uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Відкрити в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
914
Підписники
-324 години
-177 днів
+5330 днів
Архів дописів
العذر بالجهل عند الشيخ ابن عثيمين رحمه الله. 1- تفصيل الشيخ حول المسألة. https://youtu.be/DcX9WmQs7io 2- العذر يكون في أصول الدين، وأن التكفير منوطٌ بالتفريط. https://youtu.be/8boehNNH7ts 3- اشتراط الشيخ فهم الحجّة وليس مجرّد البلوغ لإقامة الحكم. https://youtu.be/laXHEOzemwY 4- ضوابط التكفير عند الشيخ. https://youtu.be/-t2C038znK4 5- تأكيد الشيخ على مذهب الإعذار عند الإمام ابن تيمية وابن عبدالوهاب، ونقل كلام لهما. https://youtu.be/mguKzsL1Hck 6- مدح الشيخ للعالم الذي يعذر الجاهل، ويبيّن الموقف الصحيح منه. https://youtu.be/Tt2cdrFL0c8 7- تكفير المعيّن عند الشيخ. https://youtu.be/KWzmgzNd1OE 8- تفصيل موانع تكفير المعيّن. وتقرير القاعدة الصحيحة في ذلك. https://youtu.be/2yTB1pFJPOY 9-مناقشة الشيخ في مسألة العذر بالجهل. https://youtu.be/I43sQgejFBs 10- نسبية (افتراضية) ظهور المسألة وخفاءِها. والرد على من يقول لا يعذر بالجهل في المسائل الظاهرة. https://youtu.be/IhEnGAV13K0 11- تفصيل الشيخ في مسألة الإعذار، ونصيحته بعدم التسرع في التكفير. https://youtu.be/M2sASNjOxF8

የአላህ እርግማን በሳሂሮች ላይ ይሁን! በነሱ ሰበብ የስንቱ ሞቅ ያለ ጎጆ ፈረሰ... የስንቱ ብሩህ ወጣት የተስፋ ብርሃን ጨለመ... ስንቷስ ንፁህ እህታችን በስቃይ አረረች... የሰውን ደስታ ነጥቆ መኖር ከምንም በላይ ያማል።

እማዬ ግፉን ችለህ ተማር ብላሀለች እሽ!? "እንዲህም ይጠናል" ============== የኔ ቤት አንተ ነህ እኔ እቤት አልገባም፡ ተማር ያልፍልናል አጥና የኔ ልባም፡ እናትህ እያለሁ ልጄማ አታነባም፡
እማዬ ግፉን ችለህ ተማር ብላሀለች እሽ!? "እንዲህም ይጠናል" ============== የኔ ቤት አንተ ነህ እኔ እቤት አልገባም፡ ተማር ያልፍልናል አጥና የኔ ልባም፡ እናትህ እያለሁ ልጄማ አታነባም፡ በችግሮች መሃል፤ ፅኑና ታታሪ ጀግና እናት ስትኖርህ፡ ከቆራጥነት ጋር፤ ተስፋ እያሳየች ነው የምታስተምርህ፡ ህይወት ካዋሳት ህግ፤ የሆነችውን ነው ለልጇ እምትነግርህ!! ....ይህችን ጀግና አየሀት...!? ....ምክሯንስ ሰማሀት....!? ...አስተውለሀል ወይ ያላትን ብልሀት..!? ...ደርባባ እናትህን እንደት አገኘሀት..እ..!? ይህች ሚስኪን እናት፤ ጎዳና ዳር ሆና በቆሎ እየሸጠች፡ በሀሳብ ጥላ ስር፤ ኑሮን ለማሸነፍ እንደተቀመጠች፡ በጨለመ ጊዜ፤ በእጇ ትንሽ ባትሪ ይዛ እንደጨበጠች፡ በወኔ ተሞልታ፤ እማዬ ለልጇ ይህን ተስፋ ሰጠች፡ ስማማ የኔ ውድ፤ በርታ ብለህ ተማር ልጄ እንዳትከፋ፡ ፅና ልክ እንደኔ፤ ብቻ ለስኬትህ አንብብ አጥና ልፋ፡ በዚህች በኛ ሐገር... እንደያዝኩት መብራት ጭላንጭል ነው ተስፋ። ስለዚህ የኔ ልጅ፤ ችግሮችን አልፈህ ደምቀህ እንድታብብ፡ እኔም ባንተ ስኬት፤ እንባየን እንዳብስ ዛሬ በባትሪ አንብብ፡ ጠንክርልኝ ልጄ፤ በየጎዳናው ላይ መኪና አትመልከት፡ እኔን ብቻ ስማኝ፤ አታስተውል ሌላ አልባሌ ስብከት፡ ከእኩዮችህ ጋራ፤ አትራጭም ውሀ አታጋጭም ቆርኪ፡ ሳትከፋ ስማኝ፤ ከሀብታም ልጆች ጋር የለህም ንክኪ፡ አትራቅ ከጎኔ፤ እኔ ባትሪ ልያዝ አንተም አንብብ እስኪ፡ ይገባኛል ልጄ፤ የጓደኞችህ ድምፅ ያጓጓል ያስቀናል፡ እኔም ይቆጨኛል፤ አቅማችን ይችናት ታዲያ እንደት ይሆናል፡ አይዞህ ህልም ካለ፤ ከጎዳናው ዳር ላይ እንዲህም ያጠናል፡ 👉..በርታ ልጄ...አይዞህ...!! .....በኑረዲን አል-አረብ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ሰላም ለእነዛ ለአይናችን እሩቅ ለልባችን_ግን_እጅግ ቅርብ ለሆኑት ለአላህ ብለን ለምንወዳቸው ለአላህ ብለው ለሚወዱን በተውሂድ መንገድ ላስተሳሰረን 💧    የሰው ልጅ ለአላህ ብሎ ከተዋደደ የአገር እሩቅ በጫራሽ የልብን ፍቅር አይቀንሰውም ብቻ እኛ ንያችንን እናስተካክል ። የአላህ ሰላምእና እዝነት አይለያችሁ http://t.me/Asselefya2

