cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Nolawi ኖላዊ

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

Більше
Рекламні дописи
6 012
Підписники
+624 години
+197 днів
+6530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ከፍ ካለው በላይ የመጣው ሄደ፣ የሄደውም አይመጣም። የነገሠው ተሻረ የተሻረው ዳግም አይቀባም። የተሞገሰው ተረገመ፣ የተወገዘው ስሙ ያው ሆኖ ቀረ። ባለ ጠጎች ደኸዩ ፣ አለ የሚባል ጠፍቶ ነበር የሚል ቃል በምድር በረከተ። ጎዳናው ይወስዳል ይመልሳል፣ ሕይወት ግን ያንን ጓደኛ፣ ያንን ውብ ዘመን፣ ያንን በክብር፣ ያንን አንቱታ አትመልስም። በዘመኑ ታላቁ እስክንድር ዓለም ፈራው፣ ዛሬ ፈሪዎች አይፈሩትም። እግዚኣብሔር ማነው? ያለ ፈርዖን ሰጠመ፣ እስካሁን ትንሣኤ አላገኘም። አውሮፓ ዱር ሳለ ግሪክ አሰለጠነች፣ ዛሬ ግሪክ በዕዳ ተዘፍቃ ብዙ ረዳት ሊያቆማት አልቻለም። የጰጰሱ ተሳሳቱ ሲባል ይወገዛሉ፣ አስኬማና በትረ ሙሴ መልሱ ይባላሉ። ቆንጆዎች ቆንጆ ነበርሁ ሲሉ ማን ያምናቸዋል? ያ ውበት ላይመለስ ጥላሽት ተቀብቷል ። ያ ተክለ ቁመና ፣ ያ እንደ ፀሐይ የሚያበራ ገላ ፣ ያ መሬት ለመርገጥ የሚጸየፍ እግር ዛሬ ጭቃ ላይ ተኝቷል ። ቤቱን ለደቂቃ የማያምነው ለዘላለም ጥሎት ሄዷል። የሚሳሳለትን ንብረት ዛሬ የማያውቀው ሰው ይጫወትበታል ። የሕይወት መንገድ መሄጃ እንጂ መመለሻ የለውም ። እኛ ወደ እነርሱ እንጂ እነርሱ ወደ እኛ አይመጡም። የዓለም ከፍታ በዝቅታ ፣ ዙፋን በመቃብር ፣ ዳኝነት በእስረኛነት ይለወጣል ። ያንተን ልዕልና ፣ አማኑኤል ሆይ ያንተን ክብር ካላሰቡ ልብን ያደክማል ። ከፍታህ ዝቅታ የለውም፡፡ ነበረ ተብሎ ታሪክ አይነገርልህም። ሁልጊዜ ያው ነህ ። እንዳንተ የሸመገለ የለም፤ እንዳንተም አዲስ የለም ። መጀመሪያ ላይ ቆመህ መጨረሻውን ታውቃለህ፤ እያወቅህ ግን ዝም ትላለህ። ለድሀው እንጀራ ትሰጣለህ ፣ መልሶ ሲክድህ የሚያማልድ ሰባኪ ትልክበታለህ ። በልካችን አትከፍለንም ፣ በልክህ ታኖረናለህ ። መሰላል ላይ የወጡ ይወርዳሉ። በአየር ላይ የተንሳፈፉ መሬት ይናፍቃሉ ። ከፍ ካሉት በላይ ከፍ ያልከው አንተ ግን በማይነገር ቅድስና ትኖራለህ። ለጠባይህ ዝቅታ ፣ ለዙፋንህ መናወጥ የለበትም። የዛሬው አሸናፊ የሁልጊዜ አሸናፊ አይደለም ። የዛሬው ፈራጅ የሁልጊዜ ፈራጅ አይደለም ። የእኔ አምላክ ግን የማለፍን ሥርዓት ድል ትነሣለህ ። ሳትቀበል ትሰጣለህ ። ሳትሾም ትሾማለህ ። አዎ ከፍ ካሉት በላይ ከፍ ብለሃል ። ልዕልናህን ልዕልናህ ያመሰግናል ። በክረምቱ ዝናብ ነጠብጣብ ልክ ብትመሰገን ልክህ አይደለም ። በምድር ላይ ያንተ ትልቅ ነገር እኛ ነን ። በሰማይና በምድር የእኛ ትልቅ አንተ ሁንልን !  ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም .
Показати все...
24👍 4🥰 1
2016-11-07 እግዚአብሔር ይናገራል 7.m4a42.61 MB
16🥰 1😢 1
እግዚአብሔር ይናገራል 7 በ#ዲያቆን #አሸናፊ #መኮንን የተዘጋጀ ስብከት አሁን በቴሌግራም ቻናል ይለቀቃል ። ይከታተሉ የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ትምህርቶችና ስብከቶች ለመከታተል ከሥር የተቀመጡትን ገጾች ይመልከቱ፡- https://t.me/Nolawii https://t.me/nolawisebketoch https://www.facebook.co m/ashenafi.mekonnen.357 https://youtu.be/3qfQp9yYmHY www.ashenafimekonen.com
Показати все...
Nolawi ኖላዊ

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

2016-11-05 የማርቆስ ወንጌል ትርጓሜ 25.m4a47.37 MB
13
የሕይወት ሥነ ሥርዓት (38) 22. ልጆችን በሥርዓት አሳድግ ምናልባት እኔ ልጅ የለኝም ይህ ምክር እኔን አይመለከተኝም እያልህ ይሆናል ። ልጆች ከእግዚአብሔር የምንቀበላቸው እንጂ የምንቀማቸው አይደሉም ። ሴት ልጅም የልጅ መንገድ እንጂ የልጅ ፈጣሪ አይደለችም ። መውለድ ጸጋ እንደሆነ አለመውለድም ስጦታ ነው ። አብርሃምና ሣራ እስከ መቶ ዓመት ልጅ አልወለዱም ። እግዚአብሔርን በአንድ ልብ ሁነው ለዘጠናና ለመቶ ዓመት ካገለገሉ በኋላ እግዚአብሔር ልጅ ሰጣቸው ። ልጅ የተቀበሉበት ዓላማም የመሢሑን መምጫ መንገድ ለማሳለጥ ነው ። በሌላ አነጋገር ልጅን ለክርስቶስ ወለዱ ። ለጧሪ ለቀባሪ ሳይሆን ልጅን ለሃይማኖት ወለዱ ። እኛ በልጆቻችን ላይ ካለን ዕቅድ እግዚአብሔር በልጆቻችን ላይ ያለው ዓላማ ይበልጣልና ። ነቢይት ሃና ብዙ ዘመን ልጅ በማጣት አልቅሳለች ። በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ምእመናን መሳለቂያ እስክትሆን ድረስ ተሸማቃለች ። እግዚአብሔር ልጅ የሚሰጠን ልጅ ያልወለዱትን እንድናሳቅቅበት አይደለም ፤ ልጅ ችሎታ ሳይሆን ስጦታ ነው ። እመ ሳሙኤል ሃና ለራስዋ ልጅን ስትመኝ ዘገየባት ፤ የዘገየው ልጅ ሲመጣ ግን ለእስራኤል ሕዝብ ትልቅ መልስ የሆነው ሳሙኤል ሆነ ። ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የወለዱትን ልጅ አላሳደጉትም ። በበረሃ ያደገው ዮሐንስ መጥምቅ ከመሸ የመጣ ነው ። የእነርሱ ደስታ የእግዚአብሔርን ክንድ ማየትና ነቀፌታቸው ሲወገድ መመልከት ነው ። ያልወለዱ የተመሰገኑበትና ብፁዓን የሚባሉበት ዘመን እንዳለ በማሰብ በመውለድ ብቻ መደሰት እንደሌለ እናስተውል ። አዎ ልጅ ባትወልድም የምታየው ልጅ በሙሉ ያንተ ነው ። ብዙ ደናግልና መነኮሳት የብዙዎች አባትና