cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ከእብዶች መንደር😉😛😛

ፍልስፍና😌 አባባሎች😃 ግጥሞች😉 ምክሮች😴 መልህክቶች😥 ገጠመኞች😲😆 ሁሉን በአንድ ላይ ያገኛሉ ከእርሶ😄😄😄 ሚጠበቀውjoin this channel😉 ቻናሉ ላይ እንዲለቀቅሎ የሚፈልጉትን መልህክት @Netsushaመላክም ይችላሉ

Більше
Рекламні дописи
198
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
-730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዐረገት በስብሃት ፡ኪዳነ ምህረት ፍሠዐ ኮነት ወበኃጥኣን፡ቤት ዐረገች ድንግል ፡ኪዳነ ምህረት ደስታ ሆነች ፡በኃጥያተኞች ቤት ነደ መለኮት ያዘለ ፡ስጋ ሞት እንዳያውቀው ይገባልና ሞት አላስቀራት ተነሳች ድንግል በልዕልና ሞትስ፡ ለማች አካል ነው ሚገባ የድንግል አካል ንዑድ ክቡር ነው አፈር ማይገባ በሞችሽ ዜና የሲሆል ነፍሳት ዳኑ ከእሳት ገቡ ከገነት ከህይወት ፍሬ ተቀጥፎ በሉ በደግነትሽ ግሩም ድንቅ አሉ ልጅሽም አለ ሲኦልን ቀርቦ ሲያስጎበኝሽ እነዚህ ሁሉ ሊድኑ አይችሉም ሞትን ካልቀመስሽ እነዚህን ሁሉ የማርክ እንደሆን አንድ ጊዜ አደለም አስሬ ልሙት ብለሽ ነገርሽው የዛን እልፍ ኃጥህ ግፉን ከላሽው ፅድቅ አለበሽው በፍቃድሽም ጥር ወር አርፈሽ ነሀሴ ዐረግሽ ወደ ልጅሽ ቀኝ በዕርገትሽ ቀን እኔ ተወለድኩ አለም ገባሁኝ ነሀሴ 16 ልደቴ ነው ❤❤❤ የኔ እናት አስቢኝ እንኳን አደረሳችሁ ዕርገታ ለማርያም ñëፁ
Показати все...
ደብረ ታቦር """"""""""""""" ብርሀን አየን የሚያስደነግጥ ፣ ድምፅንም ሰማን ምድርን የሚውጥ ፣ ሙሴ ኤልያስ ከቀኝ ከግራ ፣ ቆመው አይተናል ታቦር ተራራ ። ቡሄ አድርግልን መከራችንን ፣ በእሳት እጠራት ሀገራችንን ፣ መልካም ነው ለኛ ካንተ መሆን ፣ ክርስቶስ ለኛ ብርሀን ሁነን ። አምላክ ነው እና የሁላችን ፣ ኤልያስን ጠራው ከህያዋን ፣ ሙሴንም አመጣ ከሙታን ለይቶ ፣ አነጋገራቸው ደብረ ታቦር ወጥቶ ። ብሉይን ከሀዲስ አሳየን አስታርቆ ፣ ተራራ አወጣን ከክፋት አርቆ ፣ የአብ ድምፅ ተሰማ ልጄን ስሙት አለ ፣ በምን ይነቀላል በአብ የተተከለ ። አለን ቀጠሮ ከክርስቶስ ጋ ፣ አብልቶን የሱን ደምና ስጋ ፣ በደብረ ታቦር በድል ተራራ ፣ የአምላካችን ብርሀን በራ ። አሜን አይለየን አመት አመት ፣ ጠብቆ ያቆየን በእግዚአብሔር ቤት ፣ ብርሀን ያልብሰን የፍቅርን ሸማ ፣ በፅድቅ ያኑረን ከእምነት አውድማ ። #በረከትዘውዱ @amharic_poet @amharic_poet
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይገርማል """"""""""'' መልስ እየፈለገች አይኑን እያየችው " ምን ያስገርምሀል ? " ብላ ጠየቀችው " የዓለም ክብነት የሁሉም ልክነት የሰው አኗኗሩ ምድርና ጠፈሩ ፍጥረት አዋዋሉ ይደንቃል ይህ ሁሉ ! " አላት አሁንም ድጋሚ አይኑን እያየችው " አለም ግን ክብ ናት ? " ብላ ጠየቀችው " ቅርጿን ባላውቀውም ባልዞራት በስፍር አይቻለሁ በዓይኔ የለያየችውን..................ዞራ ስታጣምር ሰርክ እየተዜመ............የህይወት ኑዛዜ አንዴ እያፋቀረን አንዴ እያጣላን...........