الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Відкрити в Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
2 158
Підписники
Немає даних24 години
+1817 днів
+41530 днів
Архів дописів
اللهم صلِّ وسلِّم وبارك على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين.
ፍቅር አይን የለዉም አሉ ያኢላሂ ልቤን በአንተ ፍቅር ሙላልኝ ሰላም ያለው ፍቅር አላህን መዉደድ የአላህ ኢኒ አሀቡከ
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስር_⓾ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.....
የከንፈር ስንብትና የደላላው ግዞት
የየመን ምድር ላይ ስንደርስ፣ ከባዱና የመለያያችን ሰዓት እንደ መርዶ ደረሰ። በዚያ በስደተኞች መዓት መሃል፣ ሰው ሁሉ እያየንና እየተታዘበን ሳለ፣ እራቢያ ዓለምን የረሳች መሰለች። በዝምታና በናፍቆት ለረጅም ጊዜ አቅፋኝ፣ የልቧን ትርታ በደረቴ ላይ አተመችው። "አብሽር፣ ሳውዲ ገብተን እንገናኛለን" ስትለኝ፣ ድምጿ በተስፋ መቁረጥና በለቅሶ የታጀበ ነበር።
ያኔ... የመጨረሻው ስንብት መሆኑን ልቤ ቢነግረኝም፣ እግሬን ግን ከአቅፏ ለማውጣት ተቸገርኩ። ሳንወድ በግድ፣ የሥጋ ነጋዴዎቹ (ደላላዎች) እየጎተቱ ለዩን።ታዳ ፍቅርና እራሀብ አይደበቅም እንበሚባለው "አዬው እወድሃለሁ! በሕይወት ካለሁ መቼም አልረሳህም!" የሚለው ቃሏ፣ በበረሃው ነፋስ ተጭኖ ጆሮዬ ውስጥ ሲያቃጭል፣ እራቢያ ከአይኔ ተሰወረች። እንዲህ አልኩ፦
"ከእቅፏ ስወጣ - ነፍሴ ተከፈለች፣
እራቢያ ስትርቅ - ምድር ጠበበች፤
'አልረሳህም' የሚል - ያ የቃሏ እሳት፣
ውስጤን አቃጠለው - እንደ ስደት መቅሰፍት።"
ከእራቢያ ተለይቼ ወደ ደላላው "ሀውሽ" (የእስር ቤት ግቢ) ተወሰድኩ። እዚያ ስገባ ግን ያየሁት ትዕይንት ለጆሮ የሚከብድ ነበር። ለወራትና ለዓመታት ብር መክፈል አቅቷቸው፣ በደላላ ጅራፍ ገላቸው የቆሰለ፣ በረሃብና በጥም የከሳ ብዙ ወጣቶች ተቆልፎባቸዋል። እኛም "እስረኛ" ተባልን። ሽንት እንኳን መሽናት የሚቻለው በደላላው ፈቃድና ቁጥጥር ሆነ። የሰው ልጅ ክብር መሬት ጠብቶ አየሁት።
በማግስቱ... ጡንቻቸው ያበጠ፣ ፊታቸው የጨለመ ሁለት ግፈኞች መጡ። "የቤተሰብ ስልክ አምጣ!" ሲሉኝ፣ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ ሰጠሁ። እናቴ ድምጯን ስታሰማ፣ የደስታና የለቅሶ ማዕበል ሆነ። "በሕይወት አለህ?" ስትል የጠየቀችኝ ጥያቄ ልቤን ሰነጠቀው። ቤተሰቦቼ ያላቸውን ሸጠውና ለውጠው ቶሎ ብር አስገቡልኝ።
