cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

, 🖤 girls pride

Couple goal "🖤 𝒐𝒏 𝒕𝒉𝒊𝒔 𝒄𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍 𝒖 𝒄𝒂𝒏 𝒈𝒆𝒕💕 𝒎𝒖𝒔𝒊𝒄💽 Couple pic💑 ተከታታይ የፍቅር ታሪኮች 💟 𝒎𝒆𝒎𝒆 😂 Sad and love quotes💓 HBD ለማለት ለፍቅረኛዎ surprise ለማድረግ 👉 @pisces_m Friendly channel t.me/mahiwa_a

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
3 327
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

፡ የሆነ ቀን ደስ ሲልሽ ነይ…የዛኔም ደብሮት ይሆናል ወይ ደሞ እረስቶኝ ይሆናል ብለሽ እንዳታስቢ…በፍፁም አረሳሽም…በርግጥ እንደ ድሮው ላታገኚኝ ትችይ ይሆናል…ያው ሰው አደለሁ…ቢሆንም ብሸኝሽ እና በሰው ብተካሽም ዛሬም አረሳሁሽም 🖤 ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
Показати все...
#music ልቤ ከልቧ ተዛምዶ ቀረ እህቴ ቀርቶ ፍቅሬ ተባለ እንኳን ለናንተ ለኔም ገርሞኛል .... ትለያለች 😍
Показати все...
🥰 ልጩህበት🥰 ክፍል~~~~ሶስት(3) ✍አዘጋጅ፦ HEMA . . . ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ ንዴቴን ብሶቴን ናፍቆቴን ባከስመው እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!! ••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ••• "አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ ••• እኔ ከባጃጅህ አልወረድኩ አንተ ግን ከገባሁ ጀምሮ ዝም ብለህ ትጮሀለህ ስማኝ የት እና መቼ እንደምትጮህ ካላወክ ዝም ብትል ይሻላል ያለበለዚያ ሰሚ ሳይኖር ዝም ብለህ ብትጮህ የራስህ ጩኸት እራስህን ያደነቁርህ እንደሆን እንጂ ምንም አታመጣም !" ብሎኝ ሲያበቃ ደሞ ወድያው ወደሷ ዞረና "አንድ ግዜ ብቻ ልጩህ በናትሽ ?" ሲላት ቀርታኝ የነበረችው እንጥፍጣፊ ትግስት ተሟጠጠች ••• አቦ ባባ ክብር ካልወደደልህ እንዴት እንደምትወርድ ላሳይሀ እንግዲህ ብዬ እጄን ለፀብ እያሰናዳሁ ወርጄ ስጠጋው "ተው ተው ተው ቦክስ አታባክን ወጣቱ መጀመሪያውኑ እንደዚህ ወንድ ብትሆን ኖሮ አንተ ባጃጅ ውስጥ እስካሁን ማን ይቀመጥ ነበር ፈሪ ፈሪ ነገር ነህ !" እያለ ከባጃጇ ሲወርድ ልጅቷ በሳቅ ፈነደቀች ግራ ቀኝ እየተወዛወዘ ትንሽ ከባጃጇ ራቅ እንዳለ ዘወር አለና "ሞት ይርሳኝ ቻው እሺ የኔ ልጅ ልጅ አልኩ እንዴ አንቺን እንኳን አላደርስም ! ቻው እሺ የኔ ልእልት አንቺን የመሰለች ልጅ ከዚህ አስቀያሚ ሹፌር ጋር በማየቴ ደንግጫለሁ ! ፍችው በናትሽ! " እላት። "እሺ "አለችው በሳቋ መሀል "ግን መች ትፈችዋለሽ በናትሽ! እ••• እ ••እ ንገሪኛ?" እያለ ሊመለስ ሲል እኔም እየሳኩ ወደሱ ስጠጋ ፊቱን አዙሮ ከቆምንበት በስተቀኝ መንገድ ዳር ወዳለችው የማትዘጋዋ መጠጥ ቤት አመራ። ባጃጃን አስነስቼ ከዩንቨርስቲው በቅርብ ርቀት ጨለማ ውስጥ አቆምኳትና ከመሪው ላይ ተነስቼ እሷ አጠገብ ተቀመጥኩ ። ፊቷ ተቀያየረ። ካቆምንበት እንቀጥላ አልኳትና ቅድም የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነበር ? "በቃ ከፈለክ ልትሰድበኝም ከፈልክ ልታወርደኝም ትችላለህ ሌላ ምንድን ነው?" አለችኝ የጭንቀቷን ወደ ዩንቨርስቲው ዞሬ ተመለከትኩ አጠገባችን ነው ግቢው ከሩቅ ይታያል ሳቄ መጣ አብራኝ ሳቀች። ሀይ ስትደርሺ ነው እንዴ ልታወርደኝ ትችላለህ እምትይው? ስላት••• ጭንቅላቷን ወደ ግራ ሰበቀችና በዝምታ እጇን እያፍተለተለች አይን አይኔን ታየኝ ጀመር የሆነ ስሜት ተሰማኝ ታውቂያለሽ ሁለት ወንድሞች አሉኝ ግን እህት የለኝም ቢሆንም እናት አለኝ የማይሆን ቢሆንም እናትም ባይኖረኝ እራሱ አንቺ ላይ የሚጨክን አንጀት የለኝም ምንም አልደርግሽምም አልሰድብሽምም አላወርድሽምም እሺ መጀመሪያውኑ ብር እንደለለሽ ብትነግሪኝና በነፃ እንዳደርስሽ ብትጠይቂኝ ለስራ ብወጣም ከሰአቱ አንፃር ላውሬ ጥዬሽ አልሄድም ነበር ። እያሰብኩ የነበረው ምናልባት መጥፎ ባህሪ ያለው የባጃጅ ሹፌር አጋጥሟት ቢሆን ኖሮስ እያልኩ ነው። ግን ምን አጋጥሞሽ ነው ማለቴ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ?ስለራስሽም ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል "አጋጣሚው ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው ኬቱ ጋር ልጀምርልህ? ከፈለግሽው። "በናትህ አሁን መሽቷል ሞባይሌን ዶርም ጥዬው ወጥቼ ነው ከፈለክ ስልኬን ያዝና ነገ ወይ በሚመችህ ቀን ደውልልኝ አወራሀለሁ!" እዚሁ ባጃጅ ውስጥ እናድራታለን እንጂ አልፋታሽም አልኳት ኮስተር ብዬ " እያስገደድከኝ ነው ማለት ነው አለች እሷም በስሱ ከስተር ብላ ስትስቅም ስትኮሳተርም የሚያምርባት ሴት እሷን አየሁ። አሁን ከተለያየን ቡሀላ ልታገኝኝ ፍቃደኛ ሁኚ አትሁኝ እርግጠኛ ስላልሆንኩ አሁኑኑ እንድትነግሪኝ እየለመንኩሽ ነው! ከተጫንኩሽ ይቅር ብትነግሪኝ ግን የመጣሽበትን ሂሳብ እንደከፈልሽ እቆጥረዋለሁ አልኳትና አሁንም እኩል ሳቅን። "ክትክትክትክት ኧረ ባክህ እሺ ግን ባጭሩ ነው በደንብ እንድትረዳው ገባ ብዬ ብጀምርልህ ይረዝምብኛል?" አቦ ንገሪኝኛ አታጓጊኝ!። " እኔ እኔ እኔ ማለት እኔ ደሀ ከሚባል ቤተሰብ ነው የተወለድኩት ። አባቴ አናፂ ነው እናቴ ደግሞ ሽንኩርት ቲማቲም ምናምን ነው ጉሊት ውስጥ የምትቸረችረው ሁለቱም ፀሀይ ላይ ውለው ፊታቸው ጠቁሮ ከሚያገኙት ገቢ ውስጥ አብዛኛውን እኔን ከሰፈሬ እና ከትምህርት ቤት ጓደኛቼ እኩል ማድረግ ባይችሉ እንኳን ክፍተቱን በመጠኑ አጥብበው ብዙ ሳይሰማኝ እንዳድግ ለማድረግ አውለውታል። ሳይለብሱ ያለብሱኛል ለነሱ ርካሽ የተባለውን ጫማ እየተጫሙ ለኔ ውድና ሁለት ሶስት ቅያሪ ጫማ እንዲኖረኝ ለማድረግ ለነሱ የሚያስፈልጉዋቸውን ሁሉ ወደ ጎን ትተዋል ! ሳይደሰቱ እኔን ለማስደሰት የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል! ቢኮራረፉ እኔ ፉት ይስቃሉ! ቢያዝኑ እኔ ፊት ደስተኛ ለመምሰል ይሞክራሉ! በአጠቃላይ ለራሳቸው ሳይኖሩ ለኔ ደክመው ለኔ ኖረው ያስተማሩኝን ቤተሰቦቼን ለማስደሰት የምችለው በትምህርቴ ስጎብዝ ነውና ምንም ነገር ሳያታልለኝ በርትቼ በመማር ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ የሚሆን ውጤት አምጥቼ ባስደሰትኳቸው ማግስት ነበር አባዬ እኔ ወደዚህ ለመምጣት የሚያስፈልገኝን ነገር ለሟሟላት ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ያገኘውን ስራ በሙሉ እየሰራ ገንዘቡን እኔው ጋር ማጠራቀም የጀመረው •••" አለችና ዝም አለች። ምነው ቀጥይ እንጂ ስላት "ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ ! ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን። ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?" ምን ትዝ አለሽ ? አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ። አንዴ ልጩህ እንዴ?" ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን። በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፍቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች••• አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ። ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ ይቀጥላል...... ━━━━━━━━ ✦ ✎ ክፍል 4 በኋላ ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ Hema ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @hemaria6 ❥❥________⚘_______❥❥
Показати все...
🥰 ልጩህበት! 🥰 ክፍል ~~~~ሁለት(➋) ✍አዘጋጅ፦ HEMA . . . በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም ••• አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ! ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች•• •••• እንደፈራች ገባኝ እኔ ሽምቅቅ ልበልልሽ አልኩ በሆዴ ዝም ብዬ ሳያት ሳቋ መጣ ፍርሀት የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቀች የፈለከውን አርገኝ ስትይ? "በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው " እኮ የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ነው? "እየተጫናነኩኝ ነበረ እኮ እይታይክም እንዴ በቃ ሲጨንቀኝ ነው እንጂ አንተ ባጃጅ ውስጥ የገባሁት ምንም ብር የለኝም ለዛ እኮ ነው ጨንቆኝ እኮ ነው ዝም ብዬ ግንቡን ተደግፌ ስቆም የነበረው" ከጥያቄዬ እየሸሸች ስትቀበጣጥር የኔም ሳቅ መጣ ቢሆንም ለሶስተኛ ግዜ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ በዚህ መሀል መልሷን በጉጉት እየጠበኩ አንድ ሰካራም ለሱ ያቆምኩ መስሎት ነው መሰለኝ ኬት መጣ ሳይባል ግራ ቀኝ እየተጋጨ ከውሃላ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ። ድንገት ስለገባ ደንግጣ ••• "እማ" ብላ እየተጣራች ከነበረችበት መሀል ወደ ጥግ ተጠጋች ከሰውየው ራቅ ለማለት። እሱም መደንገጧን አይቶ ዘወር አለና ወደሷ ••• በመሀል በመሀል ስቅ እያለው••• "አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ - ሀበሻ ሴት ስለሆንሽ ብቻ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ አይገርምሽም" አይገርማትም አሁን ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ አልኩት ድንገት በንዴት!። ለኔ ንዴት ቦታም አልሰጠው ••• "ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ? እኔን እኮ ነው እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ብሎ ሲመልስልኝ ልጅቷ ሳቋን ለቀቀችው። ሰካራሙ ሰውዬ አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና••• "ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው እምትመስይው ! ወይኔ ልጄ ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ የልጄን ናፍቆት ለመርሳት ! ልጅ በልጅነት ሲሉ ሰምቼ ምንም ሳይኖረኝ ወልጄ ፍቅረኛዬ እኔ ላይ ጥላብኝ ስትሄድ እኔ ደግሞ አሮጊቷ እናቴ ላይ ጥየባት መጣሁ። እናቴ ግን መጣያም ቢኖራት የሚጥል አንጀት የላትም እና እኔን ፍዳዋን በልታ ያሳደገችኝ እንዳይበቃት ላስርፋት ሲገባኝ እረፍት እምትነሳ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ጥየባት ከመጣሁ ስድስት አመት ሞላኝ አንዴ ብቻ ነው ልጄን ያየሁዋት!! ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !" ተበሳጨሁ። ስማ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ እሚደገመው አሁን እምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት። "ጠጅ አልጠጣሁን አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ "እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው። ትግስቴ አለቀ ጎትቼ ላወርደው ተፈናጥሬ ስወርድ••• "በናትህ ተው እንዳትጣላ " ብላ ጮከች ልጅታ እጇን እያውለበለበች እና እንዴ ወደኔ አንዴ ወደሱ እየተመለከተች "አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ? እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር! አሁን እራሱ ኮረና ያላጠፋን ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አታውቂም? እንደኔ ከሆነ ከረና ድምጥማጣችንን ያላጠፋን ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ጨዋዎች ስለሆናችሁ ነው እድሜ ለናንተ! እውነቴን ነው አሁን እኔ ልሙት እንኳን ማክስ ሱሪስ እምታስወልቁን እናንተው አደላችሁ ። እናንተ ጨዋ ባትሆኑ ማነው ማክስ አላወልቅም የሚለው እንደ ብራዚል ሴቶች ብትሆኑ ማን ይተርፋል ? አልቆልን ነበር ሙች እውነቴን ነው! እሱ ይለፈልፋል እሷ ትስቃለች ! ሰውየው የባጥ የቋጡን እየቀባጠረ ደሜን ቢያፈላውም ለምን እንደሆነ ባላውቅም በሱ ንግግር የምትሰቀውን ልጅቷን ማየት ስላስደሰተኝ ነው መሰለኝ ሳላስበው ብዙ ታገስኩት አሁን ትወርዳለህ አትወርድም አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ "እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !" ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ! "ታድያ ለማን ነው የቆምከው? ለሷ! "ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው•••• እሀሀሀ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ ! ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!" ሲላት••• ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል••• "እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው። "ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ደሞ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው " ሲላት "በናትህ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለች ምነው በሱ ምክንያት የምታመልጪ መሰለሽ እንዴ እሱን አውርጄው የጀመርነውን እንጨርሳለን እሺ አልኳት ኮስተር ልልባት እየሞከርኩ። ባጃጁን አስነስቼ ከነፍኩ። "ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት••• "ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ ፍቀጅልኝ?" "ምን ?" "አንዴ ልጩህ በናትሽ ?" "እንዴ ለምን ምን ሆንክ?" አለችው ግራ ተጋብታ ሰውየው መች ያልቅበትና እኔ በማታ ስራ ብዙ ሰካራም ጭኛለሁ እንደዚህ ሰውዬ ግራ ያጋባኝ ሰው አልገጠመኝም ቀጠለ• "አንቺ ምን ስትሆኚ ነው እምትጮሂው?" "ምን አይነት ጩኸት?" "እሄውልሽ እኔ ደስ ሲለኝም እጮሀለሁ ሲጨንቀኝም እጮሀለሁ በናትሽ አሁን አንዴ ልጩህ ? ፈቀድሽልኝ አለና በጣም በሚያስፈራ ድምፅ አቀለጠው። እሷም ደነገጠች እኔም ባጃጁን አቁሜ በደምፍላት ወደሱ ዞርኩና አንተ ሰውዬ እብድ ነህ እንዴ?ስለው "የፈለከውን በለኝ ግን በናትህ ልጩህበት ተወኝ ?" እስቲ ወንድ ነህ ድገመው አልኩት። የጉድ ቀን አይመሽም አሉ ዛሬ የጉድ ለሊት አይነጋም ሆነብኝ እሷ በኔና በሱ ሁኔታ ትስቃለች ሰውየው ቀጠለ ልጩህበት ተወኝ ተወኝ ልጩህበት በአፌ ቢወጣ የውስጤ እንፋሎት ለየልኝ እሄ ሰውዬ አላበዛውም እንዴ ግጥምህንም አንተንም አልፈልግም ውረድልኝ እቺን ግጥም ሳልጨርስልህማ አልወርድም ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ ንዴቴን ብሶቴን ናፍቆቴን ባከስመው እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!! ••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ••• "አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ••• ይቀጥላል...... ━━━━━━━━ ✦ ✎ ክፍል 3 ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ Hema ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ For any comment👇👇 @hemaria6
Показати все...
