ቆጮ ሻጭ እና ገዥን አገናኝ ባህርዳር
Відкрити в Telegram
መኖሪያ ቤት: የንግድ ቦታ :ሆቴል :መኪና እናገናኛለን!!
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
431
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-130 днів
Архів дописів
በአምላክ እናት ስደት ያልደረሰባት መከራ የለም። ተርባለች፣ ተጠምታለች፣ ተሰድባለች፣
ተንገላታለች፣ በፀሐይ ተቀቅላለች፣ እሾህ ተወግታለች፣ እንቅፉት ተመታለች፣ ተዘርፋለች፣ የሰው ፊት አይታለች፣
ፍርፋሪ ለምናለች፣ ባይተዋር ሆናለች፣ ብርድ ተበርዳለች፣ ቤተሰቧን ናፍቃለች፣
ልጇን እንዳይገሉባት ተሰቃለች፣ አልቅሳለች ፣ በአቀበቱ በቁልቁለቱ ደክማለች፣ ... 3 ዓመት ከመንፈቅ በስደት ፣ 64 ዓመት የመከራ ፀጋ ለብሳለች።
ምንጭ 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ.....
የድንግል ማርያም ምልጃ በረከት አይለየን
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን
ፅጌ ፆም ነገ መስከረም 26 ይጀምራል
ስደቷ የሰው ዘርን ለማዳን ነበር!!!
ስደት፣ ልመና፣ ልቅሶ፣ ዝርፊያ፣ ስድብ፣ ርሀብ ፣ ጥም ፣ ባይተዋርነት ...
..........................
አምላክን ለማዳን ብላ
በማታውቀው የግብጽ በረሀ እግሯን የአሸዋው ግለት እየገረፋት ተሰደደች።
እንባ ጠራጊዋ እመ አምላክ አለቀሰች።
ከህጻነቷ ጀምሮ እስከ እረፍቷ ድረስ ልቅሶ አልተለያትም።
ስጋና ነፍስ መጋቢዋ እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች።
ሰጭዋ እናት ኮፌዳ ይዛ በየመንደሩ ፍርፋሪ ለመነች።
በእሷ ልጅ ምክንያት ሄሮድስ የገሊላን ህጻናት በጠቅላላ
እንደ ገደለ ስትሰማ በበረሀው ላይ አለቀሰች ።
+ የሚበላ ቁራሽ ለመለመን መንደር ሄደች። ባዶዋን ተመለሰች።
የልጇ የወርቅ ጫማ ተሰርቆ ጠበቃት። ቁራሽ ላላገኝ የልጄን
ጫማ አሰረኩኝ ብላ አለቀሰች።
+ ከእትማን ቤት ስትለምን ኮቲባ ልጇን ቀምታ ምድር ላይ ጣለችባት።
እመ አምላክ አለቀሰች ፣ ልጇም አለቀሰ።
+ በበረሀ ሲከራተቱ ሽፍቶች የልጇን ልብስ ገፈው ዘረፏት።
ይገሉብኛል ብላ አለቀሰች።
...............................
እመ አምላክ ስታለቅስ ልጇ ፈጣሪ አልቅሷል፣ ዮሴፍ አልቅሷል። ሰሎሜ አልቅሳለች።
መላእክት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ዑራኤል..........አዝነዋል።
ያላዘነው ዲያቢሎስ ብቻ ነው። ጥንት በሄሮድስ ልብ አድሮ እመብርሃንን አሰደደ።
አዳምን ለማውጣት ተንከራተተች።
አዳምን ለማዳን በ33 ዓም ልጇ ተሰቀለ። ከመስቀሉ ስር ሆና
አለቀሰች።
