Love - ፍቅር
Відкрити в Telegram
ስለተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አብረን እንድንማማር መድረኩን ከፍተናል። በሚመቸን እንሳተፍ። @kkzinu1 @TgKassa @Nahooom @Yona4501 @Fkr_Orthodox https://t.me/lovefkr https://t.me/lovefkrlove youtube.com/lovefkrlove https://LoveFkrLove.com www.facebook.com/lovefkrlove
Показати більше8 419
Підписники
Немає даних24 години
-207 днів
-12730 днів
Архів дописів
8 419
✌️ #እርግጠኝነት!!!
💎በህይወታችሁ ውስጥ የሆነ ቀን፣ የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቦታ "... #እርግጠኛ ነኝ!" የሚል ሰው አጋጥሟችሁ ያውቃል? አዎን! ብዙዎቻችን አጋጥሞናል።
"ከእውቀት ጋር ጥርጣሬ ይጨምራል" ይባላል።
With knowledge doubt increases.
🕰ነገር ግን የምታውቀው ትንሽ ሲሆንና የህይወት ልምድህ ካልዳበረ በሁሉ ነገር "እርግጠኛ ነኝ" ትላለህ። በተለይ አንተ የምታውቀው ትንሽ ሆኖም በሌሎች ካልታወቀማ አይፈረድብህም! የህይወት ልምድህ ትንሽ ነውና ልኩ መንገድ፣ ልኩ ነገር እሱ ብቻ ይመስልሃል። ምን ይደረግ፣ ሌላ አላየህማ! አልበራልህማ!
💡1+1 = 10 የሚለውን ስህተት ነው ብለህ እርግጠኛ ሆነህ የምትደመድመው ስለ Binary Addition እስክትማር ነው። እውቀትና መረዳትህ ሲጨምር 1+1= 2 ወይም 1+1=10 ወይም 1+1 > 2 ወይም... ብለህ የምትቀበልባቸው ሁኔታዎች እንደሚኖሩ ይገባሃል። ካልሆነስ?
💎ካልሆነማ አንዱን የገባህን መንገድ ይዘህ ሙጭጭ ትላለህ። ያ ግን ልክ አይደለም። ሁሉንም መርምር፣ መልካሙን ግን ያዝ። ሳትፈትሽ ሙጭጭ አትበል።
Understanding opens the door of many possibilities.
💡እርግጠኝነት የእድገት፣ የመሻሻል፣ የአዲስ ነገር ጠላት ነው። "ነገ የሚሆነው ዛሬ ከሆነው አይለይም" ብሎ በእርግጠኝነት መናገርን የመሰለ የመሻሻል ጠላት የለም። ያላየኸውን የቅድመ-አያትህን ድምጽና እርምጃ እንዲህ ይመስል ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገርን የመሰለ ውሸት የለም። የማላውቃቸውን የቅማያቶችን ብሔር በእርግጠኝነት መተንተንን የመሰለ በሽታ የለም።
💡ከሁሉ በላይ ግን የሰው ዘር አመጣጥ እንዲህ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መደምደምን የመሰለ ቅጥፈትና ቅዠት የለም!
💎ግዴለም! እርግጠኝነቱን እንተወው፣ ለጥርጣሬ ትንሽ ቦታ እንተው። ሁሉም ነገር ቋሚና የማይቀየር ሳይሆን ተለዋዋጭ እንደሆነ እንገምት።
jHH
❤️አሁን ያን ሁሉ የተደከመባት ሀገር እንዲህ ትሆናለች ብሎ ማን አሰበ? ያ ቤተሰብ እንዲህ እንደሚሆን ማን ገመተ? ይሄ ኢኮኖሚ እንዲህ እንደሚንፈራፈር ማን ጠረጠረ? ያ ዳይናስቲ እንዲህ እንደሚበተን ማን አሰበ? ግን ሁሉም ያልታሰበውና ያልተገመተው ሆነ።
አየህ የማይቀየረው እና ቋሚው ለውጥ ብቻ ነው።
ሌላውስ?
ሌላውማ እንደማይቀየር እርግጠኛ አይደለሁም።
"ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ተብሏልና!
✍Getu k. Toughe
# ውብ_አርብ❤️
@Lovefkrlove
@Lovefkr
8 419
✨ Happiness is not absence of sufferings but acceptance of sufferings ,Stop worrying about things which are beyond your control.