ማን እንደ እናት! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ﷺ) ዘንድ መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ ﴿يا رَسولَ اللَّهِ، مَن أحَقُّ النّاسِ بحُسْنِ صَحابَتِي؟ قالَ: أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أبُوكَ﴾ “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ማነው ለኔ ከሰዎች ጥሩና እውነተኛ ወዳጅ አድርጌ ልይዘው የሚገባ?  “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው: “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው:  “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው:  “አባትህን” አሉት።” 📚 ቡኻሪ (5971) ሙስሊም (2548) ዘግበውታል ©

*أدعيةُ الأنبياءِ عليهم السلام*✦ • * رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنْزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ* * رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنْتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ* * رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ* *وَمِنْ ذُرِّيَّتِي رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ* * رَبِّ إِنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنْتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ* * رَبِّ إِنِّي مَغْلُوبٌ فَانْتَصِرْ* * رَبِّ اشْرَحْ لِي صَدْرِي وَيَسِّرْ لِي أَمْرِي* *رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي فَاغْفِرْ لِي*

ከአገር መፍረስ ባሻገር ~ አገር እንድትፈርስ የሚመኙ፣ አገር ለማፍረስ የሚጥሩ፣ ለአገር አፍራሾች ድጋፍ የሚሰጡ ብዙ ሰዎች አሉ። ወንድሜ ሆይ! እውነት በሃገር መፍረስ የምታተርፍ መስሎህ ነው? ለመሆኑ አገር ሲፈርስ ምን ምን ሊከሰት እንደሚችል አሻግረህ ተመልክተሃል? ወይስ በሆኑ አካላት ላይ ያለህ ጥላቻና ቁጭት በሩቅ እንዳትመለከት ሸፍኖብሃል? ወንድሜ አገር ዳቦ አይደለም ፤ እንደዋዛ ቆራርሰህ በመካፈል አትገላገልም። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ይፈናቀላሉ። እንኳን አገር ፈርሶ በብሄር ግጭትና ጥቃት ብቻ የሚሊዮኖች ህይወት ተመሰቃቅሏል። ምናልባት አንተ ከሚፈናቀሉት ባትሆን እንኳ ራስህን በነሱ ጫማ ላይ አድርገህ ተመልከት። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ትዳር ይፈርሳል። ከሌላ ብሄር ጋር የተጋቡ ወገኖቻችን እጅግ ብዙ ናቸው። ይሄ ዘር እየለየ የሚገድል ትውልድ የሚተዋቸው እንዳይመስልህ። ስንት ቤተሰብ እንደሚበተን ተመልከት። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ንብረት ይወረሳል። እንኳን አገር ፈርሶ ሰላም በመጥፋቱ ብቻ የስንቱ ምስኪን ንብረት በተለያዩ ክልሎች በጉልበተኛ ተነጥቋል! * ሃገር ሲፈርስ እዚያም እዚህም መቋጫ የሌለው የድንበር ግጭት ይነሳል። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በሶማሊና በኦሮሞ የድንበር ግጭት ከሚሊየን በላይ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው አፋርና ዒሳ በየጊዜው የሚጋደለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው ዘጠኝ መቶ ሺ አካባቢ የጌዲዎ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው የወሎ ኦሮሞና የሸዋ አማራ የሚጋጨው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በደቡብ ክልል የተለያዩ ህዝቦች መካከል ግጭት የሚቀሰቀሰው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው "ወሎ ኦሮሞ ነው"፣ "ወልቃይት፣ ደራ፣ በረራ፣ መተከል አማራ ነው" የሚል ጩኸት የምንሰማው፡፡ ሃገር ከፈረሰ እነዚህ ጩኸቶች ዛሬ ከምናየው በላይ ሚሊዮኖችን የሚበላ እሳት ይቀሰቅሳሉ። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ነፍስ ይጠፋል። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ መጨረሻቸው እልቂት ነው። * ምናልባት መልኩ ይቀየር ካልሆነ በስተቀር በሃገር መፍረስ ጭቆና የሚቀር፣ ለድሃ ቀን የሚወጣ እንዳይመስልህ። ወላሂ! ዘር እየለየ፣ ሃይማኖት እየመረጠ በሚገድል ቡድን፣ ከርሱን በሚያስቀድም ፖለቲከኛ መቼም ፍትህና ነፃነት አታገኝም። የሚሻለው በጋራ ለሰላምና ለፍትህ መጣር ነው። መፍትሄው እንደ ህዝብ ከገጠመን የስነ ምግባር ዝቅጠት ለመውጣት ተባብሮ መሥራት ነው። ችግራችን ስር የሰደደ ነው። ችግራችን በማህበረሰብ ደረጃ የተንሰራፋ ነው። ስለ መንግስት ችግር ጧት ማታ ማውራቱን እንደ ንቃት ቆጥረን እራሳችንን እየሸወድን እንጂ እንደ ህዝብ መተዛዘናችን ሳስቶ መጨካከን ነግሶብናልኮ። ~ በየገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየተቋሙ ህዝብ የሚያጉላላው፣ ... ሁሉ ምንም ስቅ ሳይለው ስለ ፍትህ እየወሸከተ ነው። ~ ለብዙዎች ከትምህርት ገበታ መራቅ ሰበብ የሚሆነው፣ ዘርና ሃይማኖት እየለየ ተማሪዎቹን የሚያከላፍተው አስተማሪ ምንም ሳያፍር ስለ ፍትህና ርትእ እየጮኸ ነው። ~ ታካሚዎቹን ፊቱን አጨፍግጎ የሚያስተናግደው፣ በግዴለሽነት የሰው ነፍስ ላይ የሚቀልደው፣ ለርካሽ ጥቅም ሲል የማይገናኝ ምርመራ እያዘዘ ደካማ ወገኑ ላይ ጭካኔ የሚፈፅመው ሃኪም እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚጮኸው! ~ የተበላሸ ምግብ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት፣ ፎርጂድ እቃ፣ የተጭበረበረ ምርት፣ ... የሚሸጠው ነጋዴ እኮ ነው "መስራት አቃተን" እያለ የሚያለቅሰው። ~ ፍትህ በገንዘብ የሚሸጠው፣ ከሌባ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው፣ እምነትና ብሄር እየመረጠ ፍትህ የሚቀብረው ዳኛና ፖሊስ እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚዘፍነው። ~ ሚሊዮኖች የወጡበትን መሬት ሶስት አራት ካርታ ሰርቶ የሚቸበችበው ሰራተኛ፣ የሚሊዮኖችን ውሃና መብራት እየቆረጠ ሺ ጊዜ ብር  እየተቀበለ የሚቀጥለው ሌባ እኮ ነው ስለ ፍትህና ስለ ነፃነት የሚለፍፈው። ~ መንገዶችንና ህዝባዊ ተቋማትን ከደረጃ በታች እየሰራ በሀገር በወገኑ ላይ የሚቆምረው እኮ ነው ለሀገር ለወገኑ ተቆርቋሪ መስሎ የሚፈተፈተው። ~ መኪናና ሞተር ሳይክል አዘጋጃቶ፣ አንድ ላምስት ተደራጅቶ የሚዘርፈው፣ ህፃናት እያፈነ የሚወስደውኮ ነው እኩል ስለ ፍትህ የሚያወራው! ~ የሁለት ቀን ጨቅላ፣ የ70 አመት አዛውንት፣ አቅመ ደካማ ሴቶችን ሳይቀር የሚገድለው እኮ ነው የነፃነት ታጋይ የሚባለው። እስኪ በየትኛው ዘርፍ ነው የሚነሳ ጥሩ ነገር ያለን? ፖለቲከኞቹ የኛው ነፀብራቆች ናቸው። እኛኑ ነው የሚመስሉት። ከኛው የወጡ እንጂ ከሌላ ፕላኔት የመጡ አይደሉም። ክፋታቸው ክፍታችን፣ ንቅዘታቸው ንቅዘታችን ነው። እንደ ህዝብ በዚህ ደረጃ መልካሞች የመነመኑ ከሆኑ እንዴት ነው ፍትህና እፎይታ የምናገኘው? በቅድሚያ በራሳችን ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ወደተነሳሁበት ስመለስ፣ ስግብግብ ስሜታችን እየጋረደን፣ ቁንፅል አመልካከታችን እየሸወደን እንጂ በርግጠኝነት በሃገር መፍረስ እንደ ህዝብ ከሳሪዎች እንጂ አትራፊዎች አይደለንም። ስለዚህ ደግመን ደጋግመን ልንመለከት፣ ከጥፋት ልንርቅ፣ ለአጥፊዎች ጉልበት ከመሆንም ልንጠነቀቅ ይገባል። ጥፋትን ማስቆም ባንችል እንኳ ቢያንስ ተጋሪ ባለመሆን የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል። = https://t.me/IbnuMunewor

🌿 የእርጉዝ ሴት አምሮት በባህሪዋ ላይ ያለው ተፅዕኖ 🌸 📌 የሞሮኮ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله ተጠየቁ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌸 ጥያቄ፦ የሴት አምሮት (الوَحَم) በሴቶች ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰተው እውነተኛ ነገር ነውን? ወይስ ተራ ምናብና ቅዠት ብቻ ነው? አላህ መልካም ዋጋ ይክፈልዎትና። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 መልስ፦ الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على من أرسله الله رحمة للعالمين، وعلى آله وصحبه وإخوانه إلى يوم الدين، أما بعد: የእርጉዝ አምሮት (الوَحَم) በአረብኛ ቋንቋ የታወቀ ቃል ሲሆን፣ እርጉዝ ሴት የምትመኘውንና በዚያ ወቅት የምትፈልገውን ነገር ያመለክታል። ይህም በታዋቂ የአረብኛ መዝገበ ቃላት የተጠቀሰ ትርጉም ነው። 🌿 ነገር ግን ዛሬ ሰዎች ስለ «አምሮት» የሚናገሩት ሌላ ነገር አለ። እሱም እርጉዝ ሴት አንድን ነገር በጣም ከፈለገች፣ ያ ፍላጎቷ ካልተሟላላት፣ በሆዷ ያለው ልጅም እርሷ የፈለገችውን ነገር የሚመስል ምልክት ወይም ጥቁር ምስል በሰውነቱ ላይ ይዞ ይወለዳል ይጠቁራል የሚለው እምነት ነው። ይህንን ግን በሸሪዓ ውስጥ መሠረት የሌለው ነገር ነው። እንዲሁም ይህ እምነት በሚታመን የሸሪዓ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን አላውቅም። 🌿 ይህ ነገር በተለይ በሴቶች አንደበት የሚዘወተር እምነት ነው። እንደዚህ ያለው ነገር በሸሪዓ ውስጥ የታወቀና አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ በዲን ውስጥ የታወቀ ይሆን ነበር፤ ነቢዩ ﷺም ለሰዎች በግልጽና በበቂ ሁኔታ ያስረዱት ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ይህንን ጉዳይ በጣም ይፈልጉት ነበር፤ ለሁሉምም የሚመለከት ጉዳይ ነውና። 🌿 ነቢዩ ﷺ የተላኩትን መልዕክት በሙሉ አድርሰዋል፣ አደራውንም በትክክል ተወጥተዋል። አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ብሏል፦ ﴿ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗاۚ﴾ “ዛሬ ዲናችሁን ለእናንተ ሞልቼላችኋለሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ሞላሁ፤ እስልምናንም ለእናንተ ዲን አድርጌ ወደድኩላችሁ።” 📖 [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 3] ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 ነቢዩ ﷺ መልዕክቱን በሙሉ ማድረሳቸውን እንዲህ ብለው ለሰሐቦቻቸው አረጋግጠዋል፦ «أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟» “እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?” እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ። እንደገና፦ «أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟» “እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?” እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ። ከዚያም ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ «اللَّهُمَّ اشْهَدْ، فَلْيُبَلِّغِ الشَّاهِدُ الْغَائِبَ» “አላህ ሆይ! መስክር! እዚህ ያለው ለሌለው ያድርስ።” ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌸 ነገር ግን እርጉዝ ሴት በዚያ ወቅት ልዩ እንክብካቤ አያስፈልጋትምን? በእርግጥ ያስፈልጋታል። 🌷 ሸይኹ رحمه الله እንደሚገልጹት፣ ሴቷ በዚያ ወቅት ተጨማሪ እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ርኅራኄና ትኩረት ልትፈልግ ትችላለች። ስለዚህ ባል የባለቤቱን ሁኔታ ሊያስተውል፣ በርኅራኄ ሊያስተናግዳት፣ በተቻለውም መጠን የምትመኘውን ነገር ሊያሟላላት ይገባል። ብለዋል። 🌿 በዚህ ጊዜ እሷን ማስጨነቅ ማለት በእርግዝናዋ ላይ ተጨማሪ ጫና ማስገባት ነው። ስለዚህ ባል ከባለቤቱ ጋር በመልካም ሁኔታ ይኑር፤ ሁኔታዋንም ያስተውል፤ የሚያስፈልጋትንም ነገር በቻለው መጠን ያሟላላት። 💎 ይህንን ሲያደርግም ከአላህ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ ያድርገው። አላህ سبحانه وتعالى ምንዳን የሚሰጥ ከሁሉ የተሻለ ነው። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 ለጀግና ለባሎች የሚሆን ማስታወሻ ሚስትህ እርጉዝ ስትሆን በሰውነቷ ውስጥ አንድ ሕይወት እየተሸከመች ነው። ስለዚህ በዚያ ወቅት የምትፈልገውን በማድረግ ደስ ብሎህ አግዛት፤ ድካሟን በርኅራኄ ተመልከት፤ በቃልህም አጽናናት። 🌷 እርግዝናዋ የሚያልፍ ወቅት ነው፤ ነገር ግን በዚያ ወቅት ያሳየኸው ርኅራኄ በልቧ ውስጥ ረጅም ጊዜ ሊቀር ይችላል። 🌿 ትዳር የሚያምረው በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱ ሲደክም ሌላው እጁን ሲይዘው ነው። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ اللَّهُمَّ احْفَظْ نِسَاءَ الْمُسْلِمِينَ وَأَجِنَّتَهُنَّ وَارْزُقْهُنَّ الصِّحَّةَ وَالْعَافِيَةَ، وَأَصْلِحْ بُيُوتَهُنَّ، وَاجْعَلْ بَيْنَ الْأَزْوَاجِ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً وَسَكِينَةً. “አላህ ሆይ! የሙስሊም ሴቶችንና በማህፀናቸው ያሉትን ልጆቻቸውን ጠብቅልነረ፤ ጤናና ደህንነትን ስጣቸው፤ ቤቶቻቸውንም አስተካክልላቸው፤ በባሎችና በሚስቶች መካከልም ፍቅር፣ ምሕረትና ሰላም አድርግላቸው።” 🌸 📌 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله 🇩🇿 አልጀሪያ — 22 ረጀብ 1426ሂ / 17 ኦገስት 2005 🌿 العِلْمُ عِنْدَ اللهِ تَعَالَى 🌿 الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين. t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

