cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Central Ethiopia Regional Health Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ 🔵 https://m.facebook.com/centralethiopiarhb 📞 📩

Більше
Рекламні дописи
3 612
Підписники
+1024 години
+107 днів
+9330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የጤና ፋይናነስ ስርዓት አቅምን ለማሳደግ እና የተለያዩ የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን ማምጣት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ _____ ሁሉን አቀፍ የጤና ፋይናንሲንግ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ የጤና አገልግሎት ፍትሀዊነት ጥራት እና ተደራሽነት ማረጋገጥ ላይ ለመስራት የጤና ፋይናንሲንግ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ። የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ዶክተር አስናቀ ዋቅጅራ በጤና ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደተናገሩት በሀገራችን ያለውን የጤና ፋይናነስ ስርዓት አቅም ለማሳደግ እና የተለያዩ የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ ለማስገባት አንዲቻል ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን ማምጣት፣ ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች ብቃት እና ክህሎት ያላቸው፣ ተገቢውን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ያዳበሩ ባለሞያዎችን ለማፍራት ከምክክር መድረኩ ብዙ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ዶክተር አስናቀ ዋቅጅራ ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ በፍኖት ፕሮጀክት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተሰሩ ጥናቶች በሚጠቁሙት መሰረት ለውጥ አምጪ ስራዎችን ለመስራት የባለሞያዎች አቅም ግንባታ እና የፋይናንስ ዘርፉን መዋቅር የማጠናከር ስራ በመረጃ ላይ የተመሰረት የፋይናስ ውሳኔ አሰጣጥ ስርአት ከመዘርጋት አንጻር የጤና ሚኒስቴር በዘርፉ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዶክተር አስናቀ በቀጣይም የዘርፉ ባለሞያች ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን በማምጣት ለዘርፉ መጠናከር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሲስተር ትዕግስት ተፈራ በኦሮሚያ ክልል በአሁኑ ወቅት ያለውን የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል የተሰሩ ስራችን አንስተው ዘርፉን በእውቀት እና በአቅም ላይ የተመሰረት እንዲሆን ለማድርግ እንዲሁም የጤና ፋይንስ አሰራርን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም የጤና ሚኒስቴር እና የአጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ጴተር ቤርማን በበኩላቸው የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል በግልጽ በመነጋገር በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የጤና ፋይናንስን ልምድ ለጤናው ዘርፍ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተው በኢትዮጰያ ያለው የጤና ፋይናንሲንግ በመንግስት እና በአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን በመሆኑ የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል አለም አቀፍ ልምዶችን መቀመር እና በትኩረት መስራት እንዲቻል ዘርፉ በሚፈልገው እውቀት ታግዞ ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በዚህ መድረክ የጤና ፋይናንሲንግን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በሀገራችን ያለውን የማዋቅር እና የሰው ሀይል አደረጃጀት ምን እንደሚመስል የሚዳስስ ጥናት በአስራ አራቱም ክልሎች ባሉ የጤና ፋይናንስ፣ እቅድ እና ክትትል የስራ ክፍሎች ላይ እንዲሁም በፌዴራል ደረጃም በተመረጡ ስድስት የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍኖት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የዳሰሳ ጥናት የተሰራ ሲሆን የጤና ፋይናንስ እንዴት እንደተደራጀ፣ ምን ያክል የሰው ኃይል አለው ምን ምን ስራዎችን ያከናውናሉ፣ የጤና ስራዎችን ለመስራት ያላቸው ሞያዊ እውቀት በሚመለከት እና ስራዎችን በሚሰሩበት ግዜ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ይሰራሉ ወይ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መነሻ በማድርግ የተሰራው ጥናትም በመድረኩ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
Показати все...
👍 2
1
ግንቦት 28/2016 ዓ/ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተቋሙን የ10 ወራት አፈፃፀም በዛሬው እለት በወራቤ ዩኒቨርስቲ እየገመገመ ይገኛል ። ጤና ኢንስቲትዩቱ የ2016 በጀት ዓመት የአስር ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የቢሮው ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወራቤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ዉስጥ እያካሄደ ነው። ኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጴጥሮስ የአፈፃፀም ሪፖርቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በጤናው ዘርፍ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል ባለፉት አስር ወራት የተሰሩ ተግባራትንና ጉድለቶች ላይ መምከር እንደሚገባ ገልፀዋል። የቢሮው የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተሞክሮ ሊቀመርባቸው የሚገቡ ተግባራት መከናወን የተቻለ መሆኑን ጠቅሰው ድንገተኛ አደጋዎች ላይ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠንካራ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በክልሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መበራከታቸውን ገልፀው በዋናነትም የኮሌራ፣ የኩፍኝ እና የወባ ወረርሽኞች እንዲሁም የጎርፉ አደጋ መኖሩን ተከትሎ ችግሩን ለመቀነስ እጅግ ጠንካራ ተግባራት መከናወናቸውን እና የላብራቶሪ ተግባራት ተደራሽነቱ ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል ። የጥናት እና ምርምር ስራዎች በጥሩ መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ ያወሱት ዳይሬክተሩ የመረጃ ስርዓታችንም ለሌሎች ምርጥ ተሞክሮ እንደሚሆን ለማስቻል በጥራት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ። በአጠቃላይ ይህ መድረክ በቀሪ ጊዜያት ዉጤታማ ስራ እንድንሰራ ያግዘናል ብለዋል ዳይሬክተሩ ። በጤናው ዘርፍ ለማህበረሰቡ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የዘርፉ ባለሙያዎች የሰሯቸውን ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ዉይይት እየተደረገባቸው ይገኛል ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ
Показати все...
👍 1
በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ በማጽደቅ ተጠናቋል። ___ በጄኔቫ ስውዘርላንድ የአባል አገራትን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ እና ሌሎች የመፍትሄ ሀሳቦችን ( Resolutions) በማጽደቅ ተጠናቋል። ሃገራችን የአፍሪካ ቡድንን በማስተባበር የጋራ አቋም እንዲያዝና በቀረቡት ማሻሻያዎች ውስጥ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሳደግ ለታዳጊ ሃገራት ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ማሻሻያዎች እንዲጸድቁ ከፍተኛ አስተዋጾዖ ያበረከተች ሲሆን የሃገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፉና በተለይም በአፍሪካ ሃገራት ላይ የንግድና ትራንስፓርትና ኢኮኖሚ ረገድ አስገዳጅ ግዴታዎች የሚጥሉ ሃሳቦች እንዳይካተቱ ማድረግ ተችሏል፡፡ ከ300 በላይ ፕሮፓዛል በአባል አገራት ቀርቦ ማሻሻያ ተደርጎ የፀደቀዉ ዓለምአቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) በዋናነት በህብረተሰብ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ወቅት የሀገራት ዝግጁነትና ምላሽ አሰጣጥ አቅምን ለማሻሻል እንዲሁም አለም አቀፍ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነዉ። በዚህ መሰረት ተሻሽሎ የጸደቀው የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋና ወረርሽኝ ሲከሰት ፍትኃዊ የሆነ የህክምና ግብዓት ተደራሽነት እንዲኖርና መሰረታዊ የሆኑ የህብረተሰብ ጤና አቅም ለማዳበር የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ በተለይም ለታዳጊ ሃገራት ለማሰባሰብ እንዲቻል አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ መሆኑም ተገልጿል። በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ የአፍሪካ አባል ሀገራትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማሻሸያ ተደርጎበት የፀደቀዉ ይህ ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ አገራት ከተባበሩና በጋራ ከሰሩ ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆም እንደሚቻል አይነተኛ ማሳያና ምስክርነት መሆኑን በማበከር ደንቡ ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ወረርሽኝ ቅኝትና ቁጥጥር ፣ዝግጁነት እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እጅጉን እንደሚያግዝ ገልጸዋል። ይህ እዉን እንዲሆን ላለፉት 2 ዓመታት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል። በሌላ በኩል አገራት ለህብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ፣ እንዲሁም ቀጣይነት ያለዉ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲኖራቸዉ የሚያግዙ ሌሎች የመፍትሄ ሀሳቦችና ውሳኔዎች (Resolutions) በጉባኤዉ ቀርበዉ ፀድቀዋል። በስዊዘርላድ ጄኔቫ ሲካሄድ በነበረዉ 77ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ የተሳተፈዉ የኢትዮጵያ ልዑክም ወደ አገር ውስጥ የተመለሰ ሲሆን የ 155ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በክብርት የጤና ሚኒስትሯና የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ተሳትፎ እየተደረገበት ይገኛል፡፡
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ዓመት የሚጠበቀው ላሊና የተሰኘ የአየር ንብረት ለውጥ ለዓለማቀፍ የአየር መቀዝቀዝ ሚና እንደሚኖረው አስታወቀ። የ«ላ ሊና »መከሰት ለወራት የዘለቀውን ሙቀት መጠን ሊቀንስ እንደሚችል መተንበዩን የተመድ የአየር ትንበያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ከጎርጎርሳውያኑ 2023 አጋማሽ ጀምሮ ኤል ኒኖ ያስከተለው የዓለም ሙቀት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አስከፊ የአየር ሁኔታ እንደከሰት አድርጓል ያለው ዘገባው የ«ላ ሊና» የዓየር ለውጥን ተከትሎ መቀዛቀዝ እያሳየ መምጣቱን ገልጿል። በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ውስጥም እመርታዊ ለውጥ ሊያሳይ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት ተንብዪዋል። ትንበያው እንደሚያሳየው ምንም እንኳ በ«ላ ሊና» ክስተት ሙቀቱ በጊዜያዊነት መቀዛቀዝ ቢያሳይም የሰው ልጅ በሚያስከትለው የአየር ንብረት ለውጥ መዘዝ የዓለም ሙቀት እየጨመረ መሄዱ እንደማይቀር ነው። ይህንኑ ተከትሎም የተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ወቅቱን ላልጠበቀ ዝናብ እና ሙቀት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ነው ዘገባው ያመለከተው። የውቅያኖስ አካባቢዎችን ሙቀት እንደሚቀንስ ተስፋ የተጣለበት «ላ ኒና » በዋናነት ከነፋስ፣ ከዝናብ እና ከከባቢ አየር ግፊት ለውጥ ጋር ተዳምሮ በሞቃታማው የፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢዎች ውስጥ ያለውን የሙቀት መጠን እንደሚያቀዘቅዝ ይጠበቃል። የመንግስታቱ ድርጅት ዘገባ እንደሚያመለክተው ላ ሊና ከፊታችን ከሐምሌ እስከ መስከረም ባሉ ወራት የአየር ሁኔታዉን 60 ከመቶ እንዲሁም ከነሐሴ እስከ ህዳር ባሉ ወራት ደግሞ 70 በመቶ የመከሰት ዕድል አለው።
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram