Orthodox mezemur ኦርቶዶክስ መዝሙር
Відкрити в Telegram
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ ። መዝሙረ ዳዊት 13 : 5 - 6 o:-)- ለማንኛውም ጥያቄ በስር ባስቀመጥነው ሊንክ ሊጠይቁን ይችላሉ 👇👇 - @tan_flf -
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
283
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
+2530 днів
Архів дописів
ባሕራንኒ ይቤ /፮/
ባሕራንኒ ይቤ ኦ ዘነገደ ባህር /፪/
ርዒክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቱ ዘይብል/፪/ ባህራንኒ ይቤ /፮/
የሞቱን ደብዳቤ - - - ቅዱስ ሚካኤል
ሚካኤል አጥፍቶ - - - ቅዱስ ሚካኤል
ባሕራንን አዳነው - - - ቅዱስ ሚካኤል በሠርግ ተክቶ - - - - ቅዱስ ሚካኤል
ሠዳዴ ሳጥናኤል - - - ቅዱስ ሚካኤል
ሊቀ መላእክት - - - - ቅዱስ ሚካኤል
እኛንም አድነን - - - - ቅዱስ ሚካኤል ከሲኦል እሳት - - - - - ቅዱስ ሚካኤል
አዝከሊቀ ነብያት - - - - ቅዱስ ሚካኤል ከነሙሴ ጋራ - - - - - ቅዱስ ሚካኤል ሕዘበ እሥራኤልን - - - ቅዱስ ሚካኤል ሚካኤል ሲመራ - - - ቅዱስ ሚካኤል ቀን ደመና ጥሎ - - - ቅዱስ ሚካኤል ሌሊት እያበራ - - - - - ቅዱስ ሚካኤል ተሻገሩ ኤርትራን - - - -ቅዱስ ሚካኤል ሁሉም በየተራ - - - - ቅዱስ ሚካኤል 🎤 ዘማሪ ዲ/ን ታዴዎስ ግርማ🎤 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 📎 👇 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀•✧══╮ https://t.me/Qmamaaa ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
✞♡አይኑ ዘርግብ♡✞
አይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ልዑለ መንበር ሐመልማለ ወርቅ ሰዐሌ ምሕረት ወመተንብል ረዳኤ ምንዱባን ዘአስተዓፀቡ ያቀልል
በነ ሰናክሬም ላይ ሰይፍን የመዘዘ
የሕዝቅያስ ምሕረት በእጁ የተያዘ
መዓቱን ለአህዛብ በሞት የገለጠ
የሕዝቅያስን ሞት በሕይወት የለወጠ
የእስራኤል ድንኳኖች በደስታ ተሞሉ
ክብር ለአምላካችን ይገባል እያሉ
መልአኩን የላከ ሕዝቡንም የረዳ
ግሩም ነው እግዚአብሔር ያወጣን ከእዳ
የሰናክሬም ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነው
የኔ ረዳቴ ግን ቅዱስ ሚካኤል ነው
ከፈረሰኞች በላይ ነው ፍጥነቱ
ከተዋጊዎቹ ይበልጣል ብርታቱ
እስራኤልን መና እንደመገባቸው
ባሕታውያንን በዱር የረዳቸው
ተክለኃይማኖትን ከጉድጓድ ያወጣ
እኔንም ሳይንቀኝ ሊያድነኝ መጣ
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀•✧══╮
https://t.me/Qmamaaa
