cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ETHIO MUSIC SONG

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
154
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🌎🌎 #ሰው_እኮ! 🌎🌎 ✅ ካላገባህ ለምን አታገባም ? ✅ ካገባህ ምነው እስካሁን ሳትወልዱ ? ✅ ሁለት ልጆች ካሉህ ለምን ሶስተኛ አትጨምሩም ? ✅ ከሚስትህ ጋር ከተጋጫቹ ፍቺ እያለ ምን አሰቃየህ ? ✅ ተጫዋች ስትሆን ወረኛ ያደርጉሃል ✅ ዝምተኛ ስትሆን ውስጥህ ነገር እንደያዘ ነገር ያስቡሃል ✅ አንዳንዴ ተጫዋች አንዳንዴ ዝምተኛ ስትሆን እሱ እኮ እንዲህ ነው አይጨበጥም ይሉሃል! ✴️ኮስታራ ከሆንክ እሱኮ ፊቱ አይፈታም ✴️ባጋጣሚ ሰላም ሳትል ካለፍክ ኩራተኛ ነው ብለው ያስወሩብሃል በቃ ማውራት ነው !! 💠 ስትወፍር ያወራሉ 💠 ስትከሳ ያወራሉ 💠 ጎበዝ ከሆንክ ያወራሉ 💠 ደደብ ከሆንክ ያወራሉ 💠 ፀሀይ ሲሆን ሙቀቱ! 💠 ዝናብ ሲሆን ውይ ብርዱ! 💠 ስትናገር ተናጋሮ አናጋሪ ያደርጉሃል 💠 ግልፅ ስትሆን ይጠሉሃል 💠 ስትቀርባቸው ለጥቅም እንደሆነ ያስባሉ 💠 ስትርቃቸው ይፈልጉሃል 💠 ቀለል ብለህ ስትቀርባቸው ያረክሱሃል 💠 ስራ ከፈታህ ይንቁሃል 💠 ስራ ስተሰራ ያሙሃል 💠 ገንዘብ ካለህ ይንሰፈሰፉልሃል 💠 ካማረበህ ይቀናሉ 💠 ካስጠላብህ ያሽሟጣሉ 💠 ፀዳ ስትል ያፈጡብሃል 💠 ስትቆሽሽ ሊያዩህም አይፈልጉም 🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿 ይገርማል…!! ✴️ ሰው ሲሞት ከንፈር መምጠጥ ✴️ በሰው ውድቀት ማላገጥ ✴️ ሰው ሲያልፍለት መቅናት ✴️ ሰው ሲሰራ ማማት ✴️ ካለህ ሰዎች ያውቁሃል ✴️ ከሌለህ ሰዎችን ታውቃለህ ✴️ ካለህ ሰዎች ያውቁሃል ✴️ ከሌለህ ሰዎች ይንቁሃል 🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿 አሁንም እንገረም...!! ✳️ ጥቅም እንጂ ፍቅር የለም! ✳️ እኔ እንጂ እኛ የለም ✳️ የላይ እንጂ የውስጥ የለም ✳️ ከአፍ እንጂ ከልብ የለም ✳️ ምላስ እንጂ ተግባር የለም ✳️ ትምህርት እንጂ ዕውቀት የለም ✳️ ስደት እንጂ ገንዘብ የለም 🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿 ድንቅ ነው...!! ✅ ነጋዴው ይዋሻል ✅ ተማሪው ያላግጣል ✅ ዶክተሩ በእውቀቱ ይነግዳል ✅ ሃብታም ለድሃው አያዝንም ✅ በሽታና ሞት ቢበዛም የሚመከር ጥቂት እንጂ ብዙ የለም ✅ ብዙዎች በአለማዊ ጉዳይ ቢዚህ ሆነው ✅ መንፈሳዊውን ህይወታቸውን ረስተው ✅ ዓለማችን በጥፋት ተበከለች ✅ ክቡር ህይወት ርካሽ ሆነች @kuniversity_news @kuniversity_news @kuniversity_news
Показати все...
