cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Більше
Рекламні дописи
30 391
Підписники
+5024 години
+3367 днів
+60730 днів
Архів дописів
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ! 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
🕊 25👍 9 6🥰 4👏 2😍 2
🩸ኦ የማይሞተው ሞተ🩸 ኦ የማይሞተው ሞተ ሔደ ቀራንዮ እየተጎተተ ወድቆ እየተነሳ እንዲያ እየቃተተ ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ በአይሁድ አደባባይ ፍርድ ተንጋደደ ወንበዴ ተለቆ ንፁህ በግ ታረደ አለቀሰች ቁማ ድንግል ማርያም ተሰቅሎባት ልጇ መድኃኔዓለም እጅ እና እግሩ ታስሮ ሄደ አደባባይ እየተገረፈ ታግሶ ስቃይ የማይሞተው ሞተ ለሰው ፍቅር ብሎ ዋለ ቀራንዮ እንጨት ላይ ተሰቅሎ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ስጋውን ለመኑ እንዲፈቅድላቸው ሄደው ከመስፍኑ ገንዘው ቀበሩት በአዲስ መቃብር ቅዱስ ቅዱስ ኃያል እያሉ በክብር በሊ/መ ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 12
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"...እራሳቸውን እንደ መሮ ወርዳቸውን እንደ ሞረድ ፬ ማዕዘን ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸውን እንደ ወስፌ ፭ ችንካር ሰርተው ሳዶር በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን አላዶር በሚባል ችንካር ግራ እጁን ከግማደ መስቀል አንድ አድርገው ቸነከሩት፤ አዴራ በሚባል ችንካር ማህል ልቡንቸነከሩት ዳናት በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ከ እግረ መስቀል ጋርቸነከሩት ሮዳስ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት..." -ሕማማተ መስቀል @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
7😍 1
🩸"ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን" 🩸 ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ አዝ____ ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ ማርና ወተትን ለሚመግበው ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው አዝ______ አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም አዝ______ እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ በሊ/መ ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 8😭 6😢 3 1👌 1
🩸"እንደ የዋህ በግ" 🩸 ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን። እንደ የዋህ በግ እየተጎተተ ወሰዱት ሁሉን የያዘውን እጆቹን አሰሩት ከሰሱት በሐሰት በአውደ ጲላጦስ በርባን ግን ተፈታ ተላለፈ ኢየሱስ የሚበድሉኝን ሳልበድላቸው የሚጣሉኝን ሳልጣላቸው ብሎ ጸለየ አያውቁምና ይቅር በላቸው ኪርያላይሶን/፬/ ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን። ቀኝ ግምጃ አልብሰው የብርሃን ፊቱን ጸፍተው ይሙት በቃ ብለው ሰቀሉት ቸንክረው ከክፉ አድራጊ ጋር ጌታ ተቆጠረ የሁላችን በደል በእርሱ ላይ ነበረ ማኅበረ አይሁድ ባንድ ከበቡኝ አጥንቴ እስኪቆጠር ድረስ ገረፉኝ እርቃኔን አርገው ከወንበዴ ጋር በግፍ ሰቀሉኝ። ኪርያላይሶን/፬/ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ። በፈቃዱ ሞተ ጌታ ራሱን አዘንብሎ ሆምጣጤውን ተፋ ተፈጸመ ብሎ ጨረቃ ደም ሆነች ጨለመች ጸሐይ እርቃኑን ሲሰቀል አምላክ ኤልሻዳይ እጅግ የመረረ ሐሞት አጠጡት ራስህን አድን ውረድ እያሉኝ በብርሃን ፊቴ አይሁድ በድፍረት ምራቅ ተፉብኝ ኪርያላይሶን/፬/ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን በዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
13👍 3🙏 1
🩸ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴ ድርሰቱ ስለ ጌታ ሕማም እንዲህ አለ: << ከደቀ ፡ መዛሙርቱ፡ጋራ፡ በተቀመጠባት ፡ በዚያች ፡ ሌሊት ፡ በአባቱ ፡ፈቃድ ፡ በራሱም ፡ ፈቃድ ፡ ሰውነቱን ፡ ለሞት ፡ ሰጠ ። ሁሉን ፡ የያዘውን ፡ ያዙት ፤ ሁሉን ፡ የሚገዛውን ፡ አሠሩት ፣ የሕያው ፡ የአምላክን ፡ ልጅ ፡ አሠሩት ፤ በቍጣ ፡ ጐተቱት ፤ በፍቅር ፡ ተከተላቸው ፤ በሚሸልተው ፡ ፊት ፡ እንደማይናገር ፡ እንደ ፡ የዋሕ ፡ በግ ፡ በኋላቸው ፡ እየተከተለ ፡ ወሰዱት ። ሊቃነ ፡ መላእክት ፡ በመፍራትና ፡ በመንቀጥቀጥ ፡ ከፊቱ ፡ የሚቆሙለትን ፡ በአደባባይ ፡ አቆሙት ፤ ኃጢአትን ፡ ይቅር ፡ የሚለውን ፡ ኃጥእ ፡ አሉት ፤ በመኳንንት ፡ በሚፈርደው ፡ በርሱ ፡ ፈረዱበት ። ለሱራፌል ፡ ዘውድ ፡ የሚያቀዳጃቸውን ፡ የእሾህ ፡ ዘውድ ፡ አቀዳጁት ። ለኪሩቤል ፡ የግርማ፡ ልብስ ፡ የሚያለብሳቸውን ፡ ለመዘበት ፡ ቀይ ፡ ግምጃ ፡ አለበሱት ። ኪሩቤል ፡ በእሳት ፡ ክንፍ ፡ ተሸፍነው ፡ ከፊቱ ፡ የሚሠወሩለትን ፡ እርሱን ፡ ክፉ ፡ ባሪያ ፡ እጁን ፡ አጽንቶ ፡ ፊቱን ፡ ጸፋው ። የመላእክት ፡ ሠራዊት ፡ በፍጹም ፡ መደንገጥ ፡ ለሚሰግዱለት ፡ እየዘበቱበት ፡ በፊቱ ፡ ተንበረከኩ ። ይህን ፡ ያህል ፡ ትህትና ፡ እንደምን ፡ ያለ ፡ ትሕትና ፡ ነው ። ይህን ፡ ያህል ፡ ትዕግሥት ፡ እንደ ፡ ምን ፡ ያለ ፡ ትዕግሥት ፡ ነው ። ይህን ፡ ያህል ፡ ዝምታ ፡ እንደምን ፡ ያለ ፡ ዝምታ ፡ ነው ። ይህን ፡ ያህል ፡ ቸርነት ፡ እንደምን ፡ ያለ ፡ ቸርነት ፡ ነው ። ይህን ፡ ያህል ፡ ሰውን : ማፍቀር ፡ እንደምን ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ። ፍቅር ፡ ያምላክን ፡ ልጅ ፡ ከዙፋኑ ፡ ሳበው ፡ እስከ ፡ ሞትም ፡ አደረሰው ። በደል የሌለበትን ፡ እንደበደለኛ ፡ ሰቀሉት ። ሕይወትን ፡ የሠራውን ፡ ከበደለኞች፡ጋራ፡ ቆጠሩት ። አዳምን ፡ የፈጠሩ ፡ እጆች ፡ በመስቀል ፡ ቀኖት ፡ ተቸነከሩ ፡ ወዮ ። በገነት ፡ የተመላለሱ ፡ እግሮች ፡ በመስቀል ፡ ቀኖት ፡ ተቸነከሩ ፡ ወዮ ። በአዳም ፡ ፊት ፡ የሕይወት ፡ መንፈስን ፡ እፍ ፡ ያለ ፡ አፍ ፡ ከሐሞት ፡ ጋራ ፡ የተቀላቀለ ፡ የኮመጠጠ ፡ መጻጻን ፡ ጠጣ ፤ ወዮ ። የወልድን ፡ መከራውን ፡ የሚናገር ፡ ምን ፡ አፍ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ከንፈር ፡ ነው ፡ ምን ፡ አንደበት ፡ ነው ። የፍቅር ፡ የጌታ ፡ ሕማማት ፡ በተነገረ ፡ ጊዜ ፡ ልብ ፡ ይለያል ፡ ኅሊናም፡ ይመታል ፡ ነፍስም ፡ ትንቀጠቀጣለች፣ ሥጋም ፡ ይደክማል ። የማይሞተው ፡ ሞተ ፣ ሞትን ፡ ይሽረው ፡ ዘንድ ፡ ሞተ ፣ ሙታንን ፡ ያድናቸው ፡ ዘንድ ፡ ሞተ። የምትወዱት ፡ ሰዎች ፈጽሞ ፡ አልቅሱለት ። ወየው : ወየው ፡ ወየው ፡ ዐማኑኤል፡ አምላካችን። ወየው ፤ ወየው : ወየው : መድኃኒታችን ፡ ኢየሱስ ። ወየው ፡ ወየው : ወየው ፡ ንጉሣችን ፡ ክርስቶስ ። ወየው ፤ ወየው ፡ ወየው ፡ ጻድቃን ፡ ከዕንጨት ፡ አወረዱት ፡ ሥጋውንም ፡ ለመገነዝ ፡ ከርቤ ፡ የሚባል ፡ የጣፈጠ ሽቱንና ፡ ንጹሕ ፡ በፍታን ፡ አመጡ ። >> @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 11 6😭 4😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፩ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
3👍 2🙏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፬ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 8 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፫ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
4👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፪ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 2 2
🩸"ሕሙም ስላዳነ" 🩸 ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤ ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ፤ ወኈለቊ ኲሎ አዕጽምትየ።      ሕሙም ስላደነ በእጆቹ ዳስሶ፤ ሙትን ስላስነሳ በእጆቹ ዳስሶ፤ ይህም በደል ሆኖበት ለአምለክ ኖላዊ ሔር፤ በዕጸ መስቀሉ ላይ ዘርግቶ በፍቅር፤ ቀኝ እጁን በሳዶር ግራውን በአላዶር፤ ተቸነከረልን ጌታ በሁለት ችንካር፤ አምንስቲቲ ሙኬርያ አንቲ ፋሲልያሱ ቤተመቅደስ ምኩራብ በተመላለሱ፤ ባሕር ላይ በሄደ ልክ እንደበየብሱ፤ ለአምላክ ቤዛ ኲሉ ይህ ወንጀል ሆኖበት፤ በዕፀ መስቀሉ ላይ ተላልፎ ለመሞት፤ ሁለቱን በአንድ ላይ እግሮቹን በዳናት፤ ተቸነከረልን አምላክ የኛ ሕይወት፤ አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ በልቡ አስቦ ድኅነቴን ሊያመጣ፤ ከበጎ ልቦናው በጎ የሚያወጣ፤ ይኽ ወንጀል ሆኖበት ለአምላክ መድኅንዓለም፤ በዕጸ መስቀሉ ላይ ተዘርግቶ ለዓለም፤ ልቡን በአዴራ ደረቱን በሮዳስ፤ ተቸነከረልን ወልደ አምላክ ክርስቶስ፤ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ በዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
8👍 5😱 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-አርብ ✅የስቅለት አርብ ✅መልካሙ አርብ @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
5
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት አርብ ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ የስቅለት ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል። (ማቴ 27፡35) መልካሙ ዓርብ ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ † 13ቱ ሕማማተ መስቀል 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት) † ጌታችን ከ6-9 ሰዓት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት 1ኛ.ኤሎሄኤሎሄ ኤልማስላማ ሰበቅታኒ ማቴ.27፤46 2ኛ. እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡ ሉቃ.23፤43 3ኛ.አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራእሰጣለሁ፡፡ ሉቃ.23፤46 4ኛ.አባት ሆይየሚያደርጉትን አየውቁምና ይቅር በላቸው፤ሉቃ.2334 5ኛ. እናትህ እነኋት፤ እነሆ ልጅሽ፤ዮሐ.19፤26-27 6ኛ. ተጠማሁ፤ ዮሐ.19፤30 7ኛ. ተፈጸመ፤ ዮሐ.19፤30 † ጌታችን በመስቀሉ ከ6-10 ሰዓት በመስቀልላይ ሳለ የተፈጸሙ 7ቱ ተአምራት፤ 1ኛ. ፀሐይ ጨለመች 2ኛ. ጨረቃ ደም ሆነች 3ኛ. ከዋክብት ብርሃናቸውን ነሱ 4ኛ. የቤተመቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ 5ኛ. ዐለቶች ተሰነጣጠቁ 6ኛ. መቃብራት ተከፈቱ 7ኛ. የሞቱት ተነሡ፤ ማቴ.27፤45-46 5ቱ ቅንዋተ መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ። 1. ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት 2. አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት 3. ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት 4. አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት 5. ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ(እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት ============================= ☞ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ መከራን ታገሰ ☞ሁሉን የያዘውን እርሱን ያዙት ☞ሁሉን የሚገዛውን እርሱን የአምላካችንን እጅ አሰሩት ☞ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እርሱን ሀጢያት አሉት ☞የማይገረፍ አምላክ እርሱን የሰውን ስጋ በመልበሱ ገረፉት ☞እንደ መብረቅ የሚያንፀባርቀውን ነጭ ልብስ የሚያለብስ አምላክ እርሱን ቀይ ግምጃ አለበሱት። ☞በእሳት በተጋረዱ ዙፋን ላይ የሚቀመጥ እርሱን በመዘባበቻ ወንበር ላይ አስቀመጡት። ☞እንደ ድንኳን ሰማይን የዘረጋ እርሱን በመስቀል ላይ ሰቀሉት ☞የመላእክትን አለቆች በፊቱ በመፍራት የሚቆሙለት እርሱን በጲላጦስ ፊት አቆሙት ☞በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ ተፈረደበት ☞አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 19 12👏 1
. ጉልባን እና ምሣሌው ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ❖ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ባቄላው ይከካል ቅርፊቱ ይላጣል ምሳሌውም የጌታችንን መከራ እና አይሁዳውያን ልብሱን አውልቀውት ነበር የዚያ መታሰቢያ ነው። ❖ በሊቃውንቱ ትምህርት ጉልባን ከስንዴ እና ከባቄላ ይዘጋጃል፤ ባቄላው ይታመሳል፣ ይፈተጋል፣ይከካል ስንዴው ግን አይከካም ፣ አይፈተግም፣ አይታመስምም ይኸውም ምሳሌነቱ ስለእኛ በተዋህዶ ለከበረው አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መታሰቢያ ነው። ማለትም ባቄላው የስጋ ስንዴው ደግሞ የመለኮት ምሳሌ ነው። ምንም እንኳን መለኮት ከሥጋው ያልተለየው አምላክ ቢሆንም ሕማሙ ግን መለኮትን አላገኘውም። የተዋህዶ መዶሻ የተባለ ቅዱስ ቄርሎስ እንዳስተማረው ነገረ ተዋህዶን በጋለ ብረት እንዳስተማረው ብረን ከእሳቱ ውስጥ ቢጨምሩት ብረቱ እሳቱን ይመስላል እሳቱም የብረቱን ቅርፅ ይይዛል ብረቱን ቢመቱት ይለዝባል የማይጨበጠው እሳትም ከብረት ስለተዋሀደ አንጥረኛው ይመተዋል እሳቱን ግን አያገኘውም። መለኮት የተዋሀደው ሥጋ መከራን ተቀበለ በሥጋም ሞተ ፤ ለመለኮት ግን ሕማም ድካም ሞት አይስማማውም፤ ይኸውም መለኮት ከሥጋው አንደተዋሀደ በነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ምርኮን ማረከ ነፍሳትን ነፃ አወጣ ገነትም አስገባቸው ፤መለኮት የተዋሀደው ሥጋ ወደ መቃብር ቢወርድም በሦሥተኛውም ቀን በታላቅ ኃይል በስልጣን ክርስቶስ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ። መልካም በዓል! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 20 12🙏 10👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
🙏 21 6
🩸 "ተወዳጅ ልጅሽን" 🩸 ተወዳጅ ልጅሽን ህማሙን ስታይ ማሰብ ይሳነኛል የአንቺን ስቃይ በእሾህ አክሊል ጉንጉን የቆሰለ ራሱን በብዙ ግርፋት የታመመ አካሉን(፪) በዕፅ መስቀሉ የወረደ ደሙ  የቀራንዮ ግፍ እጅግ ማስገረሙ ደጉ ልጅሽ ታስሮ የፍጥኝ ሲሰቃይ ተሰክቶ ቀረ ዓይንሽ ወደ ሰማይ(፪) ስለመሰቀሉ አይሁድ ሲደሰቱ ሲስቁ ሲያሾፉ ቁማር ሲጫወቱ ሲዘባበቱበት አይንሽ በማየቱ ህሊናሽ ተገርፏል በሀዘን በብርቱ(፪) ብላቴናይቱ የዳዊት ልጅ ማርያም ስለደረሰብሽ ቢነገር አያልቅም ተጠማው ቢላቸው መፃፃ አስጎነጩት መርገም አስወግዶ ቢሰጣቸው ሕይወት(፪) ለመጠጡ እንዲሆን መፃፃ ከሐሞት ሰፍነግን ጨምረው በዘንግ አስጎነጩት ዳዊት በትንቢቱ እንደተነበየው በምግቤ መራራን ጨመሩ እንዳለው(፪) ይኄ ሁሉ ሲሆን ድንግል ተመልክታ መፅናናት ተሳናት በሐዘን ተነክታ ኤሎሄ ኤሎሄ ጌታ ባለ ጊዜ እጅግ ኃያል ነበር የማርያም ትካዜ(፪)     በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 19 7🥰 4🙏 1
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሐሙስ ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ ሀ. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል። የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን ይማልድ የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ (ማቴ 26፤36-46፣ ዮሐ.17) ለ. ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል ። ሕጽበተ እግር፦ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፤ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብሕን ኃጢአት እጠብ ሲሉ ከአገልጋዮቹ ጀምረው በቤተክርስቲያን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ ሐ. የምሥጢር ቀን ይባላል ። ከሰባቱ ምሥጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፤ ይኸውም ‹‹ይህ ስለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ›› ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ‹‹ይህ ስለእናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ›› በማት እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፤ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለውም ጸናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምጻቸውን ዝግ አድርገው፣ በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፤ በቅዳሴውም ጸሎተ ተአምኖ፣ ኑዛዜ አይደረግም፤ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፤ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡ መ. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡ ጸሎተ ሐሙስ ( የፋሲካ እራት) ፦ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ይህ ጽዋዕ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ››በማለቱ ይታወቃል፡፡ (ሉቃ.22፤20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል-ኪዳኑ ፍጻሜዎች፣ ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡ ሠ. የነጻነት ሐሙስ ይባላል። ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ስለሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፡፡›› በማለቱ(ዮሐ.15፤15) ከባርነት የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ በግልጥ ያስረዳናል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት ተላቅቆ፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጐናልና፡፡ ረ. አረንጓዴ ሐሙስ አምላካችን የጸለየበትን የአትክልት ቦታ ወይም ጌቴሴማኒ ለማሰብ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል። ጌታ እንዴት፣ ምን እና ለምን ጸለየ? እንዴት ጸለየ? አምላካችን የምሥጢር ሐዋርያቱን (ዮሐንስ ፣ ያዕቆብ እና ጴጥሮስ ) አምስት ትሕዛዝን (ተቀመጡ ፣ ትጉ ፣ ጸልዩ ፣ ተኙ ፣ ዕረፉ ) በማዘዝ ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰግዶ ጸለየ።(ማቴ፳፮:፴፮-፵፭) ምን ጸለየ? ሦስት ጊዜ ደጋግሞ የጸለየው ጸሎት አንድ ዓይነት ነው ይኸውም:- "አባቴ ቢቻልስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ፣ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።"(ማቴ፳፮:፴፮-፵፭) ለምን ጸለየ? ፩. ምሣሌ ይሆነን ዘንድ ነው። ፪. ፈቃዱን ማስቀደም እንዳለብን እናውቅ ዘንድ ነው። ፫. ወደፈተና እንዳንገባ መጸለይ እንደሚገባ እናውቅ ዘንድ ነው። የጸሎቱ ትርጓሜ ምንድን ነው? ፩. ዓለም እንድትድን እና ክብርን እንድታገኝ ለሞት ተላልፎ እንደሚሰጥ ገልጿል። "ያለ እኔ ሞት የዓለሙ ደኅንነት ያለ እኔ ሐሳር የዓለሙ ክብር አይቻልም እንጂ የሚቻልስ ከሆነ ይህ ጽዋዓ ሞት ይለፍልኝ። ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይደረግ እላለሁ እንጂ የኔ ፈቃድ ይደረግ አልልም።" (ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱) ፪. ሞት እንዲቀርልን እንደ ሞተ ገልጿል። "በኔ ሞት የዓለም ደኅንነት በኔ ኃሣር የዓለም ክብር የሚቻልስ ከሆነ እኔ ከሞትሁላቸው ከኔ ሞት የተነሳሣ ይህ ጽዋዕ ሞት ይቅርላቸው።(ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱) ፫. አብነት ይሆነን ዘንድ ሞትን እንደሚቀምስ ገልጿል። " ከኔ ለምዕመናን ይለፍላቸው ። እኔን አብነት አድርገው ይሙቱ ። ነገር ግን የኔ ፈቃድ ካንተ ፈቃድ ልዩ ሁኖ የኔ ፈቃድ ይሁን አልልም። የኔ ፈቃድ ካንተ ፈቃድ ጋራ አንድ ነውና ያንተ ፈቃድ ይሁን እላለሁ እንጂ። " (ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱) በዚህ ዕለት በወንጌላት የተመዘገቡ ድርጊቶችን ቀጥለን እንመልከት፡ ሀ. የፋሲካ ዝግጅት የተደረገበት ዕለት ነው ። ዝግጅቱ በሦስቱ ወንጌላት ላይ ተመዝግቧል፡፡ (ማቴ.26፤17-19፣ ማር 14፤1-16፣ ሉቃ.22፤6-13) ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ነው፤ ይኸውም እሥራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እሥራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይንም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፤ ሙሴም ለሕዝቡ ነገረ፤ ሁሉም እንደታዘዙት ፈጸሙ፤ መቅሰፍተ ከእግዚአብሔር ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የየግብጻውያን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት የእሥራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ ማለፉን ለማመልከት ነው፡፡ (ዘዳ.12፤1-13) በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እሥራኤላውያን በመጀመሪያ ወራቸው በዐሥራ ዐራተኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ ሀገራችንም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡ በአንጻሩም ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስ ሞተ በኵር የተባለ ሞተ ነፍስ ቀርቶልናልና፡፡ ‹‹ፋሲካችንም ክርስቶስ ነው፡፡›› (1ኛ ቆሮ.5፤6፣ 1ኛ.ጴጥ.1፤10) ለ. በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ለደቀመዛሙርቱ ረጅም ትምህርት አስተምሯል። ምሥጢረሥላሴየሦስትነት ትምህርት፤ ምሥጢረሥጋዌ (የአምላክ ሰው መሆን)፤ በዮሐ.14፤16የሚገኘው በጠቅላላ የዚህ ዕለት ትምህርት ነው፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎች ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንና የዳግም ምጽአቱ ነገርነው፡፡ እነዚህም በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳን፤በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲችል በረጅም ትምህርትእንዲረዱት አድርጓል፡፡ ተማሪዎቹን እሱ እያስተማራቸው ሳለ ያገባቸውን እየጠየቁ ተረድተዋል፡፡ ከዚህም እያንዳንዳችን በቤተክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቆ መረዳት እንደሚገባን እንማራለን፡፡ ሐ.ይህ ዕለት ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለ ጌታ ሆይ፣ መምህር ሆይ ብሎ በመሳም አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነዉ።
