uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

የክብሩ ነፀብራቅ✨

የክብሩ ነፀብራቅ✨

Відкрити в Telegram

ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
355
Підписники
+224 години
+197 днів
+11330 днів
Архів дописів
Church ሂዱ ⛪ Bible Hardcopy ያዙ የጌታ እራት ውሰዱ ✝🍷 @ShekinnahKBR

Listening to Emmy's new album... it's truly a new therapy! 🎧 ከራሳችን የምንጠፋበት አዲስ በረከት! 🤍 @ShekinnahKBR

.... ህይወት ራስ ተኮር፣ አምልኮ ተዝናኖት ተኮር፣ አገልግሎት ሸቀጥ ተኮር ፣ ግንኙነት ጥቅም ተኮር ከሆነበት የዘመኑ የለበጣ አካሄድ ለማምለጥ ራስን ያለ ርኅራኄ ከእውነት ጋር ማጋፈጥን ይጠይቃል:: ንፁህ ህሊናን የሚያክል ክቡር ሃብት እንዲሁም የእውነት ዓምድና መሰረት የሆነውን አምላካዊ መርህ አሽቀንጥሮ ጥሎ እርካታ የሞላበትን የክብር ህይወት መጠበቅ የደለበ ሞኝነት መሆኑ አይዘንጋ:: በአደራ የተሰጠች አንዲት ህይወት በክብር ትጠናቀቅ ዘንድ እያወቁ የአለማወቅን ወራት በቃ ማለትን ግድ ይላል:: "ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል። — ምሳሌ 1:5 ✍️Dr Lali @ShekinnahKBR

እግዚአብሔር መልካም ነው🤍

በደሙ የዳነ፣ በጉን ይመገባል.....!✍ እስራኤላውያን ከሞት የዳኑት በውጭ ጉበን በተቀባው በበጉ ደም ሲሆን፣ ለምድረ በዳው ጉዞ ጉልበት ያገኙት ግን በውስጥ በቤታቸው በበሉት በበጉ ሥጋ ነበር [ዘጸ. 12፡7-8]። ብዙ አማኞች[እኛ] በክርስቶስ ደም መዳናችንን እናውቃለን፣ ነገር ግን በየዕለቱ ክርስቶስን ራሱን መመገብና ከእርሱ ጋር በኅብረት መኖርን ቸል እንላለን። ደሙ ከሞት ከሞት አድኖናል፤ ሥጋውን (ሕያው ቃሉን) መመገብ ደግሞ የዚህን ዓለም ምድረ በዳ በድል ለመጓዝ መንፈሳዊ ኃይል ይሰጠናል [ዮሐ. 6፡53-57]! @ShekinnahKBR

ገደብ.....! 💡 በዕለት ተዕለት ህይወታችን፣ በትምህርት ቤት፣ በቤተክርስቲያን፣ በአገልግሎት እና በግል ህይወታችን ገደብ (Boundary) እንዳለን ሁሉ... Social Media ላይም የራሳችን የሆነ ጥብቅ ገደብ ያስፈልገናል። ይህን ካላደረግን እየመጣ ካለው ራስን የማጣት ማዕበል በፍጹም አንተርፍም! በተለይ ለነዚህ ነገሮች ዛሬውኑ ገደብ እናበጅ፦ 🚫 የግል ህይወታችንን አሉታዊ በሆነ መንገድ ለሚነኩ... 🚫 መንፈሳዊ እሴቶቻችንን ለሚያቃልሉና ለሚቀልዱባቸው... 🚫 ነውርን፣ ዓለማዊነትንና ኃጢአትን "በዘመናዊነት" ስም ለሚያስለምዱን! ለነዚህ ገደብ ካላበጀን ጓዛችንን ጠቅልለን ከዘመኑ ጋር በአንድ ቦይ መንጎዳችን አይቀርም። የ Social Media Boundary ማበጀት አሁን ላይ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው! ያንን ገደብ ጥሶ የሚገባ ማንኛውም ነገር ለህይወታችን ዘላቂ አደጋ ስለሆነ፣ ያለ ምንም ማመንታት Unfollow, Ban, Restrict እና Block በማድረግ ገደባችንን እናስጠብቅ! በዚህ ጊዜ አብዛኛው ህይወታችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ፣ ይህን Boundary ሳናበጅ በመንፈሳዊ ህይወታችን በርተን መቀጠል እጅግ ከባድ ነው። 🙌🏾 ✨ @ShekinnahKBR

