የክብሩ ነፀብራቅ✨
Відкрити в Telegram
ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
360
Підписники
+324 години
+137 днів
+9030 днів
Архів дописів
360
ዘጸአት 33፡12-19 ላይ የተመሰረተ
የሙሴ ደብዳቤ
አቤቱ አምላኬ
በስሜ ጠርተኸኛል፤ ሞገስም ሰተኸኛል። እንደ ባለእንጀራ ቆጥርሄኝ ሰው ከወዳጁ ጋር የልቡን እንደሚያወራ አንተም የልብህን አወራሄኝ። ነገር ግን በዚህ ሁሉ አልረካሁም ልቤ አልተረጋጋም፤ አልረጋ አለኝ፤ አቤቱ ልቤ ከድምፅህና ከአስፈርው ክንድህ የበለጠ ነገር ይፈልጋል፤ መኖሪያህን መገኘትህን አብርሆትህንና ፊትህን ይፈልጋል።
ኃያሉ ክንድህን በግብፅ ላይ እንዴት እንደዘረጋህ አየሁ። የፈርዖንን ትዕቢት እንዴት እንደሰበርከውና ባሕርን ለሕዝብህ እንዴት እንደ ከፈልከው ተመለከትሁ። በቅዱስ ተራራ ላይ ቆሜ በእጅህ የተቀረጸውን ሕግህን ተቀበልሁ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አንተን ከማወቅና ከመቅረብ ጋር አይነጻጸሩም፤ አንተን እንደ ነጻ አውጪ ብቻ ሳይሆን እንደ ቅርብ ወዳጅ ማወቅን የሚተካ ነገር የለም።
ጌታዬ ሆይ...፡ “መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ” አልከኝ። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ባይገባኝም፤ ነገር ግን ይህንን አውቃለሁ፤ መልካምነትህ አንተ የምትሰጠኝ ቁስ ሳይሆን አንተው ራስህ ነህ ። መልካምነትህ ባሕሪህ፣ ምሕረትህ፣ ክብርህ፤ ፊትህ፤ አብሮነትህ ነው። ይህን መልካምነትህን ለማየት እፈልጋለሁ፤ ከሩቅ ሳይሆን፤ በምልክትና በድንቅ ሳይሆን፤ ፊት ለፊት ለማየት፤ በእጄ ልዳስሰው እፈልጋለሁ። በህልውናህ ዓለም በአብሮነትህ ደመና ዘላለሜን ልሰወር! ሳልወጣ በዛው ልቀር፤ ልረሳ።
አብሮነትህ ከእኛ ጋር ካልሄደ፣ እባክህን ከዚህ አታውጣን። አንተ የለለህበት ጉዞ ከሞት በምን ተለየ ? ከአንተ ከኪዳኑ ባለቤት ውጪ ኪዳን መውረስ ምን ትርጉም አለው? አንተ የለለህበትን ከናዓን ከመውረስ አንተ ባለህበት ምድረ በዳ መሞትን እመርጣለሁ፤ አንተ ባለህበት መሰንበት ይሻለናል፤ አንተ ያለህበት በረሃ ገነት ነው፤ አንተ የለለህበት ገነት ገዳይ በረሃ ነው።
አምላኬ ሆይ፡ ክብርህን በታቦቱና በመገናኛው ድንኳን ላይ ብቻ ሳይሆን በውስጤም አኑረው። እርሱም እግሬን የሚመራ ብርሃን፣ ነፍሴን የሚሞላና የምያደምቅ ውበት ይሁን። ትእዛዝህን ብቻ ሳይሆን አንተንም ለማወቅ እሻለሁ፤ ፍርድህን ብቻ ሳይሆን ልብህንም ለመማር ለመረዳትና ለማወቅ እፈልጋለሁ።
አቤቱ ጌታዬ እኔ ደካማ፤ ፈሪና አፌ ትብ ነኝ: ነገር ግን አንተ መርጥከኝ፤ ያለህልውናህ መሄድ ለእኔ እንደ ሞት ነው፤ አሁንም አንድ ነገር እለምንሃለሁ፤ ክንድህንና አስፈሪነትህን ብቻ ሳይሆን ቅርበትህም፤ ገናናነትንና አሸናፊነትን ብቻ ሳይሆን አብርሆትህ ይክበበኝ ያጅበኝ። ከንዓንን ሳይሆን አብሮነትህን እንፈልጋለሁ፤ ድልን ሳይሆን ህልውናህን እሻለሁ።
አቤቱ ክብርህን አሳየኝ፤ መና አያረካኝም፤ ዕለት ዕለት የማየው ታምራትም ልቤን አይይዝም አያስገርመኝም፣በፈርኦንና በመንግስቱ ካደረከው ተዓምራቶች በላይ ልቤ ክብርህን ይፈልጋል ውስጤ ይጠማሃል፤ ኤርትራን ከከፈልክበት ከአስገራሚ ሃይልህ ይልቅ መንፈሴ አብሮነትህን ይጠማል። በመና ያልረካ፤ በእሳትና በደመና አምድ ያልረካ ጩሄት አለኝ እባክህን ክብርህን አሳየኝ! እባክህን ጌታ ሆይ ክብርህ ውስጥ ሸሽገኝ፡ መዓዛህን አሸክመኝ፡ ህያው በሆነው አብሮነትህ ውስጥ ሰውረኝ፡ ከአብሮነትህ ውጪ አቅም የለኝም፡ እውቀት የለኝም፡ ሃይል የለኝም፡ በኔ በደካማውና በአፈ ትቡ ድካመን ሸፍነህ ሞገስ የሆንክልኝ አንተ ነህ፤ አንተ ከእኔ ጋር ካልሆንክ ባዶነቴ ያሳድደኛል፤ ድካሜ አድኖ ያጠፋኛል፤ አቤቱ ያለአንተ ከዚህ አታውጣን።
እኔ ባሪያህ ያንተው ነኝና እጅህን ብቻ ሳይሆን ፊትህንም አሳየኝ፤ ተዓምራትህን ብቻ ሳይሆን አብሮነትህንም አስለምደኝ፤ ህግህን ብቻ ሳይሆን ድምፅህንም አስተምረኝ። አንተ ባልቀደምክበት መንገድ እንዲቷን እርምጃ እንዳልሄድ እንደገና በአብርሆትህ እሰረኝ።
የሚወድህ ባሪያህ ሙሴ
By:- Abi Kidan
Join my channel here 👉 Abi_Kidan_click_here
360
ጌታ ምህረትህ ይግነንልኝ
በድል ጨርሼ እቆማለሁ
ጌታ ምህረትህ ይግነንልኝ
በድል ጨርሼ እቆማለሁ
በዓይነ ህሊናዬ ዕሩቅ ተጉⶴ
ራሴን አያለሁ ምርኩዜን ይⶴ
የማይጸጽትን ሕይወትን ኖሬ
የጠራኸኝን አምላክ አክብሬ
ስል ይታያኛል እፎይ ተመስገን
ስለ ረዳኸኝ በቃው ለዚች ቀን
አንድ አንዴ እለላሁ ቶሎ አልፎልኝ
የሽምግልናን ዕድሜን ባየሁኝ
ዝም ብዬ አይደለም እንዲህ ማለቴ
የቀኑን ክፋት ነው በማየቴ
የጉብዝናዬን ወራት ያዛቸው
ሳሾፍ ስቀልድ አልለፋቸው
የአንዳንዱን ቀን የሕይወት ቀጠሮ
እሮጦ ማለፍ ቢቻል ወይ በሮ
ይመኛል ልቤ እንዳላያቻው
ባመልጥ ብሰወር ከክፋታቻው
ግን አይቻልም እስካለው በምድር
መሽቶ ሲነጋ ማየቴ አይቀር
ለእኔ አለ እንጂ የአንተ ጥበቃ
ውርደት እያየ ለክብር ሚያበቃ
ጌታ ምህረትህ ይግነንልኝ
በድል ጨርሼ እቆማለሁ
360
እንደገና ንካኝ እንደገና 2* 😭
ለፈራውም ሀይል ትሆናለህና
ለደካማው ብርታት ትሆናለህና
ሀይልህን አስታጥቀኝ ኢየሱስ ዛሬም እንደገና
ሽቶዬ ከላዬ ተሸተት ከሩቁ ልለይ በመዓዛህ
የመንግስትህ ጠረን ፅድቅህ ያውድ በኔ ነፍሴን እንደገዛህ
ነበርኩኝ እንዳልል ከፀጋህ ወድቄ ቅድስናን በአምና
አሁን ግን ባስባልከኝ በአዲስ ማንነቴ ስራኝ እንደገና
ንካኝ እንደገና በሀይልህ ለኩሰኝ
ስለአንተ እያወጀች ነፍሴ ደስ ትሰኝ
በህጉ ስላልዳንኩ በህግ አላፈራም ፀጋህን አስረዳኝ
የስጋ በጎነት የሰው ብቻ ድካም ልፋቱ እንዳይጎዳኝ
በከንቱ የባከኑ የአመታቴን ዋጋ በድል መልስልኝ
አለመታዘዜን መታዘዝ ይበቀል ሀይሌን አድስልኝ
እንደገና ንካኝ እንደገና.....
በከንቱ ሩጫ እንዳላለከልክ
ሲቸኮል እንዳላልፍ የፈቃድህን ልክ
እንደገና ንካኝ እንደገና....
ስጣደፍ እንዳልወድቅ ይዘህ አረጋጋኝ
የቀደምኩኝ መስሎኝ ክፉ አያዘናጋኝ
ውብ ቃልህ ያብሰለኝ የማትከብርበትን ገለባውን ይብላ
አይገኝ በህይወቴ ከመንግስትህ ሀሳብ ከትዕዛዝህ ሌላ
ንስር መሬት መሬት ምን አለው ከምድር ከፍታውን ትቶ
አሳ ለሞቱ እንጂ በህይወት አያቆየው ከውሃ ውስጥ ወቶ !
እንደገና ንካኝ እንደገና 😭
ያገኘሁህ ሰሞን የነበረኝ ፍቅር የመንፈሴ ብርታት
ማለት አይሁንብኝ ክብሬን በትዝታ ትጋቴን በትናንት
ፍቅርህን አብዛልኝ ናፍቆት ይባስብኝ ጥማቴን ጨምረው
ሳበኝ በመዓዛህ በፍቅር ትንፋሽ ነው ነፍሴ የምትኖረው
እንደገና ንካኝ እንደገና😭
ንካኝ 🙇🙇
Zemarit Fikrte Feleke.
360
ዘጸአት 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ። ²² የደመና ዓምድ በቀን፥ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከሕዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላለም። ፧፧፧፧፧፧፧፧፡፡፡፡፡፡ ከታየለት ጉዞ መገታት የማይችል ሰው በእግዚአብሔር የሚመራ ሰው ነው! ከዓለም System እና Season ውጪ የሚኖር ሰው በህልውናው የታጀበ ሰው ነው። Nothing Can stop him! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስሆን ተፈጥሮ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፡ በዚህ ምድር ላይ የሚያስቆምህ ሀይል አይኖርም፡ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ጋር ስሆን ጨለማ፡ብርሃን፡ ነፋስ፡ ደመና፡ ባህር፡ እሳት፡ ህያው ነፍስ ሁሉ ከእነሱ ጋር ሆነ። ብቻ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን እንጂ ሌላው አያሳስበን! Even ማንም ካንተ ጋር ባይሆንም ተፈጥሮ (Nature) ስለአንተ ከፍታ እግዚአብሔርን ሰምቶ ይታዘዝሃል! ፡፡፡፡፡፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
360
“ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤”
— ሮሜ 12፥11
Consuming fire in the name of Jesus 🔥!
