cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል

እናንብብ እንለወጥ !! " ንባብ የአእምሮ ምግብ ነው " 📞 +25190 112 2031 https://t.me/Lihket_Reading

Більше
Ефіопія7 132Амхарська5 231Книги9 551
Рекламні дописи
1 936
Підписники
+124 години
+77 днів
+1630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የመናዊቷ ደላላ በአዲስ አበባ ትጋት እንማር መልካም ቅዳሜ !! ከቤቷ ልጆቿን ይዛ ስትወጣ ወደኋላ መለስ ብላ ቤቷን አላየችም፡፡ እንደነገሩ እንኳን አልዘጋችውም፡፡ የለበሰችውን ልብስ ብቻ ለብሳ ነው ከየመን የወጣችው የመናዊቷ ኢፕቲሳም ካሊድ። ከየመን በስደት መጥታ ኑሮዋን በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አበባ ካደረገች ድፍን 9 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ኢፕቲሳም በየመን በተነሳው ጦርነት ምክንያት ጦርነትን ሽሽት ልጆቿን ይዛ ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ባህር አቋርጣ ኢትዮጵያ ገባች። ኢትዮጵያ ስትገባም እጇ ላይ ምንም ገንዘብ አልነበራትም፡፡ ነገር ግን ከሀገሯ ስትወጣ ለልጆቿ የተሻለ ህይወት ለመስጠት ቃል ገብታለችና ህይወቷን በብርታት መቀጠል ነበረባት፡፡ ታዲያ በስደት እንደመጣች ኑሮዋ ለመጀመርያ ጊዜ የሆነው ብዙዎች ሰርተው ከሚያድሩባት መርካቶ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ኢፕቲሳም ለልጇቿ የምትሰራው የተጠበሰ ብስኩት (ፓስቲ) ይሸጥ እንደሆነ የሚያልፍ መንገደኛ ጠየቃት፡፡ እሷም ከንግግሩ “ይሸጣል” የሚለውን ቃል ጆሮዬ ያዘቻት ስትል ከአዲስ ዋልታ ጋር በነበራት ቆይታ ገልጻለች፡፡ ከዚህም በኋላ ፓስቲ እየሰራች መሸጥ የገቢ ምንጯ ሆነ፡፡ ኢፕቲሳም በዚህ አልቆመችም የደጋግ ጓደኞቿ እርዳታ ተጨምሮበት ዛሬ ላይ የጀበና ቡና እና ምግብ በአነስተኛ ቦታ እየሰራች ትሸጣለች። አማርኛን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችንም ትናገራለች፤ ከሰው ጋርም ተግባቢ ናት፡፡ ከቡና እና የምግብ ስራ በተጨማሪ የድለላ ሥራ ትሰራለች። “መርካቶ ውስጥ እስካለሽ ብዙ ነገር መሞከር አለብሽ” የምትለው ኢፕቲሳም በትጋት እየሰራች ልጆቿን ታስተምራለች፡፡ ልጆቿ እናታችን ተምሳሌታችን ናት ይላሉ፡፡ የመናዊቷ ኢፕቲሳምም የስራና የቤተሰብ ኃላፊነት ሳይበግራት በድረ ገጽ የአካውንቲንግ ትምህርቷን ትከታተላለች፡፡ በትምህርቷም ሁለተኛ ዓመት ላይ ደርሳለች። ከWMCC ገፅ የተወሰደ
Показати все...
👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
We are excited about tonight's discussion, Join us this evening, as we talk about law.
Показати все...
ሰላም የ ልህቀት ቤተሰቦች: ዛሬ ማታ ስለ ህግ እንወያያለን. የህግ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው? ተናጋሪውን እንድጠይቅላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ ይላኩልን። @Ebba116 @Misgana_Tessema ማታ 3:00 ይጠብቁን።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Drowning in being positive pressures? Join our LIVE review of "The Subtle Art of Not Giving a ****" by Mark Manson. Learn how to prioritize your Cares and find freedom! #NotGivingA*** #LiveDiscussion #BookReview #lihiket
Показати все...
