cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Řäźi official

<< ህይወት ምርጫ ናት >>

Більше
Рекламні дописи
198
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#6_ዓለምን_ከመንቀፍህ_በፊት_ቤትህን_ሥርዓት_አስይዝ። ብዙ ሰዎች ዓለምን መለወጥ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የልብስ ማጠቢያቸውን ማደራጀት አይችሉም። ህብረተሰቡን ተወቃሽ ማድረግ ጊዜ ማባከን ነው። እኛ በግለሰብ ደረጃ ለአለም ችግሮች ተጠያቂ ነን። #7_የሚጠቅምህን_መሻት_ይሁንልህ። በህይወት ብዙ ሰዎች ትክክለኛውን መንገድ ዘንግተው ፈጣኑን መንገድ ይከተላሉ፡- - የወሲብ ፊልም - እጾች - መስረቅ - ሙስና... የብዙዎች ምርጫ እየሆነ ነው። የህይወትን ስቃይ ለማሸነፍ የምትኖርለት ከህይወት በላይ የሆነ ህልም ማግኘት አለብህ። የምትኖርለት ብቻ ሳይሆን የምትሞትለት አላማ ያስፈልግሀል። #8_እውነትን_ተናገር_ካልሆነ_ግን_ቢያንስ_አትዋሽ። ሁልጊዜ ስትዋሽ አዲስ ማስቀጠል ያለብህን ሌላ ውሸት ይፈጥራል። እውነትን መናገር ለአጭር ጊዜ አደገኛና ከባድ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በረጅም ጊዜ ውስጥ ዋጋ አለው። #9_የምትሰማው_ሰው_የማታውቀውን_ነገር_ሊያውቅ_እንደሚችል_አስብ። ከአንድ ሰው ጋር ስታወራ ተራህን ለመናገር ብቻ አትጠብቅ። አድምጠው። ከየትኛውም ሰው የሆነ ነገር መማር ይቻላል። #10_ንግግርህን_ግልጽ_እና_ትክክለኛ_አድርግ። አትወላውል፤ ማለት የፈለግከውን በቀጥታ ተናገር። ሁልጊዜ ስለ ግቦችህ ግልጽ ሁን። #12_RULES_FOR_LIFE ❤
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#10_የሕይወት_ቀመር_ትምህርቶች ማለት ሊመችህም ላይመችህም ይችላል ግን አንብበው ይጠቅምሀል😊 ከጆርዳን ቢ. ፒተርሰን #የሕይወት_ቀመሮች መጽሐፍ የተወሰዱ 10 ትምህርቶች #1_ከትከሻህ_ቀጥ_ብለህ_ቁም! እንደ ደካማ ሰው ከቆምክ ሰዎች ይንቁሃል። በልበ ሙሉነት መቆም የአንጎልህን ኬሚስትሪ ይለውጠዋል። ሴቶችም ይወዱታል። #2_እራስህን_ለመርዳት_ኃላፊነት_እንዳለብህ_ሰው_አድርገህ_ተንከባከበው! ሰዎች የውሻቸውን ጤና ለመመለስ ሰማይ እና ምድርን የሚያካልሉበት ዘመን ላይ ነን፤ ነገር ግን ለራሳቸው ቀኑን ሙሉ ቺፕስ እየበሉ ሶፋ ላይ ነው የሚውሉት። እራስህን የመንከባከብ ሀላፊነት አለብህ- ልክ ልጆችህን፣ እናትህን፣ ድመትህን እንደምትንከባከበው። #3_ጥሩውን_ከሚመኙልህ_ሰዎች_ጋር_ጓደኝነት_ፍጠር። ህልም ባላቸው እና ወደ ግባቸው ለመድረስ እየሰሩ ባሉ ሰዎች እራስህን ክበብ። በስኬትህ የማይደሰቱ ሆኖም ግን ጓደኛ መስለው የሚቀርቡህ ብዙ ሰዎች አሉ - እነዚህን ሰዎች አስወግዳቸው። #4_ራስህን_ከትናንት_ማንነትህ_ጋር_እንጂ_ዛሬ_ካለ_ሌላ_ሰው_ጋር_አታወዳድር። ሁሉም ሰው የራሱን መጽሐፍ (ሕይወት) እየጻፈ ነው፤ አንዳንዶቹ በምዕራፍ 20፣ አንዳንዶቹ በምዕራፍ 3 ላይ ናቸው። ሁላችንም የራሳችን መንገድ አለን። በመንገድህ ላይ አተኩር እንጂ በሌሎች ሰዎች መንገድ ላይ አትወዳደር። #5_ልጆችህን_እንድትጠላ_የሚያደርግን_ነገር_ልጆችህ_እንዲያደርጉ_አትፍቀድላቸው። ልጅችህን ተንከባከብ፤ ነገር ግን እነሱን ስነ-ስርዓት ማስያዝ ተገቢ ነው። #ቀጣዩ👇
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ሰዎች ማን እንደሆንክ ይጠይቁሀል። ማን እንደሆንክ ካላወቅክ ማን እንደሆንክ ነግረው ማድረግ ያለብህን ነገር ይጭኑብሀል።" ካርል ዩንግ ማን እንደሆንክ እወቅ👌
Показати все...
