cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ተዋህዶ ሃይማኖቴ

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የገሀነም ደጆች አያናውጧትም እ...ና...ታ...ች...ን አ...ት...ታ...ደ...ስ...ም፡፡

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
1 901
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

​​+++ምን ሰጡህ ይሁዳ+++ ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
Показати все...
ጌታችን ለወንበዴው «በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ» የሚል ልመና «እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ» ብሎ ወዲያውኑ መልሰ ሰጠ። በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው። በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግሥት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ፣ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት። «ከቁጣ የራቀ ምሕረቱ የበዛው» አምላክ ክፉ ሥራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል። "የራበው ሰው ለምግብ፣ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል።" ስለዚህ ነው ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" ያለው፤ ይህን ምሕረት ተስፋ አድርገን "ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንንት በኃጢያት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ» እያልን እንጸልያለን። (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ) #{ሕማማት መጽሐፍ ገጽ 354} @Tewahdo_Haymanote @Tewahdo_Haymanote
Показати все...
✍ ቤተ ክርስቲያን ሆይ ÷ የክብርሽና የልዕልናሽ ፀሐይ እንደ ትላንቱ ሁሉ÷ ዛሬም አይጠልቅም!!
Показати все...
ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት "የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም" ማለታቸውን የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ገልጾልናል። ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ በላይ ናት። @And_Haymanot @And_Haymanot_bot
Показати все...
✝የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ✝ "ያልተሟሸ ሸክላና ሰንበት ትምህርት ቤት ያልገባ ወጣት አንድ ናቸው።" ብፁዕ አቡነ ሰላማ ✍ እነሆ የአሳሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል #መሠረት_ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት #የ40ኛ_ዓመት_የልደት_በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜ 1-3 2011 ዓ/ም ድረስ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተዘጋጅቷል እርሶም ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ የእግዚአብሔር ቃል ይሰሙ ዘንድ ተጋብዘዋል በእለቱም፦ ☞ መጋቢ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ ☞ ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ ☞ ዘማሪ ቶማስ {መሰንቆ}... ተጋብዘዋል በመሆኑም የነፍሶን ማዕድ ተመግበው የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ልደት አብረን እናከብር ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን። #አሳድገሽኛል_ቤቴና_ውበቴ #አልለይም_ካንቺ_እስከ_እለተ_ሞቴ #የፀጋው_ግምጃ_ቤት_ክብሬና_ማዕረጌ #ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የዘላለም_ቤቴ #ሰንበት_ትምህርት_ቤት_ክብሬና_ውበቴ ✞ የአባቶቻችንን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ይጠብቅልን!!!✞ አሜን!!! ✞✞✞
Показати все...
ምሥጢረ ደብረታቦር በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ › ቅዱስ ጴጥሮስ ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8 በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡ ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ? መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ትንቢት “ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ” ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12 ምሳሌ ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር›/መሳ 4.1-3/ ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡ እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡ ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡ እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/ እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/ ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡ ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡- ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡ በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26 @Tewahdo_Haymanote @Tewahdo_Haymanote
Показати все...
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት???? ❖ @And_Haymanot ❖ አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡ ስለ እመቤታችን ሲነሳ አይናቸው ደም የሚለብሰው የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸ አንዱ ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ። -ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ። እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ። የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። -ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት። ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ:: ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም:: ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ። በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡ .....ይቆየን ከሰሞኑ እመቤታችን አንዲት ድንግል እናት ሥለመሆኗ በሰፊው እንመለሳለን፡፡ ለአባ ሕርያቆስ ፤ ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!! ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው: የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!! ❖ @And_Haymanot ❖ ❖ @And_Haymanot ❖ ❖ @And_Haymanot
Показати все...
#መልአካይ_ሰይጣን ~ ሰባሪ ዜና @Tewahdo_Haymanote 👉 "ኦርቶዶክስ" የሚለው ስም የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ነው!!!!! √Share √Share √Share «ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ራሱን ሲጠራ የነበረው የውጉዙ አሰግድ ሣህሉ (?) የተሐድሶ መናፍቃን ቡድን ያሰበውን ያህል በጎችን ከበረት ማውጣት ስላልቻለ ስሙን «ቃለ ዐዋዲ ዘኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ቀይሮ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ነኝ በማለት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ይህ በእምነታችን ኃጢአት፣ በባህላችን ነውር፣ በሕጋችንም ወንጀል የሆነ ቅጥፈት ነው። መንግስትም የሌላን ቤተ እምነት ስም በመጠቀምህ ፍቃድ አልሰጥም ማለት እየቻለ "ተቃዋሚ ካለ ሰኞ ሐምሌ 29 3:00 ሰዓት በሰላም ምኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት ምዝገባ ዳይሪክቶሬት ይቅረብ" ብሎ የማርያም መንገድ የሰጠ ይመስላል። ሰይጣን ሰዎችን ሲያታልል መልአክን እንጂ ራሱን መስሎ አይደለም። የራሱን ኃይልና ብርታት በመግለጥ፣ ከመልአክነት ይልቅ ሰይጣናዊነት እንደሚልቅ በማስረጃ በማስረገጥ አይቀርብም። ስለ ራሱ የሚያቀርበው ነገር የሌለው ባዶ ነውና፣ ሌላን መምሰል እንጂ ራስን መሆን አይሆንለትምና መልአክ-መሳይ (መልአካይ) ሆኖ ይቅበዘበዛል። ተሐድሶዎችም እንዲሁ በመብከን ተሐድሶነታቸውን ሳይሆን ኦርቶዶክስ-መሳይነታቸውን ሊነግሩን ሽሩገድ ይላሉ። 2 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! ይህ የብሔርህ አልያም የፖለቲካ ወሬ አይደለም፣ የእውነትም የእምነትም ጉዳይ ነው! ይህንን መልዕክት በውስጥ መስመር ለመምህራን፣ ለሕግ ባለሞያዎች፣ ለባለሥልጣናትና ለብጹዓን አባቶች በማካፈልና በመላክ በቤ/ክ ጉዳይ ለውጥ እንፍጠር! ዳይ ወደ ስራ [©Binyam ZeChristos ሐምለ 26 - 2011] ፪ኛ ቆሮ ፲፩ 26 “ብዙ ጊዜ በመንገድ ኼድኹ፤ በወንዝ ፍርኃት፥ በወንበዴዎች ፍርኃት፥ በወገኔ በኩል ፍርኃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርኃት፥ በከተማ ፍርኃት፥ በምድረ በዳ ፍርኃት፥ በባሕር ፍርኃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርኃት ነበረብኝ፤ 27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርኹ። 28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ዐሳብ ነው።” @Tewahdo_Haymanote @Tewahdo_Haymanote
Показати все...