወዳጁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ አስታዉቋል። ከ50 ዓመታት በላይ በሚዚቃው ኢንዱስትሪው የቆየው ድምጻዊ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ኢትዮመረጃ በአርቲስቱ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። @EthioipaNews @Adulichronicle
Показати все...
Photos from South Africa
Показати все...
ሰበር ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለሸ በደቡብ አፍሪካ ሲያደርግ የነበረውን የሰላም ንግግር ውጤት ዛሬ ይፋ ተደርጓል። የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የፌደራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ይዘት ይፋ አድርገዋል። በዚህም በዘላቂነት ግጭት ለማቆምና አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል። Source: አል አይን @ Adulizchronicle
Показати все...
#እንድታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የፌስቡክ ገጹ (ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው) ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን አስታውቋል። አየር መንገዱ ፤ ደንበኞች እንዲሁም የገጹ ተከታታዮች በፌስቡክ ገጹ የሚተላለፉ ማንኛውም መልዕክቶች የአየር መንገዱ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ ችግሩን ለመፍታት በአሁኑ ሰዓት ከሜታ ኩባንያ ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። Source:@tikvahethiopia @Adulizchronicle
Показати все...
በአዲስ አበባ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ እንደሚጀመር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል። አቶ ጥራቱ በየነ ለኢዜአ የሰጡት ቃል፦ - በመታወቂያ አሰጣጥና እድሳት ዙሪያ ለተስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ዘላቂ እልባት በመስጠት ችግሩን ለመፍታት አገልግሎቱ በጊዜያዊነት እንዲቆም ተደርጎ ነበር። - በብልሹ ተግባሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮችና ሰራተኞችን በመለየት ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተከናውኗል። - በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተለይም ችግሩ ጎልቶ በታየባቸው 37 ወረዳዎች በተደረገ ክትትል 90 አመራሮችና ባለሙያዎችን ተጠያቂ ተደርጓል። - ታግዶ የቆየው #የመታወቂያ_እድሳት ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ ይጀመራል። ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆንኑአሰራሩን የማዘመን ስራ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡ - በአሁኑ ወቅት የራሳቸው መለያና ምሥጥራዊነት ያላቸው መታወቂያ ለመስጠት የሚያገለግሉ ወረቀቶች በመታተም ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ለነዋሪው የመስጠት ተግባር ይከናወናል ብለዋል። #ኢዜአ
Показати все...
#Kenya #Ethiopia የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሀገር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል። ነገ በአዲስ አበባ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚታደሙ የተነገረላቸው ሩቶ ፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ይመክራሉ። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ምርጫ ማሸነፋቸው በIEBC በተገለፀበት ዕለት ከዓለም ሀገራት መሪዎች ሁሉ በቅድሚያ የ " እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት ያስተላለፉላቸው መሪ እንደነበሩ ይታወሳል። @tikvahethiopia @Adulizchronicle
Показати все...
ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲደራደር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ! ህወሓት የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲደራደር ያቀረበለትን ጥሪ መቀበሉን አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስትም በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ በአፍሪካ ህብረት በኩል ከህወሓት ጋር እንዲደራደር የቀረበለትን ጥሪ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ህወሓት የተደራዳሪ ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ለቀረበላቸው የድርድር ጥሪ ምስጋና ያቀረቡት ቃል አቀባዩ ህወሓት በደቡብ አፍሪካ በታቀደው ድርድር ይሳተፋል ብለዋል፡፡ ግጭት ማቆም የድርድሩ አጀንዳ መሆኑን ወቅ ጠቃሚ ይሆን ነበር ያሉት ቃል አቀባዩ ግልጽ እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸው ነጥቦች አሉ ብለዋል፡፡በድርደሩ እንደ ታዛቢ፣ ተሳታፊ እና ዋስትና ሰጭ የሚጋበዙ ተጨማሪ አካላት ስለመኖራቸው እንዲሁም የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ስለሚኖረው ሚና ማብራሪያ እንደሚገልግ አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅሰዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የተደራዳሪ ቡድኑ የጸህንነት ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ Via Alain @EthioipaNews @Adulizchronicle
Показати все...
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች‼️ ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦ •  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ • ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ • ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ • ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ •  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ • ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ • ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ • ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ • ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ • ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል • ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ • በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት • ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል • ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል። በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል። @Aduliazchronicle
Показати все...