cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ገድለ ቅዱሳን

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Більше
Рекламні дописи
6 672
Підписники
+324 години
-27 днів
-730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ ❖   ሰኔ -  ፬  -  ❖ [ ✞ እንኩዋን ለታላቁዋ ሰማዕት "ቅድስት ሶፍያ" እና ለቅዱስ "ዮሐንስ ዘሐራቅሊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ] † 🕊   ሶፍያ [ SOPHIA ]   🕊 † ሶፍያ [ "ያ" የሚለው ላልቶ ይነበብ ] በቀደመው ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተወዳጅ ስም ነበር:: ዛሬ ብዙ አሕዛብ ሲጠሩበት ብንሰማም ትርጉሙ "ጥበበ ክርስቶስ" የሚል ነው:: በዚህ ስም የሚጠሩ አያሌ ቅዱሳት አንስት ሲኖሩ አንዷ ዛሬ ትከበራለች:: † 🕊 ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት  🕊 † ቅድስቷ የተወለደችው በምሥራቅ ሮም ግዛት ውስጥ በ ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ዘመኑ የጭንቅ : የመከራ በመሆኑ ሕዝቡ በስደት ይኖር ነበር:: የቅድስት ሶፍያ ወላጆች ክርስቲያኖች ናቸውና በመልካሙ መንገድ በንጽሕና አሳድገዋታል:: ባለጠጐች በመሆናቸው አገልጋይ ቀጥረውላት : ያማረ ቤት ሰርተውላት በዚያ ትኖር ነበር:: ሁሉ ያላት ብትሆንም ሁሉን ንቃ በጾምና በጸሎት ትኖር ነበር:: ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለከተማው መኮንን [ገዢ] ሊድሯት መሆኑን አወቀች:: ወደ ቤቷ ገብታ ፻ [100] ጊዜ ሰገደች:: ወደ ፈጣሪዋም ጸለየች:- "ጌታየ ሆይ! የዚህን ዓለም ቀንበር አታሸክመኝ:: አልችለውምና:: ያንተው ቀንበር ግን የፍቅር ነውና እችለዋለሁ" አለች:: አገልጋዩዋን ጠርታ ብዙ ወይን አጠጥታት ልብስ ተቀያየሩ:: በሌሊትም ወጥታ ወደ በርሃ ሔደች:: ዓላማዋ ምናኔ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ግን ሌላ ነበር:: በመንገድ ብዙ ክርስቲያኖች በመከራ ብዛት ሲሰደዱ አገኘቻቸው:: እርሷ ስደትን አልመረጠችም:: እያጠያየቀች "ሰው በላ" ከተባለው አረመኔ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ ደረሰች:: በንጉሡ ፊት ቀርባ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አለችው:: ንጉሡ ከመልኩዋ ማማርና ከድፍረቷ የተነሳ አደነቀ:: ሊያባብላት: ሊያስፈራራትም ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው ጦር ባለው የብረት ዘንግ ደብድበዋታልና ደም አካባቢውን አለበሰው:: መሬት ለመሬት እየጐተቱ እሥር ቤት ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ፈውሷት ሔደ:: አንዴ በእሳት: አንዴም በስለት: ሌላ ጊዜም በግርፋት አሰቃዩዋት:: ከሃይማኖቷ ግን ሊያነቃንቁዋት አልቻሉም:: በመጨረሻ አንገቷን እንድትሰየፍ ንጉሡ አዘዘ:: ወታደሮቹም ፈጸሙት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቅድስት ሶፍያን በክብር አሳረጋት:: "ስምሽን የጠራ: መታሰቢያሽን ያደረገ ምሕረትን ያገኛል" አላት:: † 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ  🕊 † ቅዱሱ የነበረው በተመሳሳይ በዘመነ ሰማዕታት ነው:: አባቱ ዘካርያስ: እናቱ ኤልሳቤጥ: እርሱ ደግሞ ዮሐንስ ይባላል:: የሚገርም መንፈሳዊ ግጥጥሞሽ ነው:: የቅዱሱ ወላጆች የሃገረ ሐራቅሊ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ የተመሰከረላቸው ደጐች ነበሩ:: ዘካርያስ አርፎ ዮሐንስ በመንበሩ የተቀመጠው ገና በ ፳ [20] ዓመቱ ነበር:: በወቅቱ ከ፪ [2] አንዱን መምረጥ ነበረበት:: ፩. ለጣኦት ሰግዶ በምድራዊ ክብሩ መቀጠል ፪. ወይ ደግሞ በክርስትናው መሞት ቅዱስ ዮሐንስ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ነውና ፪ [2] ከባባድ ነገሮችን ፈጸመ:: በመጀመሪያ በአካባቢው ያሉ ጣዖት ቤቶችን አወደመ:: ቀጥሎ ወደ ንጉሡ ሔዶ በመኩዋንንቱ ፊት "ክርስቶስን የተውክ ሰነፍ" ብሎ ገሠጸው:: ከዚህ በኋላ በቅዱሱ ላይ የተፈጸመው መከራ የሚነገር አይደለም:: ያላደረጉት ነገር አልነበረም:: እሳቱ: ስለቱ: ሰይፉ: መንኮራኩሩ . . . ከሁሉ የከፋው ግን ቆዳውን ገፈው በእሳት ጠብሰውታል:: እርሱ ግን ስለ ሃይማኖቱ ይሕንን ሁሉ ታግሶ በዚህች ቅን አንገቱን ተሰይፏል:: አምላካችን እግዚአብሔር ግፍዐ ሰማዕታትን አስቦ እኛን ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ሶፍያ ተጋዳሊት ወሰማዕት ፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት] ፫. ቅዱስ ሳኑሲ ሰማዕት ፬. ቅድስት ማርያ ሰማዕት ፭. ቅዱስ አርቃድዮስና ባልንጀሮቹ [ሰማዕታት ፮. ቅዱስ አሞን ሰማዕት [ †  ወርኃዊ በዓላት ] ፩፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፪፡ ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ " እንግዲሕ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጀሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: " [ማቴ.፲፥፳፮] (10:26) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показати все...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፬ - ] .mp33.84 MB
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ለታላቁ አባት በደብረ ዳሞ ገዳም ለ37 ዓመታት ላገለገሉ 3 ታላላቅ ገዳማት በስማቸው ለተሰየመ #ለአቡነ_ሠምረ_አብ_ዘሳይንት_ወዘትግራይ ዓመታዊ ለልደት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                                                   ✝️ ✝️ ✝️                         ❤#አቡነ_ሠምረ_አብ_ዘሳይንት_ወዘትግራይ፦ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው በወሎ አምሐራ ሳይንት ነው። አቡነ ሠምረ አብ የትውልድ ዕለታቸው ሰኔ 4 ቀን ነው።በብሕትውና ከተረጋገጠላቸውና ከ47ቱ ከታወቁት ሊቃውንት አንዱ ናቸው። ❤ አባ ሠምረ አብ ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ሄደው በዚያ 37 ዓመት ተቀምው፤በኋላም ወደ ገርዓልታ ሄደው በስማቸው የተሰራውን ታላቁን  ገዳም ቆረቆሩ። (ገርዓልታ አቡነ ሠምረ አብ ገዳም)፤በዚህም ምክንያት አቡነ ሠምረ አብ ዘትግራይ ይሏቸዋል። በተጨማሪም አስደናቂ የሆነ ገዳማቸው በጎንደር ደንቀዝ ውስጥ ይገኛል። ❤ በኢትዮጵያ ውስጥ በጻድቁ ስም 3 አብያተ-ክርስቲያናት ተሰርተዋል።የዕረፍት ቀናቸውም ጥር 4 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ሠምረ አብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!።  ምንጭ፦ ዜና ቅዱሳን። @sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886 https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Показати все...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                ❤ #ሰኔ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ_ለዕረፍቱ በዓል፣ በኪም ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ሳኑሲ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን አንገቷን በመቆረጥ ሰማዕትነት ለተቀበለች ተጋድይ ለሆነች #ለቅድስት_ሶፍያ ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከአርቃድዮስ፣ ከእህቱ #የዲሙናስና ከግብጻውያን ከንጉሥ ከዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም ከገድላቸው ፍጻሜ፣ #ከአባ_አሞንና ከሚናስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ፦ የዚህም ቅዱስ አባት ስሙ ዘካርያስ ነው እርሱም የጳንጦስና የአብልያ አገሮች ገዢ ነበር የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም ይህን የተባረኩ ልጅ በተሰጡ ጊዜ ስሙን ዮሐንስ ብለው ጠሩት እርሱ ከአባቱና ከእናቱ ጀምሮ ከመጥምቀ አምላክ ዮሐንስ ጋር በስም አንድ ሁኗልና በተግሣጽና በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ሂሣቦችንና ጥበቦችን ሁሉ አስተማሩት እናቱም በዘመኗ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይወጣ ታማጽነው ነበር። አባቱም እንዲሁ ይመክረውና ያስተምረው ነበር። ❤ ከዚህም አባቱ ከሞተ በኋላ የሃያ ዓመት ልጅ ሲሆን መስፍን ሆነ የጳንጦስና የሐራቅሊ ሌሎችም አገሮች ሁሉ ተገዙለት። እንዲሁም እያለ በመልአክ አምሳል ሰይጣን ታየው እንዲህም አለው "አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሒደህ የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ አግባ ብሎ ጌታ አዝዞሃል" አለው ቅዱሱም "በውኑ ይህ መልአክ ነውን ግን አፉ የእግዚአብሔርን ስም ከሰማሁ አንጾኪያ እሔዳለሁ" አለ። ❤ ከዚህ በኋላም ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ተገናኘው ንጉሡም በአየው ጊዜ አከበረው እጅግም ወደደው። በማግሥቱም በምሳ ላይ ከእርሱ ጋራ እያለ ከሃዲ ዲዮቅልጥያኖስ አጰሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ ያንንም ጣዖት ባመጡት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ አቃለለው ስለዚህም ሥራ ንጉሡን ረገመው ሰደበውም። ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገውን በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በእሥር ቤት አሠረው። በእሥር ቤትም ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ታየው ከእርሱ ጋራም መላእክት አሉ። ይዞም ሳመው ብዙዎች ቃል ኪዳኖችንም ሰጠው። ❤ በማግሥቱም ንጉሡ ልኮ ከእር ቤት አወጣው ወደ ርሱም አቀረበውና "ለአጰሎንና ለአርዳሚስ ስገድ" አለው ቅዱሱም "የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ" አለ ንጉሡ ግን ከእርሱ ጋራ መታረቅ ሽቶ ብዙ የሽንገላ ነገርን ተናገረው። ከዚህም በኋላ ግብርን ያስገብር ዘንድ ከሹመት ጋራ ወደ ግብጽ አገር ላከው ወደ ግብጽ ገዢ ወደ ስርያቆስም ስለ ርሱ እንዲህ ሲል ጽፎ ላከ "እንሆ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤቶች አፍርሶ አዲስ እንዲአሠራ ከግብጽና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሥልጣን ሰጥቼለሁ። ቅዱሱም ይህን ምክንያት ይዞ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሶ ተዋቸው። ❤ በዚያም ወራት መኰንኑ ስርያቆስ የሰማዕታት ራስ መቆረጥን ሊያዝዝ በፍርድ አደባባይ ተቀምጦ በዚያን ጊዜ ከስዒድ፣ ዲዮስቆሮስ፣ ቢፋሞን፣ አሕራጋኖስ፣ ኪሮስ፣ ዮልዮስ እለእስክድሮስ፣ ዮሴፍ፣ ይስሐቅና እስጢፋኖስ የሚሉአቸው ሰዎች መጥተው እሊህ ሁሉም እኛ ክርስቲያኖች ነን እያሉ በግልጥ ጮኹ ያን ጊዜ መኰንኑ ይዞ ያለርኅራኄ ያሠቃያቸው ጀመር። ቅዱስ ዮሐንስ ይህን በአየ ጊዜ የሹመቱን ሥራ ትቶ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በግልጥ ጮኸ መኰንኑም ተቆጥቶ በእግር ብረት እንዲአሥሩትና ወደ እንዴና አገር ወደ መኰንኑ አርያኖስ እንዲወስዱት አዘዘ እርሱም ስለሆነው ሁሉ መረመረው ከቃሉ መልስም የተነሣ ተቆጣ በባላ እንጨት ላይ ሰቅለው በመንኰራኵር አጣበቀው እንዲጨምቁት ከዚያም