🥰 ልጩህበት🥰 ክፍል ......1 ✍🏼 አዘጋጅ ;- HEMA . . . . ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ። ከምሽቱ አምስት ሰአት ካስር አከባቢ አንድ ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የለላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች። ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ። እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ። አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ። ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፉት ባላየ ፍቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ። ደርሳ `` ይቅርታ ወንድም ጊቢ ትወስደኛለህ ኮንትራት '' አለች ዩኒቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ መሆንዋን ለማወቅ ጊዜ አላጠፋሁም ዩኒቨርስቲ ደግሞ ከከተማ ትንሽ ወጣ ይላል 200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት ግማሽ ፉቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና "200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ መጀመሪያ አሳዘነችኝ ! ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ። "እ ምናልክ " አለችኝ ። በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ። እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት "በስንት?" አለችኝ ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች :: ትንሽ በዝምታ እየተጓዝን ድንገት ዘወር አልኩና ....ሂሳብ አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽ አያዋጣኝም ! "ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት "ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?" ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ? "እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው" ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ። ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ? "እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ " ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት። ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው። እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ? "ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም ••• አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ! ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች••• ይቀጥላል ..... ━━━━━━━━ ✦ ክፍል 2 ይቀጥላል ........ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ HEMA ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @hemaria6
Показати все...
Hema ♥️📋.. ....አንድ ጊዜ ስላንቺ ግጥም ልፅፍ ጀመርኩኝና ጥልቅ መሆን እንዳለበት አስቤ ተራራውን ከአድማሷ ጋር ሳገናኝ፣ ውቅያኖሱን ከባህር ስቀላቅል መጨረሻ ላይ በዱር በገደሉ እያልኩኝ ነበር ከዛ በኃላ አንበሳ ይብላኝ ውሃ ይዋጠኝ ምንም ላውቀው አልቻልኩም።ኢሄን ለራሱ የፃፍኩልሽ የት ሆኜ እንደሆን እኔንጃ ......ግን በቃ የኔ ባህር ማለቴ የኔ ፍቅር በጣምምም አፈቅርሻለሁ 🪴✨🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹✨🪴 ♥️ Hema ♥️ ...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•........ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показати все...
ምን ብለሻቸው ነው ❤️❤️?🙈 እኔ ግራገባኝ በሀሳቤ ሳትኖሪ ካርድ ሳልሰጣቸዉ ጠሪ አክባሪ ሄዋንህ እሱዋ ነች እያሉ ይወቅሱኛል እኔ አንቺ ሆነን መች አይተዉናል እሺ ምን አልሻቸዉ እኔ ግራ ገባኝ መችነዉ ምታገባ እኔስ ምላሽ ጠፋኝ ምን ነግረሻዉ ነዉ ምን ልመልስላቸዉ ቆይ ለኔ ሳትነግሪኝ ለእነሱ ለምን አወራሻቸዉ ሄዋንህ ቢሉኝ ብዙ ቢያወሩኝ ልቤ ካልተቀበለዉ ታዳ ምን ጠቀመኝ ዉሀ ቡሀቃህ ናት ይሉኛል እየዞሩ ኧረ ሁሉም በየተራ እየተቀያየሩ ኧረ አሁንማ ሚስት እያሉኝ አመረሩ ደግሞ ሚገርመኝ ማግባትሽ እየጠበኩኝ እንደ ወንድም ልድርሽ እየተዘጋጀሁኝ ልኖስዳት ነዉ እያሉ ኧረ ለምንድነዉሚያስፈራሩኝ ፍቅር በፍቅር ካልሆነ መች በእልህ ይሰምራል ልባችን በፈጣሪ ገመድ ካልታሰረ ምን ይጠቅማል እነሱ ስላወሩ አድናቹ ስላሉ አረጓዴ እስኪ መች ሆነ ብሉ እኔ ነገርኳቸዉ ልቤ ላንቺ እዳልሆነ ቆም ብሎ አስቦ በእህትነሽ አመነ አንቺ እዳልሻቸዉ እኔም ነገርኳቸዉ በወሬ ለኔ እደማትሆኚ እኔ ነገርኳቸዉ እባክሽ ምን አለ ብለሽ አቺም ጠይቂያቸዉ 🪴✨🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹✨🪴 ♥️ for any comment👇👇 @hemaria6 ...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•........ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показати все...
Hema🌹 "የሰው አዕምሮ መፀነስ እና ማመን የቻለውን ሁሉ ማግኘት ይችላል!"... ✍ #ናፖልዮን_ሂል 🌹 Hema🌹
Показати все...
🌹 ፍቅርን በቃላት 🌹 የሚወዱህ ከተናደዱብህ ስህተት ሰርተሀል ማለት ነው! ቶሎ ታረም የሚጠሉህ ከተናደዱብህ ግን ትክክል ሰርተሀል ማለት! ቀጥልበት ! 🪴✨🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹✨🪴 ♥️ Hema♥️ ...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•........ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показати все...
ሚሻል ሲገኝ ምን ያስከፋል😌
Показати все...