ነገር ግን... አብረውኝ የተሰደዱ ጓደኞቼ ዕድላቸው የከፋ ነበር። ቤተሰቦቻቸው ብር መላክ የዘገዩባቸው ልጆች፣ በደላላው ብትር ገላቸው ሲቀጠቀጥ፣ ጩኸታቸው ግቢውን ያናውጠው ነበር። እኔ የተረፍኩት በቤተሰቦቼ መስዋዕትነት ቢሆንም፣ የጓደኞቼ ስቃይ ግን ሌላው የሕሊና ቁስል ሆነብኝ።
"ሰው በገንዘብ ታክቶ - ነፍሱ ሲገበያ፣
ጅራፉ ሲጮኽ - በግዞት መጠለያ፤
የጓደኞቼ ዋይታ - ልቤን ሲበሳው፣
የስደት መራራ - ጣዕሙ ይኸው ነው።"
"ውድ አንባቢያን ሆይ ልብ በሉ የየመን መንገድ ሁሉም ሲለሚያወቀው ያለፈበት ስለሆነ እኔ ከብዙ ጥቂቱን ጠቅሼ (ፅሁፍ$ ላ'ለማርዘም" ስል፦ትቼዋለሁ።
በዚያ የየመን "ሀውሽ" ውስጥ ለአሥራ ሰባት ቀናት በጭንቅ ቆየሁ።
የምንመገበው ደረቅ ሩዝ እንዳንሞት ብቻ የምትቀመስ የምጽዋት ያህል ነበረች። በዚያ የረሃብና የጥም ጽዋ ውስጥ ሆኜ፣ የራቢያ ፍቅር እንደ እሳት ቢያቃጥለኝም፣ ነፍሴ ግን በሹክሹክታ ትመክረኝ ጀመር። "የሙሐመድ ልጅ ሆይ ንቃ! ጌታህ እያየህ ነው፤ ሞት ሳይቀድምህ ወደ እርሱ ተመለስ" የሚለው ድምፅ ከውስጤ ይጮኻል።
አሥራ ሰባት ቀን በአፈር ላይ ተኝተን፣ በብርድና በረሃብ ተገርፈን ካለፍን በኋላ ወደ ሳውዲ ድንበር ጉዞ ተጀመረ።
በየመን ምድር ስንጓዝ ግን ሌላ መከራ መጣ፤ ዘረኝነት! በሰው አገር፣ በባዕድ ምድር ሆነን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ እየተባባልን መናከሳችን ሌላው የልብ ስብራት ነበር። ከስድስት ቀን የረሃብ ጉዞ በኋላ "ራጎ" ደረስን።
አቤት ራጎ! ሳውዲ የሄደ ሁሉ የሚያውቀው የሲኦል ደጃፍ። እዚያ የሰው ልጅ ክብር እንደ ቅጠል ረግፎ አየሁት። ሴቶችና ወንዶች በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ ታጉረን፣ የኢትዮጵያ ደላላዎች ያለ ርኅራኄ ሲገርፉን አደርን። አንዲት ኒቃቢስት እህቴ "ብር አምጪ" እየተባለች በዱላ ራሷን ስትመታ፣ ውበታቸውን አይተው እህቶቻችንን ሲደፍሩ ስመለከት... ምድር ብትዋጠኝ ተመኘሁ።
ያኔ እራቢያ ትዝ አለችኝ። ያንን ሁሉ ውበትና ቅልጥፍና ይዛ፣ እነዚህን የሰይጣን ወታደሮች እንዴት ታልፋቸው ይሆን? በሚል ስጋት በሐሳብ ሰከርኩ።
"ራጎ በደም ታጥባ - በለቅሶ ስትናወጥ፣
የእህቶች ንፅህና - በደላላ ሲገመጥ፤
እራቢያ ትዝ አለችኝ - ያቺ ውብ ጽጌረዳ፣
እንዴት ትተርፍ ይሆን - ከዚህ ሁሉ እዳ?"