አንደ ስሙኝማ ...💡 ስንቶቻችን ነን Social Media[TikTok,Fb,Instagram..] ላይ Follow የምናደርጋቸውን ሰዎች በደምብ የምንጠነቀቅ? ቅዱሳን በዚህ ዘመን ፀሎት ብቻ ሳይሆን የምናያቸውን Contents ጥንቃቄ እናድርግ ! ሁሌ ዓለማዊ ፡ ሁሌ ምሬት ፡ ሁሌ ጭንቀት ፡ ሁሌ ስለLife ንፅፅር ፡ ሁሌ ማንቋሸሽ ፡ ሁሌ አገልጋዮችን መተቸት ፡ ሁሌ ቀልድ ከምያወሩ ሰዎች ራቁ! ሀሳባችሁ ቀስ... እያለ ሳይበላሽ እነዚህን ሰዎች Unfollow አድርጉ!🙌 በነውር መክበር ፡ በውርደት መዘነጥ ታዋቂነት በሆነበት በዚህ ጊዜ በየቀኑ ማንን እንደምንከተል፡ የማንን Video እንደምናይ ቆም ብሎ ማሰብ እራስን ማትረፍ ነው! ገርሞኝ'ኮ ነው በዚህ ጊዜ እውነተኛ ጥበብና እውቀት የሚያወሩ ሰዎች ሰሚ እያጡ ነው በተቃራኒው አሳፋሪ ድርጊቶች፡ መሳደብ ፡ እብደት ፡ መንፈሳዊነት ቀርቶ Even ከባህ ያፈነገጡ አደገኛ ሀሳቦችና ድርጊቶች በአስደንጋጭ ሁኔታ ብዙ ሰሚ እና ተከታዮች እያገኙ መጥተዋል። ለምን? እናስብበት!! Seriously Unfollow Challenge መጀመር አለብን! ምን ትላላችሁ ?🤔 @ShekinnahKBR

Repost from The Bible Thinkers
“ኢየሱስ ጥያቄ ነው ስንል፣ ልዩነቱ ከሌሎች ጎልቶ ይታያል። እርሱ መልስ የማያሻው ጥያቄ፤ ጥያቄነቱ የማይደብቀው መልስ ነው።” — ፊሊሞን ነጋ ክርስቶስ የሰው ልጅ ሊመልሳቸው የሚጥራቸው ጥያቄዎች ፍጻ
“ኢየሱስ ጥያቄ ነው ስንል፣ ልዩነቱ ከሌሎች ጎልቶ ይታያል። እርሱ መልስ የማያሻው ጥያቄ፤ ጥያቄነቱ የማይደብቀው መልስ ነው።” — ፊሊሞን ነጋ ክርስቶስ የሰው ልጅ ሊመልሳቸው የሚጥራቸው ጥያቄዎች ፍጻሜ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ራሱን የሚያይበትና የሚያውቅበት መስታወትም ጭምር ነው። በእርሱ ብርሃን ስናይ፣ ስለ አምላክ ብቻ ሳይሆን ስለ ራሳችን እና ስለ ዓለማችን ሁኔታ እውነታውን እናያለን። ከእርሱ ውጪ የምንፈልገው ነገር በእርሱ ሆነን ያገኘነውን ሙላት ሊተካ አይችልም! “ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።”   — ቆላስይስ 2፥10 @biblicalthinker1

ውዳችን ሆይ ሁሉን ለአንተ ☺️ @ShekinnahKBR
ውዳችን ሆይ ሁሉን ለአንተ ☺️ @ShekinnahKBR

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፩:፫ --- ፫፤ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል።

የግል Bible Study after ቡና በጨው hits different🫠. ለBible study በቡና ነው ዴ 'ምትነቃው እንዳትሉኝ😁
የግል Bible Study after ቡና በጨው hits different🫠. ለBible study በቡና ነው ዴ 'ምትነቃው እንዳትሉኝ😁

ተስፋሽ ፡ አምላክሽ ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አትፍሪ አምላክ ፡ ደጀኔ ፡ ነው ፡ ብለሽ ፡ ተናገሪ መከታሽ ፡ ከሆነ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ በዓለም ፡ አይገኝም ፡ አንቺን ፡ የሚረታ Singer Addisu Werku @ShekinnahKBR

የእግዚአብሔር መንገድ «አቋራጩ» ላይሆን ይችላል፣ ግን «ትክክለኛው» ነው! @ShekinnahKBR

....             ከአንተ አንበልጥምና አብራልን....🙌 ስትወለድ በነቢያት አንደበት የቃልህ ፍጻሜ ዕዉን እንድሆን ዘንድ በቤተል መገኘትህ ገርሞናል! የነቢዪ የኢሳያስ ጩኼትም ከንቱ አልሆነምና። ቃልህ ተፈጽሟል።  ፈጣሪ በፍጡር ተሰዶ ለቃልህ ታማኝነት ናዝራዊ ልትባል  በትንሽዬ ከተማ መኖር ከጀመርክበት  ፣ ዳግም ያገኘንህ በሙኩራቡ አስተማሪዎች ሥር  በመጽሐፍት ጥናት ነበር። በ 12 ዓመትህ እንኳን ለቃልህ ያለህ ርሃብ በእዉነትም ልባችንን ያሞቃል። ራስህን የሰወርከዉ ለዓመታት  እዛዉ ሰምብተ ይሆናል ከመጽሐፍት ጋር ። ቃልህን መኖር ያቃተዉን የመጀመርያዉን አዳም የጣለ ባላንጣዉ  ፣ ክፉኛ ስፈትንህ   አፍህን የከፈትከዉ  ከዳዊት መዝሙር አይደል የቃልህን ሰይፍ እየመዘዝክበት። በአገልግሎትህ ጀምሩ በሙኩራብ የተረተረከዉ የኢሳያስ መጽሐፍ የቃልህ ወዳጅ እንደሆንክ በርግጥ ያረጋግጥልናል።    "መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ" ያልክበት ይህ ዘመን ያልቀየረዉ  እዉነት የአንድ ቀን ምሽት ሕልም  እንዳይደለህ አይሣንም። ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ ራስህን አገኘህ እንጅ። ኸረ ግን ያለ ቃልህ መቼ አገኘንህ?!  በትንሣኤዉ ዕለት ለድንጋዩ መንከባለል የዓይን እማኝ ለሆኑ  ለዔማዉስ መንገደኞች ፣ በዚያኑ ዕለት ታምራት ከማስደመም ይልቅ የሦስተኛ ቀን ድልህን ከመጽሐፍት አጸናህላቸዉ ።
አጽናፈ ዓለሙ ከተደመመበት ከትንሣኤ ዕለት ታምራት ይልቅ በቃልህ ልበ ሙሉ ነህ።
በዚህ ምድር አንተን ያለ መጽሐፍት ፣ መጽሐፍትን ደግሞ ያላንተ አላገኘንም። ምነኛ ብትገልጥለት ይሁን? እንዴት  ብትነካዉ፣ ምንስ ቀምሶ ይሁን? ዘማሪዉ ዳዊት በመዝ 119 እንደ አድስ አፍቃሪ😁 176 ቁጥር ስለቃልህ  ተቅኝቶ አልርካ ብሏል። የመጽሐፍት ረዥሙ ምዕራፍ። እኛ ብላተናዎች አንተን ፍለጋ ያለ ቃልህ እንዳንዳክር ፣ ፈለግህን እንድንከተል ፣ በቃልህ ልባችን መሉ እንድሆን ፣ ከማንጸጸትበት መምህራችን ከአንተ ሕይወትን እንድንቀዳ ፣ ለሕግ ጊዜ እንድበዛልንና የቃልህ ወዳጆች ታድርገን ዘንድ በፍርሃትና በትህትና በእምነት እንማጸናለን።          ያከበርከዉ ቃልህ በልባችንም ይክበድ....!🙌🥰 ተባረኩልኝ! .....

Good morning Beloveds🥰 ቀናችሁ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የተቀደሰ ይሁን🙌 @ShekinnahKBR

....🙇‍♂ ታድላን ስንቱ ያልተገለጠለት ኢየሱስ ተገልጦልናል! 🙇‍♂🙇‍♂🙇‍♂🙇‍♂🧎🧎🧎🧎 @ShekinnahKBR

አሜን ብላችሁ ተቀበሉ....🔥 በኢየሱስ ስም መሰዊያችሁ ላይ እሳት ይምጣ! ለብዙ ትውልድ የሚሆን የማይፈርስ መሰዊያ በህይወታችሁ ይሰራ! በዘመናችሁ ሁሉ መሰዊያችሁ እሳትና ክብር-አልባ አይሁን! @ShekinnahKBR

እግዚአብሔር በእንደዚህ አይነት ሕብረት ይባርከን 🙌😊 እጅግ የሚወዳቸው ሰዎች አንድ ላይ 🥰❤ @ShekinnahKBR

....እናስብበት🙌
....እናስብበት🙌

Officially started a new Bible project! 📖✨ የጀመርኩት መጽሐፍ ምን እንደሆነ አሁን አልነግራችሁም፤ በጸጋ ስጨርሰው Announce አደርጋለሁ! (በኮመንት መገመት ግን ይቻላል 😁) እስከዛው በጸሎታችሁ አስቡኝ! በጥናቴ መሃል በጣም የተነካሁባቸውን እና ልቤን የሞሉ ሃሳቦችን ግን እዚሁ ቻናላችን ላይ የማካፍላችሁ ይሆናል። እንቀጥላለን ወይ እንቀጥላለን! 🙌🏾 ✨ @ShekinnahKBR