الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Відкрити в Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
2 186
Підписники
+2824 години
+447 днів
+45130 днів
Архів дописів
اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، أَنْفَعُ بِهِ نَفْسِي وَأَنْفَعُ بِهِ غَيْرِي
اللَّهُمَّ انْفَعْنِي بِمَا عَلَّمْتَنِي، وَعَلِّمْنِي مَا يَنْفَعُنِي، وَزِدْنِي عِلْمًا
ኢማሙ ሻፊዒ ረሁመሁሏህ እድህ አሉ
العِلْمُ صَيْدٌ وَالكِتَابَةُ قَيْدُهُ ... قَيِّدْ صُيُودَكَ بِالحِبَالِ الوَاثِقَهْ
ኢልም አደን ነው መጻፍ ደግሞ ማሰሪያው ነው። አድኖችህን በፅኑ ገመዶች እሰራቸው።
لَيْسَ العِلْمُ مَا حُفِظَ، إِنَّمَا العِلْمُ مَا نَفَعَ ኢልም ማለት የተቀመጠ (የተሸመደደ) ነገር አይደለም ኢልም ማለት (ባለቤቱንና ሰውን) የጠቀመው ነው
ዕውቀት በተግባር ካልዋለ ፍሬ እንደሌለው ዛፍ ነውእንዳሉት ዲንን ዝም ብሎ መሸምደድና ማስቀመጥ ዋጋ የለውም። ዛሬ ላይ ትልቁ ክፍተታችን የማወቅ ሳይሆን የመተግበር ነው። ያወቅነውን ያህል ብንተገብር ኖሮ እኛም ተለውጠን ሌሎችንም መለወጥ እንችል ነበር። አላህ ያወቅነውን በተግባር ከሚያውሉ ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን ከሚጠቅሙ እውነተኛ የኢልም ባለቤቶች ያድርገን አንድ አዳኝ ያደነውን እንስሳ በጥንቃቄ ካላሰረው እንደሚያመልጠው ሁሉ እኛም የምንማረውንና የምንሰማውን ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀት ወዲያውኑ በፅሁፍ ካላሰፈርነውና ካላጠናከርነው በቀላሉ ይረሳና ያመልጠናል። መፃፍ የዕውቀት ጠባቂ ገመድ ነው። ✍ድንን ሸምድዶ ግን እኛ ካልተጠቀምንበት ሌሎችንም ካልጠቀምንበት ቢቀመጥ ዋጋ የለውም እና እንንቃ ሀቂቃ እንንቃ እኛም እንተግብረው ራሳችንን እንጥቀምበት ሰወችንም እንጥቀምበት ?!
Repost from የሀርቡ እና አካባቢዋ የሰለፍዮች ቻናል
📢ለሳውዲ አረቢያ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ 🇸🇦🇪🇹
ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ (ሀዋላ) መላክ ለምትፈልጉ ወገኖች፣ አሁን ምቹ እና ደስ የሚል አጋጣሚ ተዘጋጅቷል።
💸 ሀዋላዎቻችሁን በታማኝነትና በአግባቡ ለመላክ
🤝 አቡ አማር አገልግሎት ሊሰጣችሁ ዝግጁ ነው
👾 ፈጣን አገልግሎት
👾 ታማኝ አሰራር
👾ቀላል እና ምቹ መንገድ
የቤተሰብዎን እና የሚወዱትን ሰው ፍላጎት በቀላሉ ያሳኩ።
📍ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባለዉ Username ያናግሩን።
🕊@Abi_Amarr
🌿 እምነት፣ ታማኝነት እና ፈጣን አገልግሎት ከአቡ አማር ያገኛሉ! 🌿
ለተጨማሪ መረጃ ጉረባችንን ይቀላቀሉ....