🚹🚺 የሰው_ልጅ_ከሁለት_በአንዱ_ይማራል 🚺🚹 ✴️ ምክር ብትሰማ በነፃ ትማራለህ ✴️ አሻፈረኝ ካልክ ዋጋ ከፍለህ ትማራለህ ነግሬሃለሁ ✴️ ሁሉን ካላየሁ አላምንም አትበል ✴️ ከተጎዱ መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ✴️ የእድሜ ልክህን እውቀት ለመገብየት ✴️ የግድ የእድሜህ ፍፃሜ ላይ መድረስ አይጠበቅብህም ነገር ግን ከአዛውንቱ ቀስመህ ህይወትህን ማስዋብ ጥበብ ነው ✅ በቁንጅናህ ስትመካ እውቀት እንዳይለይህ ተጠንቀቅ ✅ ብልህ ከሆንክ ቆንጆ ወዳጅ እንጂ ቆንጆ ቁመና አትሻ ✅ ቆንጆ ትዳር እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ምክንያቱም ምትኖረው ከፀባይዋ ጋር እንጂ ከመልኳ ጋር አይደለም ✅ አንተ ሚጠበቅብህን አድርግ እንጂ ምላሻቸውን አትጠባበቅ ✅ ካወካት መንፈቅ ያልሞላት ሄዋን አፈቅርሃለሁ ስላለችህ በይሉኝታ እኔም አትበል የሙሸበክን ጣዕም መልኩን አይተህ ሳይሆን ቀምሰከው ነው ምትወስነው። ✅ ብዙ አመት በአንድነት ቆይተህ በቀናት መካከል ግጭት ተፈጥሮ ብትለያይ፣ አግብታም ብታያት በእድልህም ሆነ በፈጣሪ አታማር። ✅ ቀድሞውኑም የሰው ሚስት ነበረች ብለህ ለልብህ ንገረው ደሞም ሳታረጅ ሚስትህን እንድትፈልግ እድል ስለሰጠችህ አመስግናት። ✅ ትችትን አትፍራ ፤ ስህተትህን ግን አጥራው እውነትን ተናግረህ ተገፋ እውነትን በመናገር የሀሰት ወዳጅህን ታጣዋለህ የእውነት ወዳጅህን ታተርፋለህ። ✅ ለህሊናህ ተገዢ ሁን የገባህን አድርግ ያመንክበትን ተናገር በሊቆች መካከል በመሆንህ የበታችነት አይሰማህ ፤ ከአዳም በቀር አዋቂ ሆኖ የተፈጠረ የለም ከክርስቶስ በቀር ስህተት ሳይሰራ የተለቀ የለም። ✅ ሀብታም ስላጠጣህ ደሀ ላይ አትሽና ለሀብታም እየሳክ ደሀ ላይ አታፍጥ ያለሰው ሰው አልሆንክምና ሰው ከሰው አትለይ። ✅ በስልጣን የተሾምከው የሁሉ አገልጋይ እንድትሆን እንጂ እንድትኮፈስ አይደለም። ❇️ በቦታህ መምህር ያለ ቦታህ ተማሪ ሁን ቃሎችህ ቁጥብ ይሁኑ በአደባባይ እጅህን እንደሰንደቅ አላማ አውለብልበህ አስተያየት አትስጥ ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም። ❇️ አላቅምህ አትጋፋ ውሻን በእርግጫ ማላት እንካ ስጋ ማለት ነው ❇️ በሀሜት መንደር አትዋል በመቃብር ስፍራ አትደር ❇️ መልካም ሆነ ክፉ ስራህን የአመቱ አንድ ቀን እንደሚገልጠው ይህን አትርሳ "ተደብቃ የፀነሰች ሰው ሰብስባ ትወልዳለች" ❇️ ምን አለች ሸንኮሬ "ጨዋነሽ ሲሏት ሳቁ ገደላት" አንተ ህሊናህ እንጂ ሰው እንደሚልህ አትሁን ❇️ ሁሉን ላውራ አትበል ዝም ያሉት ይታዘቡሃል እውቀትህ በአላዋቂዎች ላይ ካንቀባረረህ ለውድቀት ቅርብ ነህ አስተውል ❇️ ብልህ ሰው ከሽማግሌው ምክር ሲማር ሞኙ በሽምግልናው ይማራል ! @kuniversity_news @kuniversity_news @kuniversity_news
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🚹 ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብበው ! 🚺 🟢 በቀን 3 ጊዜ ትበላለህ? 🔵 ገላህን መሸፈኛ ልብስ አለህ? 🟢 ቀን ደክመህ ውለህ ማታ ምታርፍበት ጎጆ አለህ? ✴️ እንግዲያውስ እወቅ አንተ በአለም ላይ ካሉት ከ《75%》 በላይ ሰዎች የተሻለ ኑሮ ላይ ነህ!! ✴️ ኪስህ ውስጥ አንዳንድ ምትፈልጋቸውን ነገሮች ምትገዛበትና ምትፈልግበት ቦታ ምትንቀሳቀስበት ገንዘብ ካለህ........ .....አንተ ከአለማችን 《18%》 ሃብታሞች ውስጥ!! አንዱ ነህ ✴️.ይቺን ቅጽበት ያለምንም ህመም በሙሉ ጤንነት እያሳለፍክ ነው? 🌀 በዚች ሰአት በአለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ከሚያጣጥሩትና አልጋ ላይ ሁነው ከሚሰቃዩት ውስጥ አይደለህምና ትልቁ እድለኛ ነህ 🌀ይሄን መልዕክት እያነበብክና እየተረዳከው ነው ? 🌀....ልብ በል በአለም ላይ ከ《1 ቢሊዮን》 በላይ ማየት ማንበብ ማይችሉ እንዲሁም የአዕምሮ ህመምተኞች ይህን ማድረግ አይችሉምና ከነሱ ውስጥ አንዱ ባለመሆንህ ትልቁ እድለኛ ነህ!! 🌀 ስለሌለህ ነገር እያሰብክ ከማዘን ይልቅ ቆጥረህ በማጨርሰው የፈጣሪህ ስጦታ ደስተኛ ስትሆን ህይወትህ የበለጠ ደማቅ ይሆናል!! ✅ ሁሌም ፈጣሪን እናመስግን👏 @kuniversity_news @kuniversity_news @kuniversity_news