በማግስቱ ጠዋት... ያ ፀጉሩ የቆመ፣ አፉ በጫትና በሲጋራ የከረፋ ደላላ "አ!" ብሎ ስሜን ጠራኝ። "የቤተሰብ ስልክ አምጣ" አለኝ። በሚንቀጠቀጥ እጄ ስልኩን ሰጠሁት። ለቤተሰቦቼ ተደወለ፤ በዚያ በሰቆቃ ምድር ሆኜ የናቴን ድምፅ ስሰማ ሕይወቴ ዳግም የተገኘች መሰለኝ።
ቤተሰቦችህ ብሩን ቶሎ ላኩልክ? ከራጎ ጭካኔ እንዴት ወጣህ? ወደ ሳውዲ ድንበር የመጨረሻው ሩጫ እንዴት ተጀመረ?
የሚለውን በቀጣይ በ.ክፍል ⓫
.
የራጎ "ሲኦል" እና የቁርኣን መድኃኒት
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ይቀጥላል፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_አንድ_⓫ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.........
የራጎ "ሲኦል" እና የቁርኣን መድኃኒት
በራጎ ምድር የሰው ልጅ ክብር እንደ በልግ ቅጠል ረግፎ አየሁት። ቤተሰቦቼ ብሩን ለመላክ ቢቸገሩም፣ በዚያ ግቢ ውስጥ የሚሰማው የግርፋትና የጭካኔ ድምፅ አስፈርቷቸው እንደምንም ላኩ። እዚያ ግን "የምድር ሰላም" ተነፍጎናል። መኝታው አፈር፣ ድባቡ ጭቅቅት፣ ጠረኑም ቅማልና ግማት የነገሰበት የቁም መቃብር ነው።
አንባቢያን ሆይ! ልብ በሉ። በዚያ ስቃይ መሃል ሶላት መስገድ እንኳ እንደ ቅንጦት የሚታይበት፣ የሰው ልጅ አእምሮውን ስቶ በጭንቀት የሚጮኽበት ቦታ ነው። ታዲያ በዚያ የጨለማ ቤት ውስጥ አላህ እኔንና አንድ የሀርቡ ልጅን ለምስኪኖቹ ጋሻ አደረገን።
እኛ ቁርኣን የምናውቅ በመሆናችን፣ አእምሯቸውን ስተው ለሚጮኹት ወንድሞቻችን "ሩቃ" (የቁርኣን ሕክምና) እናደርግላቸው ጀመር። በዚያ የክርፋትና የደም ሽታ በነገሰበት ግቢ ውስጥ፣ የአላህ ቃላት ሲነበብ ሰላም ይወርዳል፤ የታመሙትም ይሻላቸዋል። ደላላዎቹ እንኳ ይህንን ተአምር ሲያዩ፣ ለኔ ልዩ ክብር መስጠት ጀመሩ። እንዲህ አልኩ፦
"በራጎ ጨለማ - ግማቱ በነገሰበት፣
የቁርኣን ጸዳል - ሆነልን ብርሃነት፤
ሰው አእምሮውን ስቶ - ሲጮኽ በመከራ፣
ጌታዬ አቆመኝ - ከፈውስ ጋር አብራ።"
አምስት ቀን በዚያ ሰቆቃ ውስጥ ቆየሁ። በስድስተኛው ቀን ግን... የታሪኬ የመጨረሻውና እጅግ አስፈሪው ምዕራፍ ተበሰረ። "ወደ ሳውዲ ድንበር!" የሚል ትእዛዝ መጣ።
የሳውዲ ድንበር! ያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ደም የፈሰሰበት፣ ጥይት እንደ በረዶ የሚዘንብበት፣ ተራራውና ሸለቆው የሰው አጥንት የለበሰበት አስፈሪ ምድር። ይህንን ጉድ የሚገልጽ ቃላት ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ የሕይወቱን ዋጋ ለድንበር ጠባቂዎች ጥይት አሳልፎ የሚሰጥበት፣ ሞትና ሕይወት በአንዲት ሰከንድ የሚለዩበት ያ አደገኛ ጉዞ ተጀመረ።
"ድንበሩ ተከፍቷል - የሞት ደጃፍ ሆኖ፣
የሰው ልጅ ይጋዛል - ተስፋውን አዝሎ፤
በራጎ መከራ - ያለፍኩት እኔዬ፣
ወደ ሳውዲ እሳት - አመራሁኝ ጌታዬ።"
፦ የሞት ሸለቆና የጠይባ አደራ
-
ከራጎ ሲኦል ወጥተን በሁለት "ሻስ" መኪናዎች ተጭነን የየመንን ገደል ለገደል ሦስት ሰዓት ተጓዝን። መኪናው ሊሄድበት የማይችልበት ጋራ ስር አወረደን። "ከዚህ በኋላ የእግር መንገድ ነው፤ ጠንከር በል የሙሐመድ ልጅ!" ብዬ ለነፍሴ አሾካሾክሁላት። በዚያ በረሃ ውስጥ ሆኜ እንደ ዋሻው ባለቤቶችና እንደ ነቢዩሏህ ዩኑስ (ዐለይሂ.ሰላም) ጌታዬን እየተማጸንኩ፣ አንዲት ፕላስቲክ ውኃ ይዤ ጉዞዬን ቀጠልኩ።
-
ንጋት ሲቃረብ ወደ ሳውዲ "መርከዝ" (የድንበር ጠባቂ ጦር ሰፈር) ተቃረብን። ፀሐይ ብቅ ስትል ግን፣ ሰላማዊው ተራራ በቆሎ ጥይት ጩኸት ተናወጠ። ድንበሩ የሰቀቀን ማኅደር ነው፤ ቃላት የማይገልጹት የሞት አዝመራ! ጥይቱ ሲነጋ "ምነው ባልተፈጠርኩ!" የሚያሰኝ የፍርሃት ድባብ ነገሠ። መሬት ለመሬት እየተሳብን፣ ጥይቱ ሲጮህ ድንጋይ ተከል እየሆንን፣ ከሞት ጋር ድብብቆሽ መጫወት ጀመርን።
"ተራራው ሲጮኽ - በጥይት ነጎድጓድ፣
ነፍሴ ተሸበረች - ልትወጣ ካካል።
ድንበሩ መቃብር - ሸለቆው ሰቀቀን፣
ጌታዬ ሆይ አውጣኝ - ከዚህ የሞት ቀን።"
-
በዚህ ድንጋጤ መሃል የቀኑ ግማሽ አለፈ። ጥይቱ አላሳልፍ ብሎን ባለበት፣ ከሌላ ደላላ ጋር የመጡ ስደተኞችን አገኘን። አብዛኞቹ ሴቶች ነበሩ፤ ጥይቱ ሲጮህ በድንጋጤ ይተፋሉ፣ ያለቅሳሉ። በዚያ መሃል አንዲት ልጅ ከእኔ ጋር በአንድ ድንጋይ ስር ተጠለለች።
ተያይዘን መሬት ላይ ተለጥፈን ሳለ፣ ዓይን ዓይኔን እያየች እንዲህ አለችኝ፦ "ስማ... መልከ መልካም ሰው ትመስላለህ፤ ፊትህ ላይ ኑር (ብርሃን) አለ። አትዋሽም ብዬ አምናለሁ። እኔ የአልብኮ ልጅ ነኝ፣ ስሜም ጠይባ ይባላል። እኔ ከዚህ ተራራ በሕይወት እንደማልወጣ አውቃለሁ፤ ለአላህ ብለህ ለቤተሰቦቼ ንገርልኝ" ብላ ስልክና መልእክት የተጻፈበት ወረቀት ሰጠችኝ።
አቤት መርዶ! ገና ሳትሞት ሞቷን የተነበየች ምስኪን ነፍስ! በዚያ በጥይት እሩምታ መሃል፣ የጠይባን ወረቀት ስቀበል እጄ ይንቀጠቀጥ ነበር። በገዛ ዓይኖቿ ሞትን እያየች ለእኔ አደራ የሰጠችኝ ያቺ ልጅ፣ የታሪኬ ሌላዋ ጥቁር ጠባሳ ሆነች።
-
"ጠይባ በድንጋዩ ስር - ሞቷን ስትናዘዝ፣
አደራዋ ከበደኝ - ልቤ ሲቀመቅዝ።
'አልወጣም' ስትለኝ - በቁሟ ተረድታ፣
ተራራው ተከፈተ - ነፍሷን ሊያወጣ።"
ኢንሻ አሏህ በቀጣይው ክፍል⓬
የሞት ሽረት ሩጫና የሳዑዲ መሬት
በሚል
.ይ
ቀ
-------ጥ
-----------------ላ
-------------------------------ል ⤵️
Repost from N/a
✔️የአረብኛ ቋንቋን በጥራት እና በፍጥነት ይማሩ!➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✅ባሉበት ሆነው በኦንላይን አረብኛን በ60 ቀናትና በተመጣጣኝ ክፍያ አቀላጥፈው መናገር ይጀምሩ! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🎁 በ«ኢህሳን» ለሚመጡ የ🔤🛍 ልዩ ቅናሽ! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⬇️ አሁኑኑ ይመዝገቡ!⬇️🌟0913353613 | 0994093535 📚 ሊሳን አካዳሚ — የቋንቋ ስኬትዎ መንገድ!
ሰውም ካልፈለገ አይቀርም
የነፍስ በር ከውስጥ እንጂ ከውጭ አይከፈትም። ሰው ራሱ ለመለወጥ ካልወሰነ፣ የዓለም ጥበብ ሁሉ ቢሰበሰብለትም የሐሳብ አቅጣጫውን ማዞር አይቻልም።ተኩላ በምክር በግ አይሆንም ተኩላ በተፈጥሮው አዳኝ ጨካኝ እና የሥጋ በል እንስሳ ነው። ምንም ያህል ጥሩ ቃል ቢነገረው ቢመከር ወይም ሰላማዊ አካባቢ ቢፈጠርለት ተፈጥሮውን ለወጦ የእንስሳትን መንጋ የሚጠብቅ የዋህ በግ ሊሆን አይችልም
ብዙ ሕመም አለ ቀን በቀን ሚፀና
ዉስጥን የሚበላ አስመስሎ ደህና።
ብዙ ማጣት አለ በሳቅ የሚሸፈን
ከፊት ለፊት ደምቆ ከዉስጥ የታሰረ በብቻነት ከፈን።
ብዙ እንባ አለ አባሽ የናፈቀዉ
ሰዉ በማጣት ብቻ ቀን ሌት የሚወርደዉ።
ብዙ
ብዙ.........
Repost from Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
ሙሓደራ ቁጥር 237
ክፍል 1
ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ
"መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል''
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!"
~
እንዲህ ዓይነቱ መጃጃል በዲን ስም መፈፀሙ ነው የሚያሳዝነው። ተሶውፍ ሌላ ዓለም ነው። አሁን ይሄ ትልቅ ዒባዳ ላይ በሱ ቤት። በሃገራችንም ያለው የመንዙማ ጭፈራ ከመጠነኛ ልዩነት ውጭ ያው ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን መጃጀል ነው እንግዲህ "ነባሩ እስልምና" የሚሉት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🚨አዲስ ቻሌንጅ ለቻነል ባለቤቶች በሙሉ 🚨
➲➢ ቻናላቺሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ ማሳደግ የምትፈልጉ ብቻ አናግሩኝ
🏷 1k+ subscribers
🏷 2k+ subscribers
🏷 4k+ subscribers
🏷 6k+ subscribers
🏷 10k+ subscribers
ከ1000 ጀምሮ እንቀበላለን ℹ️
ቻናል በነፃ ለመሳደግ ያናግሩን ፍጠኑ
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ዘጠኝ_⓽ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.....
የዴኬል ሞገድና የጸጸት ማዕበል
በባሕሩ ዳርቻ ሆነን መርከብ እስኪመጣ ስንጠባበቅ፣ ቀኑ ሊመሽ አልጠግብ አለ። በዚያ የጥበቃ ሰዓት ግን ልቤ ውስጥ የእራቢያ ትዝታ እንደ ማዕበል ይናወጥ ነበር። "የማይመሽ ቀን የለም" እንደሚባለው መሽቶ፣ ወደ መርከቦቹ የሚያደርሰን የእግር ጉዞ ተጀመረ.......።
..
ሁለት መርከቦች ተዘጋጅተዋል። በባሕሩ ሽታ መካከል የእራቢያ "ሽታ" መጣብኝ። የናፍቆትና የፍቅር ነገር እንዲህ ነው፤ መከራን ያስረሳል፣ ፍርሃትንም ያደነዝዛል። እራቢያን መጥታለች በብህሩ ዳርቻ እነሱ ከኛ ቀድመው ደርሰዋል አንዱ መርከብ ለነሱ የተዘጋጄ ነው አንዱ ደሞ ለኛ የተዘጋጄ ነው።
እራቢያጋ ከሶስተቀን 'ናፍቆት" ቡኋላ' አገኘኋት። እሷና ጓደኞቿ ቀድመው ደርሰው ኖሯል። በዚያች ሰከንድ በስስት እቅፍ አድርጋኝ "አብሽር" ብትለኝም፣ እኔ ግን ከመቼውም በላይ ተሸብሬ ነበር።
ምክንያቱም... በደረቅ ምድር አላህን አምጬ፣ አሁን በማይታመን ባሕር ላይ ልቆም መሆኑ የቁም ሞት ሆነብኝ። "አላህ በዚህ ባሕር ቢያሰምጠኝስ?" የሚለው ጥያቄ የሕሊናዬ ጅራፍ ሆነ።
እንዲህም አልኩኝ
"በየብስ የበደልኩት - ጌታዬን የረሳሁት፣
ዛሬ በባሕር ላይ - ቁጣውን ፈራሁት፤
እራቢያ ስታቅፈኝ - ናፍቆቷ ቢጣፍጥም፣
የባሕሩ ግርማ - ለነፍሴ አልራራም።"
እራቢያና ጓደኞቿ በመጀመሪያው መርከብ ተጫኑ፤ እኔ ግን ወደ ሁለተኛው ተመደብኩ። ከእራቢያ ጋ በዓይናችን ተሰነባበትን። ተራዬ ደርሶ ወደ መርከቡ እንድገባ ስታዘዝ፣ ወደ ባሕሩ ዘለልኩ። ውኃው እስከ ደረቴ ድረስ ሰመጠኝ! ልቤ በፍርሃት "መቅ" አለ። የጥንት አጋሪያን (ሙሽሪኮች) መርከብ ላይ ሲወጡ ብቻ አላህን እንደሚጠሩት ሁሉ፣ እኔም ያኔ በጭንቅ ጌታዬን ተጣራሁ።
ደላላው እጄን አንጠልጥሎ ወደ መርከቡ ውስጥ ወረወረኝ። መርከቡ ውስጥ ስገባ ግን... የሰው ልጅ ክብር መሬት ጠብቶት አየሁ። እንደ ከብት ተቆልለን፣ በጨለማና በሞገድ መሃል የሞት ሽታን እናሸት ጀመር።
መርከቡ ላይ ደላላው አንጠልጥሎ ሲወረውረኝ፣ አንድ እግሬ ላይ የነበረው ጫማዬ በባሕሩ ተውጦ ቀረ። ያኔ... ባዶ እግሬንና ባዶ ነፍሴን ሆኜ ጉዞው ተጀመረ። መርከቡ ውስጥ የሰቆቃ ድምፅ ይነግሳል፤ ከፊሉ በባሕር ሕመም ይትፋል፣ ከፊሉ በፍርሃት ይጮኻል። እኔ ግን በዚያ ማዕበል መሃል ሆኜ የማስበው የነቢዩ ዩኑስን (ዐለይሂ .ሰላም) ታሪክ ነበር። እርሳቸው በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሆነው ጌታቸውን እንደተጣሩ፣ እኔም በዚህ "ተንሳፋፊ የሞት ሳጥን" ውስጥ ሆኜ ነፍሴን ስቅ ስቅ ትላለች አዛኝ ("ጌታ።እንዳላትም አውቃለች ታዳ ምን ያደርጋል (ዩኑስ አለይሂ ሰላም)እወነተኛ የአሏህ ነብይ ባሪያ ነበሩ። አሏህም ታሪካቼውን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል
﴿وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ ١٣٩ إِذْ أَبَقَ إِلَى الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ ١٤٠ فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ الْمُدْحَضِينَ ١٤١ فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ ١٤٢ فَلَوْلَا أَنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُسَبِّحِينَ ١٤٣ لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ ١٤٤
እኔስ እኔስ በደረቅ ምድር ("ገታዬን") ሳምፀው ወያሳቲር...
ከስድስት ሰዓታት የሲኦል ጉዞ በኋላ፣ የየመን ምድር ላይ እግራችንን አሳረፍን። "ፈሊላሂል ሐምድ!" ከባሕሩ ፈተና በሰላም ወጣን። ነገር ግን ውስጤ እንዲህ ይለኝ ነበር፦ "አንተ እኮ ያኔ ባሕር ላይ ሲጨንቃቸው አላህን ተጣርተው፣ የብስ ላይ ሲወጡ ግን ወደ ወንጀላቸው እንደሚመለሱት አጋሪያን (ሙሽሪኮች) ብጤ ነህ!" አታውቅምን የሙሀመድ ልጅ ትለኛለች ነፍሴ..
አሏህም እንዲህ ሲል ይነግረናል ታሪካቼውን
﴿فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ﴾
እና እኔ ከነሱጋ አልተመሳልኩኝም እላለሁ ነዓም
وقال تعالى
قُلِ ٱللَّهُ یُنَجِّیكُم مِّنۡهَا وَمِن كُلِّ كَرۡبࣲ ثُمَّ أَنتُمۡ تُشۡرِكُونَ
وقال تعالى
هُوَ ٱلَّذِی یُسَیِّرُكُمۡ فِی ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۖ حَتَّىٰۤ إِذَا كُنتُمۡ فِی ٱلۡفُلۡكِ وَجَرَیۡنَ بِهِم بِرِیحࣲ طَیِّبَةࣲ وَفَرِحُوا۟ بِهَا جَاۤءَتۡهَا رِیحٌ عَاصِفࣱ وَجَاۤءَهُمُ ٱلۡمَوۡجُ مِن كُلِّ مَكَانࣲ وَظَنُّوۤا۟ أَنَّهُمۡ أُحِیطَ بِهِمۡ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخۡلِصِینَ لَهُ ٱلدِّینَ لَىِٕنۡ أَنجَیۡتَنَا مِنۡ هَـٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّـٰكِرِینَ
<>
فَلَمَّاۤ أَنجَىٰهُمۡ إِذَا هُمۡ یَبۡغُونَ فِی ٱلۡأَرۡضِ بِغَیۡرِ ٱلۡحَقِّۗ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡیُكُمۡ عَلَىٰۤ أَنفُسِكُمۖ مَّتَـٰعَ ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَاۖ ثُمَّ إِلَیۡنَا مَرۡجِعُكُمۡ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
ወደ የድህረ-ባሕር መጠለያ (ሀውሽ) በመኪና ተጫንን። እዚያ ስንደርስ እነራቢያ ቀድመው ተከስተዋል። የባሕሩ ጨዋማ ውኃ ገላችንን አበላሽቶት፣ ፀጉራችን ቆሞ፣ መልካችን ጭምልቅልቅ ብሎ ነበር። እኔ ደግሞ ያለ ጫማ፣ በብርድ የምንቀጠቀጥ "የሙሐመድ ልጅ" ሆኜ ቆሜያለሁ።
ራቢያ አይኗ እኔን ፍለጋ ሲዋኝ ቆይቶ አገኘችኝ። በዚያ በቆሸሸና በከረፋ ማንነቴ ውስጥ ሆኜ ሳለ፣ ቅንጣት እንኳ ሳትጸየፈኝ መጥታ አቀፈችኝ።
የለመደችውን የፍቅር ስልቷን በሰው ፊት ያለምንም ሀፍረት አሳየችኝ። ወደ እግሬ ተመልክታ "ጫማህስ?" ስትለኝ፣ "ባሕር ውስጥ ቀረ" አልኳት።
"ባሕሩን ተሻግሬ - የብስ ላይ ስቆም፣
ጫማዬ ቢጠፋም - ፍቅርሽ ግን አይለቅም፤
በጨው በታጠበው - በቆሸሸው ገላዬ፣
አቀፍሽኝ እንደገና - ሆንሽብኝ ጥላዬ።"
ያ የየመን ብርድ አጥንት ይሰረስራል። እራቢያ በረጅሙ እየተነፈሰች፣ ከእኔ ጋር ያሳለፈችውን የባሕር ላይ ፍርሃት እያወራችኝ ሳለ፣ ደላላው እንደገና መጣ። ስም መጥራት ተጀመረ። የስደት ነገር... ዳግም መለያየት! ገና ሳልጠግባት፣ ገና የባሕሩን ድንጋጤ ሳልረሳው፣ ሌላ የመከራ መንገድ ተደቀነብኝ። እራቢያ እቅፍ አድርጋኝ "አልችልም! ልለይህ አልችልም!" ስትል ድምጿ በብርዱ መሃል ይንቀጠቀጥ ነበር።
በቀጣይው ክፍል.⓾...
የከንፈር ስንብትና የደላላው ግዞት
ይቀጥላል~~~~
ሳኡድ ድንበር ያቺ ብዙ ጎበዝ ያለቀባት አይናችን እያየ እያዩን ደክሟቸው ርቧቸው ውሃጠምቷቸው መላውንስናጣ እያለቀሱ አልፈናቸው የመጣነው 💦 እህህ አስተወሳቹሁት?!
ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ብለን መተን መታቹህ እዝህ አላማ ረስታቹህ ድንን መማር ትታቹህ በቲክቶክ ራቆትሺን የምወጪ እህቴ ሆይ ኒቃብም ለብሰሽ የምትሽከረከሪው እህቴ ሆይ ትገርሚኛለሽ ስት መከራ እና ስቃይ ብዙ ስብራቶችን ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ተደርሶነው በዚህ መንገድ ሳኡድ የሚገባው።
✅✅ ንቂ የተከበርሺው ሙስሊሟ እህቴ አሏህ ከዚህ በረሀ እዳትቀሪ አቅሙንና ጉልበቱን ሰቶሽ እዚህ ደርሰሽ አሏህን የሚስቆጣውን ስራ አትስሪ ተሰተሪ ክብርሺን በሂጃብሽ ስር )< ሂጃብሺን ደግሞ በሚዲያ ፎቶ መነሻ ሳይሆን ልክ እንደታዘዝሺው ቀጥ በይበት✅
كوني كما أمركِ الله، واحفظي كرامتكِ ودينكِ
وقال الله تعالى في قران الكريموَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ} (النور: 31). ልብ በይ ኢተቂሏህ ኦኽቲ الحجاب العظيم ليس مجرد غطاءٍ للصور ولفت الانتباه في وسائل التواصل، بل هو عفة، وحياء، وستر، وامتثالٌ تام لأمر الله عز وجل. كوني كما أمركِ الله، واحفظي كرامتكِ ودينكِ.