ስንት አሳየን ጊዜ አዎን አይቻለሁ ! የአለምን ክብነት የአንደኛው እውነታ ላንዱ ሲሆን ውሸት " አላት መልሱ እየገረማት እጅግ ተመስጣ እያደመጠችው " የሰው አኗኗሩ ስለምን ይገርማል ? " ስትል ጠየቀችው " አዳምና ሄዋን እንዳሸዋ በዝተው ምድርን መሙላታቸው የእነሱ ልጆች ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ መበታተናቸው ከአንድ አዳም ተፈትሎ ካንዲት ሄዋን.....ወጥቶ ልዩነት መፍጠሩ በቀለም በጎሳ..........ዘር ሀረግ መቁጠሩ ተወልዶ ማደጉ ዘር ጥሎ ማለፉ በጊዜ ጠመኔ....ህይወቱን መፃፉ ብዙ ስልጣኔ እልፍ የዓለም ኩነት አልፎ መገኘቱ የህይወት ቅጥልጥል የኑሮ ዑደቱ ከተወለደበት   እስከ ጊዜ እልፈቱ በተስፋ መኖሩ    ሞቱን መዘንጋቱ አያስገርምሽም !? " አላት በተመስጦ ሆና እያደመጠችው "እውነትም ይገርማል ! " አለችው " መልሱ እየገረማት  ሌላ መልስ የሚሻ ጥያቄ አነሳች የፀጉሯን ቁጥርጥር በስሱ እየፈታች ምን ይመልስ ይሆን ብላ እያየችው ተፈጥሮ ምኗ ደስ ይላል ? ብላ ጠየቀችው " በንፋስ ሽውታ ዛፎች ሲደንሱ ወፎች ጭድ ሰብስበው ጎጆ ሲቀልሱ የዝናብ ጠብታ መሬት ላይ ሲነጥር ሰማይ ሲጨላልም ነጎድጓድ ሲፈጥር ከአድማስ ባሻገር........ወጋገን ስትታይ እርግብና አዋፋት..........ሲበሩ በሰማይ በአረንጓዴው ሜዳ ከብቶች ሳር ሲግጡ ከእረኞቹ ጋ..............ግልገሎች ሲሮጡ ጀምበሯ ስትጠልቅ ስትመጣ ጨረቃ ከነ ሙሉ ብርሀን በከዋክብት ደምቃ አዋፋት ሲያዜሙ ጤዛዎች ሲደርቁ ለምለም ሲሆን ሳሩ  አበቦች ሲፈኩ የጠራው ምንጭ ውሀ ፏፏቴው ሲሰጥ ፍሰሀ የሰማይ ነጭ   ደመና ይህ ሁሉ ድንቅ ትወና አያስደንቅሽም ? አያስገርምሽም ? " አላት እውነትም ገረማት !! #በረከት_ዘውዱ @yegtm_hywet @yegtm_hywet @yegtm_hywet
Показати все...
አለን """"" ከቀንም ቀን ነበር ስቀን ያሳለፍነው አንጀት እስቲቆስል ከወቅትም ወቅት አለ ሰርክ ያነባንበት ማያልፍ እስቲመስል አለን እየሳቅን....ውስጣችን ሲበግን አንዴ እየፈካን ...........እየጠወለግን መኖር ግን ደግ ነው የቀናት ኩታ ደርበን........ወራትና መንፈቅ ጊዜ አልፎ ቀና ሲያደርገን....ከወደቅንበት ማዘቅዘቅ አይገርምም ዛሬም ድረስ የሕይወት ሎሌ   ከረፈፍ በኑሮ ሰማይ.....ስንከንፍ የሀዘን ደስታ........ኮሮጆ ስንክብ........ስንንድ ጎጆ አለን ከዘፍጥረት      በወረደው ተዋረድ አደምና ሀዋ በተራመዱት መንገድ ስንድህ ስንፍተለተል   በቀናት እርምጃ የዳናችን መዳረሻ እስኪገኝለት ማጋቻ እየተራመድን ሸክም ይዘን በድን ከቀለም ቅኔ አቁማዳ ከህይወት ፊደል ስንቀዳ ስንፈጥር ውስብስብ ዜማ የራስን ጩኸት ስንሰማ የስንቱን አመል ችለናል የስንቱን በደል   ትተናል እልፍ ትላንቶች አልፈናል ለአንድ ነገ........ቆመናል የህልውና  ጥያቄ ሸክፈን በእንባ......ደብዳቤ ፅፈን ፈጣሪ ካለህ ተመልከት ብለን ያለፍነው ወራት ዛሬ ላይ ያን ተሻገርናል......ተፈተን ያለ እስራት ለነገ ካኖርነው ተስፋ ለዛሬ ሸርፈን ስንቆርሰው ፈጣሪ በሰጠን ሸራ ህይወታችንን ስንደርሰው ተመስገን..............ኖረናል እንበል እንደሰው #በረከት_ዘውዱ @yegtm_hywet @yegtm_hywet @yegtm_hywet
Показати все...