🚀https://t.me/Abu_Amar_hawalla
فَصَبْرٌ جَمِيلٌ ۖ وَاللَّهُ الْمُسْتَعَانُ
መልካም ትዕግሥትም (መታገስ ይሻለኛል) መታገዣው አላህ ብቻ ነውاصبر على ما اصابك الزم مصحفك وحافظ على صلاتك احتسب وجعك فما هو إلا قدر الله وما الدنيا إلا امتحان ستنتهي ما اجتمع صبر واستعانة بالله، إلا قوي اليقين وحصل الظفر በደረሰብህ ነገር ላይ ታገስ ከቁርኣንህ ጋር ተጣበቅ (አዘውትረህ ቅራ) ሰላትህንም ጠብቅ። ህመምህንና ስቃይህን ለአላህ ብለህ አስብ (ምንዳውን ከእርሱ ፈልግ) ምክንያቱም ይህ የአላህ ውሳኔ (ቀደር) እንጂ ሌላ አይደለም። ይህችም ዓለም ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም በቅርቡም ታበቃለች ትዕግሥትና በአላህ መታገዝ (እርዳታን መፈለግ) በአንድ ላይ አይሰበሰቡም እርግጠኝነት (የቂን) የጠንከረ እና ድል (ስኬት) የተገኘ ቢሆን እንጂ።
Repost from መነሀጁ አሰለፊይ📚
🌟 የቁርአን ተፍሲር የቀጥታ ስርጭት ግብዣ 🌟
የልባችን ብርሃን የነፍሳችን ረፍት ከሆነው ከታላቁ የጌታችን ቃል ጋር የምናሳልፈው ድንቅ ጊዜ ደርሷል። እውቀትን መፈለግና በቁርአን ጥላ ስር መሰብሰብ ለሁለቱም ዓለም ትልቅ ስንቅና ስኬት ነው።
ዘወትር ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሚቀርበውንና በኡስታዝ አቡ ሀኒፋ የሚሰጠውን ተወዳጅ የቁርአን ተፍሲር ቀጥታ ስርጭት (Live)
ሱረቱል አል-አዕራፍ (ከአንቀጽ 179 ጀምሮ)
🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ
ተ
ጀ
መ
ረ
👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ
ግቡ ተከታተሉ 📢
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f
*ውድ እና የተከበራችሁ የሱና እህት ወድሞች አሰላሙአለይኩምወራህመቱላሂወበረካትሁ ቅድሚያ ለተውሂድ የሱና መድረሳ በኡስታዝ ሳዳት ከማል አቡ መርየም የሚሰጠው ደርስ ትምህርት ዋሳፕ ጉሩፕ ላይ የሌላችሁ መማር የምትፈልጉ እህት ወንድሞች ቤታችን ክፍት ነው ኑ አብረን እንማር አህለን ወሰህለን ፊኩም☕☕ 🍹🍹ግን ማሳሰቢያ!! ቅድሚያ ለተውሂድ ላይ ማንኛውም ኮድ ላይ የሌላችሁትን ብቻ ነው የሚመለከተው ያላችሁ እዛው ባላችሁት ኮድ ተማሩ ትምህርቱ አንድ ነው የሌላችሁ ግን ኑ ዲናችነን አብረን እንማር ለነገው ሂወታችን እናተርፍበታል ሌላው ደግሞ ትምህርቱ የሚተላለፈው በሁለት መንገድ ነው አንደኛው ጥያቄና መልስ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደሞ አውዶ ማዳመጥ ብቻ ነው ከሁለት አንዱን መርጣችሁ መማር ትችላላችሁ የፈለገ ጥያቄና መልስ የፈለገ አውዶ ጉሩፕ ብቻ*
ኑኑኑኑ አህለንንንንን ተማሩ እንማር ሊንኩን ሼር ሼር ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ እኛ ባንጠቀምበትም ሌሎች ይጠቀሙበት ይሆናን እና ሼር በማድረግ አጅርን እናተርፋን ሼር አድርጉ *ፊ አማኒሏህ* ባረክ አሏሁ ፊኩም 🍃🍃🍃🍃
https://chat.whatsapp.com/DHTKTa7dFSvK1daf0nqmq3?s=sw&p=a&mlu=0&amv=0
✏️ቀልደን ነው እኮ! በሚል የይቅርታ ካባ ውስጥ ተሸሽገው በሞኝ ንግግርና በቁስል ላይ እንጨት በመስደድ የሰውን ልብ ለሚያደሙ ሰዎች የሚሆን አጭርና መራር እውነት
📌 ቀልድ" እና "ቁስል" ይለያያሉ
ቀልድ የሚያስቀው ሁሉንም ነው አንተ ብቻ ስትስቅ ሌላው ሰው ግን በውስጡ እያለቀሰና እየተሰቃየ ከሆነ ያ መጫወት ሳይሆን ክፉነት ነው🩸
🏹ቃላት እንደ ቀስት ናቸው አንዴ ከአፍ የወጣ ቃል ልብ ውስጥ ገብቶ ከሰነጠቀ በኋላ ስቀልድ ነው ማለት ሰውን በስለት ወግቶ ለመጫወት ፈልጌ ነው እንደማለት ይቆጠራል
የሰዎች ስሜት መለማመጃ አይደለም የሌሎችን ድክመት ህመም ወይም ሚስጥር ለቀልድ ማዋዣ ማድረግ ካልጎለመሰ አእምሮ የሚመነጭ የብልሃት ማነስ ነው
ከመናገርህ በፊት አስብ። ያንተ "ቀልድ" የሌላው ሰው "ሰላም" እንዳይነጥቅ ተጠንቀቅ። ማክበር እንጂ ማቁሰል ቀልድ አይደለም!
እውነት ለመነጋገር አንዳንድ ሰዎች ሆን ብለው ልብን አቁስለው "ቀልድ ነው" ሲሉ መስማት በጣም ያማል
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
➫➫
➫➫⚡️ የእስላማዊ ትላልቅ ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩኝ በርካሽ ዋጋ እንዳያመልጣቺሁ እጃችን ላይ 3 ቻናል አለ 💵
➪ 5k subscribers
➪ 7k subscribers
➪ 17k subscribers
🫰መግዛት የሚፈልግ ብቻ ያናግረን 📥
🏷 DM @Abu_Nueym
🏷 DM @Abu_Nueym
📌 ማሳሰቢያ አንዳድ ጊዜ ሳትፈልጉ ትዝብት ውስጥ ትገባላቹህ መልእክቱን ሸር ማረግ እየፈለጉ ሊንኩ ግን ቅሬታ የሚሰኛቸው የቻናል ዘረኝነት እየተስፋፋ እናያለን ✅
ኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሰኢድ ኮቻ ሀፊዘሁሏህ ያለው ትዝ ይለኛል የቻናል ዘረኝነት አለ ጎበዝ ብሎ ነበረ ክክክ
እውቀትን እና መልካም መልእክቶችን ለሰዎች ማጋራት ትልቅ በጎነት ነው። ይሁንና የማንኛውንም ቻናል ፁሁፍ ስንወስድ ምንጩንና ሊንኩን ጠብቆ ማጋራት የእውነትና የታማኝነት መገለጫ ነው። የሰዎችን ድካም ማክበር ለራሳችን የምንሰጠው ክብር ነውና መልካም ነገሮችን ከነምንጫቸው እናጋራበሶሻል ሚዲያ ላይ የምናጋራቸው መልእክቶች ሁሉ የራሳችን የአስተሳሰብ ጨዋነት ነጸብራቅ ናቸው። የሌሎችን ፀሀፊያን ወይም ቻናሎች ሊንክ እየቆረጡ የራስ አስመስሎ ማቅረብ ይዘቱን ይባርከዋል ተብሎ አይታሰብም። የሰውን ድካም ሳንቀንስ ሊንኩን ሳንቆርጥ በታማኝነት ሼር የማድረግ ባህልን እናሳድግ👏✅👆🕶🕶
📌በትዳር ውስጥ ዲን እና ጥሩ ስነ-ምግባር (አኽላቅ) ተነጣጥለው የማይታዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን በሚገባ ያሳያል?
አኽላቅ በትዳር ውስጥ ?!
ስነ-ምግባር ከሌለ ዲን ብቻውን ትዳርን አያቆምም!
ዲን አለው ወይም ዲን አላት እየተባለ ብቻ ተመርጦ ነገር ግን መልካም ስነ-ምግባር (አኽላቅ) በመዘንጋቱ ምክንያት ስንት የተጀመሩ ትዳሮች በከንቱ ፈርሰዋል? ለሰው ልጅ የመጀመሪያውና ዋናው መሰረቱ መልካም ስነ-ምግባር ነው።
📌ዲን ኖሮት ስነ-ምግባሩ ያላመረለት ሰው... ይልቅስ እውቀቱ አነስተኛ ሆኖ (ጃሂል ተብሎ) ነገር ግን ስነ-ምግባሩ ያማረለትና ሰዎችን በደግነት የሚያናግረው ሰው በላጭ ይሆናል።
የሚገርመው ግን አንዳንዶቻችን የቤት ጠጋ የውጪ አልጋ ነን በውጭ ለሰዎች ስንቶብኝ በፈገግታና በጥሩ ቃላት ስንታወቅ ወደ ቤት ስንገባ ግን ፊታችን የሚከረፈስ ንግግራችን የሚጎረብጥ እንሆናለን። ትዳር ግን መረጋጋትና እርስ በርስ መተዛዘን የሚገነባበት ታላቅ ተቋም ነው።
💡 እንመራመርበት✍
ዲን ማለት በተግባርና በባህሪ የሚገለጽ እምነት እንጂ በቃላት ብቻ የሚወራ አይደለም
የትዳር አጋራችን ከማንም በላይ የእኛን መልካም ባህሪ ፈገግታና ገርነት ለማግኘት ቀዳሚ መብት አላቸው
ኢላሂ ስንምግባርን ወፍቀን ያረብ
+2
👑👑💎💎💎 የኛ መገናኛ መድረሳችን ከፍ በይልን