ሁሉም ሽልማቶች ፈተናውን ላሸነፈው ናቸው! ፈጣሪ ሁልጊዜ እንለምነዋለን ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን ተጨማሪ እንዲሠጠን ብዙ ብዙ ጥያቄዋችን እናቀርብለታለን እርሱም ይሰማናል ፤ ነገር ግን ሲያደርግልን አናውቅም ምን እየሰጠን እንዳለ ፣ ከምን እያዳነን እንዳለ በፍፁም አንረዳውም ሁልጊዜ የጠየቅነውን ሁሉ በቀጥታ እንዲመለስልን እኛ ባልነው መንገድ እንዲከናወን እንፈልጋለን! ወዳጄ የጠየቅከው ነገር ክብደቱ ምን ያህል ነው? በጣም አስፈልጎሀል ?የእውነት በህይወትክ ላይ ትልቅ ቦታ አለው? ታድያ ትላልቅ ነገሮችን በጠየቅከው ቁጥር ፈተናህ በዛው ልክ መብዛቱ ለምን አስከፋህ? ፈጣሪ እኮ ትልቁ መሻትህን እየሰጠህ ነው ታድያ መሸከም እንደምትችል ፣ በአግባቡ እንደምትይዝለት እና ምን ድረስ እንደሚገባህ ሳይፈትንህ እንዴት ይይህ አስታውስ እንጂ የምትፈልገውን ለማግኘት እኮ የሚገባህ ሰው መሆን አለብህ ስለዚህ ከስጦታው በላይ የሚገባው ሰው ስለመሆንና ፈተናህን ስለምታሸንፍበት መንገድ አስብ ሽልማቱማ በፈጣሪ እጅ ነው ስለሱ እሱ ያስብበታል፤ እመነኝ ይህን ስታደርግ ከሚገባህ በላይ ፈጣሪ ሲሰጥህ ታያለህ! ብሩህ ቀን ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ። በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ። አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ። በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ። በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው። በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ። አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር። ይህ ታሪክ ለአብዛኞቻችን አስተማሪ ይመስለናል ። በውስጣችን አዳፈንነው ያስቀመጥነው ተሰጥኦ እንዳለ እናምናለን ። መልካም ቀን❤
Показати все...
🌿#የህይወት_ድንቅ_መልህቆች 7ናቸው! ከሰው ጋር በሰላም ለመኖር፣ ከራሳችን ጋር ሰላም ለመፍጠር፣ በስኬት ጎዳና ላይ ወደ ፊት ለመገስገስ የሚረዱ ሰባት የህይወት ህጎችን እንሆ- 1.ከትላንትህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ አሁንህን እንዳይረብሽ። 2. ሌሎች ሰዎች በአንተ ዙሪያ ስላላቸው ሀሳብ ያንተ ሀላፊነት አይደለም። 3. ጊዜ ማይሽረው ቁስል የለም። 4. ደስታ በማንም እጅ ላይ አይደለችም፤ በአንተ እጅ እንጂ። 5. እራስህን ከሌሎች ጋር አታነጻጽር፤ ሰዎች ላይም አትፍረድ፤ ያለፉበትን የህይወት ውጣ ውረድ አንተ አታውቅም። 6. አብዝተህ መጨነቅህን አቁም፤ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ ሊኖርህ አይጠበቅብህም። 7. ፈገግ በል በዓለም ላይ ያለው ችግር በሙሉ ያንተ አይደለም።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በየቀኑ የሆነ ሰው ፈገግ እንዲል አድርግ! በየቀኑ ለ የሆነ ሰው መልካም ሁን! በየቀኑ የሆነ ሰው ደስ የሚያሰኘውን ቢያንስ አንድ ነገር አድርግ!!!! በመጨረሻም አንተም የሆነ ሰው እንደሆንክ አስታውስ!!! ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!!! ❤🙏
Показати все...
ህክምና ሙያ ውስጥ ዓመታትን ያሳለፈችው ቦኒ ዌር (Bonny Ware) እንዲህ ትላለች፦ ብዙ ዓመታት የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት የመጨረሻዋን ህቅታ የሚጠባበቁ በሽተኞች ጋር እሰራ ነበር፡፡ የህይወታቸውን የመጨረሻ ከሶስት እስከ አስራ ሁለት ያህል ሳምንታት አብሬያቸው እቆያለሁ፡፡ ስለፀፀታቸው አሊያም ባልሰራሁት ወይም በሰራሁት ኖሮ ስለሚሉት ጉዳይ ሲናግሩ ታዲያ ተመሳሳይ ጭብጦች ከብዙ አንደበት ይፈልቃሉ፡፡ በጣም ሲደጋገሙ ያስተዋልኳቸው አምስት ናቸው፡፡ 1.ህይወቴን ሌሎች ሰዎች እንደሚጠብቋት ሳይሆን ለራሴ ሀቀኛ ሆኜ ኖሪያት ቢሆን ኖሮ ሰዎች የኑሮ ድርሻቸው መገባደዱን ሊያውቁ እና የሆነውን ሁሉ ዞረው ሲመለከቱ በርካታ ያልተሟሉ ውጥኖች ፣ የጨነገፉ ህልሞች ፍንትው ብለው ይታዩዋቸዋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ በይሉኝታ ታስረው ራሣቸው በፈለጉት እና በፈቀዱት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች በቀየሱላቸው መስመር መጓዛቸውን ማወቁ እያንገበገባቸው ነው ወደ መቃብራቸው የሚወርዱት፡፡ 2. የማይረባ ስራ በመስራት ከመጠን በላይ ተወጣጥሬ ባልኖርኩ ኖሮ ያስታመምኳቸው ሁሉም ወንዶች ይህ ቁጭት አለባቸው፡፡ የነፍሳቸውን ጥሪ ረስተው ህይወታቸውን በማይጠቅም እና በሚያሰለች ስራ ተጠምደው አቅማቸውን እና ጊዜያቸውን በመጨረሳቸው እንዴት ነው የሚያስቆጫቸው፡፡ እንዴትስ ነው የሚያንገበግባቸው። 3. ለራሴ ደስተኛነትን ፈቅጄለት ቢኖን ኖሮ ይህ ደግሞ በሚገርም ሁኔታ የሚደጋገም ቁጭት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሊሞቱ እስኪቃረቡ ድረስ ደስታ ምርጫ መሆኑን አይረዱም፡፡ በልማድ እና በድግግሞሽ ህይወት ተተብትበው የሚኖሩት፡፡ ብዙ ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፤ ይህንን ያህል ገንዘብ ሳገኝ፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለሁ እያሉ ለኑሮዋቸው ቀጠሮ ሲሰጡ፤ ያሰቡት እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰኑ ነው። ይህንን በውስጣቸው እውነቱን ቢረዱትም ደስተኛ ለመምሰል ብዙ ጥረት ያደርጋሉ ባይሳካላቸውም ቅሉ 4- ስሜቶቼን የመግለጽ ድፍረት ቢኖረኝ ኖሮ አያሌ ሰዎች ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ሰላም ለመፍጠር ሲሉ ስሜታቸውን ይደብቃሉ ከዚህም የተነሳ መሆን የሚሹትን እና የሚችሉትን ሁሉ ሳይሆኑ እንዲሁ ያልፋሉ፡፡ ብዙዎቹንም ይህ ቂም እና የውስጥ እህህ ለህመም ዳርጓቸዋል፡፡ 5. ከጓደኞቼ ጋር ብዙ በተገናኘሁ ኖሮ የድሮ ጓደኛን ትክክለኛ ዋጋ ሁሉም አልጋ ላይ ሲውል ነው የሚረዳው። ሁሉንም መልሶ መፈለግና ማግኘት ያለመቻሉ ነው ክፋቱ፡፡ በርካቶቹ በራሣቸው የህይወት ውጣ ውረድ ተጠምደው የጓደኛነት ወርቃማ ፍሬ ሲረግፍ ልብ አላሉም፡፡ የሚያስፈልገውን ያህል ጊዜ ባለመስጠታቸው ፥ ጥረትም ባለማድርጋቸው የሚቆጩ ታማሚዎችን ማግኘት አያዳግትም፡፡ ሁሉም ሞት ደጅ ላይ ሲቆሙ ጓደኞቻቸውን ይናፍቃሉ፡፡ 🌿 ሰውና_ፍልስፍናው 🌿 🎖 @cekuaa🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊
Показати все...