👉አንዳንዶቻችን ያሰብነውን ስራ እስክንይዝ፤ የምንፈልገውን ገንዘብ እስክናገኝ፤ የምንወደውን
ሰው በእጃችን እስንካስገባ፤ የምንፈልግበት የህይወት ደረጃ ላይ እስክንደርስ፤ እያልን ደስታችን ቤታችን እንዳይገባ እንከለክለዋለን። ሞኝነታችን እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፤ ምን አልባት ያሰብነውን ብናገኝ እንኳን ላንደሰት እንችላለን፤ ምክንያቱም ደስታ ከውጫዊ ነገሮች ጋር አብሮ የሚቋጠር ቁስ ባለመሆኑ። ደስታ ሁሌም ከበራችን ቆሟል በቀጠሮ አላስገባ ብለነው ነው እንጂ።
👉ወደ ደስታ የሚውስድ ምንም አይነት መንገድ የለም፤ ይልቁንም ደስታ ወደ ምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰን ብቸኛው መንገድ ነው እንጂ። ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር፤ ያኔ ፈጣሪ ይጎደለውን በተዓምሩ ይሞላዋል።
🤞ዛሬ በመኖርህ አመስግን አሁንህንም እንዲሁ አጣጥም።
🙏 #መልካም_አዳር 🙏
✍Humanity
@Lovefkrlove
8 419
#ወቅት_ያቀበለኝ_ስሜት......
👆ህይወት እንዲሁናት መሰለኝ.. ..።
👉ከእለታት አንድ ቀን ድንገት ከእንቅልፍህ ስትነቃ .....ሁሉም ነገር የሌለህ መስሎህ በሚሰማህ ጊዜ ሁሉን ነገርህን የምትሆንልህን እናትህን አጥተህ እራስህን ታገኘዋለህ.....ትኖራለህ።
👉ደሞ ሌላ ግዜ ድንገት ሁልግዜ የምትኮራበትን የምትመጻደቅበትን አባትህን ሞቶ እራስህን ታገኘዋለህ.....ትኖራለህ።
👉ደሞ እንደገና በመኖርህ ውስጥ ድንገት ስትነቃ ፍልቅልቅ ጨቅላ ልጆችህን አጥተህ እራስህን ታገኘዋለህ......አሁንም እየኖርክ ነው። ኑሮ እየቀጠለ ነው።
🤞አሁንም በምንቃትህ ውስጥ ደሞ ድንገት በህይወት መንሸራተት ወንድሞችህ ርቀውህ አጥተሃቸው እራስህን ታገኘዋለህ ........መኖር ቀጥሏል።
🤞......ደሞ ድንገት ስትነቃ እንዲሁ የወደድከውን ያፈቀርከውን አጥተህ እንደተለመደው እራስህን ታገኘዋለህ ......ህይወት እንደቀጠለች ነው። የማጣቱ ምክንያቱ....ተፅእኖው.....አይነቱ ይለያያል።
..... #ግን ግን ሁሉም ማጣትን መለየትን ያሸክሙሃል። ሌላ ግዜ ደሞ ድንገት ሸክምን ችሎ ለመኖር በልምምድ ውስጥ ሆነህ እራስህን ታገኘዋለህ .... ከተስፋ መቁረጥ ጋር ትንቅንቅ ገጥመህ። አንዳንዴ ለመኖር የምትፈተነውን
ያክል መኖር ለማቆምም ከባድ ፈተና መሆኑን ትረዳለህ። .
.
.
#ድንገት ደሞ ሌላ ግዜ ስትነቃ የትዕግስትህ መጠን አድጎ ....ቻይነትህ ጎልብቶ ....... ማስተዋልህ በዝቶ በህይወትህ ያገኘሃቸው ... የተደረጉልህ ......ያሉህ ነገሮች በህይወትህ ካጣሃቸው ....ካልተደረጉልህ .... ከሌሉህ ነገሮች እጅግ በጣም የበዙ መሆናቸውን ተገንዝበህ ፈጣሪን ስታመሰግን እራስህን ታገኘዋለህ ። .......
.
.
በጊዜው ድንገት በመንቃታቹ ውስጥ
በየትኛው ስሜት ውስጥ ሁናቹ እራሳቹን አገኛችሁት???
@Lovefkrlove
@Lovefkr
✍balmbaras
8 419
“ #በህይወት ውስጥ የምንሰራው ትልቁ ስህተት ምንድነው?” ተብሎ ሲጠየቅ
⏰:- “ትልቁ ስህተት ጊዜ አለኝ ብሎ ማሰባችን..”