የማለዳ መልእክት (50) ~ በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ
የማለዳ መልእክት (50) ~ በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ የመስጂድ ግንባታ ላይ መሳተፍ፣ ውሃ ማውጣት፣ የደዕዋ ስራን ማገዝ፣ የወቅፍ አገልግሎት፣ ወዘተ. (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 20/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ~ የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦ https://t.me/IbnuMunewor/9934 ክፍል 1↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9938 ክፍል 2↓
የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ~ የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦ https://t.me/IbnuMunewor/9934 ክፍል 1↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9938 ክፍል 2↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9943 ክፍል 3↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9954 ክፍል 4 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9991 ክፍል 5↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10000 ክፍል 6↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10005 ክፍል 7 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10033 ክፍል 8↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10041 ክፍል 9 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10051 ክፍል 10↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10124 ክፍል 11↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10134 ክፍል 12 https://t.me/IbnuMunewor/10164 ክፍል 13 https://t.me/IbnuMunewor/10176 ክፍል 14 https://t.me/IbnuMunewor/10177 ክፍል 15 https://t.me/IbnuMunewor/10181 ክፍል 16 https://t.me/IbnuMunewor/10217

~ከሳዳት ተማሩ የሀበሻው ንጉስ ኡስታዝ ሳዳት ከማል መርሁ ወጥ ነው እውነት ያስቀድማል በዲን መዋሸትን በጥብቅ ይቃወማል ወቀሳን ሳይፈራ፣ ለዲን ዘብ ይቆማል የሽርክን ወረርሽኝ፣ በጥበብ ያክማል የቢድዓን ተውሳክ፣ በድፍረት ያርማል ውለታህ ብዙ ነው የተውሒዱ ጀግና የሱናው ነፀብራቅ፣ ስምህ ነው ገናና ድምፅህ ያስተጋባል በሁሉም ቀጠና ጠላት ያ ደ ን ቅ ሃ ል ወዳጅ  ይቅርና የኛ ቆራጥ ጀግና፣ ግልፅ ነው ቀመሩ እውነት አትደብቁ ውሸት አትቀባጥሩ በዲን ስም አትዋሹ ያለዒልም አታውሩ ሰዎች መንገድ ለቀው ውሸትን ካወሩ መልስ ይሰጣቸዋል ሳዳት መምህሩ አ ያ ስ ጨ ን ቀ ው ም  ሀገር እና ዘሩ ለ "ፍ ት ህ" መቆምን ከሳዳት ተማሩ = t.me/Abu_lmran_Alaseriy

በለሆሳስ ውስጥ ያለ አደብ ~ አንዳንዶች ዱዓአቸው ልክ እንደ መፈክር በሃይለ ቃል የታጀበ ነው። ሰው ፊት ለልመና ቢቆም የማያደርገውን ጌታውን ሲማፀን ግን አደብ ያጣል። ዱዓአችን መተናነስ፣ ዝቅ ማለት የጎላበት ሊሆን ይገባል። ድምፃችን ሰበር ሁኔታችን ዝቅ ሲል ይበልጥ ለላቀ ለአደብ የቀረበ ይሆናል። ከፍ ያለው አላህ ስለ ነብዩ ዘከሪያ ሲያወሳ እንዲህ ይላል፦ { إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَاۤءً خَفِیࣰّا (3) قَالَ رَبِّ إِنِّی وَهَنَ ٱلۡعَظۡمُ مِنِّی وَٱشۡتَعَلَ ٱلرَّأۡسُ شَیۡبࣰا وَلَمۡ أَكُنۢ بِدُعَاۤىِٕكَ رَبِّ شَقِیࣰّا (4) } {ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)። አለ "ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴ ደከመ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ፤ አንተም በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምንጊዜም) ዕድለ ቢስ አልሆንኩም፡፡"} [መርየም፡ 3-4] ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ዝቅ ባለ ድምፅ የሚደረግ ጥሪ በውስጡ ጥልቅ ኣደብ አለበት። ከንጉሳን ዘንድ ድምፅ ከፍ አይደረግምና።" [ መጅሙዑል ፈታዋ፡ 15/15] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡

የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ልጆች ~ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ስድስት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ በድምሩ ሰባት ልጆች ነበሯቸው። [ሀ] የ"ኣሉ ሸይኽ" (የሸይኽ ቤተሰብ) ዝርያ የቀጠለባቸው
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ልጆች ~ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ስድስት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ በድምሩ ሰባት ልጆች ነበሯቸው። [ሀ] የ"ኣሉ ሸይኽ" (የሸይኽ ቤተሰብ) ዝርያ የቀጠለባቸው አራት ልጆች ናቸው። ዛሬ ድረስ በሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ "እከሌ ኣሉ ሸይኽ" እየተባሉ የሚጠሩት የእሳቸው ዝርያዎች ናቸው። ይሄ የእሳቸው ዝርያ የቀጠለው በአራቱ ልጆቻቸው በኩል ሲሆን፣ ሁሉም ታላላቅ ዐሊሞችና ዳኞች ነበሩ። እነሱም፦ 1. ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦ ከአባታቸው በኋላ በዲርዒያህ ከተማ ውስጥ ዳኛ (ቃዲ) ሆነው አገልግለዋል። ታላቅ ዐሊም እና የዲርዒያህ መስጂድ ኢማም ነበሩ። * ከእሳቸው የ"ኣሉ ሑሰይን" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ ተዘርግቷል። 2. ሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦ ከታላላቅ ዐሊሞችና ፀሐፊዎች አንዱ ነበሩ። ዲርዒያህ ውስጥ ቃዲ የነበሩ ሲሆን፣ ዲርዒያህ ከግብፅ በተነሳው የኦቶማን ቱርክ ጦር ስር ስትወድቅ ወደ ግብፅ ተወስደው እዚያው ሞተዋል። * ከእሳቸው በኩል የ "ኣሉ ዐብዲላህ" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ የተገኘ ሲሆን፣ "ተይሲሩል ዐዚዝል ሐሚድ" የተሰኘውን ታዋቂው የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁት ልጃቸው ሱለይማን ብኑ ዐብዲላህ ናቸው። 3. ሸይኽ ዐሊይ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1245 ሂ.)፦ ታላቅ የፊቅህ ዐሊምና አላህን ፈሪ ሰው ነበሩ። የዳኝነት ሹመት ቢቀርብላቸውም አልተቀበሉም። * ሙሐመድ ከተሰኘው የእሳቸው ልጅ የ "ኣሉ ዐሊይ" ወይም "ኣሉ ሙሐመድ" ቅርንጫፍ ተገኝቷል። 4. ሸይኽ ሐሰን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ አባታቸው በሕይወት እያሉ ነው የሞቱት። ነገር ግን "ፈትሑል መጂድ" የተሰኘውን ታዋቂ የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁትን ልጃቸውን ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንን ተክተው አልፈዋል። ከእሳቸው የ"ኣሉ ሐሰን" ቅርንጫፍ ተዘርግቷል። [ለ] ሌሎች ልጆች (ዝርያ ያልቀጠለባቸው) 1. ሸይኽ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1250 ሂ.)፦ እውቀት ያላቸው ዐሊም ነበሩ። በዲርዒያህ የማስተማሪያ ሐለቃህ ነበራቸው። በኋላም ወደ ግብፅ ሄደው እዚያ ነው የሞቱት። 2. ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ በልጅነታቸው በአባታቸው የሕይወት ዘመን ነው የሞቱት። 3. ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ የተከበረች ዐሊማ (የእውቀት ባለቤት) የነበረች ሲሆን ተማሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተምሩ ነበር። ዲርዒያህ በኦቶማን ጦርነት በወደቀች ጊዜ ተሰዳ ቆይታ በመጨረሻም በሪያድ ከተማ ሞታለች። አስተውሉ! ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ከአንድኛው በስተቀር ልጆቻቸውን በሙሉ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች ስም ነው የሰየሟቸው። ዐብዱላህ፣ ኢብራሂም እና ፋጢማ በቀጥታ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጆች ስም ሲሆን ሐሰን እና ሑሰይን ደግሞ የልጅ ልጆቻቸው ስም ነው። ዐሊይ ደግሞ የነብዩ ዐለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ እና አማቻቸው የሆነው የታላቁ ሶሐቢይ ስም ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