🌿ለህሊናህ!
👉ወዳጄ! በሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ ትልቁ የማይዳሰስ እና ዋጋ የሚሰጠው አካል ህሊና ነው። የህሊና ወቀሳ ከሰዎች ወቀሳ በእጅጉ ይለያል። ሰው ሲወቅስህ ለጊዜው ነው፤ ህሊናህ ግን እረፍት አይሰጥህም በተኛህና በነቃህ ቁጥር ተከታትሎ ይወጋሃል። #ለህሊናህ_መኖር ስትጀምር የዓለምን ሀብት ሁሉ በእጆችህ እንደጨበጥክ ማሰብ ትጀምራለህ።

👉ለህሊናህ መኖር ስትጀምር የአንተ ምርጥ ጠላቶች ውሽት፣ ክፋት... ይሆናሉ። በሰዎች ልቦና ውስጥ ለመቀመጥ ማስመሰል በበዛበት ሳቅና ውሸት በሞላበት መውደድ ውስጥ መመላስ ሳይሆን መፍትሔው #በጎ_ህሊና_መያዝ ብቻ ነው። ህሊና በሰዎች መቸገር እና መውደቅ ውስጥ ተባባሪ እንድትሆን አይሻም። ለህሊናህ መገዛት ስትጀምር ከሚያከብሩህ ብዙ ሰዎች ይልቅ ለሚጠሉህ ጥቂት ሰዎች ማሰብ ትጀምራለህ።

👉#ያንተ_ትልቁ_ጠላት_ህሊና_ቢስነትህ_ነው። ህሊና ቢስ ከሆንክ በሰዎች ንግግር የራስህን ተንኮል ታሴራለህ። የሰዎችን እንባ እንደሙሉ ደስታ ትቆጥረዋለህ። ዱካ ላይ ለመቀመጥ እንኳን የሚቀፍህ ኩራት ይከብሃል። ምን አለፋህ ህሊና ቢስ ስትሆን ሙሉ ለሙሉ ሰብአዊነት የተለየህ ትሆናለህ። ያለ ሥራቸው ደግና ጥሩ መባል የሚፈልጉ፣ በሐሰት ክብር ለመጎናጸፍ የሚያስቡ፣ በአስመሳይነት መወደድን ለመሸመት የሚዋልሉ ሰዎች አልገጠሙህም? ከገጠመህ እነዚህ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ለህሊናቸው ሳይሆን ለክብራቸው የሚኖሩ ናቸው።
👉#ለህሊናህ_መኖር_ስትጀምር ታይቶ ለሚጠፋው ክብርህ መጨነቅ ታቆማለህ። #ዓለም_ምትታመሰው_ህሊና_ባጡ_ሰዎች_መሆኑን_አትርሳ። ማንም ሰው ከህሊና ወቀሳ ማምለጥ አይችልም። ስለዚህ #ትልቁ_ጥበብ መልካም እያሰቡ ጥሩ እየሠሩ ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው።

🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎁 @cekuaa 🎁
Показати все...
ከውጥረትህ ውጣ! የሰው ልጅ የሚደክመው የሚረሳው የሚጨነቀው አዕምሮው እረፍት ሲያጣ ነው እንጂ አካሉ ስራ ስላበዛ አይደለም፤ የምትሰራው ስራ ወይም የምታስበው ሀሳብ ከበዛብህ ትንሽ ግዜ ለራስህ ስጠው ፤ እረፍት አድርግ ተረጋጋ ራስህን ሰብስብ እና ደግመህ ተነሳ ያኔ ሁሉም ነገር ካሰብክበት በላይ ሲቀልህ ታየዋለህ! መልካም ሰኞ ተመኘን🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.