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══
"ነፍስህን በዓለማዊ ወሬዎችና በሃሜት አትቀልባት፤ ልብህን ከባድና እረፍት ቢስ ያደርጉታልና። ሁልጊዜ ወደ ውጭ ብቻ የሚያይ አእምሮ በሮቹ እንደተከፈቱ ቤት ነው፤ ማንኛውም ሌባ በቀላሉ ሊገባበት ይችላል። ሐሳቦችህን ከእግዚአብሔር ጋር በውስጥህ ጠብቃቸው።"
+ ቅዱስ ሰራፊም ዘሳሮቭ +
መከራው ክርስትናዬን
መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
በሞት መንደር በሀዘን ውስጥ በመከራ
አየውት እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ
አዝ
ክርስትያን ተብለን በክርስቶስ ስም የተጠራነው
በጥልቁ ውስጥም በእግዚአብሔር እንድናምን ነው
ለጥቂት ግዜ ቢበረታብን ስደት ሀዘኑ
አምላክ ግን መውጫ ያዘጋጃል በዚህ ተፅናኑ
አዝ
በስደት ሳለን ካፋችን ቢደርቅ የፅዮን ዜማ
ከወንዙ አጠገብ ቁጭ ብለን ሰለን ድምፁን ሳንሰማ
በእግዚአብሔር ጊዜ ከባቢሎን ምድር እንለቃለን
መሰንቆአችንን ከአርያም ዛፍ ላይ እናወርዳለን
አዝ
ደካሞች ሲሉን በስሙ ያን ጊዜ እንበረታለን
ድሆች ስንባል ባለጠጎች እናደርጋለን
በምድር ቅዱስ ህዝብ አድርጎ ለእርሱ ለየን
ጨለማው አልፎ በቸርነቱ ብርሀን አሳየን
አዝ
ከፀጋ በላይ እንዳንፈተን ይከልለናል
በቁስላችን ላይ የፈውስን ዘይት ያፈስልናል
በጊዜም ቢሆን ያለ ጊዜውም በእርሱ እንፅና
እንኳን ስደቱን ሞቱን ሊገታው ይችላልና
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
✟ተዋህዶ እማማ✟
ኢ አማኒያኑ ቢጠሏትም
መስርቷቷልና ክርስቶስ በደም
የሐዋርያት ንፅህት ሐይማኖት
ልክ ናት ተዋህዶ ቅድስት
የሶስት ሺ አመት ታሪክ ያላት
የኢትዮጵያ ክብር አክሊል ናት
ምን አጥፍታ ነው ማንንስ በድላ?
ባላንጣ ትመስል እንዲ ምትጠላ?
እንደጠላት አይቷት ለፍርድ የቸኮለው?
ተዋህዶ ቅድስት ጥፋቷ ምንድነው?
ምንም አልበደለች ምንም ክፉ አልሰራች
በታሪክ አንድምታ ቀደምት ስለሆነች
ባዕድ እንዳይወርሰው ቅርሷን መሬት ቀብራ
እውነት ቢታይባት በዛባት መከራ
ተዋህዶ እማማ አይዞሽ አይክፋሽ
ይህም ቀን ያልፍና ነግቶ ታያለሽ
እኛም ልጆችሽ ነን አትሆኝም መካን
ክርስቶስ ነውና ያንቺ ሊቀ ካህን
ድንግል ብታነሳ ሠማዕታት ብትዘክር?
ፅላት አስቀርፃ በዓላት ብታከብር?
የክርስቶስ መስቀል ኃይል ነው ማለቷ?
እምዬ ኦርቶዶክስ ምንድነው ጥፋቷ?
ድንግል ማርያም ብትል ክርስቶስ ወልዳ ነው
ቅዱሳን ብታስብ አምላክ መርጧቸው ነው
ምንም ህጸፅ የላት ስንዱ እመቤት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህይወት መንገድ ናት
ተዋህዶ እማማ አይዞሽ አይክፋሽ
ይህም ቀን ያልፍና ነግቶ ታያለሽ
እኛም ልጆችሽ ነን አትሆኝም መካን
ክርስቶስ ነውና ያንቺ ሊቀ ካህን
ሰዓታት ቅዳሴ ማሕሌት መዝሙሩ
የቃልኪዳን ታቦት ማረፍያ መንበሩ
ስጋውና ደሙ ህይወት ነው ማለቷ
ተዋህዶንስ የቱ ነው ስህተቷ?