👍 6 2
አንብብና አስተላልፋት የምወድህ አንባቢዬ ሆይ ፥ እንደምን አለህልኝ? ሕይወትስ እንዴት ነው? የማያልቀው የአንድዬ ጸጋ፥ ሰላምና ምሕረቱ ይብዛልህማ። ይህን ርእስ ገና እንዳየኸው፥ “ምን ላንብብ? ለማንስ ላስተላልፋት?" እንደምትለኝ እገምታለሁ፡፡ ይኹን እንጂ፥ እሱን ገና በጠዋቱ አልነግርህም፤ ይህችን መጣጥፍ ለመጫር ምክንያት የኾነኝን ነገር ጨምሬ ወደ ጽሑፉ መጨረሻ ገደማ ነው የምነግርህ። ከኹሉ አስቀድሞ ስለ ንባብ ወይም ማንበብ ጥቂት እንድጫጭር እያነበብህ ፍቀድልኝ። ልጆች ኾነን ሳለ፥ አባባ ተስፋዬ ሣህሉን “በቀበሌ ቴሌቪዥን”107 መስኮት ለማየት በጕጕት እንጠብቃቸው ነበር። ከጣፋጭና ተናፋቂ ዝግጅቶቻቸው ማሳረጊያ ላይ ታዲያ “ደኅና ኹኑ ልጆች፤ የዛሬ አበባዎች፥ የነገ ፍሬዎች" በምትሰኘዋ የስንብት ቃላቸው እየባባን ወደየቤታችን እንበታተናለን፤ በአባባላቸው እንደሰታለን፣ የዚያን ጊዜው “አሰባዎች” የያኔው ነገ (የአኹኑ ዛሬ መኾኑም አይደል?) ደግሞ “ፍሬዎች” እንኾናለን ብለን። አንተም ወዳጄ ይኸን ብሂል ሳታስታውሰው አትቀርም። አባባሉን አባባ ተስፋዬ አልፈጠሩት ይኾናል፤ በርግጥ። አንዳንድ ጊዜ ይህን ተናፋቂ አባባል ወደ አንባቢነት ክብር ብንለውጠውስ? ብዬ አስባለሁ። የዛሬ አንባቢዎች የነገ መሪዎች መኾናቸውን ጠንቅቀው የተረዱ ወገኖች: "አንባቢዎች መሪዎች ናቸው" ብለዉናል። እኛ መዳፍ ስናነብ፥ የቡና ሲኒ ገልብጠን ስንደናበርና ሞራ ስናጠና ኖረን አገሩን ከቡና ጠጪነት፥ ከበሬ ኢኮኖሚ፥ ከሐሜት ሰባኪያን ብኩንነትና ከበቀል የፖለቲካ አዙሪት ሳናወጣው ቀርተናል። አንዳንድ ያነበቡ የመሰላቸው ወገኖችም፥ ዐሠሥ-ገሰሱን ኹሉ ጨማምረው ስለ ዋጡ፥ በየልባቸው የተሻጠው ሥንጥር ባጥወለወላቸው ቍጥር፥ “ዐዋቂነታቸውን" ለማሳየትና “ፈላስፋነታቸውን” ለመግለጥ ሲያምራቸው፥ ወደሰማይ አንጋጦ ጽርፈት (ስድብ) መወርወር ጥበብ መስሎ ታይቷቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ “ያነበቡስ የት ደረሱ?" የሚሉ እንዳሉም ሰምተናል። መልሱ “የት አልደረሱም?” የሚል ነው። በዚህ ወቀሣ የማይስማሙና “ባለማንበብማ፥ አያቴ አይታማ” የሚሉ ወገኖች ይኖሩ ይኾናል። አንድ ግብዝ በዚሁ ርእሰ ጕዳይ በተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ላይ "የኛ አባቶች እኮ፥ እንኳን መጽሐፍ ሞራ ያነብባሉ" በማለት አደባባይ ወጥቶ በሌለ ነገር ሲጽናና ተሰምቷል። ድካማችንን ተረድተን ማስተካከሉ ይሻለናል እንጂ ከንቱ ፉከራማ ባዶ ሌማት ከድኖ “ቤቱ ሙሉ ነው" እያሉ እንደ ማጨብጨብ ይቈጠራል። በርግጥ አስተዋይነትን የግድ ከአንባቢነት ጋር ብቻ አናቈራኘውም። ፊደል ያልቈጠሩ ሕያው ቤተ መጻሕፍት በአፍሪካ ጓዳ ጐድጓዳውን ሞልተውታል፡፡ ለዚህም እኮ ነው፥ በአፍሪካ ሰማይ ሥር፥ አንድ አረጋዊ ሲሞት፥ “ ቤተ መጽሐፉ ተቃጠለ" የሚባለው። ኾኖም የማንበብ ሸጋ ዋጋ ሲጣጣል ዝም አይባልም። ከንባብ ርቀን ለመቅረታችን ማሳያ አምጡ ቢባል ከባድ አይደለም፤ “ዕንቍህን ከአፍሪካዊ ለመደበቅ ከፈለግህ፥ በመጽሐፍ ውስጥ አስቀምጠው" በማለት የተሣለቁብን የሽሙጥ ቃል ብቻውን ብዙ ሲናገር ኖሯልና። የተቈረሱ ነፍሶች 266-267 በሰለሞን አበበ
Показати все...
👍 1
መደነስ እችል ነበር! ሰዎች ከእችላለሁ ከፍታ ወደ አልችልም እንዴት ቀስ በቀስ እንደሚወርዱ ለማወቅ የፈለገ አንድ ሰው አንድን ራጅም አመታትን የፈጀ ጥናት አደረገ፡፡ የተወሰኑ ሕጻናትን ሰብስበው፣ “ስንቶቻችሁ መደነስ ትችላላችሁ” ብሎ ገና ከመጠየቁ የሕጻናቱ በሙሉ እጅ ወደላይ ወጥቷል፡፡ ሕጻናቱ በሙሉ መደነስ ይችላሉ፡፡ እስቲ ደንሱ ሲባሉ ሁሉም በየአቅጣጫው መወራጨት ጀመረ፡፡ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ይዞ መጣና፣ “ስንቶቻችሁ ማዜም ወይም መዝፈን ትችላላችሁ” አላቸው፡፡ ሁሉም እጃቸውን አወጡ፡፡ እንዲያሳዩ ሲጠየቁም ሁሉም ባሉበት ንግግር ይሁን ዜማ የማይታወቅ ድምጽ በማውጣት ማንጎራጎር ጀመሩ፡፡ ሕጻናቱ በሙሉ ማዜም ይችላሉ፡፡ እነዚህን ልጆች ከብዙ አመታት በኋላ ጎልማሳ በሆኑበት ጊዜ ተከታትለው በያሉበት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ጠየቋቸው፡፡ ሆኖም አብዛኛዎቹ መዝፈንም ሆነ መደነስ እንደማይችሉ ተናገሩ፡፡ የአብዛኛዎቹ ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ለመዝፈንም ሆነ ለመደነስ ባደረጉት ሙከራ ሰዎች ሲያሾፉባቸው ስለሰሙና ስላዩ መሆኑን ደረሱበት፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ማንጎራጎርና ሰውነትን በደስታ ማንቀሳቀስ የማይችል ሰው የለም፡፡ ነገር ግን በዙሪያችን ያለችው አለም ደረጃ በማውጣት ለዚያ ደረጃ የማይመጥን ለመሰላት ሰው ርህራሄም የላት፡፡ የዳንስና የዜማን ጉዳይ ለመነሻነት ተጠቀምንበት እንጂ እውነታው ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡ ድሮ እንደምንችለው እናስብና እናውቅ የነበርነውን ነገር ከብዙ ውጣ ውረድና የሰዎች የአመለካከት ወላፈን በኋላ ፈጽሞ እንደማንችል ቆጥረን እጃችንን አጣምረን የተቀመጥን ሰዎች ቁጥራችን ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ እንደማትችሉ ሰዎች የነገሯችሁንና ለራሳችሁም የነገራችሁትን ተወት አድርጉትና  “እችል ነበር፣ አሁንም እችላለሁ!” በማለት እንደገና ተነሱ፡፡ ትችላላችሁ! ዶ/ር  እዮብ ማሞ
Показати все...
👍 4
የድግግሞሽ ተጽእኖ! ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት ቅባት፣ ስኳርና የመሳሰሉት ነገሮች የበዛበት ምግብ ብትመገቡ ምንም ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ እንደዚህ አይነት ምግብን ግን ለወራትና ለአመታት በየቀኑ ብትመገቡ ግን በክብደታችሁና በጤንነታችሁ ላይ ለውጥ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት በስራ፣ በማሕበራዊ ግንኙነትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ውጥረት ውስጥ ብታሳለፉ ምንም ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ በእንደዚህ አይነት ውጥረት ውስጥ ግን ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታሳልፉ ግን በስነ-ልቦናችሁ፣ አልፎም በአካላችሁ ላይ ቀውስን ማስተናገዳችሁ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት በየጠዋቱ ስፖረት ብትሰሩ በአካል ቁመናችሁም ሆነ በጤንነታችሁ ላይ ምንም ለውጥ ላታዩ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ልምምድ ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታደርጉ ግን በጥንካሬያችሁ፣ በቁመናችሁና በጤንነታችሁ ላይ መልካም ለውጥን ማምጣታችሁ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት መጽሐፍትን በየቀኑ ብታነቡ በእውቀታችሁና በአመለካከታችሁ ላይ ብዙም ለውጣ ላታስተውሉ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ልምምድ ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታደርጉ ግን በእውቀታችሁም፣ በአመለካከታችሁም ሆነ በእድገታችሁ ላይ ድንቅ ለውጥ ማምጣታችሁ አይቀርም፡፡ የቀረውን ስሌት እናንተው ስሩት፡፡ በተደጋጋሚ ማድረግ የጀመራችሁት የጤና-ቢስ ልምምድ ተጽእኖ ተጠራቅሞ ሳያጠፋችሁ አሁኑኑ አቁሙ! በተደጋጋሚ ማድረግ የጀመራችሁት ጤናማ ልምምድ ደግሞ ተጠራቅሞ መልካም ለውጥን እንዲሰጣችሁ በዚያው ቀጥሉበት!
Показати все...
6👍 3
የድግግሞሽ ተጽእኖ! ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት ቅባት፣ ስኳርና የመሳሰሉት ነገሮች የበዛበት ምግብ ብትመገቡ ምንም ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ እንደዚህ አይነት ምግብን ግን ለወራትና ለአመታት በየቀኑ ብትመገቡ ግን በክብደታችሁና በጤንነታችሁ ላይ ለውጥ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት በስራ፣ በማሕበራዊ ግንኙነትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ውጥረት ውስጥ ብታሳለፉ ምንም ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ በእንደዚህ አይነት ውጥረት ውስጥ ግን ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታሳልፉ ግን በስነ-ልቦናችሁ፣ አልፎም በአካላችሁ ላይ ቀውስን ማስተናገዳችሁ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት በየጠዋቱ ስፖረት ብትሰሩ በአካል ቁመናችሁም ሆነ በጤንነታችሁ ላይ ምንም ለውጥ ላታዩ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ልምምድ ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታደርጉ ግን በጥንካሬያችሁ፣ በቁመናችሁና በጤንነታችሁ ላይ መልካም ለውጥን ማምጣታችሁ አይቀርም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ወይም ሳምንታት መጽሐፍትን በየቀኑ ብታነቡ በእውቀታችሁና በአመለካከታችሁ ላይ ብዙም ለውጣ ላታስተውሉ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ልምምድ ለወራትና ለአመታት ሳቋርጡ ብታደርጉ ግን በእውቀታችሁም፣ በአመለካከታችሁም ሆነ በእድገታችሁ ላይ ድንቅ ለውጥ ማምጣታችሁ አይቀርም፡፡ የቀረውን ስሌት እናንተው ስሩት፡፡ በተደጋጋሚ ማድረግ የጀመራችሁት የጤና-ቢስ ልምምድ ተጽእኖ ተጠራቅሞ ሳያጠፋችሁ አሁኑኑ አቁሙ! በተደጋጋሚ ማድረግ የጀመራችሁት ጤናማ ልምምድ ደግሞ ተጠራቅሞ መልካም ለውጥን እንዲሰጣችሁ በዚያው ቀጥሉበት!
Показати все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.