cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🄽🄴🄹🄰🅂🄷🄸

📌 ɪŚʟᴀᴍĬᴄ 💻 ᴛᴇÇʜɴØʟᴏɢʏ 🎭 እንዲሁም አዝናኝ መረጃወች For comment & Questions 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @Selmanulfaris_bot 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 https://t.me/joinchat/QVwtalcuWa3adgPrLgdnMA

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
277
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የጥበብ ጫፍ አንድ የሁዳዊ ወደ ሩቅ ሀገር እይተጓዘ ሳለ በመሀል የሙስሊሞች ሀገር ይደርሳል። እንደምታወቀው ይሁዳ ሁሌም ሸር እንዳሰበ ነው። እናም፦"እዚህ ከተማ ገብቼ ዑለማኦችን ማደናገር አለብኝ" ብሎ ያስባል። ከዚያም ከተማዋን ሊገባ ሲል አንድ እረኛ ያጋጥመውና በሱ ሊጀምር ወሰነ እና እንዲህ በማለት ጨወታ ጀመረ፦"እኛ ሙስሊሞች እኮ ቁርአን ለመሀፈዝ በጣም እየተቸገርን ነው። አንደኛ፦30 ጁዝ ነው በዝቷል። ሁለተኛ፦አንቀፆችም በጣም ብዙ ናቸው። ሶስተኛው እና አስቸጋሪው ፦ ቁርአን ውስጥ ድግምግሞሽ አለ። ስለዚህ ለምን የተደጋገሙ አንቀፆችን አንሰርዝም? ምክንያቱም የቃላት መደጋገም ነው እንጂ ምንም አይደለም። ድግምግሞሹን ከሰረዝን መሀፈዙም ይቀለናል።" የሁዳው ይሄን ሁሉ ሲያወራ እረኛው በፅሞና ያዳምጠው ነበር። ከዚያም እረኛው ቀና አለና፦"ንግግርህ በጣም ደስ ይላል አሪፍ ሀሳብ ነው።" አለው። የሁዳው ደስታው ወደር አጣ ነገር ግን ድብቅ ሴራው እንዳይታወቅበት ደስታውን ደበቀው። እረኛውም እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፦ "አንድ ጥያቄ አለኝ። ባንተ የሰውነት አካል ውስጥ ድግምግሞሽ የለም? ለምሳሌ፦ ሁለት እጅ ☞ሁለት አይን ☞ ሁለት እግር ☞ ሁለት ጆሮ..... ታዲያ ሰውነትህ ቀለል እንዲልልህ አንድ አንዱን ለምን አትቆርጥም? ያው ድግምግሞሽ ነው እንጂ እኮ ምንም አይደለም" ይሄን ሲለው የሁዳው ደነገጠ።ፊቱን አጨፍግጎ፦ "የእረኛዎቻቸው መልስ እንዲህ ከሆነ የዑለማኦቻቸው መልስ እንዴት ሊሆን ነው?" እያለ ከተማዋን ትቶ አለፈ። ሱብሃን አሏህ።
Показати все...
ሰበር ዜና‼ በበርካታ የሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢዎች ጨረቃ ስለታዬች፤ ነገ ቅዳሜ ረመዿን 01 ይጀመራል። የረመዳን ጨረቃ በመታየቶ ነገ ቅዳሜ ረመዳን አንድ ብሎ ይጀምራል ። እንኳን አደረሰን! ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
Показати все...
01:48
Відео недоступнеДивитись в Telegram
3.20 MB
እጅግ በጣም አስገራሚ መረጃ‼️ ======================== ✍️ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ትናንት ጀምሮ ዛሬም በቀጠለው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባለፉት ሦስት አመታት ብቻ ለኃይማኖት ተቋማት የተሰጠውን ቦታ በተመለከተ ይህን ብላለች፦ ✔️ በአጠቃላይ ለክርስትና እምነት ተከታዮች አንድ ሚሊዮን መቶ አሥራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሁለት ካሬ ሜትር (1, 112, 802) ቦታ የተሰጣቸው ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የተሰጠ ነው። ✔️ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ ሁለት መቶ ስድሳ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስምንት (260, 938) ካሬ ሜትር መሰጠቱን ተናግራለች። በሃገሪቱ ከግማሽ በላይ ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ህዝበ ሙስሊም፤ የተሰጠው ቦታ 23.4% ብቻ ነው። በመንግስት ደረጃ ይህን ያክል እውነታውን ካመኑ ይበልጥ ቢጣራ ደግሞ ከዚህም የባሰ እንደሚሆን መገመት አይከብድም። ታዲያ ይህቺ ሃገር በህዝበ ሙስሊሙ ትዕግስትና ትከሻ የቆመች ናት ብንል ማጋነን ይሆናልን⁉️ ይህም ከመሆኑ ጋር እንደ አለመታደል ሆኖ ሲመሰገን አይስተዋልም። እኔን የገረመኝ ደግሞ፤ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከማንም በላይ ብዛት ያለው መሬት የተሰጣቸው አካላት ከሌላው የባሰ ማለቃቀሳቸው ነው። ለመሆኑ በህዝበ ሙስሊሙ ቦታ ያሉት እነርሱ ቢሆኑ ኖሮና በነርሱ ቦታ ያለው ህዝበ ሙስሊሙ ቢሆን ኖሮ፤ ምን ሊፈጠር ይችል ነበር⁉️ ሃገሪቱ ለአፍታ እንኳ ህልውናዋ የሚቆይ አይመስለኝም። የኢትዮ ሙስሊምን መገፋት የማያውቅ ይወቅልን። ይህን በራሱ በመንግስት የወጣ መረጃ ሼር በማድረግ ለማያውቅ እናሳውቅ። በነገራችን ላይ እውነታው ከዚህም በላይ መሆኑን አንድ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ ባለስልጣን አውቃለሁ።