Plz like and shear
Показати все...
አንቺ የእኔ ቀለም ፡ በመልኬ የተሳልሽ   የአብራኬ ክፋይ፡ ከደሜ የተዋረስሽ እኔን ከምድርሽ፡ አፈርሽ ያበጀኝ    ናፍቆትሽ አድክሞ፡ ፍቅርሽ የሚያክመኝ አንቺ ማለት........ ህልሜን የተጋራሽ፡ ልቤን ያወቅሽ አንቺ ማለት...... ስታመም ያቃሰትሽ፡ ስድን የተደሰትሽ አንቺ ማለትማ ........ ከፍ ያልኩብሽ ማማ፡ የማለዳ ብስራት አንቺስ.... የአእዋፍ ቅኔ፡ የጨረቃ ውህደት   አንቺ እኮ........ ለሊት ብርሀን ፡ ኮከብ ያደመቀው አንቺ ቀንሽ ፀዳል ለባሽ፡ውበት የተዳራው በቃ አንቺ ማለት ፡ መላእክ ትመስያለሽ   የሚመስልሽ የለም....... ጦቢያ በማርያም አንዴ እኔን  ምሰይኝ ፡ እኔ አንቺን ባልመስልም ✍ñëፁ
Показати все...
https://t.me/orthodox_profile_picture #share #share #share #share #share #share
Показати все...
Orthodox_profile_picture

Orthodox_profile_picture 👉 የኦርቶዶክስ ፎቶዎች 👉 የኦርቶዶክስ ስዕለ አድህኖዎች 👉 ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች እና ትምህርቶች 👉 የቅዱሳን አባቶች አባባሎች 👉 የኦርቶዶክስ መዝሙሮችን profile ማድረግ ይፈልጋሉ join በማለት ቤተሰብ ይሁኑ @orthodox_profile_picture @orthodox_profile_picture @orthodox_profile_picture

በግጥም ህይወት የተዘጋጀው ውድድር 2 : 30  ተጀምሯል ቤተሰቦች #like #comment በማድረግ ውድድሩን ይሳተፉ ተወዳዳሪዎች #share👉 #like❤️ በማስደረግ ውጤታችሁን ከፍ ለማድረግ ሞክሩ like 30% የግጥም ሀሳብ እና አፃፃፍ 70% የሚይዝ ይሆናል #መልካም እድል @yegtm_hywet @yegtm_hywet @yegtm_hywet
Показати все...
አልጠብቅሽም ግን እጠብቅሻለሁ """""""""""""""""""""""" እኔ ምን አውቄ ያገሬን ገጣሚ ማን እንደመከረው እጠብቅሻለሁ የሚል ግጥም ካለ ቀርታለች ማለት ነው የቀጠረ ገላ ፈልጎ እያጣ የጠበቁት ሁሉ በጊዜ ካልመጣ ተስፋ ተለኩሶ እጠብቅሻለሁ.......እያለ ሲጠፋ በጠበቀው አካል...ጠባቂ ሲገፋ በገጣሚ ብዕር መቅረት ስለሆነ...........መጠበቅ ትንፋሹ እጠብቅሻለሁ የሚል ግጥም ካለ   መቅረት ነው ምላሹ እኔ ግን እጠብቅሻለሁ..........የሚል ግጥም ፅፌ እንድትቀሪ አልሻም እንባ እንዲሆን ትርፌ ከመጣሽ ቶሎ ነይ ከግጥሜ በፊት.............ነይ ቶሎ ድረሺ እ ጠ ብ ቅ ሻ ለ ሁ የሚል ግጥም ባልፅፍ እንደምጠብቅሽ..........ፈፅሞ እንዳትረሺ ደሞ እንዳትቀሪ  ፍፁም እንዳትኮሪ በቃ ዝምብለሽ ነይ ሳትከራከሪ ብቻ ዝምብለሽ ነይ  ግጥሙን ሳልጨርሰው ምክንያቱም ገጣሚ በብዕር ጠብቆ ከፃፈው እጠብቅሻለሁ የሚል ግጥም.......ካለ ቀርታለች ማለት ነው ግን እንዳትቀሪ @amharic_poet @amharic_poet @amharic_poet
Показати все...