Показати все...
🤦‍♀🤦‍♀በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? በሞባይልዎ ላይ እነዚህን ማስተካከያዎች ያድርጉ❓ ኢትዮ ቴሌኮም ወደ 60 ሚሊዮን የሚገመቱ ደንበኞች እንዳሉት ይነገርለታል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ 17 ሚሊዮን ያህሉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎትን ይጠቀማሉ። ኢትዮ ቴሌኮም በዝቀተኛ ዋጋ ኢንተርኔትን ለተጠቃሚዎች ከሚያደርሱ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ምናልባት እርሶም ''አሁን የገዛሁት ኢንተርኔት ከምኔው አለቀ?'' ''ካርድ ዛሬ አይደል እንዴ የሞላሁት ?'' ብለው በተደጋጋሚ እራሶን ጠይቀው ሊሆን ይችላል። በአንድሮይድ አና በአይኦኤስ ስልኮቻችን ላይ አንዳንድ ማስተካካያዎች በማድረግ የኢንተርኔትን ወጪ መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ እንጠቁማችሁ። በቅደሚያ አንድሮይድ አና አይኦኤስ ምንድናቸው? አንድሮይድ በጉግል የተሰራ የተለያዩ የሞባይል አይነቶች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ፣ ሁዋዌ፣ ኤል ጂ እና ቴክኖን የመሳሰሉ ሞባይሎች አንድሮይድ የተባለው የመተግበሪያ ስርዓትን ይጠቀማሉ። አይኦኤስ (iOS) በአፕል የተሰራ ሲሆን አይፎን፣ አይፓድ እና አይፓድ ተች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው። እንደ ፌስቡክ እና ዋትስአፕ የመሳሰሉ በእለት ከእለት በምንጠቀምባቸው መተግባሪያዎች ላይ ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ እንዴት የኢንተርኔት ወጪያችንን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደምንችል እንጠቁማችሁ። 🔰ፌስቡክ (#Facebook) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፌስቡክ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዲጫወቱ ፍቅዷል። ይህም ብዙ ዳታን ይጠቀማል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዳይጫወቱ ለማድረግ (Video #Autoplay off) ለማድረግ፡- በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ ኤንድ ፕራይቬሲ (Setting and #Privacy) >ዳታ ሴቨር (#Data Saver) የሚለውን On ያድርጉ። በአይኦኤስ (አይፎን) ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ (#Setting) >ሚዲያ ኤንድ ኮንታክት (#Media and Contact) >ቪዲዮ ኤንድ ፎቶስ (Video and Photos) >አውቶ ፕለይ (#Auto-play) >ኦን ዋይፋይ ኮኔክሽን ኦንላይን (On #Wi-Fi connections only) የሚለውን On ያድርጉ። ከዚህ በተጨማሪም በአንድሮይድ ስልኮች ላይ አነስተኛ ዳታ የሚጠቀመውን ፌስቡክ ላይት (#Facebook Lite) የተባለውን የፌስቡክ ስሪት መተግበሪያን ከጉግል ፕለይ ላይ በማውረድ መጠቀም ይቻላል። ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ፌስቡክ የሚለውን መተግበሪያ ከመጠቀም ይልቅ እንደ ኦፔራ ሚኒ (#Opera Mini) ያሉ የኢንተርኔት መቅዘፊያ መተግበሪያዎችን (#Internet Browser Apps) በመጠቀም የዳታ ወጪን መቀነስ ይቻላል። ያስታውሱ ፌስቡክን በፌስቡክ ላይት ወይም በመተግበሪያዎች ሲጠቀሙ የፌስቡክ ማራኪነት እና አማራጮች ሊቀንሱ ይችላሉ። 