🖍አየህ ጊዜ ነፃ ነው ግን በዋጋ ሊተመን የማይችል። የጊዜ ባለቤት መሆን አንችልም ግን ልንጠቀምበት እንችላለን::
ልናቆመው አንችልም ነገር ግን ልንደሰትበት ወይም ልንሰራበት እንችላለን::
እናም አንዴ ካጣነው መልሰን ማግኘት አንችልም::
#መልካም_አዲስ_አመት
#ፍቅር_አሁን !! 💚💛❤️
@Lovefkrlove
@lovefkr
8 419
#ወዳጄ_ሆይ፡-
. . . መልካም ቀን ከጣፋጭ ቁርስ ትልቃለች
የሚያስደስትህን ስታደርግ . . .ሰዎች ባንተ ሲደሰቱ ስተይ . . .ስራህ ትርጉም ሲኖረው . . .ከሰዎች ጋር በፍቅር ስትመራ
ቀንህ ውብ እና ያማረ ይሆናል።
#ወዳጄ_ሆይ፡-
" የፍቅር መንገድ ዳር ዳሩ አበባ ሰላም እና ደስታ ከመሀል አስገባ"‼️ በፍቅር አለም ሚሰለች ነገር የለም . . .
ትናንትና. . .
ዛሬ . . .
ነገም . . .
ሁሉም ቀን አዲስ ብርሀንን ይዞ ይመጣል በሁሉም ብርሀን ውስጥ ፍቅር ካለ ሁሉም ቀናቶች የሰላም እና የደስታ ይሆናሉ፡፡
💚ወዳጄ ሆይ፡-
በህይወትህ ውስጥ መቼም ልታጣቸው ማይገቡ 3 ነገሮች . . .‼️
1. ፍቅር
2. ፍቅር
3. ፍቅር
. . . ፍቅር ካለ ሰላም አለ. . .ሰላም ካለ ጤና አለ. . . ጤና ካለ ደስታ አለ . . . እነዚህን ነገሮች ስታገኝ ህይወትህ ሙሉ ይሆናል። ግን ምንጩና መነሻው ፍቅር ነው።
💛ወዳጄ ሆይ፡-
ሁሉንም ነገር ተናግረህ ፣. . . ሁሉንም ነገር አዳምጠህ ፣. . . ሁሉንም ነገር አይተህ ፣. . . .ሁሉንም ነገር ጠይቀህ አትዘልቅም ፣ . . . ሁሉም ነገር የየራሱ የሆነ ሚስጥር አለው . . . የነገሮች ገፅታ ከቆምክበት ቦታ አንፃር ልዩነት ይፈጥራልና
❤️ወዳጄ ሆይ፡-
"ከክፋት ስትርቅ ሰላም ትሆናለህ። ለሰዎች መልካም ስታስብ ውስጥህ የተረጋጋ ይሆናል። በሰዎች ደስታ ስትደሰት ጤናማ አስተሳሰብን እየገነባህ ትመጣለህ። የዛኔ ውስጥህ ከጭንቀት እና ከፀፀት የፀዳ ይሆናል።"
🙏#መልካም_ምሽት🙏
@Lovefkrlove
@lovefkr
8 419
🌙የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም
🌹ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም
😘ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም ........................እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም
🌘ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው::
ጨለማውን የደፈረ ጨረቃን፤ እሾሁን ያልፈራ ጽጌረዳዋን፤ እራሱን ያወቀ ፍቅርን ማግኘታቸው አይቀርም::
🌙The best definition I heard for "Fearlessness" was that Fearlessness is not the absence of fear but the ability to step into your fear. It's the courage to acknowledge your fear, but not letting it stop you from anything you want. Don't make your fear your Enemy. If you make your fear your enemy it will kill you but, if you make it your friend you will always win.
🌔When you make the darkness your friend you get to enjoy the beauty on the Moon. When you become your own friend, Love will find you everywhere.
✍ በሚስጥረ አደራው
🙏#ውብ_ምሽት🙏
@Lovefkrlove
@Lovefkr
8 419
💬በህይወታችሁ ተስፋ ቆርጣችሁ ታውቃላችሁ?
💬አስቸጋሪ ነገር ሲገጥማችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ፃፉልን።
🎙በድምፅ የምትልኩት በሰላም ካሳደረን በነገው ፖስት ይካተታል።
8 419
📊 የማይዘልቅ የፍቅር ጓደኛ እንድንመርጥ ከሚያደርጉን ምክንያቶች ዋንኛው የቱ ነው?
