ወደ ኢየሱስ ደረት
Відкрити в Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
276
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
-630 днів
Архів дописів
276
✨ቤዛዬ✨
የሰማነውን እውነት ማን ነመነ
አምላክ ሰውሆነ መባሉን ማን ተቀበለ
ከሰማይ ሰማያት ለመሞት ወረደ
ከከበረ ስፍራ ወደ ወረደ ቦታ
ከሚመለክበት ከላይኛው ሰማይ
ለክብሩ በማይመጥን ስፍራ ሲታይ
ለምን አትበሉ እኔን እናንተን ለማዳነው
የመጣው አዶናይ
በውርስና በእኛ የመጣው ሀጥያት
በጫንቃችን ተከምሮ ከህግ በታች
ነፃነትን ቀንጭሮ ሲያንገላታን
አይቶ ራራልን ኩነኔን ሊወስድልን
አንድ ተብሎ ተጀመረ የስቃዩ ታሪክ
እኔን እናንተን ለማዳን የመጣባት ጉዳይ
በመጨረሻው ሰአት ከራትም መልስ
ተጨነቀች ፈራች ነብሱ እስከሞት
በጌተሰማኔ ወርዶ ቢለምን አባቱን
ሶስቴ ቢደጋግም ይችፅዋ ትለፍ እያለ በልቡ
ብትወድስ ፍቃድህ እንጂ ፈቃድህ አይሁን እያለ
ቢያስገድደው የኔ እና የናንተ ጉዳይ
አባቱ ፍቃዱ ሆነ ሊያድነን በበጉ ስቃይ
ደረሰ ሰአቱ አልፎ ሚሰጥበት
ወንበዴ እንደሚዙ ሰይፍ እና ጎመድ ይዘው
ይሁዳም መጣ አሳልፎ ሊሰጠው
ከእጁ አድጎ ሲሸጥ ሴይጣን አታሎት
ስሞ ተለየው ገንዘቡን አስበልጦ
እየሱስን ሊያስገድሉት ሰበብ አስባብ ሲፈልጉ
ምንም አላገኙም ወንጀልን ከሱ
ግን መች ተዉ ነፃ መሆኑን አይተው
ይብሱንም ፈለጉ ሞቱን እየናፈቁ
በዚያች ሰአት ሊቀካህናት ልብሱን ቀደዱ
ተፉበት ጎሰሙት አይኑንም ሸፈኑ
ማን ነው የመታ ተናገር እያሉ አሾፉበት
እርሱ ግን ዝም እኔን እና እናንተን ለማዳን
መች አለቀ ስቃዩ ይሄ ጅማሬ ነው
አመላለሱት ከሸንጎ የሞትን ፍቃድ ፈልገው
ግን መች ገባቸው ለነርሱ መምጣቱ
እያዩ እውራኖች ሆነው ቀሩ
አንድ ነገር አሰቡ እንዲፈታላቸው በርበባ
ይሰቀል እየሱስ ይፈታ በርባን ብለው አወጁ
በአደባባይ ጮሁ እንደ ጀብድ ይሰቀል እያሉ
ዝም አለ እየሱስ እኛን ለማዳን
በርባኖች አደረገን ሞታችንን ሊሞትል
በጅራፍ ሲገርፉት ስጋው ከአጥንቱ ሲለያይ
አጥንቶቹ ሲቆጠሩ እንደ መዳፍ
የሞት ሞት ስያሰቃዩት ያለ እረፍት
ዝም አለ እየሱስ ለሞት የታዘዘ ሆነ
ለኛ ነበር ስቃዩ ቀየረው እንጅ በስቃዩ
በቀራኒዮ ሊሰቀል ባልደረቁ ቁስሎቹ
መስቀል አስጭነውበት ባልደረቁ ቁስሎቹ
ያለምንም ርህራሄ ፍጠን እያሉ ሲያጋፉ
ወደቀ ከመሬት በተመዠለጉ ቁስሉ
አመመወ ከበደው ህመሙ ግን
ዝም አለ እኔን እና እናንተን ለማዳን
ወሰዱ ቀራኒዮ ሊሰቅሉት እርቃኑን
የተቸነከሩ እግሮቹ እጆቹ ሲንቀጠቀጡ
ሰቀሉት በጭካኔ ከወንበዴዎች ጋር አመሳሰሉት
ከላይ ደሙ ላይቆሙ ሲፈሱ
እኔን እና እናንተን ከሀጥያት አነፁ
መች ተብራራ ሲቃዩ መች ተገለፀ መከራው
ከዚህ በላይ ሆኑዋል ሊያድነን በሞቱ
ሞት የማይበግረው የአይሁድ አንበሳ
ሀጥያትን የሞትን መውጊያው ድል ነሳ
ያኔ የነፃነት ጮራ ለኛ አፈነጠቀ
በባርነት ግዞት ላለ አርነት ታወጀ
አበቃ ከኩነኔ ነፃ ናችሁ የሚል መዝገብ በደሙ ተፃፈ
https://t.me/wedeysusedert✍️በፂ
276
ፈጣሪ የሆነ ከፍጥረቱ ዝርዝር የገባበት ጥልቅ ሚስጥር፦
ማቴ 1÷1
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
➡ከአራት ሺ አመት(2000BC) በፊት አብርሀም የሚባል የእምነት አባት ነበረ።ይህ የእምነት አባት በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግ/ር በአንተ በኩል ዘርን አስቀጥላለው
እንደ ሰማይም ኳክብት አበዛሀለው ብሎ ቃልኪዳን ገባለት።
➡እግ/ር አብርሀምን እንዲ አለው ካንተ በሚወጣው ዘር የምድር አሕዛብ ይባረካሉ አለ (ዘፍ 22÷18)ይህም የሚጠቁመው ማንን ነው፦በ (ገላ3÷16)እንዲህ ይላል
"ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፡— ለዘሮቹም፡ አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፡— ለዘርህም፡ ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ"።
➡ከላይ በማቴ 1÷1 ላይ ያለው ሀሳብ እጅግ ጥልቅ ነው።አብርሀምን እና የአብርሀምን ዘር ሁሉ የፈጠረ እግ/ር ወልድ በፍጡር ምድብ ውስጥ የገባበት ታላቅ እውነት፤
ከዘላለም በፊት የነበረ መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለው እግ/ር ወልድ እንዴት ጅማሬ ኖረው? እንዴት ተወለደ ?እንዴት እድሜው ተቆጠረ? እንዴትስ ተሰቀለ? ለምንስ ሞተ?እንዴትስ ተነሳ? ለምንስ ለምንስ የሚሉ ጥያቄዎች ዛሬ ለኛ ግልፅ ነው።
➡ፈጣሪ የነበረ ከፍጡር መንደር የገባው በአዳም በመጣው ሀጥያት የሰው ዘር ሁሉ በውርስ በተካፈለው መርገም ምክንያት ከእግ/ር ክብር መገኘት ውስጥ ርቆ
ከእግ/ር መንግስት ሳይሆን ከአለም መንግስት ተወዳጅቶ እና ተስማምቶ ሲኖር ለነበረ ህዝብ ነው።
➡ህዝብ ሁሉ (እኛንም ጨምሮ) ለሀጥያታቸው ማስተሰረያ የሚሆን የኮርማ እና የዋኖስ ደም ለካህኑ እያመጡ የበደላቸውን ብዛት ተቆጥሮ በሚሰዋው መስዋዕት ላይ ተዘዋውሮ የበደልን ስረየት ሳይሆን ሽፋን የሚሆን እንጂ የተወገደ ሀጥያትን ሳያገኙ ሲነከራተቱ ኖረዋል።
➡ሮሜ 6÷23 የሀጥያት ደሞዝ ሞት ነው።
➡ይህንን የእግ/ር ትዕዛዝ ማንም ሊተላለፈው አይችልም ሞት የሚባልም ክፍያውን እየጠበቀ ነው በስጋ ስለሰራነው ሀጥያት
➡ፈጣሪ ፍጡር የሆነበት ሚስጥር የአብርሀም የይስሀቅ የያቆብ ...የዳዊት አምላክ የዳዊት ዘር የተባለበት ምክንያት ፍቅር ነው ምን ያክል ቢወደን ነው ከሚከበርበት ከሚመለክበት ከዙፋኑ ሊዘበትበት እና እንደ እርጉም በመስቀል ሊሰቀል የወደደው?የአምላክነትን ሀይል ሳይሆን የባርያን መልክ ይዞ ባልሰራው እና በሌለበት ያጥያት ሊሞት የወደደው እኛን ለማዳን ነው ይህን ሁሉ ርቀት የመጣው።እኛ የሀጥያታችን ብዛት በጫንቃችን በስቶ ሲያንገዳግደን፤ እየሱስ መጣና ሸክማችንን ወሰደ የሚያስገርም ነው።
➡ፈጣሪ ፍጡር የሆነበት ሚስጥር እኔ እና እናንተን ለማዳን ነው።እንዲሞትልን የሚያደርገው ስራ ፅድቅ የለንም ግን በድካማችን የሚራራ ሊቀካህን አገኘን።
🔥🔥🔥Hallelujha🔥🔥🔥
https://t.me/wedeysusedertPlease react and tell me how much it has helped you.
276
የዮሐንስ ወንጌል 13:23
ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤
እንኳን በደና መጣችሁ
✨ WELLCOME✨ ወደዚህ ቻናል እየገባችሁ ያላችሁ ወዳጆች በጣም ደስ ብሎናል። ይሄ ቻናል ብዙ የምታተርፉበት ወደ እየሱስ ደረት ይበልጡንም እንድትጠጉ የሚያደርጉ ትምህት አዘል የሆኑ ነገሮች ይለቀቁበታል።
እስኪ በዚህ ቻናል ደስተኛ የሆናችሁ ምላሻችሁን react በማድረግ አሳዩን።