Показати все...
👍 17🙏 5 4
ጭፍሮቹም በዚሁ ዕለት ሌሊት የክብር ባለቤት የሆነውን ጌታችንን ይዘው ወደፊት፣ ወደኋላ እየጐተቱ፣ እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወስደውታል። መዝሙረ ዳዊት ምንባባት በአንድ ሰዓት፡- "አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ ፤ በልቡ ግን ሰልፍ ነበረ ፤ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ ፤ እነርሱ ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው" (መዝ፶፬(፶፭)፡፳፩) በሦስት ሰዓት፡- "የጻድቅን ነፍስ ያደቡባታል፤ በንጹህ ደምም ይፈርዳሉ፡፡"(መዝ፺፫(፺፬):፳፩) በስድስት ሠዓት፡- "የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና በዙሪያው ፍርሃት ነበረ በላዬ በአንድነት በተሰባሰቡ ጊዜ ፤ ነፍሴን ለመንጠቅ ተሰባሰቡ፡፡"(መዝ፴ (፴፩):፲፫ በዘጠኝ ሰዓት፡- "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ፤ የሚያሳጣኝም የለም ፤ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፡፡" መዝ፳፪(፳፫):፩-፪ ኅጽበተ እግር ሲጀመር ደግሞ "በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለው እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለው፡፡" (መዝ፶:(፶፩):፯) በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት፡- "ከዚህ በኋላ የእግር እጥበት ሥርዓት ነው ፤ ዲያቆን ሁለት ኩስኩስቶች ያቅርብ በውስጣቸውም ውኃ ይምላባቸው አንዱ ለእጅ መታጠቢያ እንዲሆን ካህኑም እስከ መጨረሻው ጸሎተ አኮቴት ይበል ፤ ጸሎተ ዕጣኑንም ደግሞ ዕጣንን ያሳርግ ፤ ስለ ሰላም ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስለ ማኅበር ይጸልይ፡፡ ሕዝቡም ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁንዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ይበሉ፡፡ አነ ዘበሰማያትም ይበልሉ ፤ ኀምሳኛውንም የዳዊትን መዝሙር ይበሉ፡፡" (ግብረ ሕማማትገጽ፭፻፵፪) "ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ይነሱ አርባ አንድ ጊዜ ኪራላይሶን ይበሉ ካህኑም መስቀል ይዞ ውኃውን ሦስት ጊዜ አሐዱ አብ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) እያለ ሦስት ጊዜ ውኃውን ይባርክ፡፡" (ግብረ ሕማማት ገጽ ፭፻፶፱) "ከዚህ በኋላ ካህኑ እንደ ሥርዓቱ ኅጽበተ እግርን ያድርግ (ይፈጽም) ከዚህ በኋላም ጥቁር ልብስ ለብሰው ሥርዐተ ቅዳሴውን ይጀምሩ የቃጭል ድምጽንም አያሰሙ፡፡" (ግብረ ሕማማት ገጽ፭፻፷፩) በአሥራ አንድ ሰዓት፡- "በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬም የተረፈ ነው" (መዝ፳፪(፳፫):፭-፮) የአይሁድ ካህናት ያለበደል እና ያለጥፋት ንጹውን ክርስቶስን ለመስቀል ሞት እንዲደርስ በጭካኔ በዕለተ ሐሙስ ከሌሊቱ 3፡00 ጀምሮ ብዙ መከራ አደረሱበት ፤ እጅጉን ተሰቃየ ፤ እያዳፉ አንዳች ሳይናገር አሰቃዩት ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢት መነጽር የተመለከተውን የጌታችንን ስቃይ እንዲህ ሲል ያመጣዋል፡- "ተጨነቀ ተሠቃየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?ከክፉዎቹም ጋር መቃብሩን አደረጉ..."(ኢሳ፶፫:፩-፰) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
6👍 5🙏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሐሙስ ✅የምሥጢር ቀን ✅የነጻነት ሐሙስ ✅አረንጓዴ ሐሙስ አምላካችን የጸለየበትን የአትክልት ቦታ ወይም ጌቴሴማኒ ለማሰብ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሐሙስ ✅ሕጽበተ ሐሙስ ✅ጸሎተ ሐሙስ ይባላል ✅የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
6
🩸በዕፀ መስቀል ላይ🩸 በዕጸ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ/2/  አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ  አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ                 አዝ መስቀል አስይዘው ኪርያላይሶን  ወደ ጎልጎታ               "  " ሲገርፉህ ሲያዳፉህ       "  " ስትንገላታ                 "  "                     አዝ ያንን አቀበት ኪርያላይሶን  ያንን ዳገት        "  " ጀርባህ ተገርፎ  "  " ስትቃትት          "  "              አዝ አንተን እያዩ   ኪርያላይሶን  ሴቶች ሲያለቅሱ  "  " እናቶች ቀርበው   "  " ላብህን ዳበሱ     "  "               አዝ መስቀል አስይዘው ኪርያላይሶን  እንዲያ ሲያዳፉህ      "  " የቀሬናው ሰው          "  "            ስምኦን አገዘህ         "  " በዘማሪት ማርታ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
