cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የቡራዩ ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት

ይህ ገፅ የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት መልዕክቶችን ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ እንዲተላለፍበት በህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚመራ ይፈዋዊ ገጽ ነው። 📞+251944247165 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @finoteselam27 inbox አድራሻችን ነው።

Більше
Рекламні дописи
1 187
Підписники
+324 години
-17 днів
+3030 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ቀዳም_ሥዑር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግስት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል ፩ ቀዳም ሥዑር ይባላል በዚህች ዕለት ከወትሮው  በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች እንጂ በዓል መሻርን አይመለከትም:: ይህች ዕለት እንደውም በጌታ ስቅለት የበለጠ ክብር ተሰጥቷታል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይሄን ሲገልጹ    " ዓለም መፈጠር በፈጸመ ጊዜ በሰንበት ቀን እንዳረፈ አሁንም ከድካምና ከመከራ ዐረፈ ከአርብ ምሽት እስከ እሁድ ሌሊት በመቃብር ውስጥ ተኛ ቀድሞ ዓለምን ከመፍጠር በማረፍዐ አከበራት አሁን ደግሞ የዓለም መድኃኒት በሞቱ ቀደሳት ቀድሞ በጸጋው ባረካት አሁን በመስቀሉ አተማት " ብለዋል ፪ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ፫ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ቀዳም ሥዑር ደስታም ኃዘንም የሚታስብባት ዕለት ናት በዕለተ አርብ ጌታ እኛን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀል እያሰብን እናዝናለን በፈጸመልን ድህነት ደግሞ ንሴብሖ እያልን እናመስግነዋለን " ገብረ ሰላም በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ " በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ትንሣኤውን ገለጠልን እየተባለ የምሥራች ቄጤማ እየታደለ ይዘመርባታል ወደ ከርሠ መቃብር መወረዱን እያሰብን እናዝናለን የነፍሳት ከሲኦል መወጣትን እያሰብን እንደሰትበታለን። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Показати все...
👍 1 1
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 45፤ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46፤ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። 47፤ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው። ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ። 48፤ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው። 49፤ ሌሎቹ ግን። ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ። 50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። 51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ
Показати все...
🙏 6
በዓለ ስቅለት በግብፅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዎድሮስ 2ኛ በተገኙበተት ተከብሯል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከካህናትና ምእመናን ጋር በሥርዓቱ ተሳትፈዋል ። |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Показати все...
👍 1
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Показати все...
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ------------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + ---------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Показати все...
👍 2😢 2
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ----------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + -------------------------------- |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Показати все...
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 22) ---------- አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ። ዐገቱኒ ከለቢት ብዙኃን ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 15፤ በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው። 16፤ በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። 17፤ እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ። በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ 18፤ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። 19፤ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ። ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት። 20፤ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ። 21፤ ገዢውም መልሶ። ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም። በርባንን አሉ። 22፤ ጲላጦስ። ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም። ይሰቀል አሉ። 23፤ ገዢውም። ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን። ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ። 24፤ ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። 25፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው። ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ። 26፤ በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ። 27፤ በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ። 28፤ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥ 29፤ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤
Показати все...
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ወኆለቊ ኲሎሙ አዕፅምትየ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ (መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 21) ---------- 16፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። 17፤ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።
Показати все...