እናት ናቸው ። እማሆይ ትሬሣን ታውቃቸዋለህ ። የሚሊየኖች እናት የሆኑ መነኵሲት ናቸው ። ልጅነት ብዙ እንደሆነ ፣ ወላጅነትም ብዙ ነው ። ይህ ዘመን የወለዱ ካልወለዱት በላይ የሚጨነቁበት ነው ። በአጭር ቃል ዘመኑ ልጅ ነጣቂ ነው ። ልጅ የወላጆቹን አሳብ ከሚያንጸባርቀው ይልቅ የዘመኑን አሳብ ማንጸባረቅ ይቀለዋል ። አውቃለሁ ባይነት ስለ ነገሠና በዕድሜ የገፉ የሚናቁበት ባሕል ስለ ተመሠረተ ወላጆች በልጆቻቸው ተከድተዋል ። ወላጅ ልጁን መገሠጽና መቅጣት የማይችልበት የሚያለያይ ዘመን ላይ ደርሰናል ። አዎ ልጆች ተሸማቀው ፣ እንዳይጠይቁ ተደርገው በፍርሃት ማደግ የለባቸውም ። በመኖር ፣ በማፍቀርም ከቀደሙአቸው ወላጆች ግን መማር አለባቸው ። ልጆች ቀለብ ከቤት ፣ ምክር ከደጅ ካደረጉ ቆይተዋል ። ወላጆቻቸውን አንሰማችሁም ተስፋ ቍረጡ እያሉ ነው ። አንዳንድ ጊዜ እኛም በወላጆቻችን ላይ የፈጸምነውን ዓመፃ በልጆች ልንቀበል እንችላለን ። ሌላ ጊዜም ልጅ እንደ ራሱ እንጂ እንደ እኛ አይደለም ። ነጻ ፈቃድ አለውና በራሱ መንገድ ቢሄድ የበደለኝነት ስሜት ሊያሰቃየን አይገባም ። የነቢዩ ፣ የቡሩኩ የዳዊት ልጆች አብዛኛዎቹ ክፉዎች ነበሩ ። ልጅን ስለቀጣነው ብቻ አይታረምም ፣ ልጅ ከቃል ይልቅ በሕይወታችን የምናስተምረው አዳሪ ተማሪ ነው ። ልጅ ከእኛ ጋር ከሚያሳልፈው ዕድሜ ይልቅ ከሰፊው ዓለም ጋር የሚያሳልፈው ሰዓት ይበልጣል ። ንጹሕና ጉልበት ያለበት ሰዓቱን ቢያንስ ለስምንት ሰዓት በትምህርት ቤት ያሳልፋል ። ቤትን ከማሳመር አገርን ማሳመር ለልጆች ወሳኝ ነው ። አገሩ ከወደቀ ምንም ብንጠነቀቅ ልጆቻችን ገንዘብ አይሆኑንም ። አገርን እየዘረፈ ለልጆቹ የሚቀልብ ብዙ ወላጅ አለ ። በጉቦ ያደጉ ልጆች አእምሮአቸው ጤነኛ አይሆንም ። የሚበሉት ደም እንጂ እንጀራ አይደለምና ። የሰለጠነ አገር ልከን ብናስተምራቸው የሰለጠነ ሱስ ውስጥ ይገባሉ ። የመጀመሪያ ልጅ የደስታችን መነሻ ነው ። ከዚህ በፊት በልጅ ተደስተን ስለማናውቅ የመጀመሪያው ልጅ ትልቅ ፍስሐ ያመጣልናል ። የመጀመሪያው ልጅ ከልምድ ማነስ የተነሣ በጣም ስለምንጠነቀቅለት ነጻነት የሚያጣ ይሆናል ። እርሱን የሚመስል ልጅ እቤት ውስጥ ስለሌለ ውሎው ከእኛ ጋር በመሆኑ ያለጊዜው ይበስላል ። ፍጹም እንዲሆን ወይም እንደ ትልቅ እንዲያስብ ስንፈልግ ብዙ ዱላ ልናበዛበት እንችላለን ። የመጀመሪያ ልጅ ፈሪ ወይም ቂመኛ መሆኑ የተለመደ ነው ። አሊያም የራሳቸው ጉዳይ ብሎ ቤተሰቡን ችላ የሚል ራስ ወዳድ ይሆናል ። ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ወላጅ ራሱን ቆጥሮ ቀንበር የሚሸከም ይሆናል ። ሁለተኛው ልጅ ሲመጣ ዓይን ሁሉ ከእርሱ ላይ ይነሣል ። በዚህ ምክንያት በቅንዓት ውስጡ ይጎዳል ። አልበላም እያለ የሚያምፀው የራሱን ጨርሶ የሌላውንም ቢበላ ደስ ይለዋል ። ራሱንም በገዛ ቤቱ ባዕድ ያደርጋል ። አንዳንድ ጊዜ የመጀመሪያ ልጆች ወላጆቻቸውን ክደው አባትና እናቴ አይደሉም እያሉ በደጅ ያወራሉ ። ፍቅር የተነፈጉ ፣ የመጀመሪያውን እንክብካቤ ያጡ ሲመስላቸው የደጅ ኀዘኔታ ለማግኘት በፈጠራ ታሪክ ራሳቸውን ያስተዋውቃሉ ። የሚገርመው የፈጠራ ታሪካቸውን እያመኑት ይመጣሉ ። የመጀመሪያ ልጅ ላይ ሥራ መሥራት ቀጣዮቹ እንዲባረኩ ያደርጋል ። ቀጣዮቹ ከወላጆቻቸው ይልቅ የበኵሩን ልጅ መከተል ይወዳሉ ። ስለዚህ የመጀመሪያ ልጅን ከመጠን በላይ መንከባከብ ተገቢ አይደለም ። ምክንያቱም አይዘልቅምና ። “የማይዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት” እንዲሉ ። ይልቁንም በኵሩ የእግዚአብሔር ነውና ለእግዚአብሔር መስጠት ፣ አገልጋይ ማድረግ ይገባል ። በኵርን ለእግዚአብሔር መስጠት ስንከለክል 12 ወልደን አንዱም የማይወደን እየሆነ መጣ ። ሰንበትን ለእግዚአብሔር ስንከለክል በሰንበት እየሠራንና እየተማርን በረከትና እውቀት የለሽ ሆንን ። እግዚአብሔርን ሰርቆ የበለጸገ ማንም የለም ። ይቀጥላል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
Показати все...
34👍 8👏 3
ማስገንዘቢያ ቤርያ መጻሕፍት መደብር በአርበኞች ሕንፃ ላይ የነበረውን ሥራ አቁሟል :: ቀጣዩን አድራሻ እስክናሳውቅ መጽሐፍ የምትፈልጉ በቀጣዩ ስልክ ተጠቀሙ 0910531997 ከአክብሮት ጋር !
Показати все...
22👍 9🥰 7👏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ወዴት ነህ  ወዴት ነህ  ብለህ አዳምን የፈለግህ ፣ ያለበትን እያወቅህ ያለበትን ያሳወቅህ ፣ በቃል ብቻ ሳይሆን በለቢሰ ሥጋ ወዴት ነህ  ብለህ የፈለግህ ፣ ከገነት ጫካ እስከ ቀራንዮ የጠፋውን ያሰስህ እኛም በተራችን እንጠይቅህ ወዴት ነህ  ለመቆምም ለመሄድም ስንፈራ ፣ ለመግጠምም ለመለያየትም ስንሰጋ ፣ ለመጀመርም ለመጨረስም ስንንቀጠቀጥ ፣ መንፈስህ የራቀን ይመስለናል ። እባክህ ወዴት ነህ  ገጻችን ሲጠቁር ፣ የልጅ አዋቂው ፊት ትካዜ ሲይዘው ፣ የመኖር መላ ጠፍቶ ሞት እንደ መፍትሔ ሲፈለግ ፣ ድሀ ያለችውን ሲነጠቅ ፣ የፈሩት እየደረሰ ፣ የጠሉት ሲወርስ ምነው አንድዬ ጨከነብን ይሉሃል ። እባክህ ራስህን ግለጥ ፤ ወዴት ነህ  ሳትለየን የተለየኸን ፣ አጠገባችን እያለህ የራቅኸን መስሎ ሲሰማን ወዴት ነህ  ብለን በተራችን እንጠይቅሃለን ። መልሱ ጥያቄ ከሆነብን ጥያቄው ምን ሊመስል ነው  ሽማግሌው በሰላም ማረፍ ፣ ሬሳው አፈር መልበስ ፣ የወጣው መግባት ፣ የተማረው ማምረት ፣ የሠራው ማግኘት ሲሳነው ወዴት ነህ እንልሃለን ፣ ለመብላት ይከፍለው የሌለው በሰው