https://youtu.be/j5KX4muFPno
ብቸኝነትን በመፍራት (64%)
በጓደኛ ተጽዕኖ (25%)
የቤተሰብ ተጸዕኖ (10%)
87 👥 pollrbot.com/p/Hfb0imoVYw==
8 419
እርስ በርስ ልዩነታችንን አስፍተን የውጭ ሃይሎች ሰላምን ያመጣሉ ብዬ አላምንም። መፍትሄው በመነጋገርና በይቅርታ ልዩነቱን መፍታት ነው። @LoveFkrLove
8 419
😏" #ኤጭ_ደሞ_ነጋ!" የሚል አለ
🙏" #እሰይ_ነጋ!" የሚል አለ::
ህይውት ውብ ብትሆንም ለአማራሪ ግን ፉንጋ ናት::በውስጡ የተሸከመው ጨለማ አስተሳሰብ የህይወትን የውበት ብርሃን ይጋርድበታል::
ህይወትም አትወደውም::ስለሚጠላት ትጠላዋለች::ዳሩ ግን ጠልታው ሳይሆን የሰጣትን መልሳ ስለምትሰጥ ነው::
ከህይወት በላይ ህይወትን የምትመለከቱበት መንገድ ዋና ነው::ምልከታችሁ የህይወት መነፅራችሁ ስለሆነ ተጠንቀቁ::አንድ ጊዜ ህይወትን የምትመለከቱበት መነፅር ከተበላሸ የምትመለከቱት ነገር ሁሉ ይበላሻል::
ምልከታችሁ ምን ይመስላል ? ውብ ነው ፉንጋ ? አመስጋኝ ነው ? አማራሪ ? ተስፈኛ ነው? ወይስ ጨለምተኛ?
በጣም እጅግ በጣም ተጠንቀቁ::
🌕የህይውትን በጎ ነገር የሚያጎላ የአመለካከት መነፅር ያዙ #አመስግኑ #ይቅር_በሉ #አፍቅሩ #ተስፋ_አድርጉ #ስጡ አሁን ውስጥ #በደስታ_ኑሩ ከህይወት ወንዝ ጋር ፍሰሱ::
#መልካም የስራ የስኬት የደስታ ጊዜ!💚
✍ማንያዘዋል እሸቱ
@Lovefkrlove
@Lovefkr
8 419
☝️ #ህይወት
☃የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ትሁን፡፡
🌄 ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ #ፍቅር_የሕይወት_ውሃ_ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።
📡ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ #ፍቅር_ስያሜ_የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።
📍የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።
☀️ አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት አትስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም፣ #ፍቅር_ውብ_ዝምታ_ነው ፡፡
✍ሸምስ ታብሪዝ
#ውብ_ምሽት
@Lovefkrlove
@Lovefkr
8 419
🥰 #ሕይወት_እንደ_ማዕበል_ሲሆን
☝️አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡
☝️ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፣ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡
አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል!
#መልካም_ምሽት ❤️
✍ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Lovefkrlove
@Lovefkr
8 419
❓እንዴት.....
📍ከምታየው በላይ ዋጋ ያለው እንዴት እንደምታየው ነው*
📍*ከምትሰማው በላት ዋጋ ያለው እንዴት እንደምትሰማው ነው*
📍ከስሜቱ በላይ ዋጋ ያለው እንዴት እንደሚሰማህ ነው*
🖍ከሁኔታው በላይ #እንዴት እንደሆነ ማወቁ ጥበብ ነው። እውነት ትክክለኛ መነጽርን ትሻለች፤ ወይም ደግሞ ትክክለኛው እይታ ከሌለን የእውነት እውነት መሆን እርባና ቢስ ይሆናል። ይህ መነጸር "እንዴት" በሚለው ጥያቄ ይቀረጻል።
🌕በዚህ መነጽር የብዙ ነገሮችን ሂደት ማየት ይቻለናል። ጫፍ ደርሰው የምናያቸው ነገሮች ጫፍ መድረሳቸውን ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደደረሱ ያስረዳናል። ቁልቁል የተወረወሩትም አዘቅት ውስጥ መግባታቸው ብቻ ሳይሆን፤ እንዴት እታች እንደደረሱ የሚያስረዳን ጥያቄ "እንዴት" የሚለው ነው።የምናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ መከወናቸው አንድ ነገር ሲሆን፤ "እንዴት" እንደሆኑ ማስረዳቱ ደግሞ ሌላ እውነታ ነው።
🖍ይህ #እንዴት የሚለው ጥያቄ ምናልባት፤ የብዙ ሁኔታዎችን ትክክለኛነት መመርመሪያ ጥያቄ ይመስለኛል። እንደውም ከጥያቄዎች ሁሉ አስፈሪውን "ለምን"ን ሳይፎካከር አይቀርም። ምክንያቱም በ"እንዴት" ጥያቄ ውስጥ የሁኔታዎች ሁሉ እርምጃና መንገድ ስለሚመረመር......
✍በሚስጥረ አደራው
🙏 #መልካም_ምሽት 🙏
@Lovefkrlove
@Lovefkr