እውነተኛ ጓደኝነት ማለት አብሮ መማር በቅንነት መተራረም እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መዋደድ ነው። አንዱ የሌላው መስታወት ሆኖ ሳያቆሽሽ የሚያጸዳ ሳይጥል የሚያቅፍ እና አብሮ የሚያድግ ውብ ስብስብ ነውالصداقة الحقيقية هي التي تبنى على التناصح، والتفاهم، والمحبة الصادقة. هم مرآة لبعضهم البعض؛ يقومون الزلل بالود، ويتعلمون معاً، ويسيرون يداً بيد نحو الأفضل እውነተኛ ጓደኝነት በምክር በመግባባት እና በሐቀኛ ፍቅር ላይ የሚገነባ ነው። አንዱ ለሌላው መስታወት ናቸው ስህተትን በፍቅር ያረማሉ አብረው ይማራሉ እንዲሁም እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ ተሻለ ነገር ይጓዛሉ👑👑👑💎💎💎
• ትዳራችን ረጅም እድሜ እንድኖረዉ
ከሚያደርጉ ሰበቦች ዉስጥ መጥፎ ነገርን ከመመልከት በፊት ወደ መልካም ነገር መመልከት ረጅም እድሜ ይኖረዋል።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
መልካም ዕድል የቻናል ባለቤቶች ቶሎ በሉ Wave መግባት የምትፈልጉ እስላማዊ ቻናል ብቻ በነፃ እናሳድጋለን
➪ 1k+ subscribers
➪ 10k+ subscribers
➪ 15k+ subscribers
➪ 20k+ subscribers
➪ 50k+ subscribers
➪ 100k+ subscribers
"⚠️ ከ1000 በታች ያላቹ እንዳትመጡ🚫
በቀን አንዴ ብቻ post ስለምናደርግ በጣም አሪፍ ነዉ
ቻናል መግዛት የምትፈልጉም አናግሩን በርካሽ📥
🏷 DM @Abu_Nueym
🌟 የቁርአን ተፍሲር የቀጥታ ስርጭት ግብዣ 🌟
የልባችን ብርሃን የነፍሳችን ረፍት ከሆነው ከታላቁ የጌታችን ቃል ጋር የምናሳልፈው ድንቅ ጊዜ ደርሷል። እውቀትን መፈለግና በቁርአን ጥላ ስር መሰብሰብ ለሁለቱም ዓለም ትልቅ ስንቅና ስኬት ነው።
ዘወትር ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሚቀርበውንና በኡስታዝ አቡ ሀኒፋ የሚሰጠውን ተወዳጅ የቁርአን ተፍሲር ቀጥታ ስርጭት (Live)
ሱረቱል አል-አዕራፍ (ከአንቀጽ 171 ጀምሮ)
🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ
ተ
ጀ
መ
ረ
👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ
ግቡ ተከታተሉ 📢
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f
المرأة هي اللمسة الرقيقة التي تحول البيت إلى وطن👑
ሴት ልጅ ማለት ቤትን ወደ እውነተኛ የትውልድ ሀገር (ሙቀት ወዳለው መጠጊያ) የምትቀይር እጅግ ረቂቅ ንክኪ ናት 💎
👑ያሰላም ጥንቁቅ ሴትልጅ በዚህ ልክ ናት💎 አልሀምዱ ሊላህ ጌታየ ፀጋህ ተቆጥሮ አያልቅም
ሕይወት ልክ እንደ አንድ ትልቅ የቡና ኮብ ናት ምን ያህል እንደምትሞሏትና ምን ዓይነት ቅመም እንደምትጨምሩባት የሚወሰነው በራሳችሁ እጅ ነው።
ስሜታችሁ ዝቅ ሲል ወይም ድብርት ሲመጣባችሁ ዝም ብላችሁ ተቀምጣችሁ ሰማዩን አትዩ። ተነሱና የሚነዝር ነቃ የሚያደርግ ምርጥ ቡና አፍሉ👌 ተናግሬለሁ
አላስፈላጊ ሐሳብና ጭቅጭቅን በሕይወታችሁ ላይ ጨምራችሁ ነገራችሁን መራራ አታድርጉት።