🔰ዋትስአፕ (#WhatsApp) ስንት የዋስትአፕ ግሩፕ (ቡድን) ውስጥ አሉ? በዋትስአፕ የሚላክሎት ፎቶ እና ቪዲዮ በፎቶ ጋለሪ ውስጥ አለ ማለት ብዙ የሞባይል ዳታ እየተጠቀሙ ነው። ዋትስአፕ የሚጠቀመውን የዳታ መጠን ለመቀነስ ይህን ይከተሉ። የዋትስአፕን ሴቲንግ (Setting) ይክፈቱ >ዳታ ኤንድ ስቶሬጅ ዩሴጅ (#Data and Storage Usage) > ከዚያም ሰሌክት ሚዲያ አውቶ ዳውንሎድ ኦፕሽንስ (Select Media Auto #Download Options) የሚለውን በመምረጥ > ዌን ዩዚንግ ሞባይል ዳታ (When Using #Mobile Data) የሚለውን በመጫን ''ኖ ሚዲያ (No Media)'' በሚለው ይቀይሩት። በይበልጥ ዋትስአፕ የሚጠቀመውን ዳታ ወጪ ለመቀነስ ኮል ሴቲንግ (Call Setting) ከሚለው በታች ያለውን ሎው ዳታ ዩዜጅ (Low Data Usage) መምረጥ ይቻላል። 🔰ዩቱዩብ (#YouTube) በዩቱዩብ ቪዲዮችን መመልከት ብዙ ዳታ ይወስዳል። በሞባይል ዳታ ቪዲዮን መመልከት ካስፈለጎው ግን የሴቲንግ ምልክቷን በመጫን 240p ወይም 144p ላይ በማድረግ በአነስተኛ ጥራት በመመልከት እስከ 60 በመቶ ሊያወጡ የሚችሉትን የHD (720p) የዳታ መጠን መቀነስ ይችላሉ። ሌላው አማራጭ የቪዲዮ ባለመብት ፍቃድ ካለ የወደድነውን ቪዲዮ ከዩቱብ ላይ የዋይፋይ አግልግሎት ያለበት ቦታ ላይ በማውረድ ለ30 ቀናት ያለ ኢንተርኔት ደጋግምን መመልከት እንችላለን። መተግበሪያዎችን ማሻሻል (Updating Apps) በስልኮቻችን ላይ ተጭነው የሚገኙ መተግበሪያዎች በፈልሳፊዎቻቸው በተለያየ ጊዜ በአዳዲስ ቅጂዎች ይሻሻላሉ። መተግበሪያዎቹን ለማሻሻል የሞባይል ዳታን መጠቀም ብዙ የኢንተርኔት ወጪን ያስከትላል። ስለዚህም የዋይፋይ (Wi-Fi) አገልግሎት ባለበት ቦታ ብቻ ማሻሻል ይመከራል። 🔰መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይፋይን ብቻ ለመጠቀም ቀጣዩን ይከተሉ። አንድሮይድ ስልኮች ላይ፡ ጉግል ፕለይ ስቶር (Google Play Store) > ሴቲንግ (Setting) > አውቶ አፕዴት አፕስ (Auto-update apps) > አውቶ አፕዴት አፕስ ኦቨር ዋይፋይ ኦንሊ (Auto-update apps over Wi-Fi only) የሚለውን ኦን (On) ያድርጉት። አይፎን ስልኮች ላይ፡ ሴቲንግ (Setting) > አይቲዩንስ & አፕ ስቶር (iTunes & App Stores) > ዩዝ ሞባይል ዳታ (Use Mobile Data) የሚለውን ኦፍ (Off) ያድርጉት። 🔰አጠቃላይ ስልካችን ሊጠቀም የሚችለውን ዳታ መቀነስ ስልክዎ አንድሮይድ መተግበሪያ ስርዓትን የሚጠቀም ከሆነ በስልክዎ ላይ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀሙ ላይ ገደብ ሊያደርጉ ይችላሉ። (ሴቲንግ) Setting > (ኔትዎርክ ኤንድ ኢንተርኔት) Network & Internet > (ዳታ ዩዜጅ) Data Usage > (ዳታ ሴቨር) Data Saver የሚለውን ኦን (On) ያድርጉ። ሌሎችንም ወደቻናላችን ይጋብዙ JOIN⬇️ 📢 @kuniversity_news @kuniversity_news
Показати все...
እህታችንን አፋልጉን ! ተማሪ አምሳለማርያም አብርሃም የካቲት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ላይ ከልደታ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ትምህርቷን ተከታትላ ከወጣች በኃላ ወደ ቤቷ አልተመለሰችም። በእለቱ የለበሰችው ልብስ ዜብራ ከለር ሹራብ ነጠላ ለብሳለች፣ ሻሽ አስራለች ቶርሽን ጫማ አድርጋለ። ያለችበትን የሚያው በስልክ ቁጥር 0913422557/0913410317/0930332864 አሳውቁን። ቤተሰቦቿ። @kuniversity_news
Показати все...
​​VALENTINE'S DAY ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም። የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ??? ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው። የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው። ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት። ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው) ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም። እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው። ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል። ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር። በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል 1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗ 2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗ 3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው። Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው። እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን??? " ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። " (ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6) እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን። @kuniversity_news @kuniversity_news @kuniversity_news
Показати все...

#እባካችሁን_አስቸኳይ_ነው😭😭😭 እኚህ እናታችን ዛሬ ጠዋት 22አካባቢ በደረሰባቸው ከፍተኛ የመኪና አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ልበመልካም ሰዎች ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ወስደዋቸዋል! እማማ ስማቸውን መናገር አልቻሉም😭አሁን በጆሮና በአፍንጫቸው ብዙ ደም እየፈሳቸው ስለሆነ ቤተሰቦቻቸውን በቶሎ ማግኘት አለብን😭 #እባካችሁን እንድረስላቸው🙏 #ሼር_SHARE እናድርግላቸው🙏 "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም" "ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት 0913061429-ፍቃዱ አበራ
Показати все...
ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት የ8 አመት ህፃን ሲሆን የጭንቅላት እጢ አለበት እንርዳው ፣ እናቱ ብቻዋን እየተሰቃየች ነው ሰው ነን ነገ ምን እንደምንሆን አናቅም። እባካቹህ በቻልነው ነገር አንርዳው በዱዓ ፣ በፀሎትም እንርዳው። አቅም ያላቹህ Please 😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ንግድ ባንክ ፡ 1000298676037 ስልክ ቁጥር ፡ 0932283075
Показати все...
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች🌈🌈🌈🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Показати все...
Join Us 💿➠ ━━━━━━━https://t.me/Ethio_music_song ══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══
Показати все...
Estegenet Hailemariam.mp35.40 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.