عَلِمْتُ أَنَّ رِزْقِي لَنْ يَأْخُذَهُ غَيْرِي، فَاطْمَأَنَّ قَلْبِي. وَعَلِمْتُ أَنَّ قَدَرِي لَنْ يُغَيِّرَهُ قَلَقِي، فَهَدَأَتْ نَفْسِي. وَعَلِمْتُ أَنَّ رَاحَتِي فِي ذِكْرِ اللهِ وَحْدَهُ، فَذَكَرْتُهُ. وَعَلِمْتُ أَنَّ عُمْرِي مَحْدُودٌ، فَلَنْ أَعِيشَ بَعْدَهُ، فَزَهِدْتُ فِي الدُّنْيَا. وَعَلِمْتُ أَنَّ الصَّبْرَ يُدْخِلُنِي جَنَّةَ رَبِّي، فَشَكَرْتُ رَبِّي. أَرَادَ إِخْوَةُ يُوسُفَ عَلَيْهِ السَّلَامُ أَنْ يَقْتُلُوهُ، فَلَمْ يَقْتُلُوهُ. ثُمَّ أَرَادُوا أَنْ يَمْحُوا أَثَرَهُ، فَارْتَفَعَ شَأْنُهُ. ثُمَّ بَاعُوهُ بِثَمَنٍ بَخْسٍ لِيَكُونَ مَمْلُوكًا، فَأَصْبَحَ عَزِيزًا فِي مِصْرَ. ثُمَّ أَرَادُوا أَنْ يَمْحُوا حُبَّهُ مِنْ قَلْبِ أَبِيهِ، فَازْدَادَ حُبُّ أَبِيهِ لَهُ. فَلَا تَقْلَقْ مِنْ تَدَابِيرِ النَّاسِ، فَإِنَّ تَدْبِيرَ اللهِ فَوْقَ كُلِّ تَدْبِيرٍ، وَاللهُ فَعَّالٌ لِمَا يُرِيدُ. يَقُولُ لِلشَّيْءِ: كُنْ، فَيَكُونُ. فَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ. https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

Repost from Abu Hayder Aliy
🕊️ ስለ መገዳደልና ሰላም ትንሽ ልበል :- የሰው ልጅ ሕይወት በአላህ ዘንድ የተከበረ ነው። አንዱ ሰው በሌላው ላይ ጥቃት ማድረስ፣ ደም ማፍሰስና መገዳደል እጅግ ከባድ ጉዳይ ነው። 📖 አላህ ﷻ
🕊️ ስለ መገዳደልና ሰላም ትንሽ ልበል :- የሰው ልጅ ሕይወት በአላህ ዘንድ የተከበረ ነው። አንዱ ሰው በሌላው ላይ ጥቃት ማድረስ፣ ደም ማፍሰስና መገዳደል እጅግ ከባድ ጉዳይ ነው። 📖 አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ﴾ «አላህ የከለከለውን ነፍስ በሕጋዊ ምክንያት ካልሆነበስተቀር አትግደሉ።» 📖 አል-ኢስራእ፡ 33 እንዲሁም አላህ ﷻ ይላል፦ ﴿وَمَنْ يَقْتُلْ مُؤْمِنًا مُتَعَمِّدًا فَجَزَاؤُهُ جَهَنَّمُ خَالِدًا فِيهَا﴾ «አንድን ሙእሚን ሆን ብሎ የገደለ ሰው ቅጣቱ ገሀነም ነው።» 📖 አን-ኒሳእ 4፥93 ነቢዩ ﷺም እንዲህ ብለዋል፦ «سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ» «ሙስሊምን መስደብ ፉሱቅ ነው፤ ከእርሱ ጋር መዋጋት ደግሞ ኩፍር ነው።» 📚 ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም አላህ ﷻ ይላል፦ ﴿وَالصُّلْحُ خَيْرٌ﴾ «እርቅ የተሻለ ነው።» 📖 አን-ኒሳእ፡ 128 🌿ስለዚህ የሚያስፈልገን ጥላቻ ሳይሆን ሰላም፣ መገዳደል ሳይሆን እርቅ፣ መበቀል ሳይሆን ይቅርታ ነው። 🌿እያንዳንዳችን ከራሳችን እንጀምር፤ ቃላችን ግጭትን እንዳያባብስ፣ እጃችን ጉዳትን እንዳያመጣ፣ ልባችንም ለወንድማችን ምሕረትን እንዲይዝ። 🤲 አላህ ሆይ! በኢትዮጵያ እና በሁሉም የሙስሊሞች አገሮች ሰላምን አውርድልን። ደም መፋሰስንና መገዳደልን አስወግድልን። ልቦቻችንን አስታርቅልን፣ በመካከላችንም ፍቅርንና ወንድማማችነትን አጠናክርልን። አሚን🤲። 🕊️ السَّلَامُ خَيْرٌ لِلْجَمِيعِ https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

Repost from Abu Zekeriya #1
أين أنتم يا إخوتي؟ 👉የት ገቡ እነዛ ዘብ ጠንካራ ወንድሞች ምን ዋጣቸው ?? 👉ተማሪ ሳለን በ አሚርነት እንዲሁም የጀማዓ ስራ ላይ ሲሳተፉ የነበሩ እና የተሾሙ ጀማዓዎን በሚገርም ጥበብ ሲመሩ የነበሩ ?? 👉በየ ዩኒቨርሲቲው የጀማዓው ቀኝ እጅ የነበሩ ?? 👉 ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደካማ ወንድም እህቶችን በማገዝ ሲተጉ የነበሩ ?? 👉በየ ሰፈሩ የጀማዓው ልብ የነበሩ ?? 👉በየ መድረሳው እና መሳጂዶች ላይ ለሱና ሲተጉ የነበሩ የት ናቹህ በአላህ ?? :- ديوان أبي تمام إِذَا ما انقَضَى يومٌ بِشَوْقٍ مُبَرِّحٍ أتى باشتياقٍ فادحٍ بعدَهُ غَدُ فلم يبقَ مني طولُ شوقي إليهم سوى حسراتٍ في الحَشا تتردّدُ አንድ ቀን በከባድ ናፍቆት ከተጠናቀቀ ከእርሱ በኋላ የሚመጣው ነገር ግን የበለጠ ከባድ ናፍቆት ይዞ ይመጣል። ለእነርሱ ባለኝ ረጅም ናፍቆትም፣ በውስጤ የሚመላለሱ የልብ ቁጭቶች ብቻ ቀርተውኛል። أين أين أين ,,,,؟؟؟ ወንድም / አቡ ዘከሪያ https://t.me/Abuzekeriya01

ጥንካሬ ከስንፍና ጋር የሚደረግ የፍልሚያ ውጤት ነው! በህይወት ውስጥ ትልልቅ ስኬቶችን ያስመዘገቡ፣ የሚታይ ለውጥ ያመጡ ሰዎች ስንፍናን አያውቁም ማለት አይደለም። ልዩነታቸው ስንፍና ሲፈታተናቸው በዝምታ ተቀምጠው አልተሸነፉም፤ ይልቅስ የዕለት ተዕለት የትግል ማዕበል ውስጥ ገብተው ድል አነሱ እንጂ። እያንዳንዱ ቀን የራሱ ፈተና አለው። ጠዋት ከምንጣፍ መነሳት፣ ሰነፍ ልብን "ዛሬም መስራት አለብኝ" ብሎ ማሳመን ከባድ ፍልሚያ ነው። ጥንካሬ ማለት ፈተና የሌለበት ህይወት መኖር አይደለም፤ ስንፍና እጅ እንድንሰጥ በሚጎትተን ሰዓት ጀርባችንን ሰጥተን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው። ስንፍና ዛሬን አፍኖ ነገ ላይ ይጥለናል። ጥንካሬ ግን ዛሬን ሰንጥቆ የነገን ድል ያበስራል። የሚገርመው ነገር፣ ጥንካሬ በአንድ ቀን የሚመጣ አይደለም። ልክ በጂም ውስጥ ጡንቻን ለመገንባት ከብደት ማንሳት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ የአዕምሮ እና የስራ ጥንካሬም በየቀኑ ከስንፍና ጋር ከሚደረግ ትግል የሚገኝ ውጤት ነው። ዛሬ ያሸነፍከው አነስተኛ ስንፍና፣ ነገ ትልቅ ስኬት ሆኖ ይመለስልሃል። መልካም ትግል። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

ለአስተውሎት ~ ፉዶይል ብኑ ዒያድ አንዱን ሰው “እድሜህ ስንት ነው” ብለው ጠየቁት። * "ስልሳ አመት" አለ። - "ስልሳ አመት ሙሉ ወደ ጌታህ እየተጓዝክ ነው፡፡ መድረሻህ ሳይቃረብ አይቀርም።" * "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!" (እኛ ለአላህ ነን፡፡ ወደሱም ተመላሾች ነን) - “ 'ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን' የሚለውን ተፍሲሩን ታውቃለህ? ለአላህ ባሪያ እንደሆነ ወደሱም ተመላሽ እንደሆነ የሚያውቅ እንደሚቆም ይወቅ፡፡ እንደሚቆም ያወቀ እንደሚጠየቅ ይወቅ፡፡ እንደሚጠየቅ ያወቀ መልስ ያዘጋጅ፡፡” * "ምንድን ነው መፍትሄው?" - "ቀላል ነው!" * "ምንድን ነው እሱ?" - "በቀረህ እድሜ መልካም ስራ፡፡ ያለፈው ይማርልሃል፡፡ ቀሪው እድሜህን ካጠፋህ ግን ባለፈውም በቀሪውም ትያዛለህ፡፡" ምንጭ፦ [ሒልየቱል አውሊያህ፡ 8/113] አስተውል። ስልሳ ዓመት ከደረስክም አስተውል። ስልሳ ካልደረስክም ገና ነኝ ብለህ አትዘናጋ ነቃ በል። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2005) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor