cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
201
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Repost from Saved by Grace️
❤️#አስደናቂው_መጽሐፍ_ቅዱስ❤️ =========================== ✍️❖ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን ለማጻፍ የተጠቀመባቸው ሰዎች በሙሉ እጅግ በጣም በተራራቀ ዘመንና ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ እንዲሁም የተለያዬ አይነት የኑሮ ደረጃ ላይ የነበሩና በእውቀት ደረጃም ፈጽሞ የተለያዩ ነበሩ። ሆኖም ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩና እየተነዱ በመጻፋቸው ምክንያት አንድ አይነት ሀሳብና ግብ ያለው መጽሐፍ ሊጽፉ ችለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21) ✍️ጸሀፊዎችን በሚመለከት እግዚአብሔር በዘመናት፣በኑሮ ደረጃና በእውቀት የሚለያዩ ሰዎችን በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱሱ እንዲጻፍ አድርጓል። ይህም የሰው ልጅ በየትኛውም ዘመን ውስጥ ቢሆን በኑሮ ደረጃው ከፍና ዝቅ ቢል በእውቀቱም ምሁርና ያልተማረ ቢሆን ሁሉንም የሚመለከት ከአምላክ ዘንድ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ ድንቅ መጽሐፍ መሆኑን ያሳያል። 📌❖የዘመን ልዩነትን በተመለከተ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያው ጸሀፊ በሙሴ እና በመጨረሻው ጸሀፊ በዮሐንስ መካከል የ1600 ዓመታት ያላነሳ የዘመን ልዩነት ነበር። ሁለቱ ሰዎች ከነበሩባቸው ረጅም ዘመናት የተነሳ የአመለካከት ፥ የባህል፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ወዘተ ልዩነቶች ቢኖሩም ጹሁፎቻቸው ግን ፈጽሞ አንዱ ከአንዱ የተስማሙ ነበሩ። 📌❖የጸሀፊዎች የኑሮ ደረጃን በሚመለከት ዝቅተኛና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበሩ ስዎችን ተጠቅሟል። ❖ለምሳሌ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበሩ፦ -አሞጽ = ላም የሚጠብቅና ዋርካ የሚለቅም ነበር ።(አሞጽ 7:14) - ጴጥሮስና ዮሐንስ = አሳ አጥማጆች ነበሩ (ማቴ 4:18-22) ❖ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበሩ፦ -ዳዊት = ንጉስ - ሰሎሞን = ንጉስ - ሙሴ = መስፍን ነበሩ 📌❖የእውቀት ደረጃን በሚመለከት እግዚአብሔር እጅግ በጣም የተማሩትንም ያልተማሩ ሰዎችንም ተጠቅሟል። ❖ለምሳሌ በጣም የተማሩ ሰዎች፦ -ሙሴ የግብጽን ጥበብ ሁሉ የተማረ ነበር (ሐሥ 7:22) -ጳውሎስ ከገማልያል የተማረ ነበር (ሐሥ 22:3) ❖ያልተማሩ ሰዎች፦ -ጴጥሮስና ዮሐንስ (ሐሥ 4:13) 📌❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው። 📌❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (English version) • 66 መጽሐፍት • 1,189 ምዕራፎች • 31,173 አንቀፆች • 810,697 ቃላት • 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ። 📌❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን • በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ • በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119 • አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው። 📌❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው። 📌❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው። 📌❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል። 📌❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው። ይኸውም፦ • መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት። • የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው። • የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው። 📌❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል። 📌❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21) 📌❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል። 📌❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ "ድመት" ብቻ ናት። ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል። 📌❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው። 📌❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለ ፀሎት 400 ጊዜ ስለ እምነት 500 ጊዜ ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል። 📌❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው። 📌❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት መላዕክት ገብርኤል ፣ ሚካኤል እና የወደቁት መላዕክት ናቸው። ✍️2 ጢሞቴዎስ 3 (2 Timothy) 15፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 16-17፤ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma
Показати все...
#መልእክት_አለኝ @anewcreature አንድ ደቂቃችሁን ልሻማ? እወዳችኋለው ትንሽ ታገሱኝ😊❤🙏 ካህኑ ኢያሱን ሰይጣን እድፋም ብሎ በእግዚአብሔር ፊት ሊከሰው በቆመ ጊዜ ካህኑ ኢያሱ ለራሱ ሊሟገት ቀርቶ ቀና ማለት አልቻለም ነገር ግን እግዚአብሔር በራሱ ስም ጠላትን ገሰፀው🙉 " እግዚአብሔርም ሰይጣንን። ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው። " ዘካርያስ 3:2 #አይገርምም_ሌላ_ሰው_እኮ_አይደለም_እግዚአብሔር_ይገስፅህ_ያለው😊 እግዚአብሔር እራሱ በራሱ ስም ሰይጣንን ስለ ኢያሱ ቆሞ ገሰፀው Wow💥 ወዳጆቼ እኛስ በስራችን መፅደቅ ይቻለናልን? ወይም በራሳችን ልፋት መዳን እንችል ነበር ወይ? አያቹ በበደላችንና በሀጥያታችን ምክኒያት ሙታን ነበርን ሙታን ማለት ህይወት አልባ ማለት ነው ህይወት አልባ ነገር ምንም ብታረጉት ስለራሱ መከራከርም መሟገትም አይችልም ስለዚህ በሀጥያታችን ሙታን ሆነን ለራሳችን መቆም የማንችል ለነበርነው ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን 💥🙏 #ጉዋደኞቼ ኢየሱስን ሳወራችሁ የሆነ ሀይማኖት እያስፋፋው እንዳይመስላችሁ በገንዘባችን ወይም በጥረታችን የማንከፍለውን እዳ በመስቀል ላይ ከፍሎ ያዳነንን እርሱን ልነግራችሁ ነው #ኢየሱስ__አለም_ያላገኘችው_ጥበቤ_ነው ከእሰርሱ ውጪ ክብርም ህይወትም የለም 👆 እወዳችኋለው #Share አድርጉ!! #JOIN_US t.me/anewcreature
Показати все...
🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

የዛሬ አምስት ዓመት የተጻፈ ቅድስት ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ <እንደ ሙሴ ሕግ> መፈጸም የነበረባት ነገር ነበር። ሕጉ <ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት። እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ተረክሳለች። በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከስጋው ሸለፈት ይገረዝ። ከደምዋም እስከምትነፃ ሰላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤ የመነፃትዋም ቀን እስኪፈፀም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ ወደ መቅደስም አትግባ> ይላል። ከርኩሰት ለመንፃት ማድረግ ያለባትንም ሕጉ ይናገራል። <የመነፃትዋ ወራት በተፈፀመ ጊዜ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት የርግብም ግለገል ወይም ዋኖስ ለሀጢአት መስዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ትመጣለች። እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል ያስተሰርይላትማል ከደምዋ ፈሳሽ ትነፃለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። ጠቦት ለማምጣት ገንዘብዋ ያልበቃት እንደ ሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግለገሎች አንዱን ለሚቃጠል መስዋዕት ሌላውንም ለሀጢአት መስዋዕት ታቀርባለች ካህኑም ያስተሰርይላታል እርስዋም ትነፃለች> ቅድስት ማርያም ይህ አይመለከታትም ብለው አስበው ይሆን? በርግጥም እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች ይኖራሉ። ወንጌላዊው ሉቃስ ግን እንዲህ ጽፏል:- <እንደ ሙሴም ሕግ የመንፃታቸው ወራት በተፈፀመ ጊዜ በጌታ ሕግ የእናቱን ማህፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት በጌታም ሁለት ዋልያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ መስዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት> ልብ ይበሉ፣ ማርያም ያመጣቸው መስዋዕት 1. ገንዘብ የሌላት ሴት የምትመጣው አንስተኛው መስዋዕት ነው። 2 መጽሐፉ እንደሚለው መስዋዕት ማቅረብ ስለነበረባት ነው ያቀረበችው ሉቃ 2፥22 ዘሁ 12፡፡ https://t.me/tewoderosdemelash/705
Показати все...
ቴዎድሮስ ደመላሽ

የዛሬ አምስት ዓመት የተጻፈ ቅድስት ማርያም ኢየሱስን ከወለደች በኋላ <እንደ ሙሴ ሕግ> መፈጸም የነበረባት ነገር ነበር። ሕጉ <ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት። እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ተረክሳለች። በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከስጋው ሸለፈት ይገረዝ። ከደምዋም እስከምትነፃ ሰላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤ የመነፃትዋም ቀን እስኪፈፀም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ ወደ መቅደስም አትግባ> ይላል። ከርኩሰት ለመንፃት ማድረግ ያለባትንም ሕጉ ይናገራል። <የመነፃትዋ ወራት በተፈፀመ ጊዜ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት የርግብም ግለገል ወይም ዋኖስ ለሀጢአት መስዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ትመጣለች። እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል ያስተሰርይላትማል ከደምዋ ፈሳሽ ትነፃለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። ጠቦት ለማምጣት ገንዘብዋ ያልበቃት እንደ ሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግለገሎች አንዱን ለሚቃጠል መስዋዕት ሌላውንም ለሀጢአት መስዋዕት ታቀርባለች ካህኑም ያስተሰርይላታል እርስዋም ትነፃለች> ቅድስት ማርያም ይህ አይመለከታትም ብለው አስበው ይሆን? በርግጥም እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች ይኖራሉ። ወንጌላዊው ሉቃስ ግን እንዲህ ጽፏል:- <እንደ ሙሴም ሕግ የመንፃታቸው ወራት በተፈፀመ ጊዜ በጌታ ሕግ የእናቱን ማህፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት በጌታም ሁለት ዋልያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ መስዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት> ልብ ይበሉ፣ ማርያም ያመጣቸው መስዋዕት 1. ገንዘብ የሌላት ሴት የምትመጣው አንስተኛው መስዋዕት ነው። 2 መጽሐፉ እንደሚለው መስዋዕት ማቅረብ ስለነበረባት ነው ያቀረበችው ሉቃ 2፥22 ዘሁ 12፡፡ …

ሰብዓ ሰገል በኮከቡ መሪነት ጌታችንን ካገኙ በኋላ ይዘውት የመጡትን ስጦታ ከመስጠት በተጨማሪ እኛ ሁላችን በሙሉ ደስታ ለምንሰግድለት ጌታ ሰግደውለታል። እነዚህ ሰዎች ለሕጻኑ ሲሰግዱ በወቅቱ በዚያ ሥፍራ ላይ ስግደት የሚገባቸው ሌሎች ሰዎች ስላልነበሩ ለማንም አልሰገዱም። ምናልባት በወቅቱ ከነበሩት ሰዎች ስግደት የሚገባው አካል ኖሮ እነርሱ ግን ሳይሰግዱ የቀሩ ከሆነ የመጀመሪያዎቹ........... እነርሱ ናቸው ማለት ነው። መጽሐፉ እንደሚነግረን የሰገዱት ለእርሱ ብቻ ነው። በእርግጥም ስግደት የሚገባው እርሱ ብቻ ነውና ለእርሱ ብቻ ለመስገድ የወሰናችሁ እውነተኛውን አምልኮ እየፈፀማችሁ ነውና በርቱ!! t.me/anewcreature
Показати все...
🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

. 🌲🌲🌲🌲🌹🌹🌹🌲🌲🌲 #እንኳን_ለብርሃነ_ልደቱ_አደረሳችሁ የልደት በዓልን ማከበር ዐላማው፥ ለተወለደው ሰው መልካም ምኞትን መግለጽና የደስታው ተካፋይ መኾን ነው። ብዙ ጊዜ ግን የልደት በዓል ይህን ዐላማ ይስትና ባለ ልደቱን ወደ ጎን ብሎ፣ በእርሱ ልደት የራስን ደስታ ማጣጣም ብቻ ይኾናል። ጌታ የተወለደው ለእኛ ነው። እርሱ የተወለደበትን ዕለት እንድናከብርለት ግን አላዘዘም። ኾኖም ለእኛ መድኀኒት ኾኖ መወለዱን ዐስበን ክብርን ለእርሱ ብንሰጥ መልካም ነው፤ ይገባናልም። ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔር፣ ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ይዞልን የመጣውን ምሥራች እንድናስተውል ይፈልጋል። መላእክት ለእረኞቹ የነገሯቸው ሰዎች ኹሉ ሊሰሙት የተገባ ምሥራች ነው፤ “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የኾነ ተወልዶላችኋል።” (ሉቃ. 2፥11)። ከድንግል ማርያም የተወለደው  ኢየሱስ በሦስት ማንነቶች ተገልጿል፤ #እርሱ መድኀኒት ነው፤ #እርሱ ክርስቶስ ነው፤ #እርሱ ጌታ የኾነ ነው። @fkrbefkr143 1ኛ. #የተወለደው መድኀኒት ነው፤ - ሕዝቡን ከኀጢአታቸው የሚያድን መድኀኒት (ማቴ. 1፥21)። ጳውሎስ በአይሁድ ምኵራብ ተገኝቶ ባሰማው ስብከት ውስጥ እንደ መሰከረው፣ ከዳዊት ዘር "እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኀኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።" (ሐ.ሼ. 13፥23)። ሰው ግን እግዚአብሔር ያመጣለትን መድኀኒት፣ ኢየሱስን ባለማስተዋል፣ ከእግዚአብሔር ያልተሰጡትን ሌሎችን መድኀኒት እያለ እድንባቸዋለሁ ብሎ ሲሞክር ኖሯል። ከኀጢአት ለመዳንና ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ብዙ ቦታ ረግጠንና ተንከራትተን ነበር። አኹንም መድኀኒቱን ፍለጋ በመንከራተት ላይ ያሉ ሞልተዋል። በዚያ መንገድ መዳን ግን አልተገኘም። ኢየሱስ ሲወለድ እግዚአብሔር በመላእክቱ በኩል ለሕዝቡ የላከው ምሥራች 'የተወለደው መድኀኒት ኢየሱስ ነውና ዳኑበት’ የሚል ነው። ምሥራቹን ሳይሰሙና ከኀጢአት ለመዳን ከዚህ መድኀኒት ጋር ሳይተዋወቁ ልደቱን ማክበር፣ ኀላፊ ደስታንና ፈንጠዝያን ከመሸመት ያለፈ ረብ የለውም። 2ኛ. #የተወለደው ክርስቶስ ነው። በተስፋ ሲጠበቅ የነበረው መሲሕ መወለዱ፣ ሲጠባበቁት በነበሩት ዘንድ የተስፋውን መፈጸም አሳይቷል። ዛሬም ብዙዎች እግዚአብሔር ያመጣውን መድኀኒት ቸል ብለው፣ ራሳቸው ወይም ሌሎች ሰዎች ያዘጋጇቸው፣ በተለያየ መንገድ ለመዳን ተስፋ የሚያደርጓቸው ሌሎች አዳኞች አሉ። አንዳቸውም ግን የተረጋገጠ ተስፋ አይሰጡም። ኹሉንም ከመሞከር ባለፈ ልብ ያረፈበት አዳኝ ፈጽሞ አላጋጠመም፤ የለምና። በእውነት ነፍሳችን ድኅነትን ከእርሱ በመጠባበቅ የምትናፍቀው መሲሕ እነሆ ተወልዷል። ወደ መሲሑ በእምነት እንኺድ፤ እናግኘውም። መሲሑን ሲጠባበቁ ከነበሩት ወገኖች መካከል እርሱን ያገኙት እንዴት እንደ ኾኑ ወንጌል ይመሰክራል፤ “ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ሾለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።” (ዮሐ. 1፥45)። ከዚያ በኋላ እነዚህ ሰዎች ከመሲሑ አልተለዩም፤ መሲሑን ተከትለውት ቀሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም ኾኑ። 3ኛ. #የተወለደው ጌታ የኾነ ነው። ጌቶች ሳይኾኑ ባሮች አድርገው ሲገዙን ከኖሩት ጌቶችና እመቤቶች ነጻ ሊያወጣንና በእኛ ላይ እርሱን ብቻ ጌታ አድርገን እንድንሾም ጌታ የኾነው ኢየሱስ ተወልዷል። "መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ኾነ በምድርም ኾነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ኹሉ ከእርሱ የኾነ እኛም ለእርሱ የኾንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ኹሉም በእርሱ በኩል የኾነ እኛም በእርሱ በኩል የኾንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።"          #የምሥራች!!! #መድኀኒት#ክርስቶስ#ጌታ የኾነው #ኢየሱስ_ተወልዶላችኋል!!! ከተስማማችሁ አሁኑኑ #Share አድርጉ 🌲🌲🌲🎋🎋🥀🌲🌲🌲🌲🌲 👇JOIN US👇 t.me/fkrbefkr143
Показати все...
ፍቅርን ♥ በፍቅር

♥♥💚💚💚♥♥♥💙💙💙♥♥ ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን ይህ Channel የናንተ Channel ነው!! ስለ ፍቅር የምናውቅበት ቤታችን ነው። ፍቅርን በተመለከተ post እንድደረግ የምትፈልጉ እና ሀሳብ አስተያየት 👉 @photopicBot ላኩልን for Promotion @Promoandcomment_bot ♥ይቀላቀሉን♥

📚📚📚😱📚📚 #አስደናቂ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_እውነታዎች በምዕራፉ ብዛት እና አከፋፈሉ ከሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚመሳሰለው መጽሐፍ ትንቢተ ኢሳይያስ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጻሕፍት፤ 39 የብሉይ ኪዳንና 27 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዳሉት ሁሉ ትንቢተ ኢሳይያስም 66 ምዕራፋት አሉት። ልክ እንደዛው ሁለ ከዚህ ውስጥ 39ኙ ምዕራፍ ስለ ህግ እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት ሲናገሩ 27ቱ ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ፀጋ እና ስለ መዳን(ድነት) ያወራሉ። 👇👇 t.me/anewcreature
Показати все...
🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

◌◌◌◈◈◈◈◉◉◉◉####◆◆◆◊◊◊ ኢየሱስ ለምን መጣ? የዛሬ ዓመት አካባቢ በቫይበር ግሩፕ ውስጥ ከአንድ ሰው ጋር በክርስቶስ መካከለኝነት ዙሪያ ውይይት አድርገን ነበር፡፡ ያ ሰው ከእኔ በፊትም ሆነ በኋላ በዚሁ ርዕሰ ጉደይ ላይ ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር ሲወያይ ነበር፡፡ ነገርየው ዓመት ያለፈው ቢሆንም አሁንም ግን በዚህ ርዕስ ላይ አናግሩኝ የሚል ጥሪውን በማቅረብ ላይ ይገኛል (አንድ ሰው በውስጥ በኩል ‹‹ይህ ልጅ ያስጠኑት ይህን ብቻ ነው እንዴ?›› ያለኝም ከዚህ በነሣት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከዛሬ ዓመቱ የዘንድሮው ለየት የሚለው ‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው ወይስ አይደለም?›› የሚለው ጥያቄው ለወጥ ብሎ ‹‹ኢየሱስ የመጣው ሊያማልድ ነው ወይስ ሊያድን?›› በሚል መቅረቡ ነው፡፡ በእርሱ እምነት መሠረት የክርስቶስ የማዳን ሥራ እና የምልጃ ሥራ ለየቅል ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንደሚያስተምረው ‹‹… በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል…›› ነው የታረቅነው (ቆላስየስ 1፡21-22)፣ ከዚህም ሌላ ‹‹ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን›› በማለት ያስረግጥልናል (ሮሜ 5፡9-10)፡፡ ክርስቶስ የሞተው ደግሞ እኛን ለማዳን ነው፡፡ ስለዚህ ሞቱ እርቃችንም መዳኛችንም ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ‹‹የሰው ልጅም ሊያገለግልና ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንያገለግሉት አልመጣም›› የሚለውም መዘንጋ የለበትም (ማርቆስ 10፡45)፡፡ ስለዚህ የክርስቶስን ምልጃ ለመካድ የሚፈልጉ ሰዎች ማደኑንና ምልጃውን የተለያዩ ነገሮች ለማድረግ የሚያደርጉት ሙከራ ከልብ እልከኝነት የሚመጣ እንቢ ባይነት እንጂ ሁለቱ የሚለያዩ ስለሆኑ አይደለም፡፡ t.me/anewcreature
Показати все...

ቅዱሳንን መስበክ ክርስቶስን መስበክ ነውን? እንዲህ ሲባል ስሰማ ወደ አእምሮዬ # ስለ ሞባይል መናገር ለቴሌቪዥን ምኑ ነው? # ስለ እሳት ማውራት ለእርግብ ምን ፋይዳ አለው? የሚል ነገር ታሰበኝ። የሆነው ሁሉ ይሁንና ቅዱሳንን መስበክ ክርስቶስን መስበክ የሚሆነው እንዴት ነው? ቅዱሳን ዋጋ የከፈሉት፣ መከራን የተቀበሉት በክርስቶስ በማመናቸው ነው። ስለዚህ ስለ ቅዱሳን መስበክ ክርስቶስን መስበክ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። በርግጥ ግን ነው ወይ? የሚለውን ቢያሳይ በሚል አንድ መጽሐፍ ማቅረቡ ብቻ በቂ ነው። ድርሳነ ሚካኤል በድርሳነ ሚካኤል መሠረት # በሚካኤል ቀን ለቤተ ክርስቲያን ዕጣን የሰጠ፣ # በሚካኤል ስም የተራበ ያበላ የተጠማ ያጠጣ፣ # በሚካኤል ስም የታረዘ ያለበሰ፣ # በሚካኤል ስም የታመመውን የጎበኘ፣ # ስለ ሚካኤል ስም እስረኛን የጠየቀ <ገሀነምን አያይም> (ገፅ 5-7)። ይህ መልዕክት የሚሰጠው ዋስትና በሚካኤል ስም በሚደረግ ነገር የዘላለም ሕይወት ይገኛል የሚል ነው። የሚገርመው ነገር በዚህ ገጸ ንባብ ውስጥ ክርስቶስ የሌለ መሆኑ ነው። ያለ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ የሚል የስህተት ትምህርት እያስተማሩ <ቅዱሳንን መስበክ ክርስቶስን መስበክ ነው> ብለው ሊያሞኙን ይሞክራሉ። t.me/anewcreature
Показати все...
🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

ን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። እርሱም በዘመነ ሥጋዌው አይሁድ፥ “አንተ ማነህ?” በማለት ላቀረቡለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ፥ “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርኹት ነኝ” በማለት እርሱነቱን ገልጦላቸዋል (ዮሐ. 8፥25)። በዚህም ሕዝቡን በክርስቶስ ያሉ የክርስቶስ ሕዝብ አሰኝቷል (ኤፌ. 2፥12፤ ዕብ. 11፥25-26)። ተልኮ መምጣት የልጅነት ግብሩ መኾኑንም በቃሉ አረጋግጧል (ዮሐ. 7፥28-29፤ 8፥26)። በሌላም አኳኋን ቅዱስ ጳውሎስ ሕዝበ እስራኤልን በምድረ በዳ እየተከተለ ውሃ ያጠጣቸው ዐለት ክርስቶስ መኾኑን መስክሯል (1ቆሮ. 10፥4)። ሙሴ፥ “እባክኽን ክብርኽን አሳየኝ” ሲል ላቀረበው ጥያቄ፥ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልክም፤ … እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ። በዐለቱም ላይ ትቆማለኽ፤ ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዐለት አኖርኻለኹ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኹ። እጄንም ፈቀቅ አደርጋለኹ። ጀርባዬንም ታያለኽ፤ ፊቴን ግን አታይም” የሚል መልስ ከእግዚአብሔር ተሰጠው (ዘፀ. 33፥18-23)። እግዚአብሔር መንፈስ በመኾኑ በመለኮታዊ ባሕርዩ መታየት ባይችልም፥ የክርስቶስ አምሳል በነበረው ዐለት ለሙሴ ክብሩን አሳይቶታል። ዛሬም ቢኾን እግዚአብሔርን ማየት የሚችል የለም። ለሙሴ በምሳሌው ዐለት ላይ ክብሩን እንዳሳየ ኹሉ፥ በአማናዊው፥ በዕቅፉ ባለውና የመለኮቱ ሙላት በተገለጠበት፥ የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ በኾነው፥ ሥጋን ለብሶ በመጣው በክርስቶስ እግዚአብሔር ተገልጧልና “እኔን ያየ አብን አይቶአል” (ዮሐ. 14፥9) ሲል መሰከረ (ዮሐ. 1፥18፤ ቈላ. 2፥9፤ ዕብ. 1፥3፤ ፤ 1፥14)። እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን፥ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአርኣያ መልአክ በአርኣያ ኰኵሕ (ዐለት) ተገለጠ ማለት፥ እርሱ ፍጡር መልአክ ነው፤ ወይም ደግሞ የዘመኑ አርዮሳውያን አፋቸውን ሞልተው እንደሚናገሩት፥ ‘ኢየሱስ ሚካኤል ነው’ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን በመልአክ አምሳል ተገልጦ ሕዝቡን መራ፤ እኛንም ሰው ኾኖ አዳነን ማለት ነው እንጂ። “ወበእንተ ዝንቱ ተሰምየ ውስተ መጻሕፍት ወልደ እጓለ እመ ሕያው በእንተ ሥርዐተ ትስብእቱ፥ ወዓዲ ተሰምየ እግዚአብሔር፥ ወልደ እግዚአብሔር፥ ወመልአከ፥ ወመዝራዕተ፥ ወነቢየ፥ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ አምላክ ወዓዲ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ ሰብእ” ትርጓሜ፥ “ስለዚህም ሰው ስለ ኾነ በመጻሕፍት ውስጥ የሰው ልጅ ተባለ። ዳግመኛም እግዚአብሔር፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ መልአክ፥ ክንድ፥ ነቢይ፥ ተባለ። አምላክ እንደ ኾነ መላልሶ መጽሐፍ ያስረዳል። ሰውም እንደ ኾነ መላልሶ ያስረዳል።” (ሃይማኖተ አበው 1986፣ ገጽ 350፤ ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቍጥር 6 እና 7)። t.me/anewcreature
Показати все...
🚩የህይወት መንገድ/The Life Way🔛🚶

👉 ይህ channel ዋናዉ አላማው📌 ▶አዳዲስ የሆኑ መዝሙሮችን ለእናንተ ማቅረብ🎷 ▶አስተማሪ ጹሑፎች በመለጠፍ ስዎችን ወደ ክርስቶስ ፍጹም ሙላት ማሳደግ📖 ▶አስተማሪ የምሁራን ንግግሮች ለእናንተ እና ▶ግጥሞች ▶ስብከቶች ለእናንተ ማድረስ ነው። 🗽ባላቹ ጸጋ በማገልገል የምትፈልጉ @anewcreature @anewcreature Any comment @GEMEDJ2111

የተቀበረ መክሊት 3ኛው ዕትም ከገጽ 54-58 ስለ ኅዳር ሚካኤል የሚከተለውን አስፍሯል “ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ በዓልየ ወሑሩ በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ሚካኤል” (የመስከረም ሚካኤል ዚቅ)። ትርጓሜ፥ “ሚካኤል አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፥ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችኹ።” “ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ ሰንበትየ ወሑር በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ከራሜ ከራሜ እም በረከትየ ወእም ፍሬ ተግባርየ ይቤ ቅዱሰ እስራኤል” (መጽሐፈ ድጓ 1959፣ ገጽ 58)። ትርጓሜ፥ “የእስራኤል ቅዱስ (እግዚአብሔር) አለ፤ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? ሰንበቴን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፥ ከበረከቴም የከረመ የከረመውን ትበላላችኹ።” መጽሐፈ ዚቅ ይህ ቃል የሚካኤል ቃል ነው ቢልም፥ ድጓው ይህን የሚሠራው ግን ለእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስም ይህ ሥራ የሚካኤል ሳይኾን የሚካኤል አምላክ የሕያው እግዚአብሔር ተግባር መኾኑን ያረጋግጣል (ዘሌ. 24፥18-22፤ ኢሳ. 59፥1)። “በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ፥ ከበረከቴም ትበላላችኹ” ለማለት የተገባው ከአንዱ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በቀር ከቶ ማነው? (መዝ. 103/104፥13)። “ሚካኤል በዓሌን አክብሩ” አለ ብለው ያልተጻፈ በማንበብ እውነቱን እንድንመሰክር ካነሣሡን፥ የሚካኤል በዓል አከባበር በተለይም የኅዳር ሚካኤል እንዴት መከበር እንደ ጀመረ ታሪካዊ የት መጣውን ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ማስረጃ በማቅረብ ማሳየት እንችላለን። በግብጽ አገር ‘ዙሐል’ ተብሎ የሚጠራ ጣዖት ነበር። የግብጽ ሰዎች ከሌሎች ጣዖታት እጅግ አደርገው ያከብሩታልና ያመልኩት ነበር። ከሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ቀጥለው የተሾሙ ብፁዓን ጳጳሳት፥ ቅዱሳን አበውም ኹሉ የዙሐልን ተመላኪነትና ተከባሪነት ማስቀረት ሳይቻላቸው እስከ 320 ዓ.ም. ያኽል የግብጽ ሰዎች ሲሰግዱለት ሲያመልኩት ኖረዋል። ዙሐል ከቀሩት ጣዖታት የበለጠ ተኣምራታዊ ኀይል ወይም የተለየ ምትሀት ኖሮት ሳይኾን፥ የቀሩት ጣዖቶች አንድ በአንድ ሲወድቁና ሲደመሰሱ የግብጽ ሕዝብ አልተጋፋም ነበር። ዙሐልን የደፈርን እንደ ኾነ ግን ሕዝብ ይነሣብናል በማለት ፈርተው ነበር። በተጠቀሰው ዓ.ም. ግን የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባ እለእስክንድሮስ እንደ ምንም ብሎ ሕዝቡን እያግባባና እያስተባበረ፥ እያባበለም ብዙዎችን በማስረዳትና በማሳመን “ዙሐል” ከምኵራበ ጣዖትነቱ ተነሥቶ በምትኩ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት እንዲገባበት አድርጎ የዙሐል በዓል በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን ይከበር ስለ ነበረ፥ ‘ኀዲገ ልማድ ጽኑዕ ውእቱ - (ልማድን መተው አስቸጋሪ)’ ነውና ሕዝቡን ለማስደሰት ሲል በዚያው በተለመደው ኅዳር 12 ቀን ይከበር ብሎ ዐዋጅ አስነግሮ ዐዋጁም ጸደቀ። (መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት 1988፣ ገጽ 152-153)። የእግዚአብሔር እውነተኛና ታማኝ አገልጋይ፥ ምን ጊዜም ቢኾን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ለማስደሰት ሲል አይኖርም። አሊያማ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሊባል አይችልም። “ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አኹን እሺ አሰኛለኹን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለኹን? አኹን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልኾንኹም” (ገላ. 1፥10፤ 1ተሰ. 2፥4)። የኅዳር ሚካኤል በዓል አከባበር የት መጣው እንዲህ ኾኖ ሳለ፥ ዛሬ ግን በዕለቱ የሚነገረው የዙሐልን በዓል ለማስቀረት ባለመቻሉ በምትክነት የተሠራ በዓል መኾኑ አይደለም፤ ‘ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣበት ቀን’ ተብሎ ነው የሚከበረው (ድርሳነ ሚካኤል ዘኅዳር)። መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ማውጣቱን አይናገርም። ርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ሚካኤልን ልኮ ሕዝቡን ከግብጻውያን እጅ ሊያድናቸው ይችላል። እንዲያውም በዘመኑ መጨረሻ በክርስቶስ አዳኝነት አምነው ለሚድኑቱ የእስራኤል ቅሬታዎች (ትሩፋን) ሚካኤል እንደሚቆም የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል (ዳን. 12፥1 ፤ ራእ. 12፥7)። ሙሴ ጽላት ተቀብሎ ከተራራው እስኪወርድ ድረስ ታግሠው መጠበቅ አቅቷቸው፥ አሮን ያቆመላቸውን ጣዖት ማምለክ በቀጠሉት፥ ዐንገተ ደንዳኖቹ የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ዐዝኖ፥ “ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ኾንኽ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋኽ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትኽ መልአክ እሰድዳለኹ” ሲላቸው በሰሙት ክፉ ወሬ ዐዘኑ (ዘፀ. 33፥1-4)። ከዚህም የምንረዳው እስከዚህ ጊዜ ድረስ እስራኤልን የመራው ፍጡር መልአክ ሳይኾን ራሱ እግዚአብሔር መኾኑን ነው። በዚህ ጊዜ ግን እርሱ ዐብሯቸው እንደማይወጣና ፍጡር መልአክ እንደሚመድብላቸው ነገራቸው። ለእነርሱ ይህ ክፉ ወሬ ነበርና በሰሙት ነገር ዐዘኑ። “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣኽስ፥ ከዚህ አታውጣን” አሉ። በመጨረሻም እግዚአብሔር “እኔ ከአንተ ጋር እኼዳለኹ፥ አሳርፍኽማለኹ አለው” (ቍጥር 14-16)። ስለዚህ እስራኤልን የመራቸው ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሚካኤል አልነበረም ማለት ነው። ሙሴና ሕዝበ እስራኤል ፍጡር መልአክ (ሚካኤል) ሳይኾን፥ ጌታ ራሱ ነጻ እንዳወጣቸውና የሚመራቸውም እርሱ ራሱ መኾኑን ተረድተዋል። በጣዖት አምልኮት እስካሳዘኑት ጊዜ ድረስም ዐብሯቸው የተጓዘው እግዚአብሔር እንደ ነበረ፥ ከዚህ በኋላ ግን እርሱ ዐብሯቸው እንደማይወጣና ሌላ ፍጡር የኾነ መልአክ እንደሚልክላቸው መናገሩ ብቻ እንኳ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው። ይህን ኹኔታ የሰሙት ሙሴና ወገኖቹ፥ በፍጡር መልአክ በመመራትና በራሱ በእግዚአብሔር በመመራት መካከል ትልቅ ልዩነት አለና በሰሙት ክፉ ወሬ ማዘናቸው፥ እርሱ ዐብሯቸው ካልወጣም ከዚያ ስፍራ እንዳያወጣቸው መማጸናቸው የነገሩን እውነተኛነት ያረጋግጥልናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝበ እስራኤል ከምድረ ግብጽ ሲወጡ በፊታቸው የወጣው መልአክ ሚካኤል ነው አይልም (ዘፀ. 3፥2-6፤ 23፥20-23፤ ሐ.ሥ. 7፥30-34)። ስሙ በግልጥ ያልተጠቀሰው ይህ የጌታ መልአክ፥ ፍጡር የኾነ መልአክ ሳይኾን ራሱ እግዚአብሔር በአርኣያ መልአክ ተገልጾ መኾኑን የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ስፍራ ያስተምረናል (ዘዳ. 32፥12፤ መሳ. 2፥1-5፤ 6፥8-9፤ መዝ. 135/136፥16፤ 104/105፥43፤ ኤር. 32፥21፤ ሆሴ. 12፥14)። አባ ስብሐት ለአብ በተባሉ አባት እንደ ተደረሰ በሚነገረውና “ሰይፈ ሥላሴ” በተሰኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ የጸሎት መጽሐፍ በረቡዕ ምንባብ ላይ፥ በምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ የታየውና ሕዝቡን የመራው የእግዚአብሔር መልአክ፥ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይላል፤ “ስብሐት ለመልአከ እግዚአብሔር ዘአስተርአዮ ለሙሴ በነደ እሳት በኀበ ዕፀ ጳጦስ መልአክኒ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ። - በእሾኽ ቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መልአክ ክብር ይኹን። መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው” (1991፣ ገጽ 66)። እግዚአብሔር ወልድ በተለየ ግብሩ ልጅ ነውና ልጅነቱን ለአባቱ የሚታዘዝ፥ የሚላክ፥ ጻድቅ ባሪያ፥ ቅን አገልጋይ፥ ፈቃድ ፈጻሚ በመኾን አሳይቷል (ኢሳ. 42፥1፤ 52፥13-15፤ 53፥11፤ ዮሐ. 17፥1-5፤ ዕብ. 5፥8)። “ቃሉን ላከ፤ ፈወሳቸውም” ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. 106/107፥20) እግዚአብሔር በአርኣያ መልአክ ወደ ሕዝቡ የላከው አካላዊ
Показати все...