17👍 13😢 9🥰 4
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ረቡዕ በዚህች ዕለት ያስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሰጠውና ሌሎችም ይታሰባሉ። በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አመዘጋገብ መሠረት በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ነገሮች ተፈጽመዋል፦ ፩. ምክረ አይሁድ ይባላል የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤ ፪. የመልካም መዓዛ ቀን ይባላል ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡ ፫. ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹ሲኒሃ ድርየም› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማቷል፡፡ ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ይሁዳ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ፡፡ ይህ ታሪክም በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ በሚከተሉት ምዕራፎች ተመዝግቦ እናገኛዋለን፤ ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡ ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን! ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
🙏 12👍 8 2👏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ረቡዕ ✅ምክረ አይሁድ ✅የመልካም መዓዛ ቀን ✅ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
8🙏 5😢 2
🩸"ጌታ ሆይ" 🩸 ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/ የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል የሄዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/ ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ/2/ እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለም ጌታ የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/ ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/ በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል ሃሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/ ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/    በሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
😢 22👍 15 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ማክሠኞ ✅የጥያቄ ቀን ✅የትምህርት ቀን @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
9😢 2
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ማክሠኞ በዚህ ዕለት አምላካችን ለጥያቄዎች በሙሉ መልስ የሰጠበት እና በስፋት ያስተማራቸው ትምህርቶች የሚታሰቡበት ዕለት ነው። ፩. የጥያቄ ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት አምላካችን ስለ ሥልጣኑ በካህናት አለቆችና በሕዝብ አለቆች"በምን ሥልጣንህ እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?"(ሉቃ፳:፩-፵፩) የሚል ጥያቄ ለፈተና የተጠየቀበት ዕለት በመሆኑ የጥያቄ ቀን ትባላለች፡፡ ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:- ፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል። ፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር። ፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል። ፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል። ፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩) መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል። ፪. የትምህርት ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች ፩. የአምልኮ መልክ ካላቸውተጠንቀቁ ፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ ፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ ፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ ፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪) የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭) በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬) በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯) በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩) በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 19👏 8 5
Показати все...