Показати все...
በሳውዲ ታሳሪዎች ጉዳይ ከንጉሥ ሰልማን ጋር ለፊታችን ቅዳሜ ቀጠሮ ተይዟል። Waa’ee hidhamtoota Saawudi irratti Mooti Salmaan walin Sanbata beellamni qabameera. የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት ለማሻሻልና በሳውዲ ታስረው የሚገኙና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸው ከፍተኛ የልዑክ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ከንጉስ ሰልማን ኢብኑ አብዱልአዚዝ ጋር ዉይይት ያደርጋሉ። በተጨማሪም ልዑኩ በቆታው ከሳውዲ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። የልዑካን ቡድኑ ከሚኒስትሮች፥ከሃይማኖት አባቶች፥ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በኢትዮ-ሳውዲ ጉዳይ ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ግለሰቦች የተካተቱበት ነው። ልዑኩ የተላከው የእስረኞችን ችግር ለመፍታትና የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል ልዑክ በመላክ ንጉሡን ማናገር እንደሚገባ በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መነሻነት መንግስት ልዑኩ ወደ ሳውዲ እንዲሄድ መንግስት መወሰኑን የደረሰኝ መረጃ ያሳያል። ልዑኩ በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ ዐረቢያ ዋና ከተማ በሪያድ ከተማ ይገኛል። የልዑኩ አባላት አስር ሲሆኑ የሚከተሉት ይገኙበታል። 1) አቶ አሕመድ ሺዴ 2) አምባሳደር ሪድዋን ሁሴን 3) ዶ/ር ጄይላን ከድር 4) ፕሮፌሰር አደም ካሚል 5) ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ 6) ቄስ ታጋይ ታደለ 7) አቶ መስፍን ገብሬ አቶ ሀይደር አብደላ 9) አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት በተመለከተ ፕሮፌሰር አደም ካሚል በዐረብኛ ቋንቋ ለንጉሡ ገለፃ እንዲያደርጉ በልዑኩ ተመርጠዋል።በመልካም መፍትሄ እንዲመለሱ እንመኛለን። ©Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል
Показати все...
ጀግናው ወደ ሚምበሩ ተመልሰዋል! ለአመታት በእገዳ ምክኒያት ሰፊው ህዝብ የሚታደምበትን የንፅፅር ስራዎች እንዳይሰሩ ተከልክለው የነበሩት ዶ/ር ዛኪር ናይክ ለሰፊው ህዝብ ይፋ በሚሆኑበት የውይይትና የንፅፅር ፕሮግራማቸው ተመልሰዋል። ሼር‼
Показати все...
አሜሪካዊው የታሪክ ተመራማሪ ማይክል ሀርት " በታሪክ የታዩና እጅግ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳደሩ የአለምን ምርጥ ሰዎች ደረጃ ባወጡበት እና ከ60,000 ኮፒ በላይ በተሸጠው መፅሀፍ ለምን ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያው ደረጃ ላይ እንዳስቀመጣቸው ሲናገር እንዲህ ይላል:- “በእርግጥ በታሪክ የአለማችን ምርጥና ታላቅ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሰዎች ተርታ ለሙሀመድ አንደኛ ደረጃ መስጠቴ አንዳንድ አንባቢዎችን ሊያስገርምና ሌሎችን ሊያጠያይቅ ይችል ይሆናል። ሆኖም ግን በአለማዊው ሆነ በሀይማኖታዊው ዘርፍ ሙሉ በሙሉ የተሳካላት ብቸኛ ሰው ሙሀመድ ነው።”
Показати все...
♡ ዱንያ ላይ እስካለን ድረስ ሀዘን መቼም ቢሆን አያልቅም ደስታም መቼም አይዘወትርም ... ⇨ ከኛ ማድረግ ሚጠበቀው በሀዘን ጊዜ ነፍሳቸንን ሰብር በደስታ ጊዜ ደግሞ ሹክርን ማለማመድ አለብን ። 
Показати все...
#አራዳዋ_ወጣትና_ፈዛዛው_አፍቃሪ_አንዷን_አፍቅሮ_ይንከራተታል "እወድሻለሁ ላገባሽም እፈልጋለሁ" ይላታል። እሷም "የኔ ወንድም ይሄ ያሳደከው ፂም አልተመቸኝም ካልተላጨኸው ልንጋባ አንችልም" ትለዋለች። በፍጥነት ሄዶ ፂሙን አስነስቶ (የነብዩን ሱና ገደል ከቶ) መጣ። ልጅቷ ስታየው "ይቅርታ የኔ ወንድም ፈተናውን ወድቀሀል ለነብዩ ሱና ክብር የሌለህ ለኔ ክብር ትሰጣለህ ማለት ዘበት ነው" ብላ በሀፍረት መለሰችው። ትልቅ ውርደት አሏሁ ተዓላ ይጠብቀን። https://t.me/Nejashi_bilalulhabesh
Показати все...
🄽🄴🄹🄰🅂🄷🄸

📌 ɪŚʟᴀᴍĬᴄ 💻 ᴛᴇÇʜɴØʟᴏɢʏ 🎭 እንዲሁም አዝናኝ መረጃወች For comment & Questions 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @Selmanulfaris_bot 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

https://t.me/joinchat/QVwtalcuWa3adgPrLgdnMA

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.