ቅዳሴ ብትቀድስ የአባቶች ስርዓት ነው
ፀናፅል ከበሮ ከያሬድ ተምራ ነው
ቀድማ የነበረች ጥንትም በሐዋርያት
የገነት መግብያ በር ተዋህዶ ንፅህት
ተዋህዶ እማማ አይዞሽ አይክፋሽ
ይህም ቀን ያልፍና ነግቶ ታያለሽ
እኛም ልጆችሽ ነን አትሆኝም መካን
ክርስቶስ ነውና ያንቺ ሊቀ ካህን
ኢ አማኒያኑ ቢጠሏትም
መስርቷቷልና ክርስቶስ በደም
የሐዋርያት ንፅህት ሐይማኖት
ልክ ናት ተዋህዶ ቅድስት
የሶስት ሺ አመት ታሪክ ያላት
የኢትዮጵያ ክብር አክሊል ናት/2/
ሾመኝ ለምስጋና
ሾመኝ ለምስጋና
ሳለሁ ብላቴና /2/
አሰለፈኝ ጌታ
ሞልቶኝ በእልልታ
አዝማለሜን አልሞ ከአጠገቤ ቆሞ ህልሜን ፈታውና ቃኘኝ ለምስጋና ብላቴናነቴን ወዶታል ልሳኔን ፊቱ ብኮላተፍ ሰማኝ ሳይፀየፍ
አዝበነፃነት ልቁም ስለፍቅሩ ላዚም አባት ከአባት በላይ ስላለኝ በሰማይ ለልጅነት ልቤ ፅናት ነው ገንዘቤ መደነቂያ አረገኝ ለፍቅሩ ለይቶኝ
አዝወደርሱ እንድመጣ ከልካዬን ተቆጣ አኖረኝ በእቅፉ ቀባኝ በመዳፉ በክንዱ ነኝ ዛሬ ለክብሩ ዝማሬ ሜልኮል ተገረሚ ምስጋናውን ስሚ
አዝበነፃነት ልቁም ስለፍቅሩ ላዚም አባት ከአባት በላይ ስላለኝ በሰማይ ለልጅነት ልቤ ፅናት ነው ገንዘቤ መደነቂያ አረገኝ ለፍቅሩ ለይቶኝ ዘማሪት ህፃን እንቁ ስላሴ
የቻናሉ ቤተሰቦች በምትችሉት አቅም ቻናሉን አሳድጉት እና እንዲለቀቅ ምትፈልጉትን መዝሙር comment. ላይ አሳውቁን
✞ አይዟችሁ በርቱ ✞ አይዟችሁ በርቱ አትጨነቁ በአንዳች ነገር አትሸበሩ የተዋሕዶ ልጆች በአገር ውስጥና በውጪው ዓለም የምትኖሩ በወጀብና በመከራ ውስጥ አለው ልጆቼ አይዟቹ የሚል የተስፋ አምላክ ነው የምናመልከው የተቆረጠውን የሚቀጥል አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የአማሃ ተንኮል የአኪጦፌል ክፉ ምክር ሁከት አንግሶ በደም ሊያጨቀይ የኢትዮጵያን ምድር እንቅልፉን አጥቶ በዘር ተቧጥሎ ቢመላለስም ሲያምረው ይቅር እንጂ አገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አትፈርስም ጎልያድ ይወድቅና ሰይፍን የታጠቀው የእምነት ጠጠር ይዞ ዳዊት ባለ ድል ነው ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን እግዚአብሔር አይጥልም አላኖራት ያለ ሲኖር አላየንም አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የትናንትና የተዋሕዶን ውለታ የረሱ ቅጥሯን አፍርሰው የካህን የምእመን ደም የሚያፈሱ መስሏቸው እንጂ አይበረክቱም የነኳት ሁሉ የገሃነም ደኞች አይችሏትም ነው የተስፋ ቃሉ አገር እንዳጠፋ ፊት ሆና የዘመተች በጳጳሷቷ ሞት ፅናት የሰበከች እምዬ ኦርቶዶክስ የጥበብ መፍለቂያ ትኑር ትልቅ ሆና በትልቋ ኢትዮጵያ አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ጌታ አምላክን የሚቃወመው የአውሬው መንፈስ ያለ ሰው ልጅ ክርስቲያን የሆንክ ማኅተብህን በጥስ አደራ በርቱ የተዋሕዶ ልጆች እጅ እንዳትሰጡ የጌታን መስቀል በአውሬው ምልክት እንዳትለውጡ መከራችን ያልፋል አጭር ነው ዘመኑ ሞት ሊሆን ለካዱ ሕይወትም ላመኑ እንደ ቀድሞ አባቶች እንደ ሰማዕታት ለመሞት ከመኖር ለመኖር እንሙት አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ዙሪያዋን ከቦ እንዲያለመልም የኢትዮጵያ ምድር ሕዝቧ እንዳይጠማው በርሃብ እንዳይሞት ጊዮን ቢፈጠር እብሪተኞቹ የፈርኦን ልጆች አይሆንም አሉ በእኛ ላይ አዘው የእኛኑ ከእኛ ሊከለክሉ ግብፅ እንድትበለፅግ እስራኤል ደይቶ ፈርኦን ግፍ ቢያበዛ የሰው ላብ ቀምቶ የራሄሎች እንባ የተጠራቀመው ዛሬም እኮ ይፈርዳል ባሕሩን ያሰጠመው
