cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ

አላህን በደስታህ ጊዜ ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሀልና!!!

Більше
Рекламні дописи
397
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
-630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ?!! ቢስሚላህ ! ከ 25 አመት በሗላ የጠፋኝን ሰዉ ወንድሜ የህያ ኢብኑ ኑህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት ባይ ገረመኝ !! የዛን ዘመን አፍላ የቁርአንና የዳዕዋ ንቅናቄን ከየት እንደመጣ ሳናዉቅ ነበር የተቀላቀለን ። ፂሙ ያደገ የፓኪስታን ልብስ የለበሰ በቀኝ እጁ ሲዋክ በግራ እጁ ሙስበሃ ይዞ የፈጅርን ሰላት ለመስገድ የሂፍዝ ተማሪዎች ዉዱእ ማድረጊያ ላይ በዛ ብርድ ወቅት እንጣደፋለን ። ከመሀላችን ሞቅ ባለ ከፍ ባለ ድምፅ “ እናንተ ወጣቶች በናንተ ጊዜ ዲን ሲደፈር ነብያችን ሰ.ዐ.ወ ክብራቸዉ ሲነካ እናንተ እያላችሁ እንዴት ይሆን ለጅሀድ ተነስ እኔ አሰለጥንሀለሁ !” የሚል የወጣቱን ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ በቁጣ ንግግር አደረገ ። ብዙዎቻችን ሙሀመድ ሱሩር በሚል የቀረበንን ሰዉ ያኔ ተዋወቅነዉ ከፈጅር ሰላት በሓላ የቁርአን ሀለቃ ላይ አብሮን ተቀመጠ ። መስጅድ ላይ በተበላሸ ምላስ የቁርአን አያቶችን እየሰባበረ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ የዋሁ ማህበረሰባችን እና ወጣቱ ተከተለዉ ። በጣም የሚገርሙ ሊታመኑ የማይችሉ ለሀገር ሲል ከኤርትራ ጋር በተደረገ ጦርነት መሳተፉንና ለኢስላም ሲል አፍጋኒስታን ድረስ ዘልቆ የተዋጋበትን ባዶ ታሪክ ለወጣቱ ይግተዉ ጀመር አንዳንዱ በየት ብለን ጅሀድ በወጣን እስኪል ድረስ የማልረሳዉ ሁሌ ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ የነበረዉ ጠዋት ከሀለቃ በሗላ ከቁርስ በፊት ወደ ዉጭ እንዳንወጣ እንከለከል ነበር ። ለምን አትሉም ? ሙሀመድ ሱሩር ካራቴ እየሰራ ጩሀቱን እንጅ ስራዉን ማየት እንዳንችል ምክኒያቱም በጩሀቱ ብቻ ካራቲስት እንደሆነ እንድንመሰክር ። ማህበረሰባችን በዚህ ብቻ አልቆመም በዲኗ ጠንካራ የሆነች ልጅ ተፈልጋ ተዳረ ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ሱሩር ማንነት ይጋለጥ ጀመረ ። ይቀጥላል !! Abdurahman Sultan
Показати все...
ከ ሐጅ ቪዛ ውጪ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈ ቀድ የሳውዲ የሐጅ ሚኒቴር አስጠነቀቀ። የሳውዲ አረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ፣ ከሐጅ ቪዛ ዉጪ በማንኛውም የቪዛ አይነቶች ሐጅ ማድረግ እንደ ማይፈቀድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለፀ። የጉብኝት ፣ የቱሪስት ፣ የትራንዚት : የስራና መሰል በሳውዲ አረቢያ የሚሰጡ ቪዛዎችን በመጠቀም ሐጅ ለማድረግ የሚሞክሩ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል። ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል። ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል። ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል። የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
Показати все...
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ? (ክፍል 2 ) ቢስሚላህ ! በቁጥር አንድ እንደ ጀመርኩላችሁ የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ። ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !። በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ። ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ። የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ። ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ። የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ …..። © Abdurahman Sultan
Показати все...
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በክፍለ-ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ዳኢዎች ጋር የትውውቅ መርሃ-ግብር ማድረጉን ገለፀ! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 07/2016) ... የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በክፍለ-ከተማው ውስጥ ከሚገኙ ዳኢዎች ጋር ባደረገው የትውውቅ መርሃ-ግብር ላይ ወደፊት አብሮና ተባብሮ ለምስራት ከስምምነት መድረሳቸውንና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ለሀሩን ሚዲያ በላከው መረጃ ገልጿል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Показати все...
ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በሀገሯ ለማሰራት የሰራተኛ ምልመላ ልትጀምር መሆኑ ተገለፀ! .. ኢትዮጵያ እና ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት ሀገር የስራ አድል አንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ለማጠናቀቅ የመጨረሻው ሂደት ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ .. የመግባቢያ ስምምነቱ በዚህ ወር መጨረሻ ይፈረማል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ የሰራተኞችን መብት፤ አሰሪዎች የስራ ውል በሚያቋርጡበት ጊዜ  ሰራተኞች ስለሚያገኙት ክፍያ፤ የሰራተኞች የሳምንት፣ የአመት እረፍት እና ተያያዥ ስምምነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ .. የሰራተኛ ምልመላው ስምምነቱ እንደተፈረመ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ኩዌት ያጋጠማትን የሰራተኞች እጥረት ይቀርፋልም ነው የተባለው፡፡ ...
Показати все...
ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡ ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ ቀን ድረስ ሐያቱን በሙሉ በደዕዋ አሳልፏል፡፡ አላረፈም። ኢስላምን ለማድረስ ሁሌ እንደተጓዘ ስለማየው ቤት ይገባ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ ብዙ ጊዜ፡፡ ዛሬ ሻሻመኔ ላይ ድንገት ማረፉን ሰማሁ፡፡ ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንልህ፡፡ ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤ በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል፡፡ ደጋግ ባሮችህ ወዳንተ እየመጡ ነው። አላህ ሆይ! ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ እንላለን ።
Показати все...
ማስታወቂያ ዩዝድ መደገፊያ ትራሶች መግዛት ለምትፈልጉ ብዛት 8 ፍሬ 4ፍሬ ትንንሽ ትራሶች ዋጋ 9600 P.N 0988159585
Показати все...
በኳታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው የአለም ሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ተፋ ከአለም አቀፍ ሙስሊም ምሁራን ኘሬዝዳንት ዶ/ር አሊ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋየው ተገልጿል። ... የታላቁ አል-ነጃሺ 00 ማዕከል ማስጀመሪያ ኘሮግራም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጋር በመተባበር የአል-ነጃሺ 00 መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሼቴቨ (ARDI)ጋር በመሆን የኘሮጀክት ማስጀመር የማብራሪያ ኘሮግራም መካሄዱ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት የጠ/ም/ቤቱ ኘሬዝዳንት በኳታር ዶሃ እያደረጉ በሚገኙት የስራ ጉብኝት ከአለም አቀፍ ሙስሊም ምሁራን ኘሬዝዳንት ዶ/ር አሊ ቀራህ ዳጊ ጋር ኘሮጀክቱ ለሃገር እና በቀጠናዉ ባለዉ ጠቀሜታ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል ተብሏል። ...
Показати все...
ልዩ “ኸበር” - በራሪ ታክሲዎች ለሑጃጆች አገልግሎት መስጠት ሊጀምሩ ነው ሳዑዲ ዐረቢያ ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሽር ጉድ ስታደርግ ቆይታ ዛሬ ሐሙስ የመጀመሪያዎቹን ሑጃጆች ተቀብላለች፡፡ ከሕንድ የተነሱት ቀዳሚዎቹ ሑጃጆች፣ ወደ ሀገሪቱ የገቡት በአየር ተሳፍረው ነው፡፡ ዛሬ መዲና የደረሱት ሑጃጆች ከሕንድ የተነሱት ብቻ አይደሉም፤ የፓኪስታን እና ባንግላዴሽ ዜጎችም ተቀላቅለዋቸዋል፡፡ ሳዑዲ በቀጣይ ቀናት እና ሳምንታት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከመላው ዓለም የሚነሱ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሑጃጆችን ተቀብላ ታስተናግዳለች፡፡ ለእነዚህ ሑጃጆች ማረፊያ እንዲሁም ከአንድ ሥፍራ ወደ ሥፍራ ለመንቀሳቀስ የትራንስፖርት አገልግሎት በበቂ መጠን ለማሟላት የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ደፋ ቀና ሲሉበት የሰነበቱበት ጉዳይ ነው፡፡ ባለሥልጣናቱ በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከዚህ ቀደም ከተለመዱ አማራጮች ውጪ በራሪ ታክሲዎችን ለማስጀመር ማቀዳቸውን ቀደም ብለው አሳውቀው ነበር፡፡ ይኸው እቅድ ወደ ተግባር የሚውሉበት ቀን ደርሶ፣ ሑጃጆች ሳዑዲ ሲገቡ ከተለመዱ የትራንስፖርት አማራጮች በተጨማሪ በራሪ ታክሲዎች እንደሚጠብቋቸው የሀገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሳሊህ አልጃሲር ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርገዋል፡፡ በራሪ ታክሲዎቹ ከንጉሥ ዐብዱልዓዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ የተቀበሏቸውን ምእመናን ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ ሆቴሎች በአየር አንሳፈው ያደርሳሉ፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ በዚህ ዓመት ለሐጅ ተጓዦች የምታቀርባቸው በራሪ ታክሲዎች ከአራት እስከ ስድስት ሰው ያሳፍራሉ፡፡ መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
Показати все...
በዘንድሮው ሐጅ አዲስ ነገር የሳውዲ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዘንድሮው ሐጅ አዲስ የመጓጓዣ አማራጭ እንደሚሞክር አሳውቋል። በ1445/2024/2016 የሐጅ ስነ መስተንግዶ ላይ በራሪ ታክሲዎችን ለትራንስፖርት አማራጭነት እንደሚጠቀም የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሳልህ አልጃዝር ዛሬ አሳውቀዋል። መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
Показати все...