ከባላው አውርደው ሥጋው እስኪቀልጥ ሆዱ ላይና ራሱ ላይ በቀጭኔ እንዲደበድቡት አዘዘ ምድሪቱም በደሙ ተመላች ከዚያም ወደ እሥር ቤት አስገቡት። ❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ ያሹት ዘንድ ዳግመኛም አመድ ጐዝጊዘው በላዩ የእሳት ፍም ከጐኑ በታች አድርገው በላዩ እንዲአስተኙት አዘወ እንዲሁም አደረጉበት። ሁለተኛም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በፊቱ ላይ በጀሮዎቹም ላይ እንዲያኖሩዋቸው አዘዘ። እንዲህም አድርገው ከወህኒ ቤት ጨመሩት። በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ሰላምታ ሰጥቶ አጸናው። በማግሥቱም ከወህኒ ቤት አውጥተው በጋሉ ብረት ዘንጎች ደበደቡት። ከዚህም በኋላ በግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጭራ ላይ በገመድ አሠሩ። ❤ ከዚህም በኋላም ባለ ሰይፍ መጥቶ እግርቹንና እጆቹን ራሱንም ቆረጠ እንዲህም የምስክርነቱን ተጋድሎ ሰኔ 3 ቀን ፈጽሞ የድል አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅድስት_ሶፍያ፦ የዚች ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያን ነበሩ በወለዱዋት ጊዜም በመልካም አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የአባቶቻችን ሐዋርያትንም ሥርዓት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጓት። ❤ ከዚህም በኋላ በአደገች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ መስፍን ልጅ ሊአጋቧት ፈለጉ ቅድስቲቱም ይህን በመንፈስ ቅዱስ ዐውቃ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ መቶ ስግደትን ሰገደች ቆማም ረጂም ጸሎትን ጸለየች በጸሎቷም ውስጥ እንዲህ አለች "የክብር ባለቤት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህ ለእኔ ለባርያህ ለሶፍያ ምራኝ ወደ ጥፍት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ የሚጠፍውንም ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው ወላጆቼ በሚመክሩብኝም በረከሰ በሥጋ ፍትወት ውስጥ የኃጢአት ባርያ እንድሆን አቤቱ አትተወኝ የከበደ የዓለማዊ ፍላጐት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትከሻዬ ዘንበል አድርገው እጂ"። ጸሎቷንም ከፈጸመች በኋላ በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ጥቂትም ቆይታ እንዲህ የሚል ሃሳብ መጣባት "ተነስቼ በስውር ልውጣ ወደ ሩቅም ሔጄ ከበረሀ ውስጥ ገብቼ ለልዑል አምላክ ላገልግል"። ❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቿ የሰጣትን የምታገለግላት ብላቷናዋን ጠራች ወይን አምጥታ እንድታጠጣትም አዘዘቻት በአመጣችላትም ጊዜ እርሷ ጥቂት ቀምሳ ያመጣችው ወይን እስኪያልቅ ትጠጣ ዘንድ ብላቷናዋን አዘዘቻት ከስካርም የተነሣ ልባ በተሰለበ ጊዜ "ልብስሽ አንጪ የእኔንም ልብስ ውሰጂ" አላቻትና ሰጠቻት ወይኑ ስካር አእምሮዋን ነስቷታልና ተኚ አለቻት በላይዋም እንቅልፍ በከበዳት ጊዜ ማን ሳያያት ቅድስት ሶፍያ በስውር ወጣች ከወላጆቿም ማደርያ ነበርና። እርቃ በሄደችበት ጊዜ በተራራና በዋሻዎች ውስጥ ሊሰወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሚሸሹ ሰዎችን አገኘች "እናንተ ከወዴት ናችሁ?" ብላ ጠየቀቻቸው የእያንዳንዳቸውን አገራቸው ነገሯት ደግማ "ወዴት ትሔዳላችሁ?" አለቻቸው እነርሱም ስለ ሃይማኖት ከዲዮቅልጥያኖስ የሆነውን ሉሁ ነገሯት። "ይቺ መንገድ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ታደርሰኛለችን" አለቻቸው "አዋ ታደርስሻለች" አሏት ከዚያም ጥቂ ተጉዛ ቁማ እረጅም ጸሎትን ጸለየች ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ደርሳ
Показати все...
ክብር ይግባውና ክርስቶስ የምታመልክ ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች። ❤ ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስ ስም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተሞላ ወደ እርሱም እንዲያቀርቧት አዘዘ በቀረበችም ጊዜ "ለአጵሎን ስገጂ አላት "የሰው እጅ ለሰራው ለረከሱ አጋንትም ማደርያ ለሆነው እንዴት እሰግዳለሁ" አለችው ይህንንም ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከብረት በተሰራ ጅራፍም እንዲገርፏት አዘዘ ሁለተኛም አንገቷን ከባድ ደንጊያ አስረው ሥጋዋ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ በከተማው ጥጋጥግ እዲጎትቷት አዘዘ ይህን አድርገው ወደ ወሂኒ ቤት አስገቧት። በማግስቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ በመጣችም ጊዜ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጰሎን ሰዊ" አላት እርሷም "ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ይሕወት ነው" አለችው። እርሱም "ከገደልኩሽ በኋላ ትነሽ ትነሻለሽን?" አላት "አንተ ሰነፍ የእኔን ተዋውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ" አለችው። ይህንንም በሰማ ጊዜ አጥንቶቷ ሁሉም እስኪሰበሩ በብረት በትሮች እዲደበድቧት አዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉባት። ❤ ዳግመኛም በብረት አልጋ አስተኝተው ከበታቿ እሳት እንዲያነዱ አዘዘ ቀኑ በመሸም ጊዜ ወደ ወህኒ ቤት እንዲያስገቧት አዘዘ። በዚያችም ሌሊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሰስ አጽናናት። በማግሥቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ምን ሕማም እንዳላገኛት ሁና በእግራ መጣች ከመታጠቢያ ቤት ታጥባና ተቀብታ የመጣች ትመስል ነበር ንጉሡም ደኅንነቷን አይቶ አደነቀ፣ "የዚችን ክርሰቲያን ሴት የሥራይዋን ጽናት እዩ ትናንት በእሳት አሰቃይተናት ነበር ዛሬ ድናለች" አለ "ሥራይንስ አላውቀውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይ የሚሽር ነው" አለችው። ❤ ከዚያም በኋላ እሺ ያሰኛት ዘንድ ሊሸነግላት ጀመረ እንቢ ባለችውም ጊዜ እራሷን በሰይፍ ሊቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ሊቆርጧት ይዘዋት ሲሆዱ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለፀላት ብዙ ቃል ኪዳኖችንም ሰጣት በማይታበል ቃሉም "መታሰቢያሽን የሚያደርገውን፣ ሁሉ በስምሽ የሚመጸውተውን፣ የገድልሽንም መጻሕፍ የሚጽፈው ሁሉ እቀበለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ" አለ። ከዚያም በኋላ አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ በጌታችንም ዘንድ የድል አክሊልን ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅድስት ሶፍያ በጸሎቷ ይማረን በረከታም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ሳኑሲ፦ ይኽም ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለጦም አዳሪዎች እየሰጠ እርሱ ግን እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር፡፡ በአንዲት ሌሊት የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት "የክብርን አክሊል ትቀበል ዘንድ ወደ መኰንኑ ሄደህ ስለ ፈጣሪህ ስለ ክርስቶስ መስክር" አለው፡፡ ቅዱስ ሳኑሲም ትእዛዙን በመቀበል እናቱን ተሰናብቶ ማርያ ከምትባል ደገኛ ሴት ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ወደ ከሃዲው ገዥ ወደ አርሳኖስ ዘንድ ሄዱ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ በከሃዲው ገዥ ፊት ቀርበው ክርስቲያን መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ገዥውም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰባቸው፡፡ ቅድስት ማርያ በስቃይ ውስጥ ሳለች ዐርፋ ሰማዕትነቷን ስትፈጽም ቅዱስ ሳኑሲ ግን በጌታችን ኃይል ታደሰ፡፡ መኰንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው ገዥ በግዞት ላከው፡፡ በዚያም እጅግ አድርገው አሠቃዩት፡፡ ተረከዙን ሰንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ ሲጎትቱት ዋሉ፡፡ ሥራየኛ ሰው አምጥተው ሥራየኛው ሰው በጽዋ የተመላ መርዝ እንዲጠጣ ቢሰጠው ቅዱስ ሳኑሲ በመስቀል ምልክት አማትቦ ቢጠጣው ምንም አልሆነም፡፡ እንዲያውም ምግብ ሆነው፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያየው ሥራየኛም "በቅዱስ ሳኑሲ አምላክ አምኛለሁ" ብሎ በመመስከር እርሱም ሰማዕት ሆነ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ሳኑሲን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘና ሰኔ 4 ቀን የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በክብር ፈጽሞ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 4 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#አቄርብ_ለከ_አሞኒ_ሰላም። #ወሶፍያ_ምስሌከ ዘተሳተፈት ሕማመ። #በእንተ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥመሩ ፍጹመ። ከዊነክሙ ትሕፅኑ ኪያየ ደክታመ። ለሊከ አበ ወይእቲ እመ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_4።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ቀስቶኒ ወተረ ወአስተዳለወ። ወአስተዳለወ ቦቱ ሕምዘ ዘይቀትል። ወአሕፃሁኒ እለ ይነዱ ገብረ"። መዝ 7፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥9-18፣ 1ኛ ዮሐ 2፥12-20 እና የሐዋ ሥራ 12፥18_ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ወይም የ­ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።                          @sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886 https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Показати все...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

00:46
Відео недоступнеДивитись в Telegram
                          †                          [ የምታሰድዳት ከሆነ ... ግድ የለም ! ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን ፥ ዘመናትም ፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት። ❞ [ ራእ.፲፪፥፲፫ ] ❝ ህፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ ❞ [ ማቴ . ፪ ፥ ፲፫ ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
1.99 MB
2
Фото недоступнеДивитись в Telegram