cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Більше
Рекламні дописи
30 159Підписники
+7824 години
+2117 днів
+55130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
የተዋሕዶ ልጆች

የሰሙነ ሕማማት ድንቅ መጽሐፍ በብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ "Thine is The Power and the Glory" አማርኛ አቻ ትርጉም: "ለከ ኃይል" @Ethiop_tewahido @Ethiop_tewahido @Ethiop_tewahido

👍 14 2🔥 1
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሰኞ ፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው። አንድምታ፡ ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው ☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ ☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡ ☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም "በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ ፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው። ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫) ምስጢሩ :- ☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 12🙏 5 1
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሰኞ ✅መርገመ በለስ ✅አንጽሖተ ቤተ መቅደስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
10👍 2
🩸"ዓለምን ለማዳን"🩸 ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው /፪/ ጌታችን ተሰቅሎ ሲያዩት መላዕክት በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው አምላኩን እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው /፪/     አዝ===== ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም ለጠላቱ የሚሞት በጭራሽ አይኖርም ጠላቶቹ ሳለን ለእኛ የሞተው ክርስቶስ ልዩ ነው ወደር የሌለው /፪/     አዝ===== እውርን ቢያበራ የሞተን ቢያነሳ በመመስገን ፈንታ ሆነበት አበሳ ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት ተከሶ ቀረበ ከጲላጦስ ፊት /፪/     አዝ===== የጸሎተ ሐሙስ ዕለት እራት የሆነው አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ፍቅር አስገድዶት ለእኛ የሞተው መልካሙ እረኛችን መድሃኒዓለም ነው /፪/ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
25👍 7🙏 2
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!! ያዳምጡት! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 24 10🥰 3
Показати все...
10
እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው??? @Ethiopian_Orthodox በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ ኪርያላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዚእነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡ ፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ ናይናን-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ እብኖዲ-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው። ታኦስ-የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ ማስያስ-የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው። ትስቡጣ-«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ – ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ-የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ @Ethiopian_Orthodox የ፵፩/41 ስግደት ምን እየተባለ ይሰገዳል? አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ ፵፩/41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ:- ፲፪/12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ ኪርያላይሶን ፭/5 ጊዜ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ(አምስቱ የጌታ ችንካሮች) እነዚህም ቢደመሩ ፵፩/41 ይሆናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
🙏 17👍 10 2🔥 2
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፩ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 11 6🙏 4
፬. በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ የስቅለቱ  መታሰቢያ  ነው፦  ምእመናኑ  በሰሙነ  ሕማማት  የሰሩትን  ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን  በወይራ  ቅጠል  ትከሻቸውን  እየጠበጠቡ  ቀን  ከሰገዱት  ስግደት  በተጨማሪ  ሌላ  ስግደት  ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ  ምሳሌ ነው፡፡  ጥብጠባው የሚደረግለት  ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ፭. አክፍሎት፡-  በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ  ከስግደት  በኋላ  ምእመናን  በየቤታቸው  ጥቂት  ነገር  ለቁመተ  ሥጋ ቀምሰው  እስከ  እሁድ  /የትንሳኤ  በዓል/  ይሰነብታሉ፡፡  ይህ  አክፍሎት  ይባላል፡፡  ከዓርብ  እስከ  ቅዳሜ  ሌሊት  ለእሁድ አጥቢያ  ማክፈል  የብዙዎች  ነው፡፡  አንዳንዶች  ግን  ከሐሙስ  ጀምረው  ያከፍላሉ፡፡  ይህም  እመቤታቸን  ያዕቆብ  እና ዩሐንስ  የጌታን  ትንሳኤ  ሳናይ  እህል  ውኃ  አንቀምስም  ብለው  እስከ  ትንሳኤ  መቆየታቸውን  ተከትሎ  የመጣ  ትውፊት ነው፡፡ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ዕለት የሚካሄደው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት እንደሚከተለው በምስል ቀርቧል: @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads:

https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

10👍 7🙏 3👏 1
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፪ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Показати все...
👍 20 8🙏 5