እጅ ታግቶ ለመኖር ሲከፍል ፣ ፈጥሮ ላልፈጠረ ተወን እንዳትባል እባክህ ወዴት ነህ  ዓለም ሰላም ሆኖ እኛ ብቻ የታወክን መስሎ ይሰማናልና እባክህ እንፈልግህ ወዴት ነህ  የክፋት አማካሪዎች ምድሩን ሞልተውታል ። ገላጋይ ጠፍቶ ቤተሰብ ያልቃል ። አሸናፊ በሌለበት ወንድማማች ይቀላላል ። ከሚደነቅ ወደሚያደቅ ምዕራፍ ስንሸጋገር ፣ ቀኛችን ግራ ሁኖ ግራ ሲያጋባን ወዴት ነህ  እንልሃለን ። የጠፋውን አዳም ፈልገህ ያገኘኸው ፣ የጠፋብንን እውነት ፈልገን እስክናገኘው እርዳን ። እየጸለይን ካለመሰማት ፣ ስምህን እየጠራን ከመለያየት እባክህ አድነን ። አሁንም በቀረችው ትንሽዋ አቅማችን ወዴት ነህ  እንልሃለን ። ስለ ድሆች እንባ አለሁ በለን ። ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.
Показати все...
😢 28 25👍 12👏 3
አሳስብ (የወጣት አገልጋይ ፈተና) በግን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመልስ እረኛ የለም ። አገልጋይም ደጋግሞ ምእመናንን ከጥፋት መንገድ መመለስ ይገባዋል ። ለመጨረሻ ጊዜ ስህተት የፈጸመ ሰው በዓለም ላይ የለም ። የሰው ልጅ በመውደቅ ሰውነቱን ፣ በመነሣት መንፈሳዊነቱን ይገልጣል ። የአንድ ጊዜ ዕድል መስጠት አማኝን ላያበዛ ይችላል ። ወጣት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በትዕግሥት እውነትን ማስተማር ፣ ደጋግሞ በመጮህም ምእመናንን ከገደል መመለስ ያስፈልገዋል ። የሚማር ሰው ሁሉ በየትኛውም ዕድሜ ቢመጣ ልጅነት ይታይበታል ። ትምህርት ልጅ ያደርጋልና ። አገልጋዩ ግን የቤቱን ጉድለት ትቶ ፣ የራሱን መጎዳት ረስቶ ቢያገለግልም አሁንም መታገሥ ያስፈልገዋል ። እውነተኛ አገልግሎት ያልተቀበሉትን መስጠት ነው ። ፍቅርን ከሰዎች አላገኘ እንደሆነ ፍቅርን መስጠት ፣ ማንም በውድቀቱ አላዘነለት እንደሆነ ለወደቁት ማዘን የአገልጋይ ወጉ ነው ። የአገልግሎት ፍጻሜው ሰማይ ነው ። ከሰማይ የመጣውን አደራ በሰማይ ያስረክባል ። አገልግሎት አልተመቸም ፣ ሰሚም አልተገኘም ተብሎ የሚቆም አይደለም ። እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ ሰው ባይሰማ “ሰማያት ስሙ ፣ ምድርም አድምጪ” ተብሎ የሚጮሁበት ነው (ኢሳ. 1 ፡ 2) ። ወጣቱ አገልጋይ ማሳሰብ አለበት ። በዕድሜ የገፉ በትክክል መያዛችንን እስኪያረጋግጡ ይደጋግማሉ ። ወጣቱ ግን ይሰለቻል ። በመደጋገም ውስጥ መስማት አለ ። ሰዎች በተለያየ ነገር ልባቸው ይሰረቃል ። እውነቱን እውነት ብለው ለመቀበል ይዘገያሉ ። ያልተቀጡ ኀጥአንን ፣ በመከራ የሚያልፉ ጻድቃንን በማየት “መታዘዝ ምን ጥቅም አለው ” ይላሉ ። ቃሉን ከራሳቸው ፣ በዙሪያቸው ካለው ዓለም ጋር በመታገል ይሰማሉ ። ሰይጣን ቃሉን እንዳንሰማ በመጀመሪያ ፣ እንዳንታዘዝ በመቀጠል ፣ በመጨረሻም ልበ ደንዳና እንድንሆን ይዋጋል ። ማሳሰቢያ የሚል ቃል ያስደነግጣል ። ማሳሰቢያ ቀጥሎ ውጤት ላለው ነገር የሚታወጅ ነው ። እግዚአብሔርን ማሞኘት የሚችል የሚመስለው ሰው አለ ። እርሱ የወደደውን አምላኩ የሚወድለት አድርጎ የሚገምትም አያሌ ነው ። ሲደጋግመው ስህተት ትክክል የመሰለው አለ ። ስላልተቀጣ እግዚአብሔር የፈቀደለት የሚመስለውም አይታጣም ። በነፍሱ እልህ ገብቶ በኃጢአት ጭቃ የሚቦካ አለ ። አንድ ቀን እመለሳለሁ ብሎ ኃጢአት እስከ አንገቱ ደርሶም የሚቀልድ አለ ። ማሳሰብ ግን ያነቃል ። ማሳሰብ በጋራ የማሰብ ውጤት ነው ። አስቤበታለሁ አስብበት ማለት ነው ። አንድን ጥፋት ከሁለት ወገን ማየት እርሱ ማሳሰቢያ ይባላል ። ለዚያ ሰው ማሰብ የሚጠቅመው ሰውዬው ለራሱ ሲያስብ ብቻ ነው ። ሰውን በግድ የሚያድን ፣ በግድም የሚያስኰንን ኃይል በሰማይም በምድርም የለም ። ተረቶችና የሰው ልጅ ምናባዊ ፈጠራዎች የሚያስደስት ትርኢት አላቸው ። ነገር ግን መጨረሻ የላቸውምና ተስፋ አይሰጡም ፣ ልብን አያሳርፉም ። የክርስትና ሃይማኖት የመጽሐፍ ሃይማኖት ነው ። ሳይንሳዊ ማረጋገጫና ሰዋዊ መላዎች ድጋፍ አይሆኑትም ። ሁሉን ስለደገፈው ጌታ የምንማርበት ነው ። ክፉ ትምህርቶች በዓለም ላይ ተዘርተዋል ። እነዚህ የማይታዩ ማሰሪያዎች ናቸው ። ወጣሁ ሲሉ እንደ አረንቋ ብዙዎችን የሚይዙ ናቸው ። የክፉ ትምህርት አባቱ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው ። ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ የተበላሸ ኑሮን ይፈጥራል ። ወጣቱ አገልጋይ እንደ ሎጥ ሚስትና ልጆቹንም ሳይቀር እየሄደ ማሳሰብ እንጂ ቆሞ መጥራት አይገባውም ። የቆሙ ሰዎች ሌላውን ለማቆም ብቁ ናቸው ። እንቅፋት የሚባለው ቆሞ የቀረ ፣ ወይም ወድቆ የቀረ ፣ የራሱ ባልሆነ መንገድ ላይ የተገኘ ነው ። ቆመን ስንቀር ፣ ወድቀን ስንቀር ፣ የራሳችን ባልሆነ መንገድ ላይ ስንገኝ እንቅፋት እንሆናለን ። ይመስለኛል ፣ ሊሆን ይችላል ፣ እንደ እኔ አተያይ ፣ እገሌ እንደሚያምነው ተብሎ ሃይማኖት አይሰበክም ። ሃይማኖት እርግጥና በራሱ በሚታመነው በክርስቶስ የተሰበከ ነው ። ያለ ዲሲፕሊን ክርስትናን ማካሄድ ፣ አገልግሎትን ባለ አክሊል ማድረግ አይቻልም ። የአመጋገብ ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ፣ የሰው ለሰው ግንኙነት ፣ የሥራ ፣ የአስተዳደር ዲሲፕሊን ያስፈልጋል ። አገልጋዩ ረጅም ርቀት ለመጓዝም ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በልክ ሊያደርገው ያስፈልጋል ። በቂ ስፖርት የሚሠሩ ተራራውን ለመውጣት ይችላሉ ። አብነት የሚያደርጓቸው ሰዎችም አሉ ። እግዚአብሐርን መምሰል ግን ከደብረ ጽዮን ፣ ከማይፈርሰው ከተማ ያደርሳል ። የሁለት ዓለም ወራሽ የሆነውን ሰው ማገልገል መታደል ነው ። ከኋላው ጥሎት የሚሄደው ሥራ ፣ ከፊት የሚቀበለው እምነት እንዲኖረው አበክሮ ማስተማር የወጣቱ አገልጋይ ድርሻ ነው ። እምነት ብቻ በቂ ነው የሚሉ ሰነፎችን ፣ በምግባሬ እድናለሁ የሚሉ ትዕቢተኞችን መገሠጽ አለበት ። በሥጋና በነፍስ ተዋሕዶ የቆመ ሰው ፣ በእምነትና ምግባር ተዋሕዶም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ። ማጥፋት እየቻለ የታገሠውን አምላክ እያሰበ ስድብን በደስታ መቀበል እግዚአብሔርን መምሰል ነው ። የሮማ ጎዳናዎች እንደ ጥንቱ ድምቀት አልታየባቸውም ። ሮም በብዙ ንጹሐን ደም የተጠመቀች የግፍ ከተማ ናት ። ዓለም ሁሉ ሮም እንድትሠራ አዋጥቷል ። የጳውሎስን ቤት ለማግኘት ስዳክር እኔ ጢሞቴዎስ በልቤ ወጣቱን አገልጋይ እንዲህ ስል መከርኩት፡- “ወዲያው ልታደርገው ያለህን ፈጥነህ አድርግ ፣ ጊዜ የሚሰጠውን ቀጠሮ አብጅለት ፣ ልታደርገው የማይገባህም ለዘላለም አታድርገው ። ቆርጦ መነሣትህ እንጂ ሺህ ጊዜ ማሰብህ ድል አድራጊ አያሰኝህም ። የፈጸምከው ካለ ሌሎች የጀመሩት ነውና ክብር ስጣቸው ፣ የጀመርከው ካለ ሌሎች የሚፈጽሙት ነውና ተተኪዎችን አፍራ ። የዘለቁ ራእዮች ፍቅር ፣ ትሕትናና መንፈሳዊ ቆራጥነት ያለባቸው ስለሆኑ እነዚህን አጥብቀህ ያዝ ። ያጣኸው የሚገኘው የያዝከውን በትክክል ስታየው ነው ። ተፈጥሮ ሁሉ አንተ ብቸኝነት እንዳይሰማህ የከበበህ ቤተ ዘመድህ ነው ። ከሁሉ በላይ የሚራዱህ ቅዱሳን መላእክት አሉና የሚዋጉህን አጋንንት አትፍራ ። የሚያበረታ ጸጋ ፣ የሚያረጋጋ ሰላም ካንተ ጋር ይሁን ! አሜን! ጢሞቴዎስ ነኝ ክፍል 19 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.
Показати все...
24👍 9🥰 6
አንተ እኮ !!! ከለምለም ቅጠል በላይ ደስታዬ ፣ ከሚፈልቀው ይልቅ እርካታዬ ፣ ከመንገድ በላይ መድረሻዬ ፣ የዕለት የዘለቄታ ሳይሆን የዘላለም ማረፊያዬ ፣ በመቃብሬ ላይ ይነሣል ብላህ የጻፍህ ፣ የተጠላሁትን ያፈቀርህ፣ የሰይጣን መልክ ሲሰጡኝ መሳይ ልጄ ያልከኝ ፣ የተነቀፍሁትን ያመንከኝ፣ ወርቅህን እኔ ጭቃው ላይ የጣልህ ፣ መክሊትህን ለአባካኙ የሰጠህ ፣ ጸጋህን ለተራቆተው የናኘህ ... አንተ እኮ እግዚአብሔር ... ። ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሐምሌ 1/2016 ዓ.ም.
Показати все...
79🥰 14👍 4
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.