👍 22 2🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሰኞ ✅መርገመ በለስ ✅አንጽሖተ ቤተ መቅደስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
11👍 6
🩸"ዓለምን ለማዳን"🩸 ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው /፪/ ጌታችን ተሰቅሎ ሲያዩት መላዕክት በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው አምላኩን እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው /፪/     አዝ===== ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም ለጠላቱ የሚሞት በጭራሽ አይኖርም ጠላቶቹ ሳለን ለእኛ የሞተው ክርስቶስ ልዩ ነው ወደር የሌለው /፪/     አዝ===== እውርን ቢያበራ የሞተን ቢያነሳ በመመስገን ፈንታ ሆነበት አበሳ ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት ተከሶ ቀረበ ከጲላጦስ ፊት /፪/     አዝ===== የጸሎተ ሐሙስ ዕለት እራት የሆነው አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ፍቅር አስገድዶት ለእኛ የሞተው መልካሙ እረኛችን መድሃኒዓለም ነው /፪/ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
28👍 11🙏 4
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሰኞ ፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው። አንድምታ፡ ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው ☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ ☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡ ☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም "በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ ፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው። ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫) ምስጢሩ :- ☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 18🙏 7 4
03:42
Відео недоступнеДивитись в Telegram
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!! ያዳምጡት! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 24 11🥰 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
11
እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው??? @Ethiopian_Orthodox በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ ኪርያላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዚእነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡ ፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ ናይናን-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ እብኖዲ-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው። ታኦስ-የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ ማስያስ-የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው። ትስቡጣ-«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ – ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ-የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ @Ethiopian_Orthodox የ፵፩/41 ስግደት ምን እየተባለ ይሰገዳል? አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ ፵፩/41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ:- ፲፪/12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ ኪርያላይሶን ፭/5 ጊዜ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ(አምስቱ የጌታ ችንካሮች) እነዚህም ቢደመሩ ፵፩/41 ይሆናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
🙏 23👍 20 3🔥 2😢 1
🩸 ሰሙነ ሕማማት 🩸   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለተ ትንሣኤ በፊት  ያለውን ሳምንት "ሰሙነ ሕማማት" በማለት ታከብረዋለች። "ሕማማት" የሚለው ቃል "ሐመ"  ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን የዚህ ስያሜ  መነሻም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት  ከአዳም እስከ ክርስቶስ የነበረው የዓመተ ፍዳ  የዓመተ ኩነኔ ወቅትም የሚታሰብበት ስለሆነ "ሰሙነ ሕማማት" ተብሏል።   በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን  በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ  ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል  የሚያዘክረውን  ምዕራፍ  ከቅዱሳት  መጻሕፍት በማንበብና  በመጸለይ  ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ  ያሬድ በመጨረሻው  ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ  ላይ  የተፈጸመውን  ነገረ  መስቀል  በተመለከተ  ያዘጋጀውን  መዝሙር  ይዘምራሉ፤  አብዝተው  ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡   ጌታችንና  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ሕማማትን መቀበሉ ስለምን ነው ቢሉ፡- ☞ፍቅሩን  ለመግለጽ፡-  ለፍጥረቱ  ይልቁንም  ለሰው  ልጆች ያለውን  ፍቅሩን  ይገልጽ  ዘንድ(ዮሐ  ፫÷፲፮)  ምንም  በደል ሳይኖርበት  ነፍሱን  አሳልፎ ሰጠ(ዮሐ  ፲፭÷፲፫) ☞የኃጢአትን ፍዳ ከባድነት ለማሳየት፡- እርሱ  ጻድቅና ንጹህ ሆኖ ሳለ ሰውን ወዶ ይህን ያህል  መከራ ከተቀበለ ሰው ኃጢአት በመሥራት  ቢመላለስ  የኃጢአትን  ውጤት  ከባድነት  ያስተምረናል፡፡  ራሱ  ጌታችንም  ከጲላጦስ  ግቢ እስከ ቀራንዮ አደባባይ መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ  ላለቀሱለት የኢየሩሳሌም  እናቶች  <<በእርጥብ  እንጨት የሚያደርጉ ከሆነ በደረቀውስ እንዴት ይሆን>> በማለት ገልጾለታል፡፡ (ሉቃ  ፳፫÷፳፪) ☞ቤዛ ለመሆን፡- በኦሪት ዘመን ሰዎች  ለሠሩት  ኃጢአት ኃጢአታቸውን  ለማስተሰርይ  ነውር  የሌለበትን  በግ  ቤዛ እንዲሆናቸው መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይህ ግን ከአዳም የተሰወረውን ኃጢአት ማስቀረት ስላልቻሉ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሁኖ መጣ <<እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ>>(ዮሐ ፪÷፳፮) ☞እርግማናችንን  ለማስቀረት፡-  <<በእንጨት  የሚሰቀል  ሁሉ  የተረገመ  ነው  ተብሎ  ተጽፏልና  ክርስቶስ  ስለ እኛ እርግማን  ሆኖ  ከሕግ  እርግማን  ዋጀን>>(ገላ  ፫÷፲፫)    በማለት  ቅዱስ  ጳውሎስ  እንደጻፈው  እርግማናችንን  ተሸክሞ ሕማማትን  መቀበሉ  የቀድሞው  ኃጢአት  ምንም  ያህል  ከባድ  ቢሆን  በታላቅ  መስዋዕትነት  እንዳስቀረልን ሊያስተምረን ነው፡፡ (ዘዳ  ፳፩÷፳፫) ☞የድኅነታችንን ክቡርነት /ውድነት/ ሊያስረዳን ፡- ድኅነታችንን  የእግዚአብሔር ልጅ ደሙን እስኪያፈስለት ድረስ እጅግ ውድ መሆኑን ሊያስተምረን፡፡ (ራዕ ፭÷፱) @Ethiopian_Orthodox   ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም  ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡  በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት : ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው:: በመስቀል መባረክ፣ ማማተብ፣ መሳቅ፣ መሳሳም፣ ከሴት ጋር መገናኘት(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 593)፣ ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም፣ ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም:: "እግዚአብሔር ይፍታህ" አይባልም(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600)፤ ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት(12፣21 እና 29) እንኳ ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው፤ መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው።(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 578)    ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም። ጸሎቱ ውዳሴማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ሕማማትና መዝሙረ ዳዊት ናቸው። የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም። ስናጠቃልለው የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡ 1.  እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል፣ መሳሳም 2.  ሩካቤ ሥጋ ማድረግ 3.  መስቀል ማሳለም እና መሳለም 4.  ክርስትና ማስነሣት 5.  ለሙታን ፍትሐት ማድረግ 6.  ክህነት መስጠት 7.  የላመ የጣመ ምግብ መመገብ 8.  መሳቅ መጫወት መጨፈር 9.  አብዝቶ ጠግቦ መመገብ 10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሣዕና ይከናወናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች: ፩.  አለመሳሳም ፡- ከላይ እንዳየነው በሰሙነ  ሕማማት  የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  እምነት  ተከታዮች መስቀል  እንደማይሳለሙት  ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን  ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ  አልሰመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ  እንስቀለው ፤እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡  በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ ፪. ሕፅበተ  እግር፡- ጌታ በፍጹም ትህትና  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  ያጠበበት፣  ከሐዋርያት  ጋር  ግብር  የገባበትና የክርስትና  ህይወት  ማሕተም የሆነውን  ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት  ነው። ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ  ዕለተ  እናንተ  ለወንድማችሁ  እንዲሁ  አድርጎ  ለማለት  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  በማጠቡ  ምክንያት  የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ፫. ጉልባን እና ቄጠማ ፡- ጉልባን ከባቄላ ክክ፣  ከስንዴ  ወይንም  ከተፈተገ  ገብስ  ጋር  አንድ  ላይ  ተቀቅሎ  የሚዘጋጀና የጸሎት  ሐመስ  እለት  የሚበላ  ንፍሮ  ነው፡፡  የጉልባን  ትውፊት  እስራኤላውያን  ከግብጽ  ተሰደው  በሚነጡበት  ጊዜ በችኮላ  ስለነበር  አቡክተው  ጋግረው  መብላት  ያለመቻላቸውን  ሁኔታ  ያመለክታል፡፡  ያን  ጊዜ  ያልቦካው  ሊጥ  እያጋገሩ ቂጣ  መብላት  ንፎሮም  ቀቅለው  ስንቅ  መያዝ  ተግባራቸው  ነበር፡፡  ይህን  ለማሰብ  በሰሙነ  ሕማማት  ቂጣና  ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ [በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በስፋት የምናየው ይሆናል።] ቄጠማ (ቀጤማ)፡-  በቀዳም  ስዑር  ቀሳውስቱን  ዲያቆናቱ  ቃጭል  /ቃለ  አዋዲ/  እየመቱ  "ገብረ  ሰላመ  በመስቀሉ ትንሳኤሁ  አግሃደ" የሚለውን  ያሬዳዊ  ዜማ  በመዘመር  ጌታ  በመስቀሉ  ሰላምን  እንደሰጠ  እና  ትንሳኤውንም እንደገለጠልን  በማብሰር  ቄጤማውን  ለምእመናን  ይሰጣሉ፡፡  ምእመኑም  ለቤተ  ክርስቲን  አገልግሎት  የሚውል  ገጸ በረከት  ያቀርባሉ  ቀጤማውንም  በራሳቸው  ያስራሉ፡፡  ይህም  አይሁድ  ጌታችንን  እያሰቃዩ  ሊሰቅሉት  ባሉ  ጊዜ  የእሾህ አክሊል  ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ  እለት  ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለምዕመናን ትልቅ ብስራት ነው።
Показати все...
👍 37 12🙏 4😱 2😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፩ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 11 6🙏 5
፬. በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ የስቅለቱ  መታሰቢያ  ነው፦  ምእመናኑ  በሰሙነ  ሕማማት  የሰሩትን  ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን  በወይራ  ቅጠል  ትከሻቸውን  እየጠበጠቡ  ቀን  ከሰገዱት  ስግደት  በተጨማሪ  ሌላ  ስግደት  ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ  ምሳሌ ነው፡፡  ጥብጠባው የሚደረግለት  ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ፭. አክፍሎት፡-  በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ  ከስግደት  በኋላ  ምእመናን  በየቤታቸው  ጥቂት  ነገር  ለቁመተ  ሥጋ ቀምሰው  እስከ  እሁድ  /የትንሳኤ  በዓል/  ይሰነብታሉ፡፡  ይህ  አክፍሎት  ይባላል፡፡  ከዓርብ  እስከ  ቅዳሜ  ሌሊት  ለእሁድ አጥቢያ  ማክፈል  የብዙዎች  ነው፡፡  አንዳንዶች  ግን  ከሐሙስ  ጀምረው  ያከፍላሉ፡፡  ይህም  እመቤታቸን  ያዕቆብ  እና ዩሐንስ  የጌታን  ትንሳኤ  ሳናይ  እህል  ውኃ  አንቀምስም  ብለው  እስከ  ትንሳኤ  መቆየታቸውን  ተከትሎ  የመጣ  ትውፊት ነው፡፡ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ዕለት የሚካሄደው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት እንደሚከተለው በምስል ቀርቧል: @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
11👍 8🙏 3👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፪ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 20 8🙏 6
"ሰላምሽ ዛሬ ነው" ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/      አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/   አዝ ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/   አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
🥰 20👍 12 12
“ሆሣዕና” በዘማሪ አቤል ተስፋዬ
Показати все...
16🥰 4👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
👍 15 4