ቡና ሲቀዘቅዝ ጣዕሙ እንደሚጠፋው ሁሉ በሕይወታችሁም ላይ ለነገሮች ያላችሁ ስሜት ለብ ያለና ቀዝቃዛ አይሁን። ወይ ፈልታችሁ ንቁ ወይ ጨርሶ ተዉት🕶
ኑሮ ያለ ፈገግታ ያለ ጨዋታና ያለ እውነተኛ ጓደኛ ልክ ያለ ቅመም እንደተፈላ ቡና ባዶ ናት። በጥሩ ወሬና በደስታ አጣፍጧት
ኑሮን በትናንሽ ሲኒዎች እየተጨነቁ መጋት ይብቃን! ክክ 🕶እንደ እኛ ሰፋ አድርገን በትልቁ መግ ሞልተን አላስፈላጊ ነገርን በቸልታ አልፈን ሕይወትን በደስታ እንጎንጨው።መልካም ዋሉ ቡና ስትጠጡ አንጎላቹህ ይሰራል ለዚክር ለቁረአን ለመሳሰሉት ለስራም ጪምር ደማችንን ያሞቀዋል👌🍓🍓🍓
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👇 እስላማዊ ቻናል መግዛት የሚፈልግ ያናግረኝ ➪ 5.5k subscribers ➪ 7.1k subscribers በርካሽ ዋጋ 💰@Nur_Acadamy
📜🔗📌በትዳር ላይ ሆኖ ሌላ ቦታ መማተር የልብ መድረቅና የአላህን ቁጥጥር (ሙራቀባህ) የመርሳት ውጤት ነው።📌
ሂጃብንና ድንበርን መጠበቅ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ ቴሌግራም...) "ወንድም ነህ" "እህት ነኝ" በሚል ስም የሚጀመሩ አላስፈላጊ የፈገግታና የጫወታ ልውውጦች የዚና መግቢያ መንገዶች ናቸው። አላህ ወደ ዚና አትቅረቡ ነው ያለው መንገዱንም ጭምር ዝጉት ማለት ነው
مَّا يَلۡفِظُ مِن قَوۡلٍ إِلَّا لَدَيۡهِ رَقِيبٌ عَتِيدٞ
ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡ (ሱረቱ አል ቃፍ 18)
በዚህ መስመር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀደዱና ሳይዋረዱ የአላህ ቁጣ ሳይወርድባቸው በአስቸኳይ ግንኙነቱን አቋርጠው ወደ አላህ ሊመለሱና ሐላላቸውን ሊያከብሩ ይገባል
📍እውነት ነው በጣም የሚያሳዝንና የሚያስገርም ነገር ነው! አላህ በሐላሉ ባርኮላቸው በትዳር ውስጥ ያለውን ክብርና ሰላም ሰጥቷቸው ሳለ ደግሞ ዞር ብለው ከሌላ ባለ ትዳር ወንድ ጋር የማይረባና የማይመጥን ግንኙነት ውስጥ የሚገቡ ሰዎችን ሲያዩ መታዘብ አይቀርም።
ትዳር እኮ የአላህ ትልቅ ጸጋ መተማመኛና መከባበሪያ የፍቅር ቤት ነው። ታዲያ ያንን ሁሉ ክብር ጥለው የአላህን ስትርና ጥበቃ አቅልለው ወደማይሆን ነገር የሚንሸራተቱት—ምናልባትም በልባቸው ውስጥ ባለው የኢማን ድክመት በስሜት መነዳትና ባላቸው ነገር ላይ ካለመብቃቃት (ቃናዓ ከማጣት) የተነሳ ነው።
📌አላህ በሐላሉ ሰትሯቸው ከዚህኛው ምን አላቸው?" ምንም የላቸውም! ከባዶ ስሜትና ከጸጸት ውጪ የሚያተርፉት ነገር የለም። የራስን ትዳር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን የሌላውንም እህት የትዳር ህይወት ማናጋትና ቤተሰብ መበተን ትልቅ በደል ነው።
📌ይህ የጊዜያችን አንዱ ትልቅ የሞራል ዝቅጠትና የማህበራዊ ሚዲያ መበላሸት ያመጣው ፈተና ነው። አላህ ልባችንን በሐላሉ የሚያረካ በትዳራችን ላይ በረካን የሚያወርድና ሁላችንንም ከእንዲህ አይነቱ የውሸትና የሃጢአት መንገድ የሚጠብቀን ይሁን። ስትሩን አይንሳን
📌አሏህ ሆይ ? በዚህ ነገር የተሰማሩትን ወድም እህቶች አተ ሂዲያውን ስጣቸው አተ በሀላላቸው አብቃቃቸው እኔንም ጠብቀኝ አሚን 📝