✤ ገድሉ ተአምራቱ ✤
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ======
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
እዝ
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው ተክልዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
ቤተሰብ በቻላቹት አንፃር ለምታቁት ሰው ሊንኩን በመላክ ተባበሩን 🙏🙏🙏🙏🙏 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏የምትፈልጉትን መዝሙር ደሞ comment ላይ አሳውቁን
ገብርኤል ሀያል
ገብርኤል ሀያል መላከ ሰላም መለከ ብስራት
የምታወጣ የእግዚአብሔርን ርስት ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን
ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን
የጽናታቸው ዝናው ሲሰማ
በዛች ባቢሎን በሞት ከተማ
ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቆመህ ተገኘህ መሀከላቸው
ውሀው ሲዘልም ቢያስደነግጥ
በጋኖቹ ውስጥ ቢነዋወጥ
ፀንተው ዘመሩ ልጅ እና እናቱ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ
ቂርቆስም ፀና ሞትን ሳይፈራ
አንተ ስላለህ ከእነርሱ ጋራ
አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
አምነው ድልነሱት ያንንመከራ
እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ
ፈጥነህ አማልደህ ከቸር ጌታዬ
ክፉውን ዘመን የማልፍበት
ጽናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት
ከመልአኩ ከቅ/ገብርኤል ረድኤትና በረከት ያካፍለን አሜን
https://t.me/Qmamaaa
ዮም ፍስኃ ኮነ (የሰርግ)
ዮም ፍስኃ ኮነ (2)
በእንተ መርዓዊ ወመርዓዊሃ {2}
ቆሟል መሰረቱ ፍስኃ ኮነ
በእምነት ተገንብቶ »
ብርሃን ይታያል »
ቤታቸውን ሞልቶ »
አዝ =====
ተባርኳል ማዕዳቸው »
ጽዋቸውም ሞልቷል »
በድካም የዘሩት »
ዛሬ ብዙ ሆኗል »
አዝ =====
የወንጌልን አጥር »
በዙርያቸው ተክለው »
ቅጽራቸው ተባርኳል »
ጠላት እንዳይቀርበው »
አዝ =====
በሥጋ ወደሙ »
ተጣምሯል ሥጋቸው »
ምለዋል በቃሉ »
ምንም ላይለያቸው »
አዝ =====
በእምነት ሠረገላ »
ተሳፍረው ደረሱ »
በቅድስና ልብስ »
ተሹመው ሊነግሡ »
አዝ =====
መዝሙር: በዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ
...........♰ሊረዳኝ መጣ ♰
ሊረዳኝ መጣ ሀያል ሚካኤል ይጠብቀኛል ሀያል ቅዱስ ሚካኤል(2×)የሙሴ ጠባቂ ኃያል ሚካኤል መንገድ የመራኸው ›› የኤርትራን ባህር ›› ከፍለህ ያሻገርከው ››
ክብርህ ከመላእክት ኃያል ሚካኤል ከፍ ከፍ ያለ ነው ›› ታላቁ አለቃከሃጢያት በረሃ ኃያል ሚካኤል መጠለያ ሆነን ›› ጠላት በመንገድ ላይ ››
