❝ ዳሩል ቁርአን ❞ የ አጫጭር ኪታቦች መድረሳ
Відкрити в Telegram
ይኽ ግሩፕ አላማው የ አሏህን ﷻ ሸሪዐ እንዲሁም የነብዩን ﷺ ሱና አጥብቆ የሚይዝ ወንድምና እህቶችን ማፍራት ነው ⌚️የቂራአት ሰዐት ከቀኑ፦ ➜ በኢትዮ 10:20 ➜ በሳዑዲ 4:20
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
728
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
"የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ።
"በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما
"አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165]
"ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" የሚለው አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው።
ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሆኑ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። (መግቢያየ ላይ የጠቀስኩትም ክስተት በዚህ መልኩ የተፈፀመ ነው።) እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ።
ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦
ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት።
በነገራችን ላይ እንኳን ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ለአስር ዓመት ልጆች! ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ደግሞ ሌላ ጥግ ማድረግ ይገባል። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው።
አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። ሌላው ቀርቶ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
©: